#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ጎይቲ አንተነህ ከሎ ሆራ አጎት ቤት እንደ መጣች ፈጽሞ መንፈሷ ሊረጋጋላት ባለመቻሉ ካርለት የምታደርገውን አጣች" ጎይቲ ጽጕሯን ስትላጭ ካርለት ብቸኝነት እንዳይሰማት አብራት ተላጨች በከሰልና በቅቤ የተለወሰውንም ቅባት መላ ሰውነቷን ስትቀባ ካርለትም አብራት ተቀባች"
ጎይቲ አንተነህና ካርለት አልፈርድ ቆጥ ላይ ከተደበቁ በኋላ ካርለት ጎይቲን ለማጽናናትና ለማደፋፈር ብትጣጣርም አልሳካልሽ አላት ጎይቲ እንዲያውም ፊቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞረችባት
ካርለት ሁኔታው አስደንጋጭ መሆኑን ብታውቅም ሦስት ወር እስኪሞላቸው ድረስ ቆጡ ላይ መቆየት ነበረባቸውና እስከዚያ ድረስ
በመካከላቸው እርቀ ሰላም እንደሚወርድ ተመኘች"
ቀኑንና ምሽቱን ቆጥ ላይ ከቆዩ በኋላ ለአንድ አፍታ ወረድ ብለው ከሎ ከመምጣቱ በፊት ለመናፈስ ወጡ" ጎይቲ አነተነህ ቆጥ ላይ መውጣቱ አልዋጥልሽ ብሏታል።
«አሁን እሱ የወንድ ልብ አግኝቶ እኔን ሊመታኝ? በየትኛው ወኔውና ጀግንነቱ፤ ወይ ሲያየኝ እሱ ራሱ ባልተርበተበተ አይደል?
ወይኔ ጎይቲ የወንድ ልጅ ዱላም ይናፍቃል ለካ?» አለች ለካርለት ይሁን ለማን እንደተናገረች ሳይታወቅ።
ወደ ጎጇቸው ሲመለሱ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከከሎ ሆራ ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ" ከሎ ሆራ ሁለቱንም ሲያይ ደንገጥ ብሎ ቆመ!
ካርለት በዓይኗ ጠቅሳ እንዲመታት ልትነግረው ፈልጋ ነበር። ለእሱ
«ና ምታት» ብላ በዓይን ለማመልከት እንዴት እንደምታደርግ ስከታስብ ግን እሱ ከቆመበት ደረሱ። ከሎ ሆራ መንገዱን ለቆ
አሳለፋቸው። ካለፉ በኋላ ግን ተሰማው፤ በባህሉ መሠረት እንዳያት ደህና አድርጎ መግረፍ ነበረበት። ያን ሲያስብ የብሽቀት ስሜት ታየበት፤ ጎይቲ አንተነህን ይወዳታል፣ ባህሉንም ያከብራል
ቅሬታና ቂም የሚይዝ ከሆነ አካል በማይጎድልበት መንገድ መምታቱ
የሚያመጣው ችግር የለም።
«ወደፊት ግን ይህን ጥፋት መድገም የለብኝም" በመምታቴ ጎይቲ አንተነህን የሚሰማት ነገር የለም። እንዲያውም እሷን ባለመደብደቤ ቅሬታ ሊያድርባት ይችል ይሆናል» እያለ፣ ራሱን ወቅሷል"
ካርለትም በበኩሏ ትንሽ በሽቋታል። ከሎ ሆራ ጎይቲ አንተነህን ፊት ለፊት ባገኛት ጊዜ ሁሉ እንዲገርፋት ተመካክረዋል። ጎይቲ
አንተነህ ደግሞ የከሎን የፍቅር ፍርሃት ባለመረዳት ሲርበተበት ስታየው ባሕርይው ያስጠላታል። ከሎ ወንድ ወንድ አልሸትሽ
ብሏታል። «ከሎ ትክክል አልሠራም። እሱ ጎይቲን ልክ ከተማ እንዳየው
ብዙ ሕይወቱን እንዳሳለፈበት በጠባይ ሊያግባባት፣ ሊያቀርባት
ፍቅሩን ሊገልጽላት ይፈልጋል" ጎይቲ ግን ወንድ ልጅ በቅድሚያ የምትፈልገው ኰስታራነት ነው ኵሩ ወንድ፣ ሸንቆጥ የሚያደርግ ወንድ፣ እሷን በፍቅር ገርቶ፣ በፍቅር አብሯት መጋለብ ይችላል
ሴት ልጅ ዱላ ሲያርፍባት የሴትነት ፍላጎቷ ከአሸለበበት ይቃል»
አምጭ አምጭ የሚላት፣ ፍቅር የሚናፍቃት፣ ድሪያ የሚታወሳት ያኔ ነው፤ ከሎ ደግሞ ይህን አልተረዳውም። እንግዳ ነገር ሆኖበታል ሕጉን እያወቀ በተግባር ግን አያከብርም። ይህ ደግሞ ስሕተቱ ነው ካርለት በእንግሊዝኛ ለጎይቲ ነገረቻት። ጎይቲ አንተነህ ግን ያለችው በጭራሽ አልገባትም እንግሊዝኛ ደግሞ የት አውቃ
ጎይቲ አንተነህ አጠገቧ ያለችው ቀውስ ብቻዋን ስትለፈልፍ ብትደነቅም፣ እሷም ተመሳሳዩን ፈጸመች።
«ይኸዋ ይህ ቦቅቧቃ! እንኳንስ ሲያየኝ እንደ ወንዶቹ ሊገርፈ
ይቅርና መንገድ ለቆ አሳለፈኝ" ባል እኔ ነኛ! እሱ ሚስት ነው እንዴት ሆኜ ከዚህ ሴት ጋር እኖራለሁ? ምነው ያን ቀን ደልቲ
ገልዲን ብዬ ባልሄድሁ ኖሮ፤ እሱን ብዬ በመሄዴ ቀናው እንጂ የታባቱ ያገኘኝ ነበር ይህ ሴት" ሴት ልጅ የባሏ ዱላ ሕይወቷ ፍቅሯ ነው" ታዲያ ይህ ሰው እኔንኮ ሕይወቴን እያጠፋ ነው" እሽ
የኔስ ነገር ይቅር ነገር ግን የሚወለዱት የሁለት ሴት ልጆች መባላቸው አይደል? ወይኔ ያልታደሉት" ወይኔ ወይኔ» እያለች፣ እንባዋ
ታወርደው ጀመር"
ካርለት ትንሿን ቴፕ ከፍታ የምትለውን እየቀዳች በማስታወሻ ደግሞ የሚሰማትን ትከትባለች» ካርለት በአንዳንድ ሁኔታ ላይ እሷም ራሷ እየተስማማች መጣች» በአገሯም፣ አንዳንድ እውቅ ሴቶች ስለ ወንድ ፍቅረኛቸውና ከእሱ ስለሚጠብቁት ባሕርይ ሲያወሱ ነካ አድርገው የሚያልፉት ነገር አለ፣ «ከፍቅረኛዩ ጋር ስንላፋ
ስንታገል፣ የፍቅር ዱላ ገላዬ ላይ ሲያርፍ ልቤ እስኪጠፋ ድረስ ራሴን እሰጠውና የሱን ደግሞ ለመውሰድ ሙሉ ፍላጎት አሳያለሁ ከዚያ በኋላ የምንሠራው የፍቅር ጨዋታ ሁሉ እንደ አይስhሬም እየጣፈጠኝ፣ መላ አካሌ ከጸጕር እስከ እግር ጥፍሬ በርካታ
ሲንበሸበሽ ይሰማኛል" እንደዚህ አድርገው ከኔ ጋር የተጫወቱ ወዶች የፍቅር ዙፋኑን ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም» ብለው
የተለያዩ ሴቶች አስተያየት ሲሰጡ ሰምታለች።
እሷም ቢሆን አንዳንድ ልምዶችን አሳልፋለች" አንድ ጊዜ፣ ስሜ ጃክ ነው ብሎ የተዋወቃት አሜሪካዊ፣ ማንችስተር ውስጥ
ለጉዳይ መጥቶ አንድ የምሽት ዳንስ ላይ ይተዋወቃሉ“ ካርለት
በእርግጥ ወደ ዳንሱ ቦታ የሄደችው ከወንድ ጓደኛዋ ከዴቪድ ጋር ነው ታዲያ አሜሪካዊው አንድ ሁለት ጊዜ በትእዛዝ መልክ ዳንስ
ጋበዛትና ሰውነቷን በጠንካራ እጆቹ ጠበቅ አድርጎ እያሸ፣
አሳመማት። ቀደም ብላ ባሳለፈችው ሕይወቷ ወንዶች እንደዚያ ሰው
አድርገዋት አያውቁም" ሰውነቷን የሚደባብሱት ቀስና ላላ አድርገው
ነው። ሰውዬው ግን መሞረዱ አንሶ በረጅም እጁ መቀመጫዋን ደህና አድርጎ ቸብ ቸብ አደረገላት «ተው» ማለት እየፈለገች፣ ቃሉ ግን
ከጕሮሮዋ አልወጣልሽ አላት" በእርግጥ፣ ዴቪድም ከሌላ ሴት ጋር እየደነሰ ስለነበር እነሱን ልብ አላላቸውም።
አሜሪካዊው ፍጹም በማታውቀው መንገድ ሰውነቷን እየመታ፣ እየሞረደ፣ ልቧን ስልቱን አስቀየረው ከንፈሯን እንኳን
ሲስማት የንከሻ ያህል ሆኖባት እግሯን አንሥታ ለመጮህ ትንሽ ቀርቷት ነበር ግን አልጮኸችም" ዳንሱ አብቅቶ ሲለያዩ ካለልብ ወደ ቦታዋ ተመለሰች እንደ ምንም ታግሣ ሁለት ጨዋታዎችን
አሳልፋ ልቧን ወደ ቦታው ለመመለስ ወደ አሜሪካዊው ሰው ሄደች።
ቆንጅት እንደምትመጪ አውቅ ነበር...» ብሎ አሜሪካዊው ተመጻድቆባታል" ግን ፊቷን አዙራ አልተመለሰችም፤ ተመልሳ ካቴና እጆቹ መሃል ወደቀች ሞራርዶ፤ ቸባችቦ፤ ብድግ አድርጎ ተሸክሟት ወደ አንድ ክፍል ሲገባ፣ እግሮቿ አልተፈራገጡም"
እጆቿ አልተወራጩም፤ አፏም አልቀባጠረም።
ካርለት ይህንን አሜሪካዊ እስከ አሁን ድረስ በዚያች ለሰዓታት ብቻ በዘለቀች የፍቅር ጨዋታ የማትረሳው ትዝታ አስታቅፏት ነግዷላ" ያንን ሰው ለብዙ ጊዜ የተካው ወንድ አልነበረም። ኖራ ኖራ ግን ሐመር ላይ ተመሳሳዩን አገኘች" የሷም ብቻ ሳይሆን የጎይቲም የሆነው ሰው በእርግጥ ለየት ያለ በመሆኑ ሳይወዱ በግድ ሌላ ወንድ ቢያስንቃቸው አይፈረድባቸውም"
ካርለት ቆጥ ላይ እንዳሉ እንዲህ በሐሳብ ተዘፍቃ ቆየችና እናቷ ትዝአሏት" ስለዚህ፣ ደብዳቤ ለመጻፍ ብዕርና ወረቀቷን
አስተካከለችና መጻፍ ጀመረች።
ውድ እናቴ፣
ምን ጊዜም እንደማፈቅርሽ፤ እንደማልምሽ የምትዘነጊ

👍23🤔1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ከሎ ሆራ ጥሩ ጥሩ የባራዝ አርጩሜ ይዞ እሱና ጎይቲ በሚዞሩበት መንደር ሲጓዙ በየምክንያቱ ጎይቲ አንተነህን በአርጩሜ
ይገርፋታል” ለሽንት ስትቆም ለምን ቆምሽ፣ እንቅፋት ሲመታት ለምን መታሽ፣ ደክሟት ቁጭ ስትል ለምን ቁጭ አልሽ እያለ
በየምክንያቱ እንዲገርፍ ባህሉ ያስገድዳል" ሴት ልጅ በኋላ ከቁጥጥር ውጭ ሆና እንዳታስቸግር፣ ባሏ እየገረፈ በማሽቆጥቆጥ ቅን ታዛዥ ሽር ያለች አገልጋይ እንድትሆን ያደርጋል"
ካርለት አልፈርድ ማስታወሻ፣ ካሜራ፣ ድንኳኗን በጨርቅ
ከረጢት ይዛ፣ የፍየል ቆዳዋን በመልበስ አብራቸው እየተጓዘች ከሎ
ጎይቲ የሚያደርጉትን ትቃኛለች የከሎ ዘመዶች ለከሎ የሚያደርጉለትን ስጦታም ትመለከታለች"
ከሎ ሆራ እናቱ ዘንድ ስጦታ ለመቀበል ላላ መንደር ሲሄድ፣ ካርለት እጅግ በጣም አዘነች" ከሎም በጣም ተሰማው። እናትዬዋ
እንዳዩት አቅፈው፣ አንገቱን ሲያሻሹ ቆዩና ካርለትና ሚስቱን ሰላም ብለው ትክዝ ብለው ቁጭ አሉ" ለልጃቸው ምን እንደሚያደርጉለት ጨነቃቸው። ለሱ ስጦታ ያዘጋጁለት መካከለኛ መጠን ያለው ሁለት
ቅል ቅቤና አንድ ቅል ማር ብቻ ነው ከሎ የእናቱን ሁኔታ አይቶ ኃዘን ተሰምቶት ዘወር ሲል፣ ካርለት ተጠጋቻቸው"
«ለምን ያለቅሳሉ?» አለች ትንሽ ዐረፍ ካለች በኋላ።
«ይእ! ልጄ የሚያስፈልገውን ያህል ስጦታ አላገኘማ።»
«እርስዎ ለልጅዎ የሚሰጡት ከብት፣ ፍየል... የለዎትም?»
«የለኝም»
«ለምን?»
«ይእ! እኔ ከብት፣ ፍየል... ኖሮኝም አያውቅም ወደፊትም አይኖረኝም" በልጃገረድነቴ ከብቶች፣ ፍየሎች፣ በጎች የአባቴ
ነበሩ" ባል ሳገባ ደግሞ፣ የባሌ ነበሩ። አሁን ባሌ ሞቷል፤ የከሎ አባት ቢኖር ለልጄ ብዙ ሀብት ይሰጠው ነበር።»
«የባልዎትን ሀብት አልወረሱም?
ይእ! ሚስት እንዴት የባሏን ሀብት ትወርሳለች? ባሏ ሲሞት ለወንድሙ በውርስ ትተላለፍና ወንድሙ ሌላውን ሀብት እንደ ወረሰ
እሷንም ይወርሳል። እኔም፣ ለባሌ ታናሽ ወንድም እያገለገልኩ እኖራለሁ"» አሁንም ባልቴቷ ፍዝዝ እንዳሉ ናቸው"
«ባልዎ የሞቱ ጊዜ መቼም እንዳሁኑ የበለተቱ አይመስለኝም፤ከታናሽ ወንድምየው ጋር ይቃበጡ ነበር?»
«ይ..እ ይሄማ ይጠየቃል፤ ባሌ እያለም ቢሆን ከታናሽ
ወንድምየው ጋር እንጨዋወታለን። እንዲያውም ከሎን የወለድኩት ከሆራ ሼላ ታናሽ ወንድም ነው።» ባልቴቷ ፈርጠም አሉ፣ የሞጨሞጨውን አይናቸውን ወደ ካርለት እየመለሱ።
«ምን? ማለቴ የከሎ ወላጅ አባት ሆራ ሼላ አይደለም ነው የሚሉኝ? የሚጠራው እኮ ከሎ ሆራ ተብሎ ነው።» ካርለት መልሱን ለመስማት ጓጓች።
«ይ..እ! በኛ ባህል አንድ ሴት ከባሏ ታናሽ ወንድም ልጅ ብትወልድ የልጇ አባት የሚሆነው ባሏ ነው። ባሏ እንኳ ሞቶ ከሌላ ወንድ ብትወልድ የልጇ አባት ስም በሟቹ ባሏ ስም ነው
ሚሆነው;»
«እና የከሎ እውነተኛ ወላጅ አባት በሕይወት አለ?»
«አዎን አለ።»
«አሁን እርስዎን የሚጦርዎ ማነው? »
«እሱና ልጆቼ።» ካርለት ይህ ለሷ እስከ አሁን ያልሰማችው አዲስ ነገር ነው" ከሎ ሆራም ስለ ወላጅ አባቱ የሚያውቅ አልመሰላትም" ምክንያቱም የግል ታሪኩን ሲነግራት አባቴ ሞቷል ብሎ ነበር።
ካርለት ወደ ከሎ ሄዳ ጉዳዩን ስትነግረው በጣም ተገረመ። ይህን ምሥጢር እሱ ቀደም ብሎ አያውቅም። ወደፊትም ለማወቅ የሚችል
አልመሰለውም።
«ካርለት አሁን የምትነግሪኝ ሁሉ ለኔ አዲስ ነገር ነውኮ፤
በጥረትሽ ወላጅ አባቴን እንዳውቅና እንዳገኝ እያደረግሽኝ እኮ ነው»
አላት ከሎ።
ካርለት፣ «ምንም አይደለም፣ ይልቁንስ አባትክን ማግኘ;
ይኖርብናል» አለችው።
።።።።።።፡፡።።።።።።።።።።።።
ጂሚ ሼላ ብዙ አላረጀም። ሰውነቱ ስላለው ጠንካራ ቢሆንም ዕድሜውን ከ60 በላይ ነው። ካርለትና ከሎ ሆራ እሱ ዘንድ ሲመጡ ከጎጆው ፊት ለፊት በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ ፀሐይ እየሞቀ አገኙት። ካርለት ጂሚን ስታየው ደንገጥ ብላ ከሎን ዞራ አየችው ከሎ ሆራና ጂሚ ሼላ በጣም ይመሳሰላሉ። ካርለት ጂሚን እንዳየች
ከሎ ሆራ አርጅቶ ከፊት ለፊት የተቀመጠ መስሏት ነበር"
ጂሚ ሼላ ከሎ ሆራን ለመጠየቅ ሻንቆ መንደር ሄዶ ሳለ ካርለትን
አይቷታል። ስለዚህ እንዳያቸው አወቃቸው" እነሱም ሄደው አጠገቡ
ቁጭ አሉና በሐመር ባህል መሠረት ዕረፍት ከወሰዱ በኋላ፣
«እንዴት ነዎት?» አሉት።
«ደህና ነኝ" እናንተስ እንዴት ናችሁ?» አለ ጂሚ ሼላ።
«ከሎ ለእርስዎ ምንዎ ነው?»
«የወንድሜ ልጅ ነው"» ጂሚ ካርለትን በተመስጦ
ተመለከታት።
«መልኩ ግን ቁርጥ እርስዎን ነው የሚመስለው?»
«ሆራ ሼላና እኔም እንመሳሰል ነበር እኮ።»
«ከሎ የእርስዎ ልጅ እንደሆነ ሰምቻለሁ" እንዴት ነው?»
ካርለት ዋናው ነጥብ ላይ ዘላ ጥቡልቅ አለች።
«እንዴት ተደርጎ?» ጂሚ ሼላ መልሶ ጠየቃት"
«እርስዎ ከከሎ እናት ጋር... ያረጉ አልነበረም? »
«ያማ ባህል ነው።»
«እና እንዴት ከሎ የማን ልጅ እንደሆነ ያጡታል?»
«ይሕ! በሐመር ባህል ልጅ ከወንድም ተወለደም፣ ከውሽማ በአባትነት የሚታወቀው ባል ነው። እኔም ከከሎ እናት ጋር ወንድሜ እያለም ሆነ፣ ከዚያን ወዲህ ግንኙነት ቢኖረኝም ከሎ ከማንኛችን
እንደ ተወለደ የምታውቀው እናቱ ብቻ ናት"»
ካርለት ነገሩ ገባት። «በሐመር ማኅበረሰብ የልጇን ትክክለኛ ወላጅ አባት የምታውቀው እናት ብቻ ናት ለካ!» ብላ፣ ተደንቃ
ቆየችና፣ «ለምን ስምዎ ጂሚ ተባለ?» አለችው፣ ጂሚ ሼላን።
«አንድ ጂሚ የሚባል ፈረንጅ እዚህ መጥቶ፣ ከአባቴ ጋር ተዋውቆ ነበር። እንዳጋጣሚ እናቴ እሱ ከዚህ ሳይሄድ እኔን ወለደችኝ በሐመር ባህል እንግዳ መጥቶ በአጋጣሚ ልጅ ቢወለድ ስሙ
በዚያው ሰው ስም ነው የሚጠራው።»
ካርለት ነገሩ ወዲያው ገባት" ምክንያቱም በዚህ መልክ በሷ ስም የሚጠሩ ሁለት ሕፃናት ታውቃለች
«የከሎ ሆራ እናት፣ የከሎን ትክክለኛ አባት ጠይቄያቸው እርስዎ እንደሆኑ ነገሩኝ» ስትለው፣ ጂሚ ምንም መልስ ሳይሰጣት ከሎ
ሆራን ዓይን ዓይኑን ሲያይ ቆየና እጁን ጎተት አድርጎ ያዘው" ከሎ የወላጅ አባቱ ጣቶች እጁን ሲነኩት፣ ደስታ አይሉት ኃዘን ቅጡ የጠፋ ስሜት በመላ አካሉ ተስለከለከበት" ትንሽ ቆይተው አባትና
ልጅ ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው ተቃቀፉ። የወላጅና ልጅ ፍቅር
በመካከላቸው ታየ ካርለትም የደስታ እንባ አነባች የሐመር ፀሐይ
ግን ወደ መሠወሪያዋ ወደቀች"
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከሎ ሆራ በፈቃድ ከዩኒቨርሲቲው በተገለለ በሁለተኛ ዓመቱ
ትምህርቱን ለማጠናቀቅ አዲስ አበባ ሄደ። ከሎ አዲሳባ ዩኒቨርሲቲ
ገብቶ ትምህርቱን ከጀመረ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለስቲቭ ደወለለት። ቀጠሮ ተሰጣጡና እሑድ ዕለት ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ከሎ
ከስቲቭ ቀድሞ በቀጠሮው ቦታ ተገኘ። ስቲቭ ልክ በሰዓቱ ሲገባ፣ከሎ ገና ከበሩ ወደ ቀኝ ሲታጠፍ ተመለከተው። ስቲቭ፣ የሆነ ፖስታ ይዞ የመሮጥ ያህል ሲራመድ፣ ከሆቴሉ ማዕዘን ላይ ካለው ሶፋ ላይ ነጫጭ ጥርሶቹን የሚያብለጨልጨውን ከሎን ተመለከተው። ስቲቭ
በማስብበት ወቅት ላገኝህ በመቻሌ በጣም ተደስቻለሁ» አለ ስቲቭ፣
የፈገግታውን መጠን እየጨመረ።

👍34🥰2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስሞንት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ካርለት የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የሥራ ፈቃዷን ልትጨርስ የቀራት አንድ ሳምንት ብቻ ነው ከዚህ በፊት ከአንድም ሁለት ጊዜ፡
የጥናት ፈቃዷን አራዝማለች" ዘመናዊው ሕይወቷን በመዘንጋት ለሐመሩ ንጹሕ ሕይወት ረክታለች" ዛሬ የሐመር ሕዝብ ለሷ የለንደን
ሕዝብ ነው።
ከእንግዲህ ወዲያ ካርለት ኢትዮጵያዊት ነች" ለንደን
የሥጋ ዘመዶቿ፣ ሐመር ደግሞ የመንፈስ ወዳጆቿ የሚገኙበት ነው" በዚህ ቀን ካርለት ከከሎ ጋር ስለ ማኅበረሰቡ የወደፊት ዕጣ
ተነጋግረው ነበርu ካርለት፣ «ሐመሮች በእርግጥ የሚያውቁት ራሳቸውን ነው ከነሱ ውጭ ያለው ዓለም ምን እንደሚመስል
አያውቁም። ይሁን እንጂ ከዓለማችን ውጭ በራሳቸው ደሴት
ተጠልለው ዝንተ ዓለም መኖር አይችሉም" ተወደደም ተጠላ
በክልላቸው ሳይንስ የፈጠራቸው ተሽከርካሪዎችና በራሪዎች
ያልፋሉ። ስለ እነሱ ሌላው ሲያውቅ፣ እነሱም ስለ ሌላው ለማወቅ መቻል አለባቸው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ድልድይ የሐመር ወጣቶች ሲሆኑ፣ የዘመኑን ትምህርት መቅሰም መቻል አለባቸው» ብላ ነገራዋለች" ከሎም ሐሳቧ የሱም እምነት እንደሆነ አረጋግጦላታል"
ካርለት፣ ሐመርን ለመልቀቅ የተወሰኑ ቀናት ሲቀራት ሆዷ
ተሸበረ ተጨነቀች" የገርሲ፣ ፌጦ፣ ኩንኩሮ፣ ጨዋንዛ፣ ግራር ዘንባባ፣ አጋም፣ ጠዬ፣ አንቃ፣ ሌሊሚ፣ ጨውሊምባ፣ ሾላ፣ ዋንዛ፣
እንኮይ...ደኑ የአሰሌ፣ የካራ ሰንሰለታማ ተራራ፣ የላላ፣ የሻንቆ፣የወሮ…መንደር፤ የሐመር ልጃገረድ፣ ጐረምሳ፣ አዛውንት፣
ሽማግሌ፣ ባልቴት ቀብራራው ደልቲ ገልዲ በአእምሮዋ እንደ
ፔንዱለም ባለማቋረጥ እየተመላለሱ (ጨክነሽ ጥለሽን ልትሄጂ እያሉ፣ ልቧን አንጠለጠሉባት።
ካርለት ቀሪውን ጊዜዋን ከብቱን፣ ሰውን፣ ጫካውን ፎቶ ስታነሣ ሰነበተች። ልቧ ግን እንደ ታረደ ዶሮ እየተነሣ ፈረጠባት ስትመጣ
ዳር ዳር ቆመው የተመለከቷት ሐመሮች የጕዞዋን ዜና ሲሰሙ
ሕሊናቸው ኩምሽሽ ብሎ ዓይናቸው በእንባ ሲሞላ ተመለከተች ስትቀርባቸው ሊወጓት ቀንዳቸውን ያዞሩባት የነበሩት ከብቶች
ጠረኗን እየፈለጉ ተጠግተው እጆቿን ላሷት።
ካርለት በሕይወቷ እንዲህ ልብ ሰራቂ የሆነ የሰውና የተፈጥሮ ፍቅር አጋጥሟት አያውቅም። ስለዚህ፣ ልቧ ደረቷን ሲረግጥ፣
ሕሊናዋ አነባ! ዓይኖቿም አለቀሱ።
ካርለት ሐመርን ልትለቅ አንድ ቀን ሲቀራት የኢቫንጋዲ ጭፈራውን ለመካፈል አሸዋማ፣ ገላጣና ዙሪያውን በለመለሙ የሐመር እፅዋት ተከቦ ፍቅር እየተቦካ ወደሚጋገርበት፣ ንብ አበባ
ወደምትቀስምበት፣ አዕዋፍና ሰዎች ጥዑም ዜማቸውን ወደሚያዜሙበት፣ የእፅዋት፣ የአራዊት፣ የአዕዋፍ፣ የሰው ዳንኪራ
ወደሚረገጥበት ስፍራ ተጓዘች።
ካርለት በኢቫንጋዲ ጭፈራ ወቅት ሁሌም እንደምታደርገው
ጀግናውን በዓይኖቿ አማተረች" ጀግናው እየዘለሉ አየሩን ከሚቀዝፉት ጐረምሶች መካከል የለም ካርለት፣ «አምላኬ!» ብላ፣
እንደ መኪና ጎማ ተነፈሰች" በጭንቀት ዓይኖቿ ሲቅበዘበዙ ግን ደልቲ ገልዲ ካለወትሮው ተክዞ፣ ራቅ ብሎ ቆሞ አየችው" ጀግናውን ተክዞ አይታው አታውቅም። ቀጭኔ፣ አንበሳ...የገደሉት አነጣጣሪ
ዓይኖቹ ቦዘው ስታይ ሰውነቷ ተዝለፈለፈባት። ጭንቀት ያዘለው ዶፍ
ዝናብ ሊያለብሳት መጣሁ ወረድሁ እያለ አጕረመረመባት። ካርለት
በደመ ነፍስ ወደ እሱ እየተንቀሳቀሰች፣ «ምን ሆኖ ይሆን?» ብላ ራሷን ጠይቃ ፊት ለፊቱ ሄዳ ቆመች።
«ካርለት» አላትና ዝም ብሎ ዓይን ዓይኗን ተመለከተ
«ምን ሆንክ ደልቲ?» ብላ ጠየቀችው።
ዝም ብሎ ዓይኖቹን ከሷ ላይ አንሥቶ ወደ ጨረቃዋ ወረወራቸው" ካርለት ዘለሽ እቀፊው እቀፊው አሰኛት።
ካርለት» አለ ደልቲ ዓይኖቹን ሳያወርድ።
«አቤት» አለችው:
ደልቲ ገልዲ ግን ዝም አለ ተመልሶ።
እንደ ባልጩት ድንጋይ እያብለጨለጨ የተከፋፈለው የጭኑና
አጁ ጡንቻ፣ ሣንቃው ደረቱ፣ የሚንቦገቦጉት ትናንሽ ዓይኖቹ በጨረቀዋ ብርሃን ካርለት ስታይ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋት
መላ አካሏ እሳት ላይ የወደቀ ቋንጣ ይመስል ኩምትርትሩ ወጣ"
«ወይ አምላኬ፣ ምናለ የልቡን በነገረኝ፤ ምናልባት
መለያየታችን አስጨንቆት ይሆን? መቼም ማለት የፈለገው ነገር አለ
ከአንደበቱ እንዳያወጣው ግን እየተናነቀው ነው» ብላ አሰበች"
ይህን ስታስብ፣ «ካርለት መሄድሽ ነው?» የሚል ከደልቲ ጕሮሮ አፈትልኮ ወጣ"
«አዎ መሄዴ ነው» አለች ካርለት፣ «ምን ሊለኝ ይሆን አምላኬ» ብላ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተችው» ደልቲ ግን አሁንም ጸጥ አላት።
«ትወደኝ ነበር?» ብላ የሞኝ ጥያቄ ጠየቀችው ደልቲ ግን ትክ ብሎ አይቷት፣ «አይ» አላት፣ በምፀት" ካርለት መልሱ ከልቡ እንዳልሆነ በሚገባ ተረዳች" ካርለት ያኔስ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆነች ጀግናው እንደገና ጣላት። ስለዚህ፣ እጇን ሰዳ እጁን ያዘችውና ወደ
ሰንበሌጡ ይዛው ገባች“ ከዚያ ጭፈራው በዓይነት በዓይነት ቀጠለ ዳንኪራው ተመታ። አሁንም እንደ ባለፈው ተመልካች በሌለበት የተፈጥሮ አዳራሽ ትርዒታቸውን ለራሳቸው አሳዩ። ዳንኪራው ግን
እንዳለፈው ተስፋ ሰጪ ሳይሆን ለየት ያለ፣ የሰቀቀን፣ የኃዘን፣
የህምታ ውዝዋዜ ሆነ።
በነጋታው ፀሐይ ከወደቀችበት ተነሥታ ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ ካርለት ዕቃዎቿን በስቴሽን ዋገን መኪናዋ ላይ ከከሎ ጋር አስተካክለው ጭነው እንደ ጨረሱ ሐመሮች ከየመንደሩ ተሰባስበው
ሴቶቹ ደረታቸውን እየደቁ ሲያለቅሱ፣ ወንዶቹ በርኮታቸው ተቀምጠው ተከዙ። ካርለት ዓይኗ በእንባ ሊጠፋ ተቃረበ" የሁለት
ዓለም ዘመዳሞች ሲለያዩ አምርረው አዘኑ"
ካርለት፣ ከሎ ሆራና ጎይቲ በሽማግሎች ተመርቀው፣ ጀርባቸው በከብት እበት ከተቀባ በኋላ ሦስቱም መኪና ውስጥ ገብተው መኪናዋ ተንቀሳቅሳ አቧራው ሲነሣ የሐመር ጭንቅላቶች ወደ መሬት
አቀረቀሩ" ካርለት ትንሽ ከተጓዘች በኋላ ኢቫንጋዲ የጨፈረችበትንና
የቦረቀችበትን የሐመር ጫካ ለመሰናበት መኪናዋን አቁማ ስትወርድ፣ ከሎና ጎይቲም አብረው ወረዱና እንባቸውን አወረዱ..
ወፎች ግን እየዘመሩ፣ ቱር እያሉ እየበረሩ፣ እየተዳሩ ምግባቸውን መፈለጋቸውን አላቆሙም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዋናው የመኸር ወቅት የሐመር የተፈጥሮ ውበትና ልምላሜ የክቱን አውጥቶታል" እፅዋት ለምልመው አብበዋል የከስኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ሆኖ ይፈሳል። የቡስካ ተራራ አሁንም ከቦታው ሳይንቀሳቀስ የሐመሮች የታሪክ ሐውልት ሆኖ ፈገግታውን በልምላሜ ያሳያል"
ከአሰሌ ሰንሰለታማ ተራራዎች እስከ ኬንያ ጠረፍ፣ ከኤርቦ እስከ አሪ ማኅበረሰብ የሐመሮች ዘፈንና ዳንኪራ አሁንም ከጫፍ እስከ ጫፍ ያስተጋባል። የሐመር ተፈጥሮ ለሰዎች ብቻ ሳይሆን ከድንቢጥ ወፍ እስከ ጥንብ አንሳ ጆፌ አሞራ፣ ከትል እስከ ተሳቢው
ዘንዶ ከከብት እስከ ሚዳቋና ድኩላ ይፈነጭበታል"
ሁሉም የተፈጥሮ ድምፁን ባሰማ፣ እንቅስቃሴ ባደረገ ቁጥር ውብ የሙዚቃ ቅማሬ ከጋራ ጋራ፣ ከቋጥኝ ቋጥኝ ይስተጋባል" የሐመር ምድር ለሚመጡትም ለሚሄዱትም ሁሌም ያው ነው" መለምለም፣ ማበብ፣ መጠውለግ፣መድረቅ..ተልሶ ደግሞ መለምለም።
ደልቲ ገልዲን መኪናዋ የሚወዳቸውን ጭና በአራት እግሯ ከቡስካ በስተጀርባ ተሠውራበታለች መዝናኛዎቹ፣ መደሰቻዎቹን
ሌባዋ ይዛ በአቧራ ደመና ገብታ ጠፍታበታለች" ደልቲ አሁን ሁለት እግር ያለው ከሌላ ፍጡር ያልተለየ መሆኑን ሳይረዳ አልቀረም
የጎሽን ጀርባ በአንድ ምት ብቻ አከርካሪውን አድቅቆ
የሚያንበረክከው አንበሳ መጨረሻ የዝንብ መዝናኛ መሆኑ የማይቀር እውነት መሆኑን ደልቲ የግድ ሊመለከተው፣ ሊደርስበት ነው"

👍28❤3
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ልክ በስድስተኛ ወሩ እንግሊዝ አገር ውስጥ በሚገኘው የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ሁለት ቆዳ ለባሽ ሴቶች፣ አንድ
ሳዳጎራ ያገለደመ ወጣት፣ ተቃቅፈው በመግባት ቦታቸውን ይዘዋል"
አፉን ከፍቶ የነበረው አዳራሽ ቀስ በቀስ ሞልቶ ተጨናነቀ" የዕለቱ
አንትሮፖሎጂካዊ ጥናት አቅራቢ የአፍሪካ ውስጥ ምርምሯን ይዛ ወደ መድረክ ወጣች።
«…ክቡራትና ክቡራን፣ በተመራማሪነቴ የሠለጠነው ዓለም
ከረሳው ተፈጥሮና ሕዝብ መካከል ተገኝቼ፣ ለዘመናት የዳበረ ባህልና ጥበብ ያለውን ክልል ለማየትና ሕይወቱንም ለመኖር ችዬ እኔ ያገኘሁትን ዕውቀት ለቀሪው ዓለም ሕዝብ ለመግለጽ በመብቃቴ
ደስታዩ ወደር የለውም።
«የሐመር ተፈጥሮ፣ ሰው ሠራሽ ብክለት ያልተጠናወተው ንጹሕ
ተፈጥሮ ነው። በዓለማችን ፍጹም ደስታ ያለው ሕዝብ አለ የሚል እምነት የለኝም" ደስተኛ ሕዝብ አለ ከተባለ ግን ከሐመር ሕዝብ
የበለጠ ደስተኛ፣ ግልጽ፣ በመካከሉ ጠንካራ መፈቃቀር ያለው ያለ
አይመስለኝም።
«በዘመናችን እንደ ብርቅ የሚታየው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሐመሮች ለብዙ ዘመናት የሕልውናቸው የማዕዘን ድንጋይ አድርገውት ኖረዋል" ከዚህ በተጨማሪም፣ የሐመሮች የዳበረ የከብት አረባብ ዘዴ፣ የአመጋገብ ሥርዓት፣ ብሒሎችና ትውፊቶች ወዘተ.ዝብርቅርቁ የወጣውን የዘመነውን ዓለም ዓይነ ልቦና የሚስብ
እንደሆነ አምናለሁ።
«...ለማጠቃለል
ያህል፣ እኔ የምናገረው የማውቀውን ብቻ
ሳይሆን የሚሰማኝንም ጭምር ነው" በእርግጥ ሐመር ላይ ሊሻሻሉ፣
ሊያድጉና እገዛ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ቁም ነገሮች እንዳሉ
አምናለሁ" ሆኖም ግን ከሠለጠነው ዓለም የአካባቢ ብክለት ችግር፣
የበሽታ መስፋፋት፣ ተፈጥሮአዊ ካልሆነ የአኗኗር ሥርዓት ችግር አንፃር የሐመር ተፈጥሮ ማራኪ ነው" ሕዝቡም ንጹሕ ሕሊና፣የዳበረ የአኗኗር ልምድ፣ ተፈጥሮአዊ ፍቅርና በራሱ የሚተማመን
ሕዝብ መሆኑን ሳረጋግጥ በዓለማችን እውነቱን በመመስከር ከታወቁት ምስክሮች ራሴን እንደ አንዱ እቈጥረዋለሁ።
«..ቀሪው ዓለም አፍሪቃውያንን መርዳት ብቻ ሳይሆን፣አሁንም ከአፍሪቃውያን ብዙ የሚማረው እንዳለ ማወቂያው ጊዜ
አሁን ነው» የሚለው፣ በጽሑፍና በተንቀሳቃሽ ሥዕል የተደገፈው
ጥናቷ ተመልካቿን ከመቀመጫው ናጠው።
ተመራማሪዋ በባዶ እግሯ፣ ቆዳዋን እንደ ለበሰች ጥናቷን ስታቀርብ ቆይታ ስታጠቃልል ያችን ችግርና ሰቆቃ ተቋቁማ፣ የሁለቱን ዓለም ልዩነትና አለመግባባት አስወግዳ፣ እውነተኛ ሰብአዊ ፍቅርንና ሕይወትን ያሳየች ተመራማሪ የአድናቆት ጭብጨባና ጩኸት ለደቂቃዎች በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ
በማይታወቅ መልክ ቀረበላት። ካርለት አልፈርድ ተባባሪዋንና ጓደኞቿን ይዛ ወደ መድረክ ስትወጣ ጭብጨባው ይበልጥ ጋለ"
ከሎና ጎይቲም ሕሊናቸው በደስታ ረካ።
ሦስቱም ጓደኛሞች በሐመር ደን መካከል እንዳደረጉት ሁሉ፣በማንቸስተሩ የጉባኤ አዳራሽም ተቃቅፈው አነቡ እየሣቁ አለቀሱ።
በአውሮፓ ሕይወት ከሎ ብዙውን ጊዜውን በትምህርት አሳለፈ
ጎይቲ ግን ከካርለት ቤተሰቦች ጋር ተቀመጠች" ጎይቲ በዓይን ማየት
ቀርቶ በወሬ እንኳን በአሳለፈችው ሕይወት ያልሰማችው ጉድ ውስጥ
ስትገባ በእውኗ መቃዠት አበዛች።
ከካርለትና ከከሎ ጋር መጀመሪያ ከሐመር ሲነሡ የመኪናው ጕዞ ደስ ብሏት ነበር" ከካርለት ጋር በመኪና መካ፣ ቱርሚ፣ ጂንካም
ሄዳ ስለነበር እንደ ልማዷ መኪናዋ ስትጓዝ የሐመር ሰዎችና እፅዋት ወደ ኋላ ሲሮጡ እሷ በሣቅ ፍርስ ብላለች" አንዴ ወደፊት፣ አንዴ ወደኋላ ስታይ እንደ ቆየች ግን የሆነ ነገር ሆዷን አሸበራት" ወዲያው
ለካርለትና ለከሎ፣ «ይእ! አያችሁልኝ የኔን ነገር አገሩን ሁሉ ስሰናበት አያ ደልቲን ግን ሳልሰናበተው ስመጣ? ምናለ እናንተዬ
ብትመልሱኝ? አሁን ባል በማግባቴ አንጀቱ የተኰማተረው አንሶት
መሄዴን ሲሰማ ሆዱ መንቦጫቦጩ ቀረ! ጀግና ሰው ልቡ ቶሎ
ይቀየማል» አለች።
«ጎይቲ አሁንማ ብዙ ርቀን መጥተናል" ቀደም ብለሽ አስበሽው ቢሆን ኖሮ ብንመለስም አይከብድም ነበር" አሁን ግን ብዙ ርቀናል" አንቺስ አያ ደልቲ የሚገኘው ከስኬ ወንዝ አሸዋ ላይ ተጋድሞ
መሆኑን እያወቅሽ ለምን ሄደሽ ሳትሰናበችው ቀረሽ?» አላት ከሎ
«ይእ! እናንተ ልቤን አጠፋችሁታ" እንዲህ አሁን ሆዴን ሊያጥወለውለኝ እዚች መኪናይቱ ላይ መውጣቱም አጓጓኝና
እረሳሁት እንጂ ምነው እናንተዬ ኧረ ኃዘኑ ቅስሙን ይሰብረዋል"ጀግና ሰው ዕድሜው አጭር ነውI መርቀኝ፣ ላገርሽ ያብቃሽ በለኝ ሳልለው ወጥቼ ስመለስ ባጣው ጸጸቱ ዕድሜ ልኬን ይወጣልኛል?» አለች"
«ጎይቲ አያ ደልቲን አሁንም ታልሚዋለሽ ማለት ነው። ድሮ የተቃበጣችሁት አይበቃም?» አላት ከሎ ፈርጠም ብሎ"
«ይእ! ኧረ እይልኝ የአያ ደልቲ ጨዋታ እንደ ከተማ ልብስ የሚወልቅና
የሚታጠብ መሰለህ! ሆድ ዕቃ ውስጥ ነው የሚቀመጥ ያ ደልቲ አንፈራጦ ብቻውን ይዞት የነበረውን ስፍራ አንተ ገብተህ እሱን ወደ ጥግ ወሰድከው እንጂ ከሆድ
አልጣልከው" እኔና እሱ የአንድ ጎሳ ልጅ መሆናችንና አንተ ባዕድ ሆንህ እኔና አንተን አገናኘን እንጂ የዚያ ጀግና ሎሌ ሆኜ ብኖር
ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር» ብላ በሣቅ ስትፍለቀለቅ፣ ካርለትና ከሎአብረው አጀቧት።
ካርለት ጎይቲ በሐመርኛ ቋንቋ የተናገረችውን ካዳመጠች በኋላ፣
«ምነው ሰው ሁሉ እንዳንቺ ግልጽ በሆነ፣ እውነተኛ ስሜቱን ባልደበቀ እዚህ ወርቅ መሳይ ብልጭልጭ ዓለም እውነተኛው ወርቅ
ሕይወት ሐመር ላይ አለ ቢሉት ማን ጆሮውን ይሰጣል" መተማመን
ቀርቶ መጠራጠር ዘውድ በጫነበት በዚህ የውሸት ዓለም እስከ መቼ መኖር ይቻላል?» ብላ፣ ስታስብ ካይኖቿ ስር መጀመሪያ ጉም መሰለ ነገር፣ በኋላ ተከታትሎ እየተስረገረገ የሚንኳለል ትኵስ እንባ
ዓይኗን ሲሞላ፣ መኪናዋን አቁማ መሪው ላይ ተደፍታ መንሰቅሰ ጀመረች።
ጎይቲ መጀመሪያ ካርለት እየሣቀች መስሏት ነበር" የቀላው? ፊቷንና የራሰውን ዓይኗን ስታይ ግን ልቧ በኃዘን ተሰብሮ ቆየችና፣
“ይእ! ምነው አይደክማት እሷ ብቸዋን ደፋ ቀና እያለች እኛ ዝም አልናት። በይ አንቺስ ከምታለቅሺ ዕርዱኝ አትይም? እንደ እርፍ
ወዲያ ወዲህ የምታማስይውን እንደሁ አያቅተኝም። መዘወሩንም
ቢሆን አላጣውም» አለቻት
«ጎይቲዬ አመሰግናለሁ" መንዳቱ ለአንቺ እንኳ ይhብድሻል ባይሆን መኪናውን ከሎ ያሽከርክር፣ ወደፊት ግን አንቺም
ታሽከረከሪያለሽ» ብላ ቦታዋን ለቀቀችለት"
ጎይቲ አንተነህ ደስ ያላት ጕ" እያንገሸገሻት ሄደ" አንገቷ
ደፍታ የማታውቀው ጎይቲ ሆዷን አቅፋ፣ አንገቷን አዘነበለች
ጎይቲ በአውሮፕላኑ ጕዞም ሆነ በአውሮፓው ሕይወት ቋንቋውን ገጽታውን የማታውቀው ትያትር ተመልካች ሆና ሁሉም ነገር
ታከታት። ኵሩው አረማመዷ ስብር ስብር አለ ጥርሶቿ በከንፈሮቿ በጥብቅ ተጋረዱ" የሐመሯን ሸጋ ህምታ ሰፈነባት" ፀሐይ ከእሷ በጣም ርቃ ሙቀቷ ሳይሰማትና ብርሃኗ ሳያስደስታት ወጥታ ገባች
ጨረቃን ከናካቴው ከሰማይ ላይ አጣቻት" ሲያዩት የሚያብለጨልጨውና የሚያምረው ሰው ሠራሽ ውበት፣ እየቆዩ በሄዱ ቁጥር
እያፈናት መጣ" መለምለም፣ ጠውልጎ መድረቅ፣ ተልሶ
መለምለም የማያውቀው የተፈጥሮ ቅመም የጎደለው የቴክኖሎጂው
ዓለም ለውጥ አልባ በመሆኑ እጅ እጅ አላቸው። ንጹሕ አየር፣ ተለዋዋጩ የተፈጥሮ ውበትና የሚያውደው መዓዛ፣ የአዕዋፍ ዝማሬና
የአውሬዎች ጩኸትና ግሳት፣ የጨረቃ ወቅት ዳንስና ጣፋጩ የጫካ
ውስጥ ፍቅር በእዝነ ሕሊናቸው ውል እያለ አስቈዘማቸው"

👍29😁1