#ጌትዬ
አመመኝ
ከመውደቄ ብዛት ፣ መነሣት ደከመኝ፤
አትመርምረኝ
ማረኝ፤
ምራኝ፤
ጥራኝ፤
ለዓለም አልሆንኩም ፣ ለዓለሞህ ሥራኝ፤
ኝ የማበዛብህ
ኝ የምጠራብህ
እኝኝ ያለ ዘመነ ነፍሴን ቢያደክሞብህ፤
ብትጠራኝ ብዬ
ጠራሁህ ጌታዬ፤
እስቲ ወዬ በላኝ
አንተን ዘነጋሁኝ ሰው እየደለለኝ ቦታህን
ሲወርሰው፤ተአብየና እብሪት ራሴን
ስለኩስ ፤ በገሃነብ ክብሪት
ስነድ እያየከኝ
ዝም ለምንድን አልከኝ?
ይኸው ስንት ኖርን?
ይኸው ስንት አኖርን?
ስለኖርን ምን አመጣን?
ከምላስ ቤት መቼ ወጣን?
ላንተ እንለው አጣን፤
ቁጣው ተውና ፣ በቁንጥጫ ቅጣን፤
አባትም አይደለህ ጨክነህ አትጨክን
እናትም አይደለህ ፣ ፍቅር አታባክን፤
ልክ ነህ ትክክል
ካንተ ሌላ ክልክል፤
ፍጹም ነው ዐመልህ፤
አንተን ምን ሊያክልህ፤
አንተን ማን ሊያክልህ፤
አንደ መስመር ኑሮ፣
ሲቸከቸክ ዞሮ
ቃል እየደገመ፧
ሥጋ እየታመመ፤
ነፍስ እየጠመመ፤
ሐቅ እየዘመመ፤
ቀን ከተበላሸ
ነገ ተኮላሸ፤
የከበቡ ሁሉ፤
ወዳጅ ተባባሉ፤
እኔስ ለብቻዬ፤
መጮኸ ነው ጌታዬ፤
እዬዬ ... እዬዬ
ጀማ ሁነኝ ብዬ፤
አሁንስ ደከመኝ፤
እዚህ እውነት የለም ፤ አንተጋር አስቅመኝ፤
አትመርምረኝ፤
ማረኝ፤
ምራኝ፤
ጥራኝ፤
ለዓለም አልሆንኩሞ፣ ለዓለምህ ሥራኝ፤
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
አመመኝ
ከመውደቄ ብዛት ፣ መነሣት ደከመኝ፤
አትመርምረኝ
ማረኝ፤
ምራኝ፤
ጥራኝ፤
ለዓለም አልሆንኩም ፣ ለዓለሞህ ሥራኝ፤
ኝ የማበዛብህ
ኝ የምጠራብህ
እኝኝ ያለ ዘመነ ነፍሴን ቢያደክሞብህ፤
ብትጠራኝ ብዬ
ጠራሁህ ጌታዬ፤
እስቲ ወዬ በላኝ
አንተን ዘነጋሁኝ ሰው እየደለለኝ ቦታህን
ሲወርሰው፤ተአብየና እብሪት ራሴን
ስለኩስ ፤ በገሃነብ ክብሪት
ስነድ እያየከኝ
ዝም ለምንድን አልከኝ?
ይኸው ስንት ኖርን?
ይኸው ስንት አኖርን?
ስለኖርን ምን አመጣን?
ከምላስ ቤት መቼ ወጣን?
ላንተ እንለው አጣን፤
ቁጣው ተውና ፣ በቁንጥጫ ቅጣን፤
አባትም አይደለህ ጨክነህ አትጨክን
እናትም አይደለህ ፣ ፍቅር አታባክን፤
ልክ ነህ ትክክል
ካንተ ሌላ ክልክል፤
ፍጹም ነው ዐመልህ፤
አንተን ምን ሊያክልህ፤
አንተን ማን ሊያክልህ፤
አንደ መስመር ኑሮ፣
ሲቸከቸክ ዞሮ
ቃል እየደገመ፧
ሥጋ እየታመመ፤
ነፍስ እየጠመመ፤
ሐቅ እየዘመመ፤
ቀን ከተበላሸ
ነገ ተኮላሸ፤
የከበቡ ሁሉ፤
ወዳጅ ተባባሉ፤
እኔስ ለብቻዬ፤
መጮኸ ነው ጌታዬ፤
እዬዬ ... እዬዬ
ጀማ ሁነኝ ብዬ፤
አሁንስ ደከመኝ፤
እዚህ እውነት የለም ፤ አንተጋር አስቅመኝ፤
አትመርምረኝ፤
ማረኝ፤
ምራኝ፤
ጥራኝ፤
ለዓለም አልሆንኩሞ፣ ለዓለምህ ሥራኝ፤
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
❤19👍13👏2🤔1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
አጸፋ
ምሽቱ አልቆ ሊነጋጋ ስለነበር የምሥራቅ ፀሐይ ውጋጋን ታየ፡
ፋንቲን በኃይል እያተኮሳትና እንቅልፍ ሳይወስዳት ነበር ያደረችው::አስታማሚዋ ሴር የፋንቲንን ሁኔታ በማየት መድኃኒት ለመፈለግ ሄዱ፡፡መድኃኒቱን እየፈለጉ ሳለ ዞር ሲሉ መሴይ ማንደላይንን በድንገት
በማየታቸው ሳያስቡት ይጮሃሉ:: መሴይ ማንደላይን እርሳቸው ከነበሩበት ክፍል ገና መግባቱ ነበር፡፡
«መጡ እንዴ ጌታዩ!» አሉ፡፡
«ያቺ ምስኪን እንዴት ናት?
«አሁን ትንሽ መለስ ብሉላታል:: በጣም ሲያማት ጊዚ ተጨንቀን
ነበር፡፡ ፋንቲን ግን ክቡር ከንቲባ ከዚህ የጠፉት ልጄን ሊያመጡ ቢሄዱ ነው ብላ በማመንዋ ነው መለስ ያለላት በማለት ለመሴይ ማንደላይን ሴርዋ አስረዱ:: ሴርዋ ምንም እንኳን ወደ ልጅትዋ አለመሄዱን ቢያውቁም ጥያቄ
መጠየቅ ኣልደፈሩም::
“ደህና ናታ!›› አለ፡፡
“ታዲያ አሁን ልጅዋን እለማምጣትዎን እንዴት እድርገን ነውዐየምንነግራት? » ሲሉ ሴርዋ ጠየቁ፡፡
ጥቂት አሰበና «እሱ ይመራናል» አላቸው::
ግን መዋሸት የለብንም» አሉ ሴርዋ በዝግታ፡
መስኮት ስለተከፈተ የመሴይ ማደላይን ገጽታ በጉልህ ታየ
«እንዴ፣ ምን ሆነዋል!» አሉ አስታማሚዋ:: (ገጸዎ በጣም
ተለዋውጧል::»
«ተለዋውጧል!» አለ፡፡
መስታወት አነሱ:: እርሱም መስታወቱን ተቀብለ መልኩን ከየ::
«እውነትም ተለዋውጫለሁ!» ሲል አረጋገጠ፡: ግን ይህን ያለው
አሳቡ ለሁለት ተከፍሎ እንደሆነ ያስታውቅበት ነበር::
ሴርዋ አነጋገሩና ጠቅላላ ሁኔታውን ሲያዩ ቀፈፋቸው:: መሴይዐማንደላይን ሊከፍተው ሲል አልከፈት ስላለህ በር አስተያየት እየሰጠ
ፋንቲን ከነበረችበት ክፍል ገባ፡፡ የመስኮት መጋረጃዎችን ገለጠ፡፡ ወደ ፋንቲን ጠጋ ብሎ አያት፡፡ እንቅልፍ ወስዷት ነበር፡፡ ስትተነፍስ እያቃሰተች ነው:: ፊትዋ ፍም መስሎአል፡፡ ቆዳዋም ገርጥቶአል::
መሴይ ማንደላይን ሳይነቃነቅ ከአልጋዋ አጠገብ ቆሞ አተኩሮ
ተመለከታት፡፡ አንዴ ወደ እርሱ አንዴ ደግሞ ከግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ወደ ነበረውና ክርስቶስ ወደ ተሰቀለበት መስቀል ተመለከተ፡፡ ከሁለት ወር
በፊት ፋንቲን አሞአት ከዚያች ክፍል ውስጥ ስትተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊጠይቃት ሲሄድ እንቅልፍ ወስዷት እንደተመለከታት ዓይነት ነበር አሁንም ያያት:: አሁንም እንደዚያኑ እለት እርሱ ሊጸልይላት እርስዋ እንቅልፍ ወስዷት ተኝታለች:: ልዩነቱ ከሁለት ወር በኋላ የእርስዋ ፀጉር በይበልጥ
ሽበት ጣል ጣል ሲያደርግበት የእርሱ ፀጉር በሽበት ተሸፍኖ ነጭ ሆኖአል።
ሴርዋ አብረው ወደ ክፍሉ አልገቡም:: ሰውዬው በአንድ እጁ
ከንፈሮቹን ይዞ ነው የቆመው:: ፋንቲን ዓይኖችዋን ስትገልጥ አየችው::
ፈገግ ብላ፡
«ኮዜትስ?» ስትል ጠየቀችው::
«ኮዜትስ» ብላ ስትጠይቀው ልክ ይዞአት እንደመጣ አረጋግጣ በማመን ስለነበር ምን ብሎ እንደሚመልስላት ባለማወቁ ዝም ብሉ ተገትሮ ቀረ።
ይህን ጊዜ እርስዋ ንግግርዋን ቀጠለች፡፡
«ልጄ ጋ እንደሄዱ ተስፋ አደርጋለሁ:: እንቅልፍ ወስዶኝ ነበር፤ ግን አይቼዎታለሁ:: ብዙ ጊዜ አይቼዎታለሁ:: ሌሊቱን በሙሉ ዓይኔ እርስዎ
ተከትሎ ነው የሄደው:: መላዕክትም እርስዎን ተከትለው ሲሄዱ ነበር ግርማ ሞገስዎ ደግሞ በጣም... በጣም ደስ ነበር የሚለው፡፡
ቀና ብሎ ከሴትዮዋ ራስጌ የተንጠለጠለውን መስቀል አየ፡፡
‹ግን ንገሩኝ እስቲ፣ ኮዜት የት አለች? ከእንቅልፌ ስነቃ እንዳያት
ለምንድነው ከአጠገቤ ያላስተኛችሁዋት?»
ሳያስበው በድንገት አንድ ነገር ተናገረ፡፡ ደግነቱ ምን እንዳለ በትክክል ሳይሰማ ሐኪሙ በር ከፍተው ገቡ::
«የእኔ ልጅ» አሉ፤ «ረጋ በይ! ልጅሽ መጥታለች፡፡»
የፋንቲን ዓይን እንደ ብርሃን በራ:: በደስታ ብዛት መላ ሰውነትዋ
ተቅበጠበጠ፡፡ እጇን በኃይል አሻሸችው::
«ወይ ልጄ! አምጡልኝ ልያት?» ስትል ጠየቀች፡፡
ያኔ እንደተወቻትና እሽሩሩ እንደምትባል ፉልቁ ሕፃን እንደሆነች አድርጋ በመገመት ልታቅፋትና እሽሩሩ ልትላት ፈለገች::
«አትቸኩይ» አሉ ሐኪሙ፤ «ሰውነትሽ እንደዚህ ደክሞ ከእርስዋ ጋር መጫወት አትችይም፡፡ ከልጅሽ ጋር አሁን በድንገት ብትገናኙ ሲቃ
ይዞሽ ክፉ ነገር ላይ ሊጥልሽ ስለሚችል ትንሽ ብትታገሽ፡፡ መጀመሪያ እኛ አንቺን በቅጡ ማዳን አለብን፡፡
መሴይ ማንደላይን ከአልጋው አጠገብ ወንበር ላይ ተቀምጦአል፡፡
ፋንቲን ወደ እርሱ ዞር ብላ «ግሩም ድንቅን ኣለች:: ስታየው መንፈስዋን
በጣም አረጋግታ ስለነበር ምናልባት «አሁንስ ተሽሉአታል፤ ልጅዋን ብታይ ምንም አትሆንም» ብሎ ያስባል ብላ ከእርሱ ጋር ጨዋታ ቀጥላ በጥያቄ
አጣደፈችው::
«ታዲያ መንገዱ ደህና ነበር? እንዴት የተባረኩ ሰው ቢሆኑ ነው
ለልጄ ብለው ከእዚያ ድረስ መልፋትዎ? መቼም እኔን እንኳን ሳትረሳኝ አትቀርም:: ልጆቹ እኮ ቀላል ፍጡሮች አይደሉም:: የለበሰቻቸው ልብሶች ንጽህናቸው የተጠበቀ ነው? እነሚስተርና ሚስስ ቴናድዬ በንጽህና ነበር
የያዝዋት? ሰውነትዋስ እንዴት ነው? እንዴት ነው የናፈቀችኝ! ቆንጆ ልጅ አይደለችም ክቡር ከንቲባ? በጨለማ ስትጓዘ መንገድ ላይ እኮ ብርድ ሳይጉዳችሁ አልቀረም:: አንድ ጊዜ ብቻ እንዳያት ለአንድ አፍታ ልታስጉቡዋት አትችሉም? ወዲያው ትሄዳለች፡፡ የቤቱ ጌታ- እርስዎ ኖት ፤ ታዲያ ይህን
አይፈቅዱልኝም? መሴይ ማንደላይን እጅዋን ያዘ፡፡ «ኮዜት በጣም ቆንጆ ናት» አለ:
“ጤነኛ ናት ፤ አትቆዩም ፤ ታያታላሽ:: አሁን ግን ብዙ አትናገሪ ! ይደክምሻል:: ደግሞም ሳልሽ እንዳይቀሰቀስ አትገለጭ::
እርሱ ይህን እንዳለ በሃይል አሳላት:: እጅዋን እንደያ፤ በጭንቀት ዓይን ተመለከታት:: አባበ የደረሰበትን ሊነግሪ ት ነበር፡፡ ግን በዚህ ሁኔታ እንዴት ብሎ ይንገራት! ሐኪሙ ካያት በኋላ ወጥቶ ሄደ:: ሰርዋ ከክፍሉ ውስጥ አብራቸው ቆዩ:: ሁሉም ዝም፣ ዝም ተባብለው ነበር
ፋንቲን በድንገት ጮኸች::
«ድምፅዋን ሰማሁት፤ ወይኔ ልጄ! ድምፅዋን ሰማሁት!»
በአካባቢው የጎረቤት ልጅ ነበረች፡፡ ያጋጣሚ ነገር ይህች ልጅ፤ብቻዋን እያወራች ትሮጣለች:: ትምህርት ቤት የተማረችውን ዘፈን እያዜመች
ነበር የምትሮጠው:: ፋንቲን የሰማችው የዚህችን ልጅ ድምፅ ነበር፡፡
«ውይ. ይ፧ የእኔይቱ ኮዜት እኮ ናት! ድምፅዋንኮ አውቀዋለሁ
አለች::
የልጅትዋ ድምፅ እየራቀ ሄደ:: ድምፆዋ ቢርቅም ፋንቲን ለመስማት ሞከረች:: ድምፁ ጨርሶ ሲጠፋ ጥላ የተጠለለባት መሰላት፡፡ «ምን የተረገሙ
ሐኪም ናቸው፤ ልጄን እንዳላይ የሚከለክሉኝ» አለች በማጉረምረም።
ሆኖም ውስጥ ውስጧን ደስ ብሎአታል፡፡ ትራስዋን በእጅዋ አቅፋ ይዛ እርስ በራስዋ መነጋገርዋን ቀጠለች፡፡ «እንዴት ደስ ብሎኝ ነው የምኖረው
የአትክልት ቦታ ይኖረኛል፡፡ መሴይ ማንደላይን እንደሚሰጡኝ ቃል ገብተውልኛል፡፡ ልጄ ከሳሩ ላይ እየፈነደቀች ትጫወታለች፡፡ ከዚያ ቁጭ ብለን ደግሞ
«ተረት ተረት» እያልን እንጫወታለን፡፡ ኮዜት ቢራቢሮ ለመያዝ ስትሮጥ እኔ ቁጭ ብዬ አያታለሁ፡፡ ታዲያ ይሄ መቼ ይሆን የሚሆነው?»
በጣቶችዋ መቁጠር ጀመረች:: «አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት፣ አራት፡፡
ሰባት ዓመት ይሆናታል ማለት ነው:: ከአምስት ዓመት በኋላ እኮ አንገትዋን መስበር ትጀምራለች:: ያኔማ እህትዋ ናት ነው የምትባለው::»
በአሳብዋ ተገርማ መሳቅ ጀመረች፡፡

👍17
መሴይ ማንደላይን የፋንቲንን እጅ ለቀቀ:: የሚነፍስ ነፋስን እንደሚሰማ ሰው ፋንቲን የተናገረችውን አቀርቅሮ አዳመጠ፡፡ ፋንቲን በድንገት ንግግርዋን አቆመች፡፡ ቀና ብላ አካባቢዋን ቃኘች:: ሰውነትዋ በፍርሃት ተንቀጠቀጠ፡፡
ከዚያ በኋላ ቃል አልተነፈሰችም:: ከተኛችበት አልጋ ቀና አለች።
ከደረትዋ በላይ ራቁትዋን ሆነች:: ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እንደዚያ ልብ ዘርታ ትጫወት የነበረችው ሴትዮ አሁን በድንገት ተለዋወጣ ዝልፍልፍ አለች::
«ያንተ ያለህ! ምነው ፋንቲን፤ ምን ነካሽ?» ሲል መሴይ ማንደላይን
ጠየቃት::
መልስ አልሰጠችውም:: አፍጥጣ ትመለከትበት ከነበረው አቅጣጫ
ዓይንዋን አላዞረችም:: በአንድ እጅዋ የመሴይ ማንደላይንን እጅ ጨብጣ በሌላው እጅዋ ወደኋላው እንዲያይ አመለከተችው::
ፊቱን አዞረ:: ዣቬርን ከዚያ ቆሞ አየው::....
💫ይቀጥላል💫

❤9👍2
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እንደዚያ ልብ ዘርታ ትጫወት የነበረችው ሴትዮ አሁን በድንገት ተለዋወጣ ዝልፍልፍ አለች::

ፊቱን አዞረ:: ገናቬርን ከዚያ ቆሞ አየው::
ከዚያ በኋላ ምን እንደሆነ እንመልከት::
በጣም ከመሸ ነበር መሴይ ማንደላይን ፍርድ ቤቱን ለቅቆ የወጣው::ወዲያው እንደወጣ ከበራፍ ይጠብቀው በነበረው ሠረገላ በቀጥታ ወደ ቤቱ
ተመለሰ፡፡ ሊነጋጋ ሲል ነበር ሞንቴስ ሰር ሞንቴስ ከተባለ ሥፍራ የደረሰው::ከዚያም እንደደረሰ ለመሴይ ላፌት ደብዳቤ ከላከ በኋላ ነበር ፋንቲንን
ለመጠየቅ ወደ ተኛችበት ክፍል የሄደው::
ፍርድ ቤቱ ሻምፕማቲዩን በነፃ ካሰናበተ በኋላ ሕግ አስከባሪውና
ዳኞቹ ተመካከሩ፡፡ የተመካከሩት መሴይ ማንደላይንን ያሳሰሩት ወይም አያሳስሩት እንደሆነ ነበር፡፡ መታሰር እንዳለበት ወስነው በአለበት እንዲያዝ ትእዛዝ ሰጡ፡፡ ሕግ አስከባሪው በአስቸኳይ ወደ ከተማው ፖሊስ አዛዥ
ወደ ዣቬር ወዲያውኑ መልክተኛ ልኮ ከንቲባውን እንዲይዝ ትእዛዝ
አስተላለፈለት::
ዣቬር ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነሳ መልእክተኛው ደርሶ ትእዛዙን
ሰጠው:: መልእክተኛው የፖሊስ አባል ሲሆን ይህም መለዮ ለባሽ ፍርድ ቤቱ ውስጥ ምን እንደተከሰተ ለዣቬር ባጭሩ አስረዳው::
የትእዛዙ ፍሬ አሳብ «የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ከንቲባ መሴይ ማንደላይን ከእስር ቤት ያመለጠው ዣን ቫልዣ መሆኑ ስለታወቀ የፖሊሱ ኣዛዥ
በቁጥጥር ስር እንዲያውለው ፍርድ ቤቱ አዟል» የሚል ነበር፡፡
ዣቬር አንድ የአስር አለቃና አራት ወታደሮችን አስከትሎ ከከንቲባው
ቤት ሄደ:: መሴይ ማንደላይን ፋንቲን ከነበረችበት ክፍል መሆኑን ጠይቆ ከተረዳ በኋላ በቀጥታ ወደዚያ ሄዶ በሩ ላይ ተሰክቶ በነበረው ቁልፍ በሩን ቀስ ብሎ ከፍቶ ገባ፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ በሩን ከፈተው እንጂ ወደ ውስጥ ለመግባት
አልደፈረም:: ካፖርቱን እስከ አንገቱ ግጥም አድርጎ ቆልፎ ቆቡን አጥልቆአል፡፡ወደ ክፍሉ ያስገባው መላ ሰውነቱን ሳይሆን አንገቱን ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም
በሩ ስለተከፈተ ማን እንደሆነ በግልጽ ይታያል፡፡ እንደዚያ ሆኖ ምናልባት ለአንድ ደቂቃ ያህል ዝም ብሎ ቆሞ ይሆናል:: ይሄኔ ነው ፋንቲን አይታው
ለመሴይ ማንደላይን የጠቆመችው፡፡ ሁለቱ ተያዩ:: ዣቬር አልተነቃነቀም:: ያ ግዙፍ ሰውነቱ እንኳን ካፖርት ደርቦበት እንዲሁም ይከብዳል፡፡ ፊቱን አጠቋቁሮ ፧ ጥርሱን አግጥጦና
ዓይኑን አፍጥጦ «አገኘሁህ» በማለት ሲያይ በጣም ያስፈራል፡፡
በመጨረሻ ዣን ቫልዣን በመያዙ አካሉ ውስጥ የነበረው ያንን ሰው
አሳድዶ የመያዝ ጽኑ ፍላጎትና ምኞት ተጎልጉሎ ወጥቶ ገጹ ላይ ታየ:: «ዛሬስ ድል መታሁ» የሚለው ደስታው ደግሞ ከዚያች ከጠባብ ግምባሩ ላይ በጉልህ ወጣ፡፡
ዣቬር በዚያች ቅጽበት መንግሥተ ሰማይ ገብቷል፡፡ የዣቬርን
ቁመናና ሁኔታ ረስተን የዘወትር ፍላጎቱና ምኞቱ ምን እንደሆነ ብናጤን «ትክክለኛ ፍርድ ፤ እውነትና ብርሃን የክፉ ሥራ አጥፊዎች ናቸው የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እነዚህም የሕግ፣ የሥልጣን፣ የሕሊናና
የመሳሰሉት የበቀል መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ከዚያ ክፍል ውስጥ ቆሞ : የሚታየው ይህን ለማስፈጸም ነበር፡፡ በእርሱ ዓይን ርህራሄ፣ ፍርሃትና ይሉኝታ የሕግ ጠላቶችና የትክክለኛ ፍርድ እንቅፋቶች ሲሆኑ ይህ ሰው
ፍርድን ላለማዛባት ምንም ነገር ያደርጋል፡፡ የዘወትር እምነቱ ከህብረተሰብ መካከል ቅጥፈት፣ ተንኮልና ወንጀል ጨርሶ ማስወገድ ሲሆን ይህን
ከማስፈጸም ወደኋላ ስለማይል «የነገሮች መነሻዎች ምንድናቸው» የሚል አስተያየት አያውቅም:: ዓላማውና ምኞቱ ሕግን ማስከበር ነው:: ይህ
እምነቱ ነው ፊቱ ላይ እየታየ ገና ሲመለከቱት የሚዋጋ በሬ ያስመሰለው።
መሴይ ማንደላይን ከመንጋጋው ፈልቅቆ ካወጣት ወዲህ ፋንቲን
ዣቬርን አላየችውም፡፡ ስለዚህ በጠዋት የመጣው እርስዋን ለመያዝ እንጂ ለሌላ ነገር ነው ብላ አልገመተችም:: ፊቱ ያስጠላታል፡፡ የእርሱን ፊት
ለረጅም ጊዜ ካየች ሞትዋ የተቃረበ ይመስላታል:: ስለዚህ ፊትዋን በእጅዋ ሽፈነችው::
«መሴይ ማንደላይን ያድኑኝ፧ ከዚህ ጉድ ያወጡኝ» ስትል ጮኸች፡፡
«አይዞሽ፣ አንቺን ሳይሆን እኔን ፍለጋ ነው የመጣው::»
ከዚያም ወደ ዣቬር ዞር ብሎ «ምን እንደምትፈልግ አውቃለሁ
አለው::
ዣቬር «ፈጠን በል» ሲል መለሰ፡፡
ዣቬር ይህን ሲናገር ከቆመበት አልተነቃነቀም:: ግን ዘወትር
የጠላቸውን በሚያይበት ዓይን ነበር ዣን ቫልዣን ያየው:: ከሁለት ወር በፊት ፋንቲንን ያያት ልክ እንዳሁኑ አጥንት ሰርስሮ በሚገባ ዓይነት አስተያየተ ነበር፡፡ ለዚህ ነው አሁንም የፈራችውና «አድነኝ ብላ» የጮኸችው::
ዣቬር እንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ::
«እንሂድ፣ ምነው ወደኋላ!» ሲል ጠየቀ፡፡ ያቺ የተከፋች ሴት ኣካባቢዋን ቃኘች፡፡ ከክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሴርዋና ከንቲባው መሆናቸውን ተገነዘበች፡፡
ይህ ሰው የመጣው «እኔን ሊወስድ እንጂ ለሌላ ሰው አልመጣም» ብላ ስለደመደመች ሰውነትዋ ተንቀጠቀጠ፡፡ ሆኖም ወዲያው ጨርሶ የማይታሰብ
ነገር አየች:: ያየችው ነገር በእውን ሳይሆን በቅዠት እንኳን ሊታያት
የማይችል እንደሆነ ገመተች::
የፖሊሶ አዛኝዥ ዣቬር የመሴይ ማንደላይንን ማንቁርት ይዞ ሲጎትትና መሴይ ማንደላይን አንገቱን ሲደፋ ተመለከተች:: ዓለም ከፊትዋ የተደፋ
መሰላት::
ዣቬር ሰላሣ ሁለት ጥርሶቹን በመሉ እያሳየ ከት ብሎ ሳቀ::
«የእኛ ከንቲባ!» በማለት በይበልጥ አንቆ ያዘው::
መሴይ ማንደላይን አንገቱን ለማስለቀቅ አልሞከረም፡፡ ግን «ዣቬር» ሲል ተናገረ::
ዣቬር ጣልቃ በመግባት አቋረጠው:: ክቡር የፖሊስ አዛዥ ብለህ ጥራኝ» አለው::
«ክቡር» አለ ዣን ቫልዣ ፧ ብቻችንን ብንሆን አንድ የምጠይቅህ ነገር
ነበረኝ::
«ጮክ በል፣ ድምፅህን ከፍ ኣድርገህ ተናገር:: ሰዎች እኔን ሲያናግሩ ጮክ እያሉ ነው የሚያነጋግሩኝ» አለ ዣቬር፡፡
ድምፁን ዝቅ አድርጎ ዣን ቫልዣ ንግግሩን ቀጠለ::
«አንተን በግል የምለምንህ ጉዳይ አለኝ፡፡››
‹‹ጮክ ብለህ ተናገር ብዬህ እኮ ነበር፡፡»
«ግን የምነግርህ ነገር እኔና አንተ እንጂ ሌላ ሰው መስማት ስለሌለበት ነው::
“ጉዳዩ መሰለህ፤ በአንተ ጉዳይ እኔን ምን አስጨነቀኝ፣ አልሰማም::
ዣን ቫልዣ ጠጋ ብሎ በችኮላ አሁንም ድምፁን ዝቅ እድርጎ
የሚከተለውን ተናገረ::
« ሦስት ቀን ብቻ ስጠኝ! የዚህች የተከፋች ሴት ልጅ ሄጄ ላምጣላት::የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ እኔ እከፍላለሁ:: ከፈለግክ አብረን ልንሄድ እንችላለን፡፡
«በእኔ ላይ ነው የምታሾፈው» አለ ዣቬር፡፡ «እስከዚህ ሞኝ
አትመሰለኝም ነበር:: ሦስት ቀን ስጠኝና የዚህችን ሴት ልጅ ላምጣ' ትለኛለህ:: በጣም ታስቃለህ፡፡»
የፋንቲን ሰውነት ተንቀጠቀጠ፡፡
«ልጄን» ስትል ጮኸች፡፡ «ልጄ ዘንድ ሊሄዱ ነዋ! ወይኔ ልጄ፧
አልመጣችም ማለት ነዋ! ሲስተር ይንገሩኝ፤ ልጄ የት ናት? መሴይ
ማንደላይን፤ ክቡር ከንቲባ ልጄን እፈልጋታለሁ!»
ዣቬር ከፍተኛ ድምፅ በማሰማት መሬቱን በጫማው ረገጠው::

👍18
«ይህቺ ደግሞ ምን ትለፈልፋለች፧ አፍሽን ዝጊ፡፡ ይህች የተረገመች
አገር ገና ብዙ ታሳየናለች:: ይገርማል! ከእስር ቤት ያመለጡ ሽፍቶች የሚዳኙበት፧ ሸርሙጦች እንደ ልዕልት የሚንቀባረሩበት አገር! ይህ ሁሉ ይለወጣል፣ እንዳለ አይቆይም፣ የጊዜ ጉዳይ ነው:: ፋንቲንን አፍጥጦ እያየ የዣን ቫልዣን ክራባትና ኮሌታዎች በይበልጥ አጥብቆ ያዘ፡፡
«ከአሁን ወዲያ ክበር ከንቲባ ወይም መሴይ ማንደላይን የሚባል ሰው የለም:: ይህ ከእጄ የገባው ፍጡር ዣን ቫልዣ የተባለ ሌባ፣ ቀጣፊና ሽፍታ ነው:: ከአሁን በኋላ እንደለመደው አያመልጠኝም፤ አግኝቼዋለሁ፡፡»
ፋንቲን ወገብዋን በሁለት እጆችዋ ደግፋ ቀና ኣለች:: ዣን ቫልዣን
ኣየችው፡፡ ከዚያም ዣቬርን ተመለከተች፡፡ ቀጥላም ዓይንዋን ሴርዋ ላይ ተከለች፡፡ ለመናገር እንደፈለገ ሰው ኣፍዋን ከፈተች:: ንግግር አይሉት ማጉረምረም ቃል ከአፍዋ ወጣ፡፡ ጥርሶችዋ እንደገጠሙ ናቸው:: የደከሙ
እጆችዋን ዘረጋች፡፡ ግን ቀስ እያለ ባህር ውስጥ እየሰጠመ እንደሚሄድ ሰውነት ዝግ እያለች ከትራሱ ላይ ዘፍ አለች፡፡ የአልጋው ድጋፍ ጭንቅላትዋን መታት:: በጀርባዋ ከአልጋው ላይ ተደፋች:: አፍዋ አረፋ ደፈቀ፡፡ ዓይንዋ
ፈጥጦ ቀረ፡፡ ነፍስዋ ከሥጋዋ ተለየች::
ዣን ቫልዣ አንቀው ከያዙት የዣቬር እጆች ላይ እጆቹን እሳረፈ።እንደ ሕፃን ልጅ እጆች በቀላሉ በማስለቀቅ ከለበሳቸው ልብሶች ኮሌታ የዣዜርን እጆች አላቀቀ፡፡ ከዚያም ይህችን ሴት ገደልካት» ሲል ጮህበት፡፡
"ገደልካት ኣልክ!!» ብሎ በማንጓጠጥና በንዴት ተናገረ:: «እኔ ያንተን ልፍለፋ ለመስማት አልመጣሁም:: ወታደሮች ከምድር ቤት ይጠብቁኛ
ከቤቱ ጥግ ትልቅ የብረት ዱላ ተቀምጦ ነበር፡: ዣን ቫልዣ ትልቁን
የብረት ዱላ አነሳ፡፡ ዣቬር ወደ በሩ ሽሸ፡፡ ዣን ቫልዣ ዱላውን እንደ ያዘ ወደ ፋንቲን ሄደ:: ከዚያም በቀላሉ በማያስማና በጣም ዝግ ባለ ድምፅ ዣቬርን እያየ ተናገረ::
«አሁን ባትረብሸን ይሻልሃል፡፡»
የፖሊሱ የዣቬር ሰውነት በእርግጥ ነፋስ እንደሚያወዛውዘው ቅጠል
ተንቀጠቀጠ፡፡ ወታደሮቹን ለመጥራት ፈለገ:: ግን ዣን ቫልዣ በእድሉ የሚጠቅም መሰለው:: ስለዚህ የበሩን መቃን ተደግፎ ዓይኑን ከገዣን ቫልዣ
ሳያነሳ ከነበረበት ቆሞ ቀረ::
ዣን ቫልዣን ይዞት በነበረው የብረት ዱላ ክርኑን አስደግፎና ግንባሩን በእጆቹ ይዞ በድንዋን ፋንቲን አፍጥጦ ተመለከታት:: ቃል ሳይተነፍስ እንደዚያ ሆኖ በተመስጥኦ ለረጅም ጊዜ ቆየ:: ባይናገርም ለፋንቲን ምን
ያህል እንዳዘነ መላ ዕውነቱ ይመሰክራል፡፡
በተመስጥኦ ሕሊናውን ረስቶ ከቆየ በኋላ ረጋና ዝቅ ባለ ድምፅ ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎ በማንሾካሾክ ፋንቲንን አናገራት::
ምን አላት? ይህ የተፈረደበት ወንጀለኛ በሞት ከዚህ ዓለም ለተለየች ሴት ምንስ ሊል ይችላል? የተናገራቸው ቃላት ምን ነበሩ? ማንም አልሰማም፤
አላወቀምም:: ሟችዋ ፋንቲን ሰምታው ይሆን? ማን ያውቃል?
ዣን ቫልዣ የፋንቲንን ጭንቅላት በሁለት እጆቹ ይዞ ከትራስ ላይ
አስተካክሎ አስተኛው:: ሲያስተኛው አያያዙ ልክ አንዲት እናት ልጅዋን በጥንቃቄ እንደምታስተኛ ዓይነት ነበር፡፡ የለበሰችውን ፒጃማ አስተካከለ
በኋላ ከአንገትዋ ላይ የነበረውን ማሰሪያ አጥብቆ አሰረላት:: ከዚያም ግንባርዋን በፀጉርዋ ሸፈነው:: ሞት ወደ ታላቅ ብርሃን የሚወስድ ጕዳና ስለሆነ አተኩሮ ሲመለከታት ፊትዋ የሚያበራ መሰለው::
የፋንቲን እጆች ከአልጋው ግራና ቀኝ ተንጠልጥለሆኑ ነበር ዣን
ቫልዣ ተንበርክኮ አንድ እጅዋን ቀስ አድርጎ አንስቶ ሳመው ከዚያም ከአልጋው ላይ አሳረፈው:: ቀጥሉ ብድግ ብሎ በመነሳት ዣቬርን አየው
«አሁን ልትወስደኝና ልታስረኝ ትችላለህ» አለው::
ፋንቲን ማንም ሰው ከሚቀበርበት የመቃብር ቦታ ተቀበረች፡፡
መቃብራቸው ላይ ስማቸው ከማይጻፍና እነማን እንደሆነ ከማይታወቁ ሰዎች መቃብር አጠገብ ነበር የተቀበረችው:: መቃብርዋ የዘላለም አልጋዋ
ሆነ::...

😢10👍7
#ጉዞ_ወደ_ፍቅር
ቀድሞም አምን ነበር
አካላቴ እንደኾንሽ ፤
ቀድሞም ዐውቀው ነበር
ለ'ኔ እንደተፈጠርሽ።
ይኸው . .
በጉዘቴ መኻል መንፈሴ ተረታ
ድንገት ባጋጣሚ ፣ ታየኝ ውብ ፈገግታ።
የዘላለም ሣቅሽ በቅጽበት ተሰማኝ
ግብሬን ዘነጋኹት እንደኾንኩኝ መናኝ።
ቢኾንም ዐውቃለኹ . .
ብዙ ጊዜ አይወስድም ባ'ንቺ በኩል ብኼድ
ፍቅር አይደለም ወይ ? የፈጣሪስ መንገድ።
🔘ተስፋኹን ከበደ🔘
ቀድሞም አምን ነበር
አካላቴ እንደኾንሽ ፤
ቀድሞም ዐውቀው ነበር
ለ'ኔ እንደተፈጠርሽ።
ይኸው . .
በጉዘቴ መኻል መንፈሴ ተረታ
ድንገት ባጋጣሚ ፣ ታየኝ ውብ ፈገግታ።
የዘላለም ሣቅሽ በቅጽበት ተሰማኝ
ግብሬን ዘነጋኹት እንደኾንኩኝ መናኝ።
ቢኾንም ዐውቃለኹ . .
ብዙ ጊዜ አይወስድም ባ'ንቺ በኩል ብኼድ
ፍቅር አይደለም ወይ ? የፈጣሪስ መንገድ።
🔘ተስፋኹን ከበደ🔘
❤16👍10🥰1
ፈላስፋ አይደለሁ...
ገባሽ አነባለሁ፤
ያውም እልፍ አእላፍ፤
ስለማነብ ነው፤ ነገር ሁሉ የማልፍ።
ማለት...
በሄድሽበት ሁሉ፣
"እሱ ጥጋብ ሙሉ"
ስትዪኝ...
ዝም ጭጭ መልሴ፤
"አሳቢ አያወራም" ፧ እያልከት ለራሴ።
ገባሽ .. አነባለሁ፤
በሄድሽበት ሁሉ፣ መንገዱ ሲቀናሽ፣
"የትሞ የሚጋደሞ፣ እሱ ታላቅ ቅናሽ"
እያልሽኝ... ዝም ጭጭ የምለው፣
የመሀሙድ ዘፈን፣ስለሞሰማ ነው።
(ዝሞታ ነው መልሴ)
ነጋልሽ መሰለኝ ፣ ጆሮ ልታደሚ፤
እኔን ካላነሣሽ ፣ ስለማትሰሚ።
አሁን ይኸው አሁን ፣ ሴት አቅፌ እያየሽ
"አንቺ ስንተኛው ነስ?"
ትያለሽ?
የሷን ቁጥር ትተሽ፣
የሪስሽን ባወቅሽ።
(አንቺ ስንተኛ ነሽ?)
አቤት ያንቺ ዲስኩር ፣ እኔን ለመጠርጠር፤
እንደ ዕድር ዕቃ ፣ መመዝገብ መቆጠር።
(ስትወጂ)
እንደዉ ሙች ልበልሽ
ከሴት ሁሉ ጋራ
ስሜ ቢብጠለጠል ፣ በነገር ቢሸፈን፣
አንቺ ጋር ማ ሊደርስ
ቆዳዬን ነው እንጂ ፣ አንሶላ መች ገፈን።
ኤጭ
ስካንስ ለፈፍኩኝ ፣ ላልችል አባብዬ፤
መናገር ድካም ነወ ፧በ ጂብራል ተብዬ።
የትሞ ስሕተኛኹ፣ የትም ተኛ ብለሽ፣
በሄድሽበት ሁሉ ፣ ጥንብ እሩክሴን ጥለሽ፣
አፍሽ ስሜን ወስዶ ሲያመሰቃቅለው፣
ዝም ጭጭ የምለው፣
ማንሞ ጋር ብተኛ
«እኔኮ የማውቀው ፣ አለማወቄን ነው።»
(የሚል አንብቤ ነው)
ገባሽ.… አነባለሁ።...
ሕይወት እስከሞቱ
ንፁህ ስላልሆነ ፣ ብሽቀት ስለበዛው
እውቀት ቀባብቶ ነው
የስሕተቱን አመድ ፣ ምሁር የሚያወዛው፤
ገባሽ? ...
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
ገባሽ አነባለሁ፤
ያውም እልፍ አእላፍ፤
ስለማነብ ነው፤ ነገር ሁሉ የማልፍ።
ማለት...
በሄድሽበት ሁሉ፣
"እሱ ጥጋብ ሙሉ"
ስትዪኝ...
ዝም ጭጭ መልሴ፤
"አሳቢ አያወራም" ፧ እያልከት ለራሴ።
ገባሽ .. አነባለሁ፤
በሄድሽበት ሁሉ፣ መንገዱ ሲቀናሽ፣
"የትሞ የሚጋደሞ፣ እሱ ታላቅ ቅናሽ"
እያልሽኝ... ዝም ጭጭ የምለው፣
የመሀሙድ ዘፈን፣ስለሞሰማ ነው።
(ዝሞታ ነው መልሴ)
ነጋልሽ መሰለኝ ፣ ጆሮ ልታደሚ፤
እኔን ካላነሣሽ ፣ ስለማትሰሚ።
አሁን ይኸው አሁን ፣ ሴት አቅፌ እያየሽ
"አንቺ ስንተኛው ነስ?"
ትያለሽ?
የሷን ቁጥር ትተሽ፣
የሪስሽን ባወቅሽ።
(አንቺ ስንተኛ ነሽ?)
አቤት ያንቺ ዲስኩር ፣ እኔን ለመጠርጠር፤
እንደ ዕድር ዕቃ ፣ መመዝገብ መቆጠር።
(ስትወጂ)
እንደዉ ሙች ልበልሽ
ከሴት ሁሉ ጋራ
ስሜ ቢብጠለጠል ፣ በነገር ቢሸፈን፣
አንቺ ጋር ማ ሊደርስ
ቆዳዬን ነው እንጂ ፣ አንሶላ መች ገፈን።
ኤጭ
ስካንስ ለፈፍኩኝ ፣ ላልችል አባብዬ፤
መናገር ድካም ነወ ፧በ ጂብራል ተብዬ።
የትሞ ስሕተኛኹ፣ የትም ተኛ ብለሽ፣
በሄድሽበት ሁሉ ፣ ጥንብ እሩክሴን ጥለሽ፣
አፍሽ ስሜን ወስዶ ሲያመሰቃቅለው፣
ዝም ጭጭ የምለው፣
ማንሞ ጋር ብተኛ
«እኔኮ የማውቀው ፣ አለማወቄን ነው።»
(የሚል አንብቤ ነው)
ገባሽ.… አነባለሁ።...
ሕይወት እስከሞቱ
ንፁህ ስላልሆነ ፣ ብሽቀት ስለበዛው
እውቀት ቀባብቶ ነው
የስሕተቱን አመድ ፣ ምሁር የሚያወዛው፤
ገባሽ? ...
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍15🤔6🥰1
#በብረትና_ቻፕስቲክ_በተከበበ #ከተማ_እንሆ_የመለአክ
#ድምፅ_ተሰማ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
እንዲት ፍቅረኛ ነበረችኝ፡፡ ይሄን አደረጎኝ ሳትል ርግፍ አድርጋ ተወችኝ፡፡ የተወችኝ ሰሞን
አዕምሮዬ ነገር እየቀላቀለ አስቸግሮኝ ነበር፡፡ የምይዝ የምጨብጠውን አጥቼ ነበር፡፡ ብዙ ነገር ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ ከተለያየን ከአምስት ወር በኋላ እንደወለደች ስሰማ "አንዲት ሴት
የምታረግዘው ስንት ወር ነው?" ብዬ አሰብኩ፡፡ መቼም ከእኔ አለማርገዟ ጥያቄ አልነበረውም፧
ምክንያቱም “ከጋብቻ በፊት ዝንቤን እሽ እንዳትል!" ብላኝ ስለነበር ቃሏን አክብሬ ከመሳም
ዘልዬ አላውቅም፡፡
ለዛውም ከንፈሯን እያሳደድኩ ነበር የምሰማት፡፡ በደቡብ በኩል ከንፈሬን ሳሞጠሙጥ ወደሰሜን
እየዞረች፤ ከሰሜን ስንደረደር ወደ ምስራቅ እየሸሸቶ ፍዳዬን አብልታኝ ነበር የኖርነው፡፡ ስንትና
ስንቴ ከንፈሯን የሳተ ከንፈሬ ባዶ አየር ስሟል፡፡ አየር ስታስመኝ ከርማ በመጨረሻ አየር ላይ
ትታኝ ሄደች፡፡ ደግሞ እኮ የአካሄዷ ክፋት “ቻው” ማለት ማንን ገደለ ? "አልፈልግህም ማለት ምን ችግር አለው ? አንድ ቅዳሜ ደውዬ "ዛሬ አንገናኝም እንዴ ፍቅር?” ስላት “ለምንድን ነው የምንገናኘው ?” ብላ ግራ የገባው ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡ በቃ በዛው ቀረች፡፡
እና ይሄው በተለያየን በአምስት ወሯ ወልዳ አረፈችው:: ነርስ ነበረች፤ በኋላ ስሰማ አንድ
ዶክተር ነው አሉ ያገባት፡፡ እኔ ሳድግ “ዶከተር እሆናለሁ” እንዳልኩት ፍቅረኛዬ “ሳድግ ዶክተር አገባለሁ” ብላ ሳትመኝ አልቀረችም። ከዛ በኋላ የሴት ዘር ጠላሁ፡፡ በተለይ ነርስ የሚባሉ
ሴቶች፧ ዶክተሮች ራሳቸው በሽታ ፈዋሽ ሳይሆኑ በሽታ መስለው ታዩኝ፡፡ ለዛ ነው ሆስፒታሎች
ሲኦል የሚመስሉኝ፡፡ ለእኔ በሽታ ማለት ወደሞት ሳይሆን ከሞት የባሰ ወደምጠላቸው ነርስና
ዶክተሮች የሚወስደኝ የሲኦል መንገድ ነው፡፡
ሰሞኑን ታዲያ ወደ አንድ የግል ሆስፒታል ጎራ ብዬ ነበር፡፡ በሕይወታችን ውስጥ የጠላታችንን ደጅ የሚያስጎበኙን የባሱ ጠላቶች ይገጥሙን የለ ! በቃ አመመኝና ወደምጠላው ሆስፒታል ሄድኩ፡፡ ሆስፒታሉ ውስጥ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሴት ነርሶችን ስመለከት “ይህ ነገር የግል ኮሌጅ ነው ? ወይስ የግል ሆሰፒታል ?" ብዬ አሰብኩ፡፡ ገና በሩ ላይ ስደርስ አንዲት በተናገረች ቁጥር ከንፈሯ ጆሮዋ ጥግ እና ጥግ እየደረሰ የሚመለስ
እዚያው ሃዲድ ክንፈሯ ላይ የደፈደፈችው ቻፕስቲኮ አፏን ፀሐይ ላይ የተቀመጠ የቅቤ ቅል
ያስመሰለው ነርስ ወደኔ መጣችና በቁሙ የሞተ ፈገግታ እያሳየችኝ፣ ምን ልርዳከ ? አለችኝ፡ ስትናገር ቃላቶቹ ያዳልጣቸዋል ቻፕስቲኩ ይሆን ?1 ጥርሷ በብረት ታስሯል፡፡ እሰኪ እሁን እስኪፈታላት ብትታገስ ምን ትሆናለች ? 'ካልሳቅሽ ወዮልሽ!' ያላት አለ ? መቼም የዚህች ነርስ ጓደኛ ብሆን (አይበልብኝና ከንፈሯን አንድታሳስረው ነብር የምመከራት፡፡
እኔ እንኳን የመጣሁት እናንተን ለመርዳት ነው” አልኩ ስለ ክፍያቸው ውድነት ማሸሞሬ ነበር፣
እርሷ ግን ፊቷ በፈገግታ ተጥለቀለቀ፤ አቁነጠነጣት፡፡ 'የተናገርኩት ይሄን ያህል ያስደስታል ወይንስ የእውነት የእርዳታ ድርጅት ልኮኝ የመጣሁ መስሏት ነው?' እያልኩ ስገረም "ኦ.ው.ኬ.! አዲስ የተመደቡት ዶክተር እርስዎ መሆን አለብዎት?” ብላኝ እርፍ፡፡ አቤት ኦኬ ላይ ከንፈሯን እንዴት አንደምታደርገው ! አንዳንድ የከተማችን ዘመነኛ ሴቶች በእንግሊዝኛ የከንፈር ቀመር
አማርኛ ካላወራን እያሉ ከንፈራቸውን ለጥጠውት ሊሞቱ ነው፡፡
ልጅቱ በደስታ ተጥለቀለቀች፡፡ ክርስቶስ ሊፈውስህ መጣ” የተባለ የእድሜ ልክ በሽተኛ
እንኳን እንደሷ አይፍነከነክም፡፡ የቃልኪዳን ቀለበቷን አውልቃ ሳትደብቀው በፊት (ማን ይሆን
ያገባት?) ፈጠን ብዬ እኔ እንኳን ልታከም የመጣሁ በሽተኛ ነኝ” አልኳት፡፡ ወዲያው ፊቷ
የተጥለቀለቀው የሳቅ ማዕበል ድራሹ ጠፍቶ፣ “ተከተለኝ” አለችና ወደ ካርድ ክፍል መራችኝ፡
እየተቆናጠረች፣ የሆነ ሰበር ሰካ የማለት ሙከራ ዓይነት፡፡ እች አረማመድ ለአዲሱ ዶክተር
ተቀምራ የተቀመጠች ሳትሆን አትቀርም፡፡
ካርድ ክፍሉ ውስጥ አንድ እግሯን አጥፋ ተሸከርካሪ ወንበር ላይ የተጎለተች ሌላ ቻፒስቲካም
“ስምህ አለችኝ፣
“ስሜ ምን ሆነ ” ስል ጠየቅኳት፡፡ ልክ አማርኛ ዘጠነኛ ቋንቋዬ ሳይመስላት አልቀረም፡፡
“አይ ስምህ ማነው ማለቴ ነው"
" እ..አብረሃም !"
እድሜህ ስንት ነው ?” (ማስቲካዋን ቀጭ)
"250 ብር ክፈል!”አለችኝ፡ከፈልኩ፡፡ ካርዱን እያቀበለችኝ፡፡ አየሁት ሰሜን አሳስታ ነው የፃፈችው፡፡
ስሜን አሳስተሸዋል” አልኳት፣ በመስተዋቱ ሸንቁር ጎንበስ ብዬ፡፡
ሶሪ! እስኪ….አብርሃም.…አይደል ስምህ?” አለች ስህተቷ አልገባትም፡፡
"አዎ አንቺ ግን አርሃም ብለሽ ነው የፃፍሽው" ብ" ን ረስተሻታል፡፡"
ኮስተር ብላ አዲስ ካርድ አወጣችና እያቀበላችኝ፣ ስምህን ሞልተህ ትሰጠኝ አለችና፣ የቅሬታ
ፈገግታ እያሳየችኝ። የዚህችም ጥርስ በብረት ታስሯል፡፡ ደምዛቸውን ቻፕስቲክና የጥርስ ማሰሪያ ብረት የሚከፍሏቸው ነው የሚመስሉት፤ ወይስ "ሆዴን ከመቻል ተርፎ ጥርሴን የሚያሳሰር ባል ወላ ጓደኛ አለኝ" መልዕክት ነው ?! መቼስ የአዲስ አበባ ወንድ ብሩ ተረግሟል፡፡
ስሜን ሞልቼ ሳበቃ “እድሜዬንም ልሙላልሽ” አልኳት፤ ሆነ ብዬ ለማበሳጨት ነበር፡፡ የመንጠቅ
ያህል ካርዱን ከእጄ ላይ ወሰደችና የምትሞላውን ነገር ሞልታ፣ “ዶ/ር ሰናይት ጋር ነህ፡፡ ከፊትህ
አምስት ሰው ይቀድምሃል” አለችኝ፡፡ በጣም ተበሳጭታለች፡፡
“ይቅርታ ወንድ ዶክተር የላችሁም ?" አልኳት፡፡ በረዥሙ ተንፍሳ ካርዴን ተቀበለችኝና ዶከተር አምሃ” ብላ ፃፈችበት፡፡
“አመሰግናለሁ!" አልኳት በሚያበሳጭ ድምፅ፤ ከዛም ካርዱን አየሁትና ተመልሼ… “ይቅርታ የዶክተሩን ስም ማን ነበረ ያልሽኝ?” አልኳት።
በግርምት አየችኝና “ዶ/ር አምሃ 3 ቁጥር ላይ” አለች ቃሉን ረገጥ አድርጋ፡፡
“እማ' ነው የሚለው፤ ኤች· የለችም” አልኳት ካርዱን እያሳየኋት፡፡ (የእውነትም
የለችም ነበር)፡፡ ስልችት ብያት አንገሽግሻት በመጨረሻ ትዕግስቷ አስተካከለቻት፡፡
ወረፋ ስጠብቅ ከፊቴ የሚቀድሙኝ አራት የሚሆኑ ሴት ታካሚዎች እየገቡ በጣም ከቆዩ በኋላ በጣም እየሳቁ ይወጣሉ፡፡ አረማመዳቸው ራሱ ይቀየራል፡፡ እየተንኳተቱ ገብተው እንደ ሞዴል
እየተውረገረጉ ይወጣሉ፡፡ "ውስጥ የተቀመጠው ዶክተር ነው ወይስ ኮሜዲያን'?” እያልኩ ሳስብ
ተራዬ ደረሰና ለመሳቅ ተዘጋጅቼ ገባሁ፡፡ ወይ መሳቅ !
ጎልማሳ፣ መላጣ ዶከተር ኮስተር ብሎ በእስክርቢቶው ወንበር ጠቆመኝ፡፡ ስታይሉ ነው መጨረሻ
ላይ ያስቀኛል
እሺ አብርሃም እንዴት ነው የሚያደርግህ?” አለኝ ከበፊቱ በባሰ ኮስተር ብሎ፤ የመጨረሻዋን ሴት እኔ ያሳረርኳት ሳይመስሰው አይቀርም መላጣ ምናባቱ ያኮሳትረዋል?!
በሩ ተንኳኳ፡፡
“ይግቡ!” አለ፡፡ የመጨረሻዋ ታካሚ ነበረች ተመልሳ የገባችው:: ስልኳን ረስታ ልትወስድ ነበር፡
(በሽታዋ አልዛይመር ነበር እንዴ?)
ዶክተሩ ፈገግታው ፈነዳ፡፡ “ኦኬ !" ብሎ ተነስቶ በሁለት እጁ አቀበላት፡፡ ዳሌዋ ሰፋ ያለ መልከመልካም የሃብታም ሚስት ነገር ናት፡፡ ልክ ስልኳን ሲሰጣት
የሆነ አይነት ለየት ያለ መተያየት ያየሁባቸው መሰለኝ።
“ቴንኪው ዶክተርዬ !” ብላው በተረከዝ ረጅም ጫማዋ ወለሉን እየደቃችው እና እየተውረገረገች
ወጣች።የሽቶዋ ጠረን ግን ክፍሉን ሞላው። ዶክተሩ ከተዘጋው በር ላይ ዓይኑን መለሰ ፈገግታውን አከሰመው፡፡ ልክ እፍ እንዳሏት ሻማ ወደ እኔ ሲዞር ፈገግታው ድርግም ብላ ጠፋች።

👍24❤1
“ይቅርታ(ካርዴን አየት አድርጎ) አብርሃም... እንዴት ነው የሚያደርግህ ?
ነገርኩት፡፡
ያስቀምጡሃል?
“አያስቀምጠኝም”
“ያስመልስሃል?”
"እያስመልሰኝም”
(ስልኬን ብረሳም አያስመልሰኝም ብለው አሪፍ ነበር፡፡ 'በሽተኛ ቅኔ አያምርበትም ብዬ ተውኩት፡፡)
“ምግብ ይዘጋሃል?”
“አይዘጋኝም"
“የመቆረጣጠም ስሜት አለው”
“የለውም !
ታይፎይድ ለማለት ቋምጦ ነበር፡፡
ስላበሳጨኝ ባጭሩ ነበር የምመልስለት፡፡ 250 ብሬን ከፍዬ ይገላምጠኛል እንዴ ደሞ ? ይህን
የሕፃናት ምኞት የሆነ ስራውን ሊኮራበት ይፈልጋል፡፡ ደግሞ ምን ያጣድፈዋል? ከእኔ በፊት"
የገቡት ሴቶች ለሌላ ስራ የመጡ እስኪመስለኝ ነበር የቆዩት።
“እጅጌህን ሰብስብ” አለኝ ማዳመቋጫውን ጆሮው ላይ እየሰካ:: አረ ይሄን ሰው አንድ በሉት ጉርድ ሸሚዝ ለብሼ እጅጌህን ሰብስብ ይላል፡፡ ለምን ከቀልቡ አይሆንም ?!
ቀጥሎ ደረቴ ላይ ማዳመጫዋን ለጠፉትና (አቤት መቀዝቀዟ) “ተንፍስ' (ትንሽ ወደ እዛ ዙር
አለ እንዳልተነፍስበት) አንጀቴን አሳረረው፡፡ አጥንታም ደረቴ ላይ ቀዝቃዛ ማዳመጫውን ለጥፎ
ተንፍስ!” ይለኛል፡፡ ከእኔ በፊት ያክማትን ሴት ደረት እያሰበ መሆን ከለበት፡፡ (ታዲያ ምን አቆየው ? ወይስ የተጎዳ ልቤ ዶክተር መሆኑን አውቆ ሲጮህበት ሰምቶ ይሆን?) ወረቀት ላይ ምልክት አደረገና ወደ ላብራቶሪ ላከኝ፡፡ ላብራቶሪ ማለት በተለይ የግል ሆስፒታሎች ቫይረስ፣ባከቴሪያ፣ ጀርም እና የታካሚውን ብር ፈልገው የሚያገኙበት ቦታ ነው!!
ወደ ላብራቶሪው ስገባ መልዓክ ጠበቀኝ፡፡ በቃ መልዓክ ነጭ ጋውን ለብሶ ውብ የሆነች ልጅ
ከመቀመጫዋ ተነስታ ተቀበለችኝ፡፡ ያውም በፈገግታ!! አቤት ፈገግታዋ ሲያምር ልክ የህንድ ፊልም ሳይ አክተሩ ያፈቀራትን ሴት ሲያይ እንደሚፈዘው ፈዘዝኩ:: አቤት ፈገግታ! ምን የተባረከ በሽታ ነው ዛሬ እዚህ የጣለኝ ? ጥርሷ በብረት አልታሰረም፡፡ (ከእስራቱ ነፃ ወጥቶ ይሆን?) ቁመቷ ደግሞ ሲገርም! እኔ እንኳን ረዥም የምባለው ትከሻዋ ላይ ቀረሁ! በዛ ላይ የድምፅዋ መለስለስ ! ወላ መስረቅረቅ..! ቆዳዋ ጥርት ከማለቱ ብዛት እንገቷ ስር ያለው ደም ስር ጥቁር አረንጓዴ ሆኖ ይታያል፡፡ ወረቀቱን አየችና “ምን ገጠመህ አብርሽ?" አለችኝ፡፡ አፌ
ቁርጥ ይበል ! መኪና ሙሉ ብርቱካን፣ ተሳቢ መኪና ሙሉ ሙዝ፣ ቦቴ መኪና ሙሉ የማንጎ
ጭማቂ ይዞ ሌላ ሰው የሚጠይቀኝ እሷ በሳምንት አንዴ "ምነው አብርሽ?” ብትለኝ እመኑኝ
እፈወሳለሁ!!
"ትንሽ አመመኝ አልኳት፡፡ ካለወትሮው የራሴ ድምፅ ጨዋ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ እንድታዝንልኝ
ሳልፈልግ አልቀረሁም፡፡
"ቆየብህ ” ጥያቄዋን ቀጠለች፡፡ መርፌና ስሪንጅ እያዘጋጀች፡፡ ጋዜጠኞች ጥያቄና አጠያየቅን
ከዚህች ልጅ ቢማሩ ምናለበት?
አይይ ትላንት ነው የጀመረኝ አልኳት። ወደዛ ወደነዚህ ስትል ዓይኔ አብሯት ይንከራተታል።
አቤት ዓይኔ ሲያሳዝን! ደግሞ መቀመጫዋ ሲያምር! ጨክና እዚህ መቀመጫ ላይ መቀመጧ
ገረመኝ፡፡
ኦ፡ ጥንቁቅ ልጅ መሆን አለብህ ፤ በጊዜ ነው የመጣኸው::እስቲ እጅህን እዚህ ጋር አድርገው!
ጨብጠው ! ክንዴ ላይ ያረፉት ውብ ጣቶቿን ተመስጬ አያለሁ፡፡ባቶቿ የእኔ ደም ስሮች መሰሉኝ: ጥፍር ቀለም አልተቀባችም፡፡ ቀይ እና ረዥም ጣቶቿ ተወዳዳሪ የላቸውም፡፡
የላስቲክ ጓንት 🧤 ስታጠልቅ ክፍት አለኝ፡፡ በጣቶቿ ውበት ብቻ ልፈውስ ተቃርቤ ነበር፡፡ ይልቅ
የገረመኝ አለንጋ ጣቶቿ ላስቲከ ለብሰውም ውበታቸው አለመደብዘዙ፡፡ ደሜ ወደ ስሪንጁ ሲገባ አየሁት፡፡ ልንገራችሁ አይደል! “አብርሽ እግረመንገዴን ለቀይ መስቀል ደም ልውሰድ እንዴ?” ብትለኝ እንስራ ሙሉ ደም በደስታ እለግስ ነበር፡፡ አይ ቀይ መስቀል... ምን እለ ይህችን
መልዓክ ቀመስ ልጅ በቴሌቪዥን ብቅ አድርጎ “ደም ስጡ !" ቢልና ህልሙን ቢያሳካ፣ አንዴ
ፈገግ ስትል ለኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከፈሰሰው ደም በላይ፡ አይተነውም ሳናየውም ከፈሰሰው
ደም በላይ እንለግስ ነበር።
“አሳመምኩህ እንዴ አለቸኝ ድንገት ፈገግ ብላ፡፡ ለኔ ግን ፈገግግግግግግግግግ ፡፡ሆነ! የላብራቶሪው ቅራቅንቦች ሁሉ የሳቁ መሰለኝ። አጉሊ መነፅሩ እግሩን አንስቶ የሳቀ መሰለኝ ።
አጋነንኩት ደግ እደረግኩ !!
“ኧረ እላመመኝም !" አልኩ ፈገግታዋን በፈገግታ እየመለስኩ፡፡ እሷን የሆንኩ መሰለኝ፡፡ በቃ
ሳቋ ግድግዳውም ላይ፡ መደርደሪያውም ላይ፤ እኔም ላይ ነጥሮ ይመለሳል፡፡ ዓለም የገደል
ማሚቱ ይሁንልሽ" ብሎ የመረቃት ስው አለ።
ይህችን የመሰለች ቆንጆ እዚህች ቀዝቃዛ ከፍል ውስጥ መገኘቷ ገረመኝ፡፡ ቁራጭ ቁንጅና
ይዘው ከተማን የሞሉት ምድረወልጋዳ፣ ወልካፋ፣ ጉረኛ፣ ቻፕስቲካም፣ ሂዩማንሄራም፣ ከሃዲ
ሁሉ ታይፈስ እየያዛቸው እዚህ በመጡና በቅናት ደም ግፊት ጨምረው በሄዱ! ትንሽ የፕላስቲስ ብልቃ እየሰጠችኝ “መፀዳጃ ቤት ትሄድና በዚህች ትንሽ. ታመጣለህ
አለችኝ ፣ ደበረኝ፡ ለምን እንደሆነ እኔንጃ! በዕርግጥ እቺን ለመሰለች ልጅ፣ ቆንጆ እንቡጥ አበባ ይዞ መሄድ እንጂ ከመፀዳጃ ቤት ቀብልቃጥ “ ይዞ መሄድ ደስታ ሊፈጥር አይችልም፡፡ ምን ይደረግ ሰኔና ሰኞ ገጠመብኝ፡፡ ቢሆንም በዚህች ትንሽ ታመጣለህ” ስትለኝ ራሱ እሷ ስትጠራው ሲያምር! 'ይሄ ነገር ከዚህ በፊት ስሙ እንዲህ ያምር ነበር እንዴ!” አልኩ ለራሴ ወጥቼ ወደ መፀዳጃ ቤቱ ስሄድ አንዲት ጠረንገሎ ነርስ ቆማ በስልክ እያወራች ትገለፍጣለች
ማስቲካ እያላመጠች ፀጉሯን ስልክ ባልያዘው እጇ እያፍተለተለች በስልክ የሞቀ ወሬ ይዛለች፤ “ይቅርታ ሽንት ቤቱ በየቱ ጋር ነው?” አልኳት ሆን ብዬ መፀዳጃ ቤት የሚለውን፣ ቃል አልተጠቀምኩም፡:ስልክ እንደያዘች ያላየሁ በመምሰል ነበር ጮከ ብዬ የጠየቅኳት፡
በምልከት ጠቆመችኝ የስልኩ ወግ ያጓጓት ትመስላለች፡፡ አሁን ከዘጋው የደወለላት ሰው መቼም
የማይደውልላት ይመስል፡፡
“ይቅርታ ወደ ግራ ነው?" ያልገባኝ መስዬ ጠየቅኳት፡፡
ስልኩን በእጁ መዳፍ እፈነችና ወደ ቀኝ በዛጋ ስትታጠፍ አለችኝ በትህትና ድምጽዋን ዝግ
አድርጋ ዓይኗን እያስለመለመች፡፡ ትህትና አያምርባትም፡፡ የትወና ትህትና መሆኑ ያስታውቅባታል
እንዳንድ ሴቶች ትህትና አያምርባቸውም፡፡ እንደሰፊ ሹራብ ፈታቸው ላይ ሲንዘላዘል ከልባቸው
አንዳልሆነ ያስታውቅባቸዋል፡፡ ትህትና በቀመር አያምርም፡፡ ትህትና ከእውነተኛ ማንነት
ሌሎችን ሳይሆን ራስን ከማክበር ፈንቅሎ የሚወጣ ባህሪ ነው:: ብዙ ቦታ ያጋጥመኛል
ያልፈጠረባቸውን ባህሪ ዓይናቸውን እያስለመለሙና ድምፃቸውን ለመስማት እስከሚያስቸግር ዝግ
አድርገው “ጨዋ ለመባል የሚሞከሩ ለዛ ቢሶች፡፡ አንዴ የእኔ ፍቅረኛ የነበረችው ነርስ ነበረች
ፊቴ ቁማ መንገድ የጠቆመችኝን ነርስ ታዲያ በምልከት ያሳየሽኝ እኮ ወደ ግራ ነው ግራና
ቀንሽን ሳትለይ ነው የሽንት ቤት አቅጣጫ ጠቋሚ አድርገው የቀጠሩሽ?!” ብያት መንገዴን
ቀጠልኩ፡፡ ስልኩን በመዳፏ እንዳፈነች በግርምትና በብስጭት አፈጠጠችብኝ፡፡ ሳልሰማ የአዕምሮ ህክምና ጀመርን እንዴ?” ሳትል አትቀርም፡፡
መፀዳጃ ቤቱ እየተፀዳ ስለነበር የፅዳት ስራተኛዋ "ይቅርታ እዛ ተጠቀም ለጊዜው” አለችኝ
ትህትና፡፡ የሴቶችን መፀዳጃ ቤት እያሳየችኝ፡፡ "አይይይ! ከተፀዳ ሲኦል ያልተፀዳ መፀዳጃ
ቤት ይሻላል” አልኳት፡፡ አልገባትም፡፡ ምን ይገባታል? ከመኖር ብዛት ሴትነት ገነት መስሏት!!

👍33❤1
የላብራቶሪ ውጤቴ ጋር የወሰድኩት ነገር አስደሳች ነበር፡፡ የላብራቶሪ ቴክኒሻኗን ስልክ !!
ሃሃሃ “በደማችን ያመጣነውን ስልክ ማንም አይቀማንም ማለት ዳድቶኝ ነበር፡፡ ደግሞ ስሟ
ሲገርም “መና” ጠበቅ አድርጋችሁ እንብቡት !! ይሄን ስም ሌሎች ሴቶች ላይ ከሰማችሁት
ስትፈልጉ ላላ አድርጋችሁ ማንበብ ትችላላችሁ፡፡
ለመና ግጥም ፃፍኩላት፤
አይንሽን ለማየት ሁልጊዜ እንድመጣ፤
ከሰኞ እስከ ሰኞ ምናል ጤና ባጣ
'አብርሽ ተሻለህ?” በቀጣዩ ቀን ደውላ መና ደህንነቴን ጠየቀችኝ፡፡ የሰው መውደድ ይስጥህ!
ከተባላችሁ መልዓከንም እንደሚያጠቃልል እንዳትረሱ!
“አብርሽ እንዳልጠይቅህ ቤትህን ደበቅክ ከ 3 ቀን በኋላ ደውላ.…
ጉድ በል ጎጃም…አለ !
“…እኔ የምልሽ መናዬ ደም ስትወስጅ በስህተት ልቤን ወስደሽው ይሆን እንዴ..?” ያልኳት ፊቷ ላይ የይለፍ ምልከት ካየሁባትና ተቀጣጥረን አራት ኪሎ አካባቢ ቡና ከጠጣን በኋላ ነበር፡፡
ሳቀችልኝ…! በሳቅ ፍርስስስስ አለችልኝ፡፡ ያወራኸው ይጣፍጥልህ ተብላችሁ ከተመረቃችሁ መልዓከትም ይስቁላችኋል፡፡ ሌላ ቀን የፅሁፍ መልዕክት ላከችልኝ hi Arish…:: b ተረስታለች፤ “ቢ" ፊደልን ድሮም አልወዳት እንኳን ረሳቻት!!
✨አለቀ✨

😁30👍13❤1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
ኮዜት
ኦርዮን የተባለ መርከብ
ከአሁን በኋላ በጣም ዝርዝር ውስጥ ባንገባ ይሻላል፡፡ ግን በሚቀጥለው ቀን ጋዜጣ ላይ የወጣውን ባጭሩ መጥቀስ ደህና ሳይሆን አይቀርም፡፡
«ዣን ቫልዣ የተባለ ወንጀለኛ ካመለጠበት ተይዞ ለፍርድ ቀርቦአል፡፡ይህ ወንጀለኛ ከእስር ቤት ካመለጠ በኋላ ስሙን በመቀየሩ በቀላሉ በፖሊሶች
ሳይያዝ ቆይቶ ነበር፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው ከጮሌነቱ ብዛት ከሀገራችን በስተሰሜን ለምትገኝ አነስተኛ ከተማ ከንቲባ እስከ መሆን ደረሰ፡፡ በዚህች ከተማ ውስጥ ብዙ ጥቅም የሚያስገኝለት ሥራም ሠርቷል፡፡ በመጨረሻ ግን በባለሥልጣኖች ታላቅ ጥረትና ድካም ማንነቱ ታውቆ ለመያዝ በቅቷል፡፡
በተያዘበት ወቅት በእቁባትነት ያስቀመጣት ሴት አዳሪ በድንጋጤ ሞታለች፡፡
ይህ እንደ ጎልያድ በጣም ጉልበተኛ የሆነ ሌባና ቀማኛ በድንገት ቢያመልጥም
በፖሊሶች ጥረት ከሦስት ቀን በኋላ ከፓሪስ ወደ ነበረበት ከተማ በሚጓዝ መኪና ውስጥ ሊገባ ሲል ተይዟል፡፡ ከተያዘ በኋላም ለሦስት ቀን የተሰወረው ከባንክ የነበረውን ከፍተኛ ገንዘብ ለማውጣት እንደሆነ ተደርሶበታል::
የነበረውም ገንዘብ ከስድስት እስከ ሰባት መቶ ሺህ ፍራንክ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከባንክ ያወጣውን ገንዘብ ግን የት እንዳስቀመጠው ከራሱ በቀር ማንም ስላላወቀ ገንዘቡን ለመውረስ አልተቻለም:: ይህ ዣን ቫልዣ የተባለ ቀማኛ የአንድ ሕፃን ልጅ ገንዘብ በመዝረፉ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ቀርቦአል፡፡ይህ ሽፍታ የተከሰሰበትን ጉዳይ ለመካድ አልፈለገም፡፡ ገንዘቡን የዘረፈው
ዣን ቫልዣ ብቻውን ሳይሆን የዘራፊዎችን ቡድን በመምራት እንደሆነ በሥራቸው የተመሰገነና አንደበተ-ርቱዕ የሆኑ የመንግሥት ባለሥልጣኖች አረጋግጠዋል:: ይህም በመሆነ የዣን ቫልዣ ወንጀለኛነት ስለተረጋገጠ
በሞት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል፡፡ ወንጀለኛው ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወይም ወደ ንጉሡ ይግባኝ ብሎ ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲለወጥለት ቢጥርም አልሆነለትም:: ዣን ቫልዣ ቱሉን ወደሚገኘው ወህኒ ቤት
ወዲያውኑ ተወስዶአል፡፡ ዣን ቫልዣ ቀደም ሲል የተሰጠው የእስር ቤት ቁጥር ተለውጦ አዲስ ቁጥር ተሰጥቶታል፡፡ አዲሰ ቁጥር 9430 ነው::
ወንጀለኛው ዣን ቫልዣ ለጥቂት ቀናት በተሰወረበት ሰሞን
ባለሥልጣኖች ሞንትፌርሜ ካተባለ መንደር ሲንሸራሽር መታየቱን ተናግረዋል:: ሞንትፐርሜ ከተባለ መንደር ውስጥ አንድ ወደ ዱር አዘውትሮ
መሄድ የሚወድ ሽማግሌ ነበር:: ሽማግሌ በአንድ ወቅት እስር ቤት
እንደነበር ሕዝቡ ይናገራል:: ፖሊሶችም በዓይነ ቁራኛ ይጠብቁታል:: ይህም ሽማግሌ ሥራ በማጣቱ በጣም ዝቅተኛ በሆነ ክፍያ የአውራ ጉዳና ጠጋኝ
ሆኖ እንዲሠራ መንግሥት ይቀጥረዋል፡፡
አንድ ቀን የተበላሽ መንገድ ለመጠገን በጠዋት ወደ ሥራው ቦታ ሲሄድ ከጫካ ውስጥ ከአንድ ዛፍ አጠገብ አካፋና ዶማ ተቀምጦ ያያል:: ከዚያም በመቆፈሪያውና በአካፋው አንድ ጊዜ እቃ እንደጠፋበት ሰው
አካባቢውን ያስሳል፤ ቆይቶ ደግሞ ትንንሽ ጉድባዎችን በጥድፊያ ይቆፍራል::
ይህን ተግባር ሲፈጽም የአንድ ትምህርት ቤት ዳይሬክተርና የአንድ ሆቴል ቤት ባለቤት የሆነው ሚስተር ቴናድዬ የተባለው የኮዜት አሳዳሪ በማየታቸው በጣም ይገረማሉ፡፡ «ታስሮ እኮ ነበር» ይላል ሚስተር ቴናድዬ ፤ «ጫካ ውስጥ እኮ ምን እንዳለ አይታወቅም፧ ምን ይሠራ ይሆን!»
ሁለቱ ሰዎች ጓደኛሞች ሲሆኑ ሽማግሌው ጋርም ቅርበት ነበራቸው:: በሌላ ቀን ሚስተር ቴናድዬ ተንኮል አስቦ ሰውዩው በመጠጥ ኃይል ወገቡ እስኪጐብጥ ድረስ በማጠጣት ያሰክሩታል፡፡ ይህ ቡላትሩስ የተባለው ግለሰብ በጣም ብዙ ስለጠጣ ብዙ ይለፈልፋል፡: በስካር መንፈስ የተናገረውን
በማቀናጀት የትምህርት ቤት ዳይሬክተሩና ሚስተር ቴናድዬ ከሚቀጥለው መደምደሚያ ላይ ይደርሳሉ::
«አንድ ቀን ጠዋት ሊነጋጋ ሲል ቡላትሩስ ወደ ሥራው ቦታ
ሲሄድ አካፋና ዶማ ከቁጥቋጦ ስር ተወሽቀው በማየቱ በጣም ይገረማል፡፡ ሆኖም መሣሪያዎቹ ምናልባት ከሠፈርተኞች መሃል አንዱ ረስቷቸው የሄደ ይሆናሉ ብሎ ከመገመቱ በስተቀር ምንም ነገር ሳያደርግ ያልፋቸዋል፡፡ ነገር
ግን በዚያው ቀን ወደማታ ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ቡላትሩስ የሚያውቀው ሰው በትልቅ ዛፍ ተከልሎ ይመለከታል፡፡ ቡላትሩስን ግን አላየውም፡፡ ሰውዬው ለአገሩ ባዳ ለሰው እንግዳ ሲሆን በእነቴናድዬ አተረጓጉም ቡላትሩስ
ግለሰቡን የሚያውቀው እስር ቤት ነው:: ይህ ሰው ከዛፉ ከለላ ወጥቶ ጥቅጥቅ ወዳለው ጫካ አመራ፡፡ ሽማግሌው ምንም እንኳን ቢሰክርም
የሰውዬውን ስም ለመናገር አልፈቀደም:: ግለስቡ አንድ በጋ የተጠቀለለ አነስተኛ ሻንጣ መሳይ ነገር ይዟል፡፡ ከሁለትና ከሦስት ሰዓት በኋላ ሰውዬው
ጥቅጥቅ ካለው ጫካ ተመልሶ ወደ ውጭ ሊወጣ ቡላትሩስ አይቶታል፡፡
ሲመለስ ግን የያዘው ሻንጣ ሳይሆን ዶማና አካፋ ብቻ ነበር፡፡ በሚቀጥለው ቀን በጠዋት ሰውዬው በሄደበት አቅጣጫ ቡላትሩስ ይሄዳል፡፡ ግን ያ
ግለሰብ ከዚያ ሥፍራ አልነበረም:: በላትሩስ ምን ብሎ ያስባል? «ማታ ሰውዬው ይዞት በነበረው ዶማ ጉድጓድ ቆፍሮ ያንን ሻንጣ መሳይ ነገር ከቀበረ በኋላ በያዘው አካፋ አፈሩን በመመለስ ደፍኖታል:: መቼስ የቀበረው
ነገር ሰው አይሆንም፣ ምክንያቱም ሳጥንዋ ትንሽ ናት:: ስለዚህ የቀበረው ገንዘብ ነዋ» በማለት ደመደመ::
ስለዚህ ገንዘቡን ለማግኘት ቡላትሩስ ፍለጋውን ቀጠለ፡፡ ወጣ፣ ወረደ ፣ አዲስ የተነካካ አፈር ባገኘ ቁጥር ቆፈረ፤ መሬቱን ጠራረገ፣ የወደቀ ቅጠል
አገላበጠ፡፡ ግን ልፋቱ ሁሉ ከንቱ፡ ሆኖ ምንም ነገር አላገኘም::
ቡላትሩስ በሰከረ ቁጥር ይህን ታሪክ በመዘላበድና በመቀባጠር
ያወራል፡፡ ሆኖም ማንም ሰው ምንም ነገር ስላላገኘ ወሬው ከጊዜ በኋላ እየተረሳ ሄደ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በ1923 ዓ.ም. ወደ ጥቅምት ወር መገባደጃ ላይ የቱሉን ከተማ
ነዋሪዎች ኦርዮን የተባለ የጦር መርከብ ሲመጣ በሩቁ ያያሉ፡፡ ሰው ተሰባስቦ መርከቡን ይጠብቃል፡፡ መርከቡ ጉዳት ደርሶበት ለጥገና ነበር
የመጣው:: አንድ ቀን ጠዋት የመርከቡ ሠራተኞች የጥገና ሥራ ሲሰሩ ያልታሰበ አደጋ ይደርሳል፡፡
የመርከቡ ሠራተኛ ከመርከቡ ጫፍ ላይ ቆሞ ገመድ እየጠቀለለ ሳለ መቆሚያውን ስቶ ሊወድቅ ይንገዳገዳል፡፡ ቀጥ ብሎ ለመቆም ጥቂት ከታገላ
በኋላ ለመመለስ ስላልቻለ ጥልቀት ካለው ባህር ውስጥ ሊወድቅ ሲል ባንድ እጁ ገመድ ይዞ ይንጠላጠላል፡፡ ከዚያም በሁለት እጁ ገመዱን ጥፍር
አድርጎ ላለመውደቅ ትግሉን ይቀጥላል:: ገመዱን ከለቀቀ በርቀት ተወርውሮ ጥልቀት ካለው ባህር ውስጥ ሊወድቅ ሆነ፡፡ ከዚያ ርቀት ከወደቀ እንደሚሞት
ያውቃል፡፡ ሰውዬውን ለመርዳት መሞከር ማለት ደግሞ ከትልቅ አደጋ ውስጥ መውደቅ ማለት ነበር፡፡ ግለሰቡን ለማዳን የሚሞክር ሰው ከባህሩ
ውስጥ መውደቅ ማለት ነበር፡፡ ግለሰቡን ለማዳን የሚሞክር ሰው ከባህሩ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ከዚያ የነበረ ሁሉ የሚያውቀው ነበር። ስለዚህ ግለሰቡን ለመርዳት ማንም አልደፈረም:: ሰውዬው ግን እየደከመ ሄደ::

👍17❤1🥰1
እጆቹ ተንቀጠቀጡ:: ከአደጋው ለማምለጥ ሲሞክር የተንጠለጠለበት ገመድ
በይበልጥ እየተወዛዝ ግለሰቡን በይበልጥ ያወራጨዋል፡፡ ከዳር የቆመ ሁሉ «ከመቼ መቼ ገመዱን ለቅቆ ይሰምጣል» እያለ በጭንቀት ዓይን ያየዋል፡፡ የሚገርመው ሰውዬው በፍርሃት ተውጦ እርዳታ እንዲያደርጉለት
እንኳን አልጮኸም:: አንዳንድ ሰዎች ግን ከፍርሃታቸውና ከድንጋጤያቸው ብዛት የተነሳ «ሰውዬው ሲወድቅ አናይም) በማለት አቀረቀሩ:: አንዳንዶቹም
ፊታቸውን አዞሩ፡፡ ከተሰበሰበው ሰው መካከል ድንገት አንድ ሰው ብቅ ብለ" ግለሰቡ ተንጠልጥሎ ወደነበረበት ገመድ እየተንጠላጠለ ሲመጣ ታየ:: ይህ ሰው የለበሰው ልብስና ያጠለቀው ቆብ የእስረኛ ስለነበረ የተፈረደበት ወንጀለኛ ለመሆኑ ተመልካች ሁሉ አወቀ፡፡ ያደረገው ቆብ ባለ አረንጓዴ ቀለም ስለነበር ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ወንጀለኛ እንደሆነ ሰው
አልተጠራጠረም:: ወደ መርከቡ ጫፍ ሲቃረብ ኃይለኛ ነፋስ ስለነፈሰ ያደረገው ቆብ ነፋስ ይዞት ሄደ፡፡ ይህን ጊዜ ፀጉሩ ሽበታም ለመሆኑና ሰውዬው በእድሜ ጠና ያለ ለመሆኑ ታወቀ፡፡
ቀደም ሲል በግርግሩ ወቅት ከሕግ ፊት ቀርበው ከተፈረደባቸው መርከቡ ላይ ከነበሩት እስረኞች መካከል አንደኛው ወደ ጠባቂዎች አዛዥ
ሄዶ «ኃላፊነቱ የራሴ ይሁንና ይህን ሰው ለመርዳት ስለምፈልግ እድሉ
ይሰጠኝ» ብሎ ሲጠይቅ ተሰምቷል፡፡ አዛዡ በዓይን ጥቅሻ እሺታውን ሲገልጽለት ወዲያው የብረት መዶሻ አንስቶ የታሰረበትን የእግር ብረት በአንድ ምት ከበጣጠስ በኋላ ወፍራም ገመድ አነሳ፡፡ ገመዱን ይዞ ወደ
መርከቡ ጫፍ መውጣት ጀመረ::
ከመቅጽበት ከመርከቡ ጫፍ ደርሶና ጥቂት ቆም ብሎ ትንፋሽን
ከሰበሰበ በኋላ ሰውዬው የተንጠለጠለበትን ርቀት በዓይን ግምት ለካ::ዓይኑን ቀና አድርጎ ወደ ሰማይ አይቶ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ።
የተመልካች ልብ ቀጥ ብሎ እንደቆመ ያህል ትንፋሽ ረጠረው:: ከመርከቡ ጠርዝ ላይ ቆሞ በያዘው ገመድ ወገቡን በመጠፈር አሰረ:: ገመዱን አጥፎና
ደህና አድርጎ ከመርከቡ ጫፍ ጋር አያያዘውና ኣጥብቆ ካሠረ በኋላ እስከ
መጨረሻው ወደታች ለቀቀው:: ከዚያም ገመዱን ይዞ በገመድ ላይ እየተንጠላጠለ ወደታች መውረዱን ቀጠለ:: አሁን እንግዲህ በገመድ
የተንጠለጠለው አንድ ሰው ብቻ ሳይሆን ሁለት ሰዎች በመሆናቸው
የተመልካች ልብ ይበልጥ በጭንቀት ተወራጨ:: አንዳንድ ሴቶች ማልቀስ ጀመሩ::
ሁሉም ዝም ስላለ የዝንብ ስርያ እንኳን ለመስማት ይቻላል፡፡ ሰው
ሁሉ በኃይል የተነፈሰ እንደሆነ «ነፋሱ አይሉ ሁለቱን ሰዎች በይበልጥ በማወዛወዝ ከባህሩ ላይ ይጥላቸዋል» በማለት መናገር ቀርቶ በኃይል
የሚተነፍስ እንኳን ጠፋ::
ወንጀለኛው እስረኛ ዝግ ብሎ በመውረድ የመርከብ ሠራተኛው
ከተንጠለጠለበት ደረሰ፡፡ መርከበኛው ከዚያ ወዲያ አንድ ደቂቃ እንኳን ቢቆይ ኖሮ ተስፋ በመቁረጥ ጥልቀት ካለው ባህር ውስጥ ይገባ ነበር።
ወንጀለኛው ተንጠልጥሎ ከወረደበት መንታ ገመድ በአንደኛው መርከበኛውን አጥብቆ አሰረው:: የአሰረውም በአንድ እጁ ሲሆን በሌላው እጁ
እንዳይወድቅ ገመዱን አጥብቆ ይዟል፡፡ ካንጠለጠላቸው ሁለት ገመዶች በአንደኛው መርከበኛውን በሚገባ መታሰሩን ካረጋገጠ በኋላ እየደገፈው ቀስ እያሉ ወደ ላይ ይወጡ ጀመር፡፡ ከመርከቡ ጫፍ ደረሱ፡፡ ቀስ ብለው
በሌላ አቅጣጫ ማለት የተሻለ መቆሚያ ወዳለበት ሥፍራ ሄዱ፡፡ የተሻለ መቆሚያ ካለበት ሥፍራ ሲደርሱ ወንጀለኛው እስረኛ መርከበኛውን ተሸክሞ
ሰዎች ወደነበሩበት ሥፍራ ይዞት ወረደ:: ከዚያ በኋላ ሰውዬው በጣም ተጐድቶ ስለነበር እንዲንከባከቡት ለሥራ ጓደኞቹ አስረከበው::
ይህን ጊዜ የተሰበሰበው ሕዝብ በኃይል አጨበጨበ፡፡ እስረኞችን
ይጠብቅ የነበረ የአሥር አለቃ፣ ሴቶችና ሌሎች ግለሰቦች ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡ የተቀሩት ደግሞ «ደስ የሚል ትርዒት» በማለት በመተቃቀፍ ተሳሳሙ:: እልልታው ቀለጠ፡፡ የተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ «ለዚህ ጀግና ምህረት ይገባል» ሲል አስተጋባ፡፡
እስረኛው ግን ወደ ቦታው ተመልሶ ከሌሎች እስረኞች ጋር መደባለቅና የተመደበለትን ሥራ መሥራት እንደነበረበት እልዘነጋም:: ቶሎ ከሥራው
ቦታ ለመመለስ እየሮጠ ሄደ፡፡ ከዚያ የነበረ ዓይን ሁሉ ተከተለው:: ድካም ሳይሰማው እየሮጠ በመሄዱ ሰው ሁሉ ተገረመ:: ሆኖም በድንገት ቆም
ሲል «አይ ቢደክመው ነው» ሲል ሰው ገመተ፡፡ ግን ወዲያው ሰው በኃይል ተንጫጫ:: ወንጀለኛው እስረኛ ከባህሩ ውስጥ ወደቀ፡፡
የወደቀበት ሥፍራ በጣም አደገኛ ሲሆን የወደቀው ከሁለት መርከቦች መካከል ነበር:: «ሊሰምጥ ይችላል በማለት ከዚያ የነበረ ሕዝብ ሁሉ ጠረጠረ፡፡ አራት ሰዎች ወዲያው በጀልባ ተከተሉት:: ሕዝበ እንደገና
ተተራመሰ፤ ልቡም ተሸበረ:: እስረኛው ተንሳፍፎ ሳይወጣ ቀረ:: ፍለጋው ቀጠለ፡፡ ግን ስላልተገኘ ፍለጋው መና ሆነ፡፡ መሽቶ ለዓይን ያዝ እስኪያደርግ ድረስ ቢፈለግም የሰውዬው አስከሬን እንኳን አልተገኘም::
በሚቀጥለው ቀን የቱሉን ጋዜጣ የሚቀጥለውን ጽሑፍ አወጣ::
«ኖቬምበር 17 ቀን 1823 ዓ.ም. ትናንት ኦርዮን ከተባለ መርከብ ላይ የነበረ የተፈረደበት እስረኛ ሊሰምጥ የነበረውን መርከበኛ ካዳነ በኋላ ከባህር ውስጥ
ስለወደቀ ሰምጧል:: አስከሬን ከባህሩ ውስጥ ብዙ ቢፈለግም ሊገኝ አልቻለም፡፡የወንጀለኛው እስረኛ መለያ ቁጥር 9430 ሲሆን ሰውዬው ዣን ቫልዣ የተባለ እስረኛ እንደሆነ ታውቋል፡፡»....

👍22
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
ለሞተ ሰው የገቡትን ቃል ማክበር
ሞንትፌርሜ የተባለ ከተማ የሚገኘው ከኮረብታ ላይ ሲሆን የከተማው ሕዝብ ውሃ ችግር አለበት፡፡ ውሃ ለማግኘት ሴቶች ራቅ ካለ ሥፍራ ይሄዳሉ፡፡ ከከተማው ራቅ ብሎ ከሚገኘው ጫካ ውስጥ ብዙ ኩሬዎች
ነበሩ፡፡ ከኩሬዎቹ ደግሞ ራቅ ብሎ የከተማው ሕዝብ የሚጠቀምበት
ምንጭ አለ፡፡ ምንጩ ያለበት ቦታ ከከተማው ቢያንስ አሥራ አምስት ደቂቃ ያስኬዳል፡፡
ስለዚህ በሞንትፌርሜ ከተማ ለአንድ ቤተሰብ የሚያስፈልገውን ውሃ ማሟላት ቀላል ሥራ አልነበረም፡፡ ሀብታሞች የመንግሥት ባለሥልጣኖችና
የእነቴናድዬ ሆቴል ቤት ባለቤቶች ውሃ እየገዙ ነበር የሚጠቀሙት:: አንድ ባልዲ ውሃ በአንድ ፔኒ ይገዛሉ፡፡ ውሃውን የሚሸጥላቸው አንድ ሽማግሌ ነው:: ሽማግሌው ውሃ ልማት መሥሪያ ቤት ውስጥ ሥራ ቢኖረውም ደመወዙ በጣም አነስተኛ ስለነበር ኑሮውን ለማሟላት ከተጠቀሰው ምንጭ
ውሃ እየቀዳ ይሸጣል፡፡ ሰውዬው አንዳንድ ቀን በጣም ከመሸ በኋላ እንኳን በጨለማ ውሃ ለመቅዳት ይሄድ ነበር ይባላል::
የሽማግሌው የኑሮ ውጣ ውረድ ምናልባት አንባብዬ ካልረሳት ከኮዜት የተለየ አልነበረም:: ኮዜት እነቴናድዬን በሁለት መንገድ ነበር
የምትጠቅማቸው:: ከእናትዋ ገንዘብ ይላክላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ልጅትዋ
እቤት ውስጥ በሥራ ትረዳቸዋለች:: ምንም እንኳን የኮዜት እናት ገንዘብ መላክዋን ብታቋርጥም ኮዜትን ከቤታቸው እንዳላበረርዋት ቀደም ሲል
አንብበናል፡፡ ያላባረርዋት ሠራተኛ ከመቅጠር ስላዳነቻቸው ነበር፡፡ እቤት ውስጥ ውሃ ሲያልቅ ውሃ ለመቅዳት ወደ ምንጩ ትሄዳለች:: ማታ ማታ በጨለማ ወደ ምንጩ መሄድ በጣም ስለሚያስፈራት ውሃ ከመሸ እንዳያልቅ በጣም ትጠነቀቅ ነበር፡፡
በ1923 ዓ.ም የገና በዓል በሞንትፌርሜ ከተማ በጣም በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡ ሰው ሁሉ ከየቤቱ ወጥቶ መሸታ ቤቶችን ያደምቃል፡፡ በገናው
ዋዜማ ከነቴናድዬ ሆቴል ቤት ብዙ ጠጪዎች ሻማ በርቶላቸው ይጠጣሉ።ጫጫታው፣ ግርግሩ፧ ሁካታውና የሲጃራው ጭስ ሌላ ነው:: የሚስተር ቴናድዬ ባለቤት እራት እየሠራች ነበር:: ሚስተር ቴናድዬ ከጠጪዎች ጋር
አብሮ እየጠጣ የፖለቲካ ወሬ ያወራል፡፡
ኮዜት ዘወትር ከምትቀመጥበት ከእሳት ማንደጃ አጠገብ የተቀደደ
ልብስ ለብሳ ቁጭ ብላለች:: ከሚነደው እሳት አጠገብ ቁጭ ብላ ለእነቴናድዬ ልጆች ሹራብ ትሠራለች፡፡ አጠገብዋ አንዲት ትንሽ ድመት ከወንበር ስር
ብቅ ጥልቅ እያለች ትጫወታለች፡፡ ከሚቀጥለው ክፍል ውስጥ የሚጫወቱት ልጆች ሳቅና ጨዋታ በጉልህ ይሰማል:: የእነቴናድይ ልጆች ነበሩ ከክፍሉ ውስጥ የሚጫወቱት
ከጭስ መውጫው አጠገብ የለፋ የበሬ ቆዳ ተንጠልጥሏል፡፡ የሕፃን
ልጅ ለቅሶ መጠጥ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ጫጫታን ዘልቆ ይሰማል፡፡ ክረምት ከመግባቱ በፊት የተወለደ ሕፃን ሲሆን «ብርዱ ስላየለበት ሳይሆን
አይቀርም የሚያለቅሰው» አለች እናቱ፡፡ እናቱ “እሹሩሩ» እያለች አባበለችው፡፡አሁንም ሕፃኑ እያመረረ ሲያለቅስ ጊዜ «ምነው ይህን ልጅ አንድ ብትዪው»
አሊ ሚስተር ቴናድዬ::
እባክዎን ይተውት! ስልችት ነው ያለኝ» አለች እናቱ፡፡፡ ልጁ ማልቀሱን ቀጠለ፡፡
አራት እንግዶች ገቡ፡፡
ኮዜት ተክዛ ቁጭ እንዳለች ነው:: ምንም እንኳን እድሜዋ ገና
ስምንት ዓመት ቢሆንም ሁኔታዋና አመለካከትዋ የአሮጊት ይመስላል:: «አሁን እንግዲህ ለእንግዶቹ እግር መታጠቢያ የሚሆን ውሃ አምጪ ሊሉኝ
ነው ፤ እንስራ ውስጥ ያለው ውሃ እንደሆነ አልቋል› በማለት ኮዜት
አሰላሰለች::
ወዲያው ከአንግዶቹ መካከል አንደኛው መጥቶ «ምነው ለፈረሴ
ውሃ ሳትሰጡት» ይላል፡፡
«ምነው ተሰጥቶት» አለች ሚስስ ቴናድዬ::
«የለም፣ አልተሰጠውም» ሲል እንግዳው ተከራከረ::
ኮዜት ከተቀመጠችበት ተነሳች::
«ምነው ጌቶች» አለች:: «ፈረሱ እንደሆነ ጠጥቷል፡፡ ባልዲ ሙሉ
ውሃ ሰጥቼው ጠጥቷል:: እኔ ነኝ ደግሞ የሰጠሁት::»
የተናገረችው ልክ አልነበረም፤ ኮዜት እየዋሸች ነበር፡፡
«ይህች ከእኔ ጭብጥ የማትበልጥ አንዲት ፍሬ ሕፃን ልጅ የምታወሪው ቅጥፈት ከጋራ ይበልጣል አለ መንገደኛው:: እመኑኝ ፈረሴ አንድ እፍኝ
ውሃ እንኳን አላገኘም:: ውሃ ሲጠማው የሚያሰማውን ድምፅ በትክክል አውቀዋለሁ::»
ኮዜት ሳታመነታ ቅጥፈትዋን በመቀጠል ማስተባበያዋን በጣም በደክመ ድምፅ ተናገረች፡፡
«ግን እኮ ብዙ ውሃ ነው የጠጣው::»
«በይ ነይ» አለ መንገደኛው:: ‹‹በቃሽ ብዙ አትለፍልፊ:: ለፈረሴ
ዓይኔ እያየ ውሃ ስጪው፤ ድርቅናሽን ግን ብትተዪው ይሻላል፡፡»
ኮዜት ቀደም ሲል ተቀምጣበት ከነበረው ጠረጴዛ ስር ሄዳ ቁጭ
አለች::
«ትክክል ነው፤ ፈረሱ ውሃ ካላገኘ ውሃ እንዲሰጠው ይገባል» አለች
ሚስስ ቴናድዬ::
ከዚያም በዓይንዋ አካባቢውን ቃኘች::
«ይህቺ ልጅ የት ሄደች?» ስትል ጠየቀች::
ከጠረጴዛ ስር ተወሽቃ አየቻት::
«ምን አባሽ ይወሽቅሻል፧ በይ ነይ ውጪ» ስትል ጮጮኸችባት::
ኮዜት ተነሳች ፣ የጠጪዎችን እግር ረግጣ ሌላው ደግሞ
እንዳይጮህባት እየተጠነቀቀች ተራመደች::
ሚስስ ቴናድዬ ጩኸትዋን ቀጠለች::
«አንች ውሻ» አሁን ቶሎ ብለሽ ለፈረሱ ውሃ እንድትሰጪው::
«ግን እሜቴ» አለች ስትፈራ ስትቸር፤ «ውሃው እኮ አልቋል::
«ታዲያ ወደ ምንጩ ቶሉ ወርደሽ ቀድተሽ አትመጪም!» ካለች
ቦኋላ በሩን ከፈተችላት::
ኮዜት ጭስ ቤት የነበረውን ባልዲ ይዛ ወጣች፡፡ የባልዲው ውፍረትና
ቁመት ከእርስዋው ቁመት ይበልጥ እንደሆነ ነው እንጂ አያንስም:: ከውስጡ ገብታ ተመቻችታ ለመቀመጥ ትችላለች::
ሚስስ ቴናድዬ የምትሠራው ሾርባ በስሎ እንደሆነ ለማየት የእንጨት
ማማስያውን ነክራ አውጥታ እያጉረመረመች ላሰችው::
«የምንጭ ውሃ እኮ ሾርባ አያጣፍጥም፤ ወይስ ይህቺ የተረገመች ልጅ ምናምን ትጨምርበት ይሆን! ወይስ ሽንኩርት አሳንሼው ነው!»
ኮዜት ባልዲውን ተሸክማ እንደቆመች፧ በሩም እንደተከፈተ ነው።
ጊዜው ስለመሽ አብሯት የሚሄድ ሰው እየጠበቀች ነበር፡፡
«ምን አባሽ ይገትርሻል፧ አትሄጅም እንዴ» ስትል ሚስ ቴናድዩ
ጮኸችባት::
ኮዜት ወጥታ ሄደች:: በሩ ተዘጋ፡፡
ከእነቴናድዬ መሸታ ቤት ፊት ለፊት የነበረው የአሻንጉሊት መሸጫ
ሱቅ ሻማ አብርቶ ስለነበር የሻማው መብራት መንገዱን ያሳያል እንጂ ጨለምለም ብሏል፡፡ እንዳጋጣሚ ደመና ዞር ኖሮ ሰማዩ ላይ አንድ ኮከብ እንኳን አይታይም፡፡ ከሱቅ ውስጥ አንድ ትልቅ ጨርቅ የለበለ ኣሻንጉሊት
ነበር፡፡ አሻንጉሊቱ በጣም የሚያምር ዓይነት ሲሆን ኃላፊ፣ አግዳሚ እንዲያየው ከመስኮት አጠገብ ተሰቅሏል፡፡ ነገር ግን ያንን የመሰለ አሻንጉሊት ለልጅዋ
ለመግዛት አቅም ያላት ወይም ያለአግባብ ገንዘብ የምታባክን እናት ሞንትፌርሜ ከተማ ውስጥ ስላልነበረች ኣሻንጉሊቱ ከሱቁ ውስጥ ለብዙ ጊዜ ተቀምጦአል፡፡ የእነቴናድዬ ልጆች ከቤታቸው በወጡና በገቡ ቁጥር ያዩታል፡፡ ኮዜትም ዘወትር ዓይንዋን ትጥልበታለች::
ያን እለት ማታ ኮዜት ባልዲዋን ተሸክማ ወደ ምንጩ ውሃ ልትቀዳ
ስትሄድ አሻንጉሊቱን ትኩር ብላ አየችው:: «እመቤቴ» ብላ ለአሻንጉሊቱ ስም አውጥታለት ነበር፡፡ እንደዚያን እለት ቀረብ ብላ አይታው አታውቅም::

👍14
መከፋትዋንና ተልኮዋን ረስታ አሻንጉሊቱን በማየት «ውይ እንዴት ታምራለች» ስትል አሰበች::
ያቺ የተከፋች ሕፃን ሱቅ ውስጥ ከረሜላውን፣ አሻንጉሊቱን፣
ቆርቆሮውንና ምናምኑን ማየቱ ደስታ ሰጣት:: ሱቀ ደግሞ የመዝናኛ ቤት መሰላት:: ብዙ ባየች ቁጥር መንግሥተ ሰማይ የገባች መሰላት:: ከትልቅ
አሻንጉሊት አጠገብ ሌሉች ትንንሽ አሻንጉሊቶችም ነበሩ።
የልጅ ነገር፣ ውሃ እንድትቀዳ የተላከች መሆንዋን ረስታ እነዚያን
ኣሻንጉሊቶችን ማየትዋን ቀጠለች:: አንድ ወጪ ከጌቶችዋ ሆቴል ቤት ሲወጣ በሩ ተከፈተ:: ሚስስ ቴናድዬ በሩቁ አየቻት፡፡ «አንቺ እርጉም፧ እስካሁን እዚሁ ነው እንዴ ያለሽው? ቆይ ጠብቂኝ፤ መጣሁልሽ፤ ምን አባሽ
ከዚያ እንደገተረሽ ትነግሪኛለሽ» በማለት እየጮኸች ከቤቱ ወጣች፡፡
ኮዜት ባልዲዋን እንደተሸከመች እግሬ አውጪኝ አለች:: በአላት
ኃይል በመሮጥ ወደ ምንጩ ገሰገሰች:: የእነሚስተር ቴናድዬ ሆቴል ቤት ከመንገድ ዳር ከመሆኑም በላይ አጠገቡ ትልቅ ቤተክርስቲያን አለ:: ኮዜት ከቤተክርስቲያኑ እስክትርቅና
ከዋናው መንገድ እስክትወጣ ድረስ ብርሃን ስለነበር ብዙ አልተቸገረችም::
ግን ከዚያ እየራቀች ስትሄድ በጨለማ ተዋጠች:: ኮሽታ በሰማች ቁጥር የባልዲውን ማንጠልጠያ በሚቃጨል ድምፅ ታሰማለች:: ወደ ምንጩ
የሚወስደው መንገድ ጠመዝማዛና ብቸኛ ነው:: ከየቤቱ የሚታየው የብርሃን ጭላንጭል ድፍረት ስለሰጣት ኮዜት ቤቶች እስካየችና ሰው በሚኖርበት
አካባቢ እስካለፈች ድረስ አልፈራችም:: ቤት ከሌለሰት ጭር ካለ አካባቢ ስትደርስ ግን በጣም ስለፈራች ልብዋ በኃይል ይመታ ጀመር፡፡ ወደ መጨረሻው ከነአካቴው መንገድ መቀጠሉን ፈርታ ራስዋን እያከከች ቆመች
በጨለማው እስከታያት ድረስ ለማየት ብትሞክር ከአውሬ በቀር ሰው የለም፡፡ ከቆመችበት አካባቢዋን ስታጤን አውሬዎችና መናፍስት በሳሩ ላይ የሚጓዙ መሰላት፡፡ በጣም ፈራች፡፡ ግን ፍርሃትዋ ድፍረት ሰጣት:: ምን
አባታቸው፣ ምንጩ ስለደረቀ ውሃ አጣሁ እላቸዋለሁ» ካለች በኋላ ወደኋላ ተመልሳ ጉዞዋን ቀጠለች:: ወደፊት አንድ መቶ እርምጃ ያህል ከተጓዘች በኋላ ቆም ብላ አሳብ እንደገባውና እንደተጨነቀ ሕፃን እንደገና ፀጉርዋን ማከክ ጀመረች፡፡ ሚስስ
ቴናድዬ የጅብ አፍዋን ከፍታ፧ እንደ እሳት የሚለበልበውን ምላስዋን
አንግታ፤ በቁጣ የሚታጀበውን ፊትዋን አኮሳትራና ዓይንዋን አፍጥጣ በአሳብ ታየቻት። «ምን ልታደርገኝ ትችላለች? ባዶ እጄን ስመለስ እንዴት ትሆናለች?
ምን መግቢያ አለኝ?» ስትል ራስዋን ጠየቀች፡፡ ከፊት ለፊትዋ የሚስስ ቴናድዬ ቁጣና ዱላ፤ ከኋላዋ በጨለማ ተገንነት የሚቅበዘበዙ የአውሬ
መንጋዎች ታይዋት:: የሚስስ ቴናድዬ ቁጣና ዱላ ከኣውሬዎቹ መንጋጋ ይበልጥ አስፈራት:: ፊትዋን አዙራ ወደ ምንጩ ጉዞዋን ቀጠለች:: መሮጥ ጀመረች፡፡ ግራና ቀኝ ሳትል ብዙ ዛፎች ከነበሩበት ጫካ ውስጥ ገባች፡፡
ትንፋሽ እስኪያጥራት ድረስ ሩጫዋን ቀጠለች:: እየተንገዳገደች አሁንም
ሩጫዋን ቀጠለች::
እየሮጠች ሳለ ሆድዋ ስለባባ ማልቀስ ፈለገች፡፡ ግን ያለቀሰች እንደሆነ ምናልባት አውሬዎች ድምፅዋን ሰምተው እንዳይመጡ ፈርታ እንደ ምንም ብላ ዋጥ አደረገችው::
ምንጩ ከነበረበት ደረሰች:: ቆም ብሎ ለመተንፈስ እንኳን ጊዜ
አልወሰደችም፡፡ ሥፍራውን በጣም ለምዳው ስለነበር ከምንጩ በላይ ዝቅ
ብሎ የተጋደመውን የዋርካ ዛፍ ቅርንጫፍ ያዘች፡፡ ወዲያው አጎንብሳ የያዘችውን ባልዲ ከምንጩ ላይ ደቀነች:: ባልዲው ሲሞላ ቶሎ ብላ አንስታ
ከሳሩ ላይ አሳረፈችው:: ባልዲውን እንዴት ኣድርጋ እንዳነሳችው ለራስዋም ገረማት::
አሁን አሟልጮ እንዳይጥላት የባልዲወን ጆሮ ለቅቃ ከሚያንሸራትተው መረጋገጫ ላይ ወጣች:: ቶሎ ብላ ለመመለስ ፈለገች።ግን ባልዲው በጣም ሞልቶ ስለነበር አሁን ላንሳና ልሸከምህ ብትለው አቃታት፡፡ በአላት ኃይል ተጠቅማ ከመሬት እነቃነቀችው:: ግን ይዛው
ለመጓዝ የማይሞከር ነገር ሆነ፡፡ እንደገና ከማሳረፍ በቀር ሌላ ምርጫ አልነበራትም:: ውሃው እንዳይፈስ ቀስ ብላ ለማስቀመጥ ስትሞክር አዳልጧት
ከመሬት ተዘረረች፡፡ ውሃው ግን አልፈሰሰም:: ከወደቀችበት ዓይኖችዋን ጨፈነች፡፡ ቆይታ ገለጠቻቸው:: ወደ ሰማይ አንጋጣ ተመለከተች፡፡ ሰማዩ በደመና ተሸፍኗል፡፡
ከወደ ኮረብታው ቀዝቃዛ አየር ይነፍሳል፡፡ ዛፎቹ በጨለማ
ተውጠዋል፡፡ ቀረብ ያሉ ቅርንጫፎች የአውሬ ቅርጽ ስለያዘ በጣም ያስፈራሉ፡፡ ነፋሱ ሲያወዛውዛቸው የማያፏጭ ድምፅ ያሰማሉ፡፡ የደረቁ
የዛፍ ቅጠሎች አየር ይዟቸው ሲሄድ አንድ ነገር በርሮ የሄደ
ስለሚያስመስላቸው በፍርሃት ልብ ይሰነጥቃሉ፡፡ በአጠቃላይ አካባቢው ዘልሎ የሚውጥ ነበር የሚመስለው፡፡
ጨለማ መላ ሰውነትን ይረብሻል፡፡ የሰው ልጅ መድኃኒት ብርሃን
ነው፡፡ ከጨለማ ውስጥ የገባ ልብ ሁሌም እንደተረበሸ ሲሆን ዓይን ጨለማን ሊያይ ሕሊና ችግርንና መቅሰፍትን ነው የሚመለከተው፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በጨለማ ብቻውን ከጫካ ውስጥ ሲሄድ ሰውነቱ በፍርሃት ይንቀጠቀጣል፡፡ ከጨለማው ውስጥ አንድ ነገር የተደበቀ ይመስለዋል፡፡ በተለይ ለሕፃናት ጨለማ በጣም! እጅግ በጣም አስፈሪ ነው፡፡
ኮዜት ሕፃን ሆና ሳለ ከጨለማ ውስጥ ብቻዋን በመሆንዋ ፍርሃት
መላ ሰውነትዋን አርገበገበው፡፡ ሰውነትዋ ከመንቀጥቀጥ አልፎ ተንሰፈሰፈ። ዓይኖችዋ ተቅበዘበዙ:: «ምናልባት እኮ ነገም እንደዛሬው በጨለማ ውሃ
ቅጂ ይሉኝ ይሆናል» ስትል አሰበች፡፡
ሳታስበው በድንገት ከዚህ ጭንቀት ለመላቀቅ 1፣ 2፣ 3፣ 4 እያለች ወደ ላይ ቁጥር መቁጠር ጀመረች፡፡ አሥር ላይ ስትደርስ እንደገና ከአንድ ጀምራ ቆጠረች፡፡ «እንዴ ምን ማድረጌ ነው» በማለት ቶሎ ብላ ከወደቀችበት ብድግ አለች፡፡ አሳብዋ ሁሉ ኣንድ ሆነ፡፡ ይኸውም ከዚያ አስፈሪ ጨለማ
በርራ የምትወጣበት መንገድ መሻት ነበር፡፡ የሚስስ ቴናድዬ ቁጣና ዱላ እጅግ የሚያስመርር ስለነበር ያለ ውሃ ወደ ቤትዋ መመለስ አትችልም። የባልዲውን እጄታ በሁለት እጆችዋ አጥብቃ ያዘች:: በስንት ችግር ባልዲውን
ከመሬት ኣነሳችው፡፡
እየተንደረደረች ወደፊት ተራመደች፡፡ ጥቂት እንደተጓዘች በጣም ከብዷት ስለነበር ባልዲውን ከመሬት አሳረፈችው:: በኃይል ተነፈሰች፡፡ እንደገና ባልዲውን አንስታ መጓዝ ጀመረች:: መጀመሪያው ይበልጥ ጥቂት ከተጓዘች በኋላ እንደገና አረፈች:: ትንፋሽዋን ከዋጠችና እጆችዋን ካፍታታች በኋላ ጉዞዋን ቀጠለች:: ስትጓዝ እንደ አሮጊት ወደፊት ጎብጣና አቀርቅራ
ነበር፡፡
የባልዲው ክብደት እጅዋን አዛለው:: በውሃ የተነከረው እጅዋ ብረቱን ጨብጦ ብዙ በመቆየቱ እንደበረዶ ቀዝቅዟል:: እረፍት በወሰደችና ባልዲውን
ከመሬት ባስቀመጠች ቁጥር ውሃ እየተረጨ ከባዶ እግርዋ ላይ ይፈስሳል::ይህች የስምንት ዓመት ሕፃን በዚህ ዓይነት ከጨለማ ውስጥ መከራዋን ስታይ ያያት ፈጣሪ እንጂ ከዚያ ሥፍራ ሰው አልነበረም::
ብዙ ያረፈች እንደሆነ ቤት ስትደርስ በጣም ይመሽና ብዙ ቆየሽ ብላ እመቤቲቱ እንደምትደበድባት ታውቃለች፡፡ ስለዚህ ጥቂት ሄዶ ብዙ ማረፉን
አልወደደችውም፡፡ እንዲያውም ባረፈች ቁጥር ሚስስ ቴናድዬ የምታያት መሰላት፡፡ በጣም ደክሞአታል፧ ግን ጫካውን ጨርሳ ወደ ሜዳው ገና አልዘለቀችም፡፡ አሁን በመጨረሻ በአላት ኃይል ተጠቅማ ቶሎ ቶሎ እየተራመደች ሄደች:: በእርግጥም ብዙ ተጓዘች፡፡ ግን በአንድ ወቅት በጣም ስለደከማት «ምን ዓይነት አበሳ ነው» ስትል አለቀሰች:: ከአንድ ከምታውቀው ዋርካ ስር ቁጭ አለች::

👍19
በዚያች ሰዓት ዞር ስትል አንድ ግዙፍ ሰው ተከትሉአታል:: ሰውዬው ቃል ሳይተነፍስ የባልዲውን እጄታ ከኮዜት እጅ ነጥቆ ከያዘ በኋላ ጉዞውን
ቀጠለ፡፡ ኮዜት ተከተለችው:: በችግር ጊዜ አስፈሪ የሆነ ነገር ሲገጥም አስፈሪነቱ ስለማይታ፡ ይሆናል ኮዜት ሰወዬው አላስደነገጣትም፧ አልፈራችውምም:: እርሱ ግን ለካስ እርስዋ ሳታየው ከሩቅ ቦታ ጀምሮ ይከተላት ነበር::
ሰውዬው አናገራት፤ ያናገራት ግን በሹክሹክታ ሲሆን ድምፁ ጎርነን
ያለ ነው:: «የእኔ ልጅ ይሄ ባልዲ እኮ አንቺ ችለሽ የምትሽከሚው አይደለም አላት::
ኮዜት አንገትዋን ቀና በማድረግ የሰውዬውን ገጽታ ለማየት ከሞከረች በኋላ «አዎን፤ አባባ» ስትል መልስ ሰጠችው::
‹በይ ተይው፤ እኔ እይዝልሻለሁ» አለ ሰውዬው፡፡ ኮዜት ደስ አላት፤ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
«እውነትም በጣም ይከብዳል» አለ ለራሱ በልቡ፡፡
«ልጄ ስንት ዓመት ይሆንሻል?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ስምንት ዓመቴ ነው::»
«ይህን ውሃ ተሸክመሽ ብዙ ነው የተጓዝሽው?»
«ከዚያ ማዶ ምንጩ ካለበት ነው የመጣሁት::
«ቤትሽስ ከዚህ ብዙ ይርቃል?»
«ከዚህ አንድ አሥር ወይም አሥራ አምስት ደቂቃ ያስኬዳል፡፡»
ሳይነጋገሩ ጥቂት ተጓዙ፡፡
«እንግዲያውማ እናት የለሽም ማለት ነዋ?» ሲል ጠየቃት::
«እኔ እንጃ»
ስትል መለሰችለት፡፡ «እናት ያለኝ አይመስለኝም ፤
ሌሎች ልጆች ግን እናት አላቸው:: እኔ ግን የለኝም፡፡»
ከዚያም ለአጭር ጊዜ ዝም ዝም ተባባሉ:: ልጅትዋ ቀጠለች::
«ከመጀመሪያው ጀምሮ እናት የነበረኝ አይመስለኝም::» ሰውዬው ቀጥ ብሎ ቆመ:: ባልዲውን አስቀመጠው፡፡ የልጅትዋን ትከሻ ያዘ፡፡ በጨለማ ፊትዋን ለማየት ሞከረ::
«ስምሽ ማነው?» አላት::
«ኮዜት»
ሰውዬው ኮረንቲ የያዘው መሰለው:: እንደገና አፍጥጦ አያት:: እጁን ከትከሻዋ ላይ አንስቶና ባልዲውን ተሸክሞ መንገዱን ቀጠለ፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ ሌላ ጥያቄ ጠየቃት::
«አንቺ ልጅ፤ የት ነው የምትኖሪው?»
«ያውቁት እንደሆነ ሞንትፌርሜ ከተማ ወስጥ ነው የምኖረው::»
«አሁን ወደዚያው ነው የምንሄደው?»
«አዎን::»
አሁንም ዝም ብሎ ሳይናገር መንገዱን ቀጠለ፡፡
«በዚህ ጨለማ ውሃ ቅጂ ብሎ የላከሽ ማነው?»
«መዳም ቴናድዩ ናቸው::>>
«ይህች መዳም ቴናድዩ የምትያት ሴት ምን ትሠራለች?»
«እመቤቴ! ሆቴል ቤት አላቸው::»
«ሆቴል ቤት!» አለ:: እኔም ከዚያ ለማደር ስለሆነ የምሄደው መንገዱን ምሪኝ::
እሺ አላት ደስ እያላት ልክ ሆቴል ቤቱ በር ላይ ስትደርስ ሰውየው ባልዲውን ሰጣት ኮዜት ቀልጠፍ ብላ ወደ ውስጥ ገባች በር ላይ የተቀበለቻለት መዳም ቴናድዩ "አንቺ እስካሁን"ብላ የጀመረችውን ሳትጨርስ "እሜቴ አልጋ የሚፈልግ ሰው መቷል" አለች ኮዚት ከመዳም ቴናድዩ ቁጣ ለማምለጥ የውሸት ፈገግታ በማሳየት ወደ እንግዳው ዞር አለች
«እርሳቸው ናቸው?» ስትል ጠየቀች፡፡ ማዳም ቴናድዬ
«አዎን እመቤቴ» አለች ኮዜት::
«እኔ ነኝ አለ ሰውዬውም እጅ ለመንሳት ቆቡን እየነካካ::
«ሀብታም መንገደኞች ትህትና አይታይባቸውም:: ከሁኔታውና
ከአለባበሱ ሀብታም ሰው እንዳልሆነ ለመገመት አያስቸግርም» በማለት
አሰበች::
«ግባ» አለች ሴትዬዋ፡
ሰውየው ወደ ቤት ገባ፡፡ ሚስስ ቴናድዬ አተኩራ ተመለከተችው::
ሱሪው፣ ቆቡ፣ ጫማው፣ ባርኔጣው የተጎሳቆሉ ነበሩ:: ሴትዬዋ ወደ ባልዋ ሄዳ አንድ ነገር ጠየቀችው:: ባልዋ ከጠጪዎች ጋር አብሮ እየጠጣ ነበር፡፡ ባልየው ጣቱን በመነቅነቅ የጠየቀችው ነገር እንደሌለ ገለጸላት::
ይህን መልስ እንዳገኘች ወደ ሰውዬው ተመልሳ፡-
«ጀግናው፧ አዝናለሁ፤ ክፍል አልቋል» አለችው::
«ከፈለጋችሁበት አስተኙኝ እንጂ በጣም ደክሞኛል ሌላው ቢቀር
ማድቤት እንኳን ቢሆን ካነጠፋችሁልኝ ከዚያው አድሬ ተገቢውን ሂሣብ እከፍላለሁ፡፡»
«አርባ ሰስ፡፡»
«አርባ ሶስ! ይሁን ግድየለም::»
«ሂሣቡ በቅድሚያ ነው የሚከፈለው::»
ከሚጠጡት ሰዎች መካከል አንዱ «አርባ ሱስ» ሲል ከሴትዮዋ ጆሮ
ተጠግቶ ተናገረ፡፡ ክፍሎቹን የምታክራዩት ሃያ ሰስ አይደለም እንዴ?”
«ለእርሱ አርባ ነው» አለች ሴትዮዋ:: «ለድሃ በአርባ ነው
የማከራየወ::
« እውነትሽን ነው አለ ባልየው በዝግታና በማይሰማ ድምፅ፡፡
እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ቤት ያበላሻሉ፤ ብዙ መክፈል አለባቸው::»
ባልና ሚስቶ ከእንግዳው ጋር ሲነጋገሩ ሰውዬው የያዘውን እቃ
ከመሬት አስቀምጥ ከአግዳሚ ወንበር ላያ ቁጭ አለ:: ባለፈረሱ የባልዲውን ውሃ ይዞ ወጣ፡፡ ኮዜት...ከተለመደው ስፍራ ማለት ከምግብ ቤቱ ጠረጴዛ ስር
ቁጭ ብላ የሹራብ ስራዋን ቀጠለች:: ከመቀመጥዋ በፊት ተከፍቶ ከነበረው ፋሽኮ ቪኖ በብርጭቆ ለእንግዳው ሰጠችው::
እንግዳው የጠየቀው ቪኖ ይቅረብለት እንጂ አልጠጣውም፡፡ ዝም ብሎ ወደ ኮዜት እያየ ያጤናታል፡፡
ኮዜት ተጎሳቁላለች፤ ግን መልክዋ በጣም ቆንጆ ነው፡፡ ሰውነትዋ
ገርጥቷል፡፡ እድሜዋ ስምንት ዓመት ቢሆንም በሚገባ ላጤናት ስምንት ይቅርና ስድስት ዓመት እንኳን የሞላት አትመስልም፡፡ ትልልቅ ዓይኖችዋ ሰርጉደው ወደ ውስጥ ገብተዋል፡፡ በዘወትር ልቅሶ በልዘዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ
እንደታመመ ወይም እንደታሰረ ሰው ከንፈሮችዋ ደርቀዋል፡፡ እጆችዋ እንደ ሞረድ ተከታትፈው ሻክረዋል፡፡ ሥጋዋ አልቆ በአጥንት ብቻ ቆማ የምትሄድ
እስክትመልስ ከስታለች:: ሁልጊዜም ስለሚበርዳት ጉልበቶችዋን ኣጣጥፋ
መቀመጥ ልማድዋ ሆኖአል፡፡ የለበሰችው ልብስ ቡትቶ ስለነበር ከብዙ ቦታ ላይ ገላዋን በማሳየቱ በቁንጥጫ ብዛት የጠቆረው ሰውነትዋ በቀዳዳዎቹ
ገሃድ ወጥቷል፡፡ የዚህች ልጅ አመለካከት፣ ድምፅ፣ ዝምታና ጠቅላላ ሁኔታ የሚያመለክተው አንድ ነገር ነው. ፍርሃት:: በዚህም ፍርሃት የተነሣ ነው ወንዝ እንደመጣች ልብስዋን በእሳት ደረቅ ፧ ሰውነትዋ እንደራሰና ልብስዋ እንደረጠበ በቀጥታ ከጠረጴዛው ስር የተቀመጠችውና
ሥራዋን የቀጠለችው::
«እራት ይፈልጋሉ?» ስትል ሚስስ ቴናድዬ መንገደኛውን ጠየቀችው::
በአሳብ ተውጦ ስለነበር መልስ አልሰጣትም::
«ምን ዓይነት ሰው ነው?» አለች በጥርሶችዋ መካከል እየተናገረች::
«ምን የዘጋው ነው:: የእራት መብያ እንኳን ገንዘብ አልያዘም፡፡ የአልጋ
ሂሣብ ብቻ ሊከፍለኝ ነው እንዴ! ይሄማ ምኑ ይታመናል!»
የመኝታ ቤት በር ተከፈተ፡፡ ኢፓኒንና አዜልማ ገቡ፤ በጣም የሚያምሩ ልጆች ናቸው:: የከተማ እንጂ የገጠር ልጆች አይመስሉም:: የለበሱት
ልብስ በጣም የሚያምር ሲሆን ንጽህናቸው ሌላ ነው:: ደስታ ያልተለያቸው ለመሆናቸው ገጽታቸው ይመሰክራል፡፡
“እንግዲህ መጣችሁ! ቤቱ ሊረበሽ ነው አላች ሚስስ ቴናድዬ የውሽት ቁጣ በመቆጣት::
ከእሳቱ አጠገብ ሄደው ቁጭ አሉ:: አሻንጉሊቶቻቸውን አውጥተው መጫወት ጀመሩ:: አልፎ አልፎ ኮዛት የሹራብ ሥራዋን እያቆመች ቀና
ብላ ታያቸዋለች:: ኢፓኒና አዜልማ ግን ኮዚት ከዚያ ለመኖርዋ እንኳን
አያስተውሉም:: ለእነርሱ ኮዚት ውሻ ናት እንጂ ሰው አይደለችም::
የሦስቱ፡ ልጆች ዕድሜ ቢደመር ሃያ አራት ዓመት አይሞላም:: እነዚህ ልጆች የኅብረተሰቡን ገጽታ የሚጠቁሙ ሲሆኑ በአንድ በኩል ቅናትን በሌላ በኩል ደግሞ ሐሜትንና ንቀትን ያመለክትል

👍20
#ብዙዎች_ይላሉ . . !
ብዙዎች ይላሉ . . .
እንዴት ትችላለኽ ... ?
ከነፋስ መፏከር
ከግዑዝ መማከር
እንደምን ይቻላል . . . ?
ውቅያኖስን መክፈል
ተራራን ማካፈል
እኮ እንዴት ይኾናል . . . ?
ከዋክብትን ማርገፍ
ጨረቃን መደገፍ
እንዴትስ ይኾናል . . . ?
ብርሃንን ሽሮ ፣ መቆም በጨለማ
ፍጥረታትን ረስቶ . . .
ተፈጥሮን መጋጠም በሰውኛ ዜማ።
ብዙዎች ይላሉ . . .!
ይኽን የማያውቁ . .
አንቺ ካለሽ ጎኔ ኹሉም ይታለፋል
እንኳንስ ተፈጥሮ እግዜር ይሸነፋል።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
ብዙዎች ይላሉ . . .
እንዴት ትችላለኽ ... ?
ከነፋስ መፏከር
ከግዑዝ መማከር
እንደምን ይቻላል . . . ?
ውቅያኖስን መክፈል
ተራራን ማካፈል
እኮ እንዴት ይኾናል . . . ?
ከዋክብትን ማርገፍ
ጨረቃን መደገፍ
እንዴትስ ይኾናል . . . ?
ብርሃንን ሽሮ ፣ መቆም በጨለማ
ፍጥረታትን ረስቶ . . .
ተፈጥሮን መጋጠም በሰውኛ ዜማ።
ብዙዎች ይላሉ . . .!
ይኽን የማያውቁ . .
አንቺ ካለሽ ጎኔ ኹሉም ይታለፋል
እንኳንስ ተፈጥሮ እግዜር ይሸነፋል።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍11❤5👎5🔥2