አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
486 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በብረትና_ቻፕስቲክ_በተከበበ #ከተማ_እንሆ_የመለአክ
#ድምፅ_ተሰማ


#በአሌክስ_አብርሃም


እንዲት ፍቅረኛ ነበረችኝ፡፡ ይሄን አደረጎኝ ሳትል ርግፍ አድርጋ ተወችኝ፡፡ የተወችኝ ሰሞን
አዕምሮዬ ነገር እየቀላቀለ አስቸግሮኝ ነበር፡፡ የምይዝ የምጨብጠውን አጥቼ ነበር፡፡ ብዙ ነገር ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ ከተለያየን ከአምስት ወር በኋላ እንደወለደች ስሰማ "አንዲት ሴት
የምታረግዘው ስንት ወር ነው?" ብዬ አሰብኩ፡፡ መቼም ከእኔ አለማርገዟ ጥያቄ አልነበረውም፧
ምክንያቱም “ከጋብቻ በፊት ዝንቤን እሽ እንዳትል!" ብላኝ ስለነበር ቃሏን አክብሬ ከመሳም
ዘልዬ አላውቅም፡፡

ለዛውም ከንፈሯን እያሳደድኩ ነበር የምሰማት፡፡ በደቡብ በኩል ከንፈሬን ሳሞጠሙጥ ወደሰሜን
እየዞረች፤ ከሰሜን ስንደረደር ወደ ምስራቅ እየሸሸቶ ፍዳዬን አብልታኝ ነበር የኖርነው፡፡ ስንትና
ስንቴ ከንፈሯን የሳተ ከንፈሬ ባዶ አየር ስሟል፡፡ አየር ስታስመኝ ከርማ በመጨረሻ አየር ላይ
ትታኝ ሄደች፡፡ ደግሞ እኮ የአካሄዷ ክፋት “ቻው” ማለት ማንን ገደለ ? "አልፈልግህም ማለት ምን ችግር አለው ? አንድ ቅዳሜ ደውዬ "ዛሬ አንገናኝም እንዴ ፍቅር?” ስላት “ለምንድን ነው የምንገናኘው ?” ብላ ግራ የገባው ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡ በቃ በዛው ቀረች፡፡

እና ይሄው በተለያየን በአምስት ወሯ ወልዳ አረፈችው:: ነርስ ነበረች፤ በኋላ ስሰማ አንድ
ዶክተር ነው አሉ ያገባት፡፡ እኔ ሳድግ “ዶከተር እሆናለሁ” እንዳልኩት ፍቅረኛዬ “ሳድግ ዶክተር አገባለሁ” ብላ ሳትመኝ አልቀረችም። ከዛ በኋላ የሴት ዘር ጠላሁ፡፡ በተለይ ነርስ የሚባሉ
ሴቶች፧ ዶክተሮች ራሳቸው በሽታ ፈዋሽ ሳይሆኑ በሽታ መስለው ታዩኝ፡፡ ለዛ ነው ሆስፒታሎች
ሲኦል የሚመስሉኝ፡፡ ለእኔ በሽታ ማለት ወደሞት ሳይሆን ከሞት የባሰ ወደምጠላቸው ነርስና
ዶክተሮች የሚወስደኝ የሲኦል መንገድ ነው፡፡
ሰሞኑን ታዲያ ወደ አንድ የግል ሆስፒታል ጎራ ብዬ ነበር፡፡ በሕይወታችን ውስጥ የጠላታችንን ደጅ የሚያስጎበኙን የባሱ ጠላቶች ይገጥሙን የለ ! በቃ አመመኝና ወደምጠላው ሆስፒታል ሄድኩ፡፡ ሆስፒታሉ ውስጥ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሴት ነርሶችን ስመለከት “ይህ ነገር የግል ኮሌጅ ነው ? ወይስ የግል ሆሰፒታል ?" ብዬ አሰብኩ፡፡ ገና በሩ ላይ ስደርስ አንዲት በተናገረች ቁጥር ከንፈሯ ጆሮዋ ጥግ እና ጥግ እየደረሰ የሚመለስ
እዚያው ሃዲድ ክንፈሯ ላይ የደፈደፈችው ቻፕስቲኮ አፏን ፀሐይ ላይ የተቀመጠ የቅቤ ቅል
ያስመሰለው ነርስ ወደኔ መጣችና በቁሙ የሞተ ፈገግታ እያሳየችኝ፣ ምን ልርዳከ ? አለችኝ፡ ስትናገር ቃላቶቹ ያዳልጣቸዋል ቻፕስቲኩ ይሆን ?1 ጥርሷ በብረት ታስሯል፡፡ እሰኪ እሁን እስኪፈታላት ብትታገስ ምን ትሆናለች ? 'ካልሳቅሽ ወዮልሽ!' ያላት አለ ? መቼም የዚህች ነርስ ጓደኛ ብሆን (አይበልብኝና ከንፈሯን አንድታሳስረው ነብር የምመከራት፡፡

እኔ እንኳን የመጣሁት እናንተን ለመርዳት ነው” አልኩ ስለ ክፍያቸው ውድነት ማሸሞሬ ነበር፣
እርሷ ግን ፊቷ በፈገግታ ተጥለቀለቀ፤ አቁነጠነጣት፡፡ 'የተናገርኩት ይሄን ያህል ያስደስታል ወይንስ የእውነት የእርዳታ ድርጅት ልኮኝ የመጣሁ መስሏት ነው?' እያልኩ ስገረም "ኦ.ው.ኬ.! አዲስ የተመደቡት ዶክተር እርስዎ መሆን አለብዎት?” ብላኝ እርፍ፡፡ አቤት ኦኬ ላይ ከንፈሯን እንዴት አንደምታደርገው ! አንዳንድ የከተማችን ዘመነኛ ሴቶች በእንግሊዝኛ የከንፈር ቀመር
አማርኛ ካላወራን እያሉ ከንፈራቸውን ለጥጠውት ሊሞቱ ነው፡፡

ልጅቱ በደስታ ተጥለቀለቀች፡፡ ክርስቶስ ሊፈውስህ መጣ” የተባለ የእድሜ ልክ በሽተኛ
እንኳን እንደሷ አይፍነከነክም፡፡ የቃልኪዳን ቀለበቷን አውልቃ ሳትደብቀው በፊት (ማን ይሆን
ያገባት?) ፈጠን ብዬ እኔ እንኳን ልታከም የመጣሁ በሽተኛ ነኝ” አልኳት፡፡ ወዲያው ፊቷ
የተጥለቀለቀው የሳቅ ማዕበል ድራሹ ጠፍቶ፣ “ተከተለኝ” አለችና ወደ ካርድ ክፍል መራችኝ፡
እየተቆናጠረች፣ የሆነ ሰበር ሰካ የማለት ሙከራ ዓይነት፡፡ እች አረማመድ ለአዲሱ ዶክተር
ተቀምራ የተቀመጠች ሳትሆን አትቀርም፡፡

ካርድ ክፍሉ ውስጥ አንድ እግሯን አጥፋ ተሸከርካሪ ወንበር ላይ የተጎለተች ሌላ ቻፒስቲካም
“ስምህ አለችኝ፣
“ስሜ ምን ሆነ ” ስል ጠየቅኳት፡፡ ልክ አማርኛ ዘጠነኛ ቋንቋዬ ሳይመስላት አልቀረም፡፡
“አይ ስምህ ማነው ማለቴ ነው"
" እ..አብረሃም !"
እድሜህ ስንት ነው ?” (ማስቲካዋን ቀጭ)
"250 ብር ክፈል!”አለችኝ፡ከፈልኩ፡፡ ካርዱን እያቀበለችኝ፡፡ አየሁት ሰሜን አሳስታ ነው የፃፈችው፡፡
ስሜን አሳስተሸዋል” አልኳት፣ በመስተዋቱ ሸንቁር ጎንበስ ብዬ፡፡
ሶሪ! እስኪ….አብርሃም.…አይደል ስምህ?” አለች ስህተቷ አልገባትም፡፡
"አዎ አንቺ ግን አርሃም ብለሽ ነው የፃፍሽው" ብ" ን ረስተሻታል፡፡"

ኮስተር ብላ አዲስ ካርድ አወጣችና እያቀበላችኝ፣ ስምህን ሞልተህ ትሰጠኝ አለችና፣ የቅሬታ
ፈገግታ እያሳየችኝ። የዚህችም ጥርስ በብረት ታስሯል፡፡ ደምዛቸውን ቻፕስቲክና የጥርስ ማሰሪያ ብረት የሚከፍሏቸው ነው የሚመስሉት፤ ወይስ "ሆዴን ከመቻል ተርፎ ጥርሴን የሚያሳሰር ባል ወላ ጓደኛ አለኝ" መልዕክት ነው ?! መቼስ የአዲስ አበባ ወንድ ብሩ ተረግሟል፡፡

ስሜን ሞልቼ ሳበቃ “እድሜዬንም ልሙላልሽ” አልኳት፤ ሆነ ብዬ ለማበሳጨት ነበር፡፡ የመንጠቅ
ያህል ካርዱን ከእጄ ላይ ወሰደችና የምትሞላውን ነገር ሞልታ፣ “ዶ/ር ሰናይት ጋር ነህ፡፡ ከፊትህ
አምስት ሰው ይቀድምሃል” አለችኝ፡፡ በጣም ተበሳጭታለች፡፡
“ይቅርታ ወንድ ዶክተር የላችሁም ?" አልኳት፡፡ በረዥሙ ተንፍሳ ካርዴን ተቀበለችኝና ዶከተር አምሃ” ብላ ፃፈችበት፡፡

“አመሰግናለሁ!" አልኳት በሚያበሳጭ ድምፅ፤ ከዛም ካርዱን አየሁትና ተመልሼ… “ይቅርታ የዶክተሩን ስም ማን ነበረ ያልሽኝ?” አልኳት።

በግርምት አየችኝና “ዶ/ር አምሃ 3 ቁጥር ላይ” አለች ቃሉን ረገጥ አድርጋ፡፡

“እማ' ነው የሚለው፤ ኤች· የለችም” አልኳት ካርዱን እያሳየኋት፡፡ (የእውነትም
የለችም ነበር)፡፡ ስልችት ብያት አንገሽግሻት በመጨረሻ ትዕግስቷ አስተካከለቻት፡፡

ወረፋ ስጠብቅ ከፊቴ የሚቀድሙኝ አራት የሚሆኑ ሴት ታካሚዎች እየገቡ በጣም ከቆዩ በኋላ በጣም እየሳቁ ይወጣሉ፡፡ አረማመዳቸው ራሱ ይቀየራል፡፡ እየተንኳተቱ ገብተው እንደ ሞዴል
እየተውረገረጉ ይወጣሉ፡፡ "ውስጥ የተቀመጠው ዶክተር ነው ወይስ ኮሜዲያን'?” እያልኩ ሳስብ
ተራዬ ደረሰና ለመሳቅ ተዘጋጅቼ ገባሁ፡፡ ወይ መሳቅ !

ጎልማሳ፣ መላጣ ዶከተር ኮስተር ብሎ በእስክርቢቶው ወንበር ጠቆመኝ፡፡ ስታይሉ ነው መጨረሻ
ላይ ያስቀኛል

እሺ አብርሃም እንዴት ነው የሚያደርግህ?” አለኝ ከበፊቱ በባሰ ኮስተር ብሎ፤ የመጨረሻዋን ሴት እኔ ያሳረርኳት ሳይመስሰው አይቀርም መላጣ ምናባቱ ያኮሳትረዋል?!

በሩ ተንኳኳ፡፡

“ይግቡ!” አለ፡፡ የመጨረሻዋ ታካሚ ነበረች ተመልሳ የገባችው:: ስልኳን ረስታ ልትወስድ ነበር፡
(በሽታዋ አልዛይመር ነበር እንዴ?)
ዶክተሩ ፈገግታው ፈነዳ፡፡ “ኦኬ !" ብሎ ተነስቶ በሁለት እጁ አቀበላት፡፡ ዳሌዋ ሰፋ ያለ መልከመልካም የሃብታም ሚስት ነገር ናት፡፡ ልክ ስልኳን ሲሰጣት
የሆነ አይነት ለየት ያለ መተያየት ያየሁባቸው መሰለኝ።

“ቴንኪው ዶክተርዬ !” ብላው በተረከዝ ረጅም ጫማዋ ወለሉን እየደቃችው እና እየተውረገረገች
ወጣች።የሽቶዋ ጠረን ግን ክፍሉን ሞላው። ዶክተሩ ከተዘጋው በር ላይ ዓይኑን መለሰ ፈገግታውን አከሰመው፡፡ ልክ እፍ እንዳሏት ሻማ ወደ እኔ ሲዞር ፈገግታው ድርግም ብላ ጠፋች።
👍241