[ዓድዋ]
ዋ! ..... ያቺ ዓድዋ
ዋ! ...
ዓድዋ ሩቋ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋቋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋቋ።
ዓድዋ.....
ባንቺ ብቻ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስቷ፣
የደም ትቢያ መቀነቷ።
በሞት ከባርነት ሥርየት፣
በደም በነፃነት ስለት፣
አበው የተሰውብሽ ለት።
ዓድዋ!
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ፣
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ።
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ፣
ታድማ በመዘንበልዋ።
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ፣
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ።
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ፣
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ፣
ብር ትር ሲል ጥሪዋ፣
ድው እልም ሲል ጋሻዋ፣
ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ።
ያባ መቻል ያባ ዳኘው፣
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣
ያባ በለው በለው ሲለው፣
በለው በለው በለው በለው።
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል፣
ማስቻል ያለው አባ መቻል።
በዳኘው ልብ በአባ መላው፣
በገበየሁ በአባ ጎራው፣
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው፣
በለው ብሎ በለው በለው።
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ዓድዋ የትናንትናዋ፣
ይኸው ባንቺ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና፣
በነፃነት ቅርስሽ ዜና፣
አበው ተነሱ እንደገና።
....... ዋ! ........ ያቺ ዓድዋ፣
ዓድዋ ሩቅዋ ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
ዓድዋ .......
🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን🔘
ዋ! ..... ያቺ ዓድዋ
ዋ! ...
ዓድዋ ሩቋ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋቋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋቋ።
ዓድዋ.....
ባንቺ ብቻ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስቷ፣
የደም ትቢያ መቀነቷ።
በሞት ከባርነት ሥርየት፣
በደም በነፃነት ስለት፣
አበው የተሰውብሽ ለት።
ዓድዋ!
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ፣
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ።
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ፣
ታድማ በመዘንበልዋ።
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ፣
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ።
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ፣
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ፣
ብር ትር ሲል ጥሪዋ፣
ድው እልም ሲል ጋሻዋ፣
ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ።
ያባ መቻል ያባ ዳኘው፣
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣
ያባ በለው በለው ሲለው፣
በለው በለው በለው በለው።
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል፣
ማስቻል ያለው አባ መቻል።
በዳኘው ልብ በአባ መላው፣
በገበየሁ በአባ ጎራው፣
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው፣
በለው ብሎ በለው በለው።
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ዓድዋ የትናንትናዋ፣
ይኸው ባንቺ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና፣
በነፃነት ቅርስሽ ዜና፣
አበው ተነሱ እንደገና።
....... ዋ! ........ ያቺ ዓድዋ፣
ዓድዋ ሩቅዋ ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
ዓድዋ .......
🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን🔘
#አታውቃት #እንደሆን
ሰው እንደ ሰው ቢቆም ፥ በእናት ሐገር ምድሩ
ያለዋጋ አይደለም ፥ ወዲህ ነው ምሥጢሩ
አያት ቅድመ አያቱ ፥ ጠላትን ሲመቱ
እንደዝናብ ሲወርድ ፥ የጥይት መዓቱ
ሲንጣጣ ሲያሽካካ ፥ ጦር አውርዱ ኹላ
ያፈገፈገ የለም ፥ ከቶም ወደ ኋላ።
ከኋላ ምሽት አለች ፥ ከአንድ ወንዝ የተቀዳች
ከቀሚሷም ወርዶ ፥ የሚድኹ ልጆች
የእርሻም መሬት አለ ፥ በላብ ወዝ የራሰ
የሽምብራ ጥርጥር ፥ በወግ ያደረሰ
የቤተስኪያን ደውሉ ፥ የመስኪድ አዛኑ
ኢምንት እምነቱ ናት ፥ የሰው ማዕዘኑ።
አይሸሽም አይፈራም ፥ ያቅራራል ቀረርቶ
ሽለላ ያሰማል ፥ ዘራፍ ደረት ነፍቶ
ግዳይ እንደ ጣለ ፥ በሞት ነው የሚፈካ
ከጠላ ጠላ ነው ፥ ከማረም አይነካ
ጀግና ዕድሜ እየተጫነው ፥ ምን በመልኩ ቢጃጅ
ፈርቶ ሞት አያውቅም ፥ ጦር ቀምሶ ነው 'ሚባጅ።
ቆመህ ስትራመድ ፥ ዛሬ በነጻነት
ደፍረህ ስትናገር ፥ ቀና ብለህ ካንገት
ትርጉሙ እንዲገባህ ፥ ውሉን እንዳትስተው
ኢትዮጵያዊነትህን ፥ ሀ ብለህ መርምረው።
የማንነት ካስማዋ ፥ የአንድነት ማማዋ
አታውቃት እንደሆን ፥ ይህቺው ናት ዓድዋ።
በ 🔘እሱባለው አበራ🔘
ሰው እንደ ሰው ቢቆም ፥ በእናት ሐገር ምድሩ
ያለዋጋ አይደለም ፥ ወዲህ ነው ምሥጢሩ
አያት ቅድመ አያቱ ፥ ጠላትን ሲመቱ
እንደዝናብ ሲወርድ ፥ የጥይት መዓቱ
ሲንጣጣ ሲያሽካካ ፥ ጦር አውርዱ ኹላ
ያፈገፈገ የለም ፥ ከቶም ወደ ኋላ።
ከኋላ ምሽት አለች ፥ ከአንድ ወንዝ የተቀዳች
ከቀሚሷም ወርዶ ፥ የሚድኹ ልጆች
የእርሻም መሬት አለ ፥ በላብ ወዝ የራሰ
የሽምብራ ጥርጥር ፥ በወግ ያደረሰ
የቤተስኪያን ደውሉ ፥ የመስኪድ አዛኑ
ኢምንት እምነቱ ናት ፥ የሰው ማዕዘኑ።
አይሸሽም አይፈራም ፥ ያቅራራል ቀረርቶ
ሽለላ ያሰማል ፥ ዘራፍ ደረት ነፍቶ
ግዳይ እንደ ጣለ ፥ በሞት ነው የሚፈካ
ከጠላ ጠላ ነው ፥ ከማረም አይነካ
ጀግና ዕድሜ እየተጫነው ፥ ምን በመልኩ ቢጃጅ
ፈርቶ ሞት አያውቅም ፥ ጦር ቀምሶ ነው 'ሚባጅ።
ቆመህ ስትራመድ ፥ ዛሬ በነጻነት
ደፍረህ ስትናገር ፥ ቀና ብለህ ካንገት
ትርጉሙ እንዲገባህ ፥ ውሉን እንዳትስተው
ኢትዮጵያዊነትህን ፥ ሀ ብለህ መርምረው።
የማንነት ካስማዋ ፥ የአንድነት ማማዋ
አታውቃት እንደሆን ፥ ይህቺው ናት ዓድዋ።
በ 🔘እሱባለው አበራ🔘
አድዋ-በአፍ አይገባም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።፡።፡፡፡።።፡
አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል
አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል
ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል
ለዛሬም ታሪክ አባት ነው፤ “ነገም ሌላ ቀን ነው” ለሚል
አድዋ ሰው-ዛብ፣ የደም-ድልድይ
አንድም ፍልሚያ፣ አንድም ራእይ
ልብ ላለው ልብ ያነዳል
ለምር ቀን ስንቅ ይሆናል!!
ነጻነት አይለመንም
ያው ጥንትም ተጽፏል በደም
አገር ድንበሯ ሲነደል፣
ያው ዛሬም ተማግሯል በፍም
የአጋም-አጥር ተደግፎ
ጎረምሳ ኮረዳም ቢስም
በወርቅ-አልጋ በእርግብ-ላባ
ተኝቶ ማደር ቢቻልም
አገር ከፍቷት ሰላም የለም
አድዋ ሞተው ሲኖሩ እንጂ ተተርኮ በአፍ አይገባም!
ዱሮም ዛሬም በአፍ አይገባም!
****
🔘በነቢይ መኮንን🔘
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።፡።፡፡፡።።፡
አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል
አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል
ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል
ለዛሬም ታሪክ አባት ነው፤ “ነገም ሌላ ቀን ነው” ለሚል
አድዋ ሰው-ዛብ፣ የደም-ድልድይ
አንድም ፍልሚያ፣ አንድም ራእይ
ልብ ላለው ልብ ያነዳል
ለምር ቀን ስንቅ ይሆናል!!
ነጻነት አይለመንም
ያው ጥንትም ተጽፏል በደም
አገር ድንበሯ ሲነደል፣
ያው ዛሬም ተማግሯል በፍም
የአጋም-አጥር ተደግፎ
ጎረምሳ ኮረዳም ቢስም
በወርቅ-አልጋ በእርግብ-ላባ
ተኝቶ ማደር ቢቻልም
አገር ከፍቷት ሰላም የለም
አድዋ ሞተው ሲኖሩ እንጂ ተተርኮ በአፍ አይገባም!
ዱሮም ዛሬም በአፍ አይገባም!
****
🔘በነቢይ መኮንን🔘
“የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ”
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡
እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት
እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት
ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት እርስት ሆነው ተቀበረበት፡፡
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ስፍር ትከዳለች እንጂ
አትረጋምና ያለተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አንድነት ያውቃሉ
#ዓድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቼ ተወለደ
የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ፡፡
ደንገላሳ ሲዘል እየተንጓደደ
የሮማውን ኩራት በእግታ አሰገደ፡፡
አገርህን ምኒልክ እንዳሁን ፈትሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅም እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡
አባተ በመድፋ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጐጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን
ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላዔ ሰብአ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን፡፡
(ተክለ ጻድቅ መኩሪያ)
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡
እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት
እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት
ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት እርስት ሆነው ተቀበረበት፡፡
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ስፍር ትከዳለች እንጂ
አትረጋምና ያለተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አንድነት ያውቃሉ
#ዓድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቼ ተወለደ
የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ፡፡
ደንገላሳ ሲዘል እየተንጓደደ
የሮማውን ኩራት በእግታ አሰገደ፡፡
አገርህን ምኒልክ እንዳሁን ፈትሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅም እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡
አባተ በመድፋ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጐጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን
ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላዔ ሰብአ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን፡፡
(ተክለ ጻድቅ መኩሪያ)
👍2
#ዴዝዴሞና
ከረፋፈደ በኋላ ነበር የትያትር ቤቱ የኋላ ረድፍ ላይ ቦታ ይዞ የተቀመጠው፡፡ የያዘው ክፉ የፍቅር ልክፍት ነው በዚህ ቲያትር ቤት ውስጥ እንዲገኝ ያደረገው፡፡ ለሼክስፒር የተውኔት ድርሰቶች ፍቅርና ስሜት ኖሮት አያውቅም፡፡ እሱ ፍቅር የያዘው ከገፀባህሪዋ ስም ጋር ሞክሼ ስም ካላት የራሱ ዴዝዴሞና ጋር ነው፡፡ ክፉ የቅናት ዛር መንፈሱን ከተቆጣጠረው ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፡፡ እርዳታ ፍለጋ ሃኪም ጋር ሄዶ “ፓራኖያ አለብህ” ተብሏል፡፡ ከወንድ ጋር ያያት ሴት ሁሉ እስዋ ትመስለዋለች፡፡ ከንግግርዋ፣ ከአዋዋልዋ፣ ከአመሻሽዋ፣ ከአለባበስዋ፣ ከጓደኞችዋ፣ ከቤተሰቦችዋ፣ከትናንት ታሪክዋ ጋር የተገናኘ የቅናት መንፈስ ተጠናውቶታል። ስልክ ስታወራ በቅናት ልቡ ይመታል፡፡ ትንሽ ካመሸች ጓደኞቿ ጋር ሁሉ እየደወለ ወይም እየሄደ ሊሰልላት ይሞክራል፡፡ ባልና ሚስት ሳይሆኑ ሌባና ፖሊስ ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ በእንቅልፍ ልብዋ የሆነ ነገር ብታልጎመጉም፣ በሱ ነገር እየተጨነቀ፣ ፍችውን ለማወቅ ሲባዝን ያድራል፡፡
ለእሷ ካለው እውር ጭፍን ፍቅር የተነሳ “ኦቴሎ”ን ሊያይ ቲያትር ቤቱ የመጨረሻ ወንበር ላይ ቢሰየምም፣ መጋረጃው ተገልጦ ቲያትሩ የጀመረው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነበር፡፡
ቃሲዮን ሲያይ፣ እጁን ቡጢ ጨበጠ፡፡ ይሄ ነው ሚስቴን ሲዳራ የሚያድረው እያለ ጥርሱን በቁጣ ያፋጫል፡፡ ኢያጎ ለኦቴሎ በመሰሪ ቋንቋው የዴዝዴሞናን አለመታመን በጆሮው ሲያንሾካሹክ፣ እሱም ከኦቴሎ ከራሱ በላይ ቁጣው ገነፈለ፡፡
ወደዚህ ቲያትር ቤት ለመግባት ዋና ምክንያቱ፣ ፍቅረኛው ትላንት በስልክ ከወንድ ጋር ስትቀጣጠር በመስማቱ ነው፡፡ ሁሉንም ንግግር በትክክል ባይሰማም “ማዘጋጃ” እና “አስር ሰዓት” የሚሉት ቃላት ግን አላመለጡትም፡፡
ኦቴሎ በኢያጎ ስብከት በቁጣ ሲንጎራደድ፣ ድንገት አይኑ ውስጥ ገባች፡፡ ፊት ካለው ረድፍ ወንበር ላይ አንድ ጎረምሳ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ተቀምጧል፡፡
እሷ ለመሆንዋ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ከአመት በፊት የገዘላትን ሻሽ አንገትዋ ላይ ጣል አድርጋዋለች፡፡ ረጅም ፀጉርዋንም ቢሆን አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ እንዴት የሚስቱ ፀጉር ይጠፋዋል፡፡ ቢሆንም የማይቀና ጥሩ ባል ለመሆን በመሞከር፣ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ቁጥርዋን መታ፡፡ ይጠራል፡፡ ግን አይነሳም፡፡ ሻሹን በደንብ አስተዋለ፡፡ ራሱ ነው፡፡ የሚያያት ከጀርባዋ ቢሆንም፣ ከት ብላ ስትስቅ፣ ሰውየውም አብሯት ሲስቅ ተመለከተ። አሁንም ደግሞ ደወለ፡፡ ሶስቴ ከጠራ በኋላ “የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ ጥሪ እያስተላለፈ ነው” አለች፤ ኦፕሬተርዋ፡፡
እሱ ላይ ስልክ እየዘጋች ከማንም ውርጋጥ ጎረምሳ ጋር ስታስካካ ሊታገስ አልቻለም፡፡ ሜሴጁን ማዥጎድጎድ ጀመረ፡፡
“አንቺ ውሻ፣ ሸርሙጣ፣ ድሮስ ማን ይፈልግሻል!” አንዱ ነው፡፡
ቲያትሩ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡ ኦቴሎም የዴዝዴሞና አልፍኝ ለመግባት እርምጃውን ጀምሯል፡፡
ሁለተኛውን ሜሴጅ ጻፈ፡፡
“በረጅም እንጨት አልነካሽም፡፡ ድሮስ እኔ አላቅሽም ወዘተረፈ …”
ለሃያ ደቂቃ ያህል ስምንት ሜሴጆችን አከታትሎ ቢጽፍም፣ የፍቅረኛው ሜሴጅ የመጣው ግን ዘጠነኛውን ሊጽፍ ሲያስብ ነበር፡፡
እንዲህ ይላል፡-
“ረስተኸው ይሆናል፡፡ እኔ ግን አልረሳውም። ዛሬ የተገናኘንበት ቀን ነበር፡፡ ልክ በዛሬው ዕለት፣ ከአራት አመታት በፊት፣ ምሽቱን ወጣ ብለን እንድናሳልፍ አስቤ ነበር፡፡ ስጦታም አዘጋጅቼልሃለሁ፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ለገዛህልኝ ሻሽ እሺ ያልኩህ ጊዜ ትዝ ይልሃል፡፡ የኔ ፍቅር፤ የገዛሁልህን ሮሌከስ ሰዓት፣ ማዘጋጃ ቤት አጠገብ ካለው ስዊዝ ሰዓት ቤት ውሰድ፡፡ የኔ ፍቅር ደህና ሁን፡፡
በፍጥነት ተነስቶ እየተንደረደረ፣ ወደ ፊት ወንበሮች አመራ፡፡ ሻሹን እያየ ወደሷ ቀረበ፤ አጠገብዋ ሲደርስ ፊትዋን በእጁ አዞረው። ዴዝዴሞና አልነበረችም፡፡ ሁለቱ ፍቅረኞች በድንጋጤ ፈጠው እያዩት ነበር፡፡
ኦቴሎ ዴዝዴሞናን ያነቀው በዚያ ቅፅበት ነበር፡፡
🔘ከመሐመድ ኢድሪስ🔘

👍4
#የሴት_ክብር_በአፍሪካ
፧
ሴት ስትንኳሰስ
ሴት ስትዋረድ ~ ሴት ስትደፈር፣
በምትኖርባት
አፍሪካ በሚሏት ~ አህጉር፣
የሴቶችን ክብር
በፍትህ ዓይን ~ መዝና ስትሰፍር፣
አመት ሴትን ረስታ
አንዱን ቀን መርጣ ትኖራለች ማርች8ን ስታከብር።
፡
አይ አፍሪቃ!!!!
፧
፧
ሴት ስትንኳሰስ
ሴት ስትዋረድ ~ ሴት ስትደፈር፣
በምትኖርባት
አፍሪካ በሚሏት ~ አህጉር፣
የሴቶችን ክብር
በፍትህ ዓይን ~ መዝና ስትሰፍር፣
አመት ሴትን ረስታ
አንዱን ቀን መርጣ ትኖራለች ማርች8ን ስታከብር።
፡
አይ አፍሪቃ!!!!
፧
#እኛው #ነን...
እኛው ነን የገፋን እኛው ነን የከፋን
እኛው ነን ያጠፋን እኛው ነን የጠፋን
ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን ተስኖን
ሰፊ ሀገር ይዘን በሀሳብ አየጠበብን
በፍቅር ተሳስቦ አብሮ መራመድ አቀበት የሆነብን
ቂም እየቆጠርን ቂም እየመነዘርን
በዛሬ መንጋጋ የትላንት ድርቆሽ የምናመነዥክ
በዛሬ ምድጃ የትላንቱን አመድ ታቅፈን የምንሞቅ
በአንድ ላይ ከመጓዝ በየፊና ሩጫ አረፋ የምንደፍቅ።
እኛው ነን እኛው ነን
ከእምነት የተፋታን ከፈጣሪ የራቅን።
እኛው ተጋፊዎች እኛው ተገፊዎች
እኛው አሳዳጆች እኛው ተሳዳጆች
ካሳለፍነው ህይወት ካሳለፍነው መከራ መማር የተሳነን
ደመና ወራሾች።
በማስመሰል ጥበብ በአድርባይ አንደበት በሸፍጥ
የሰለጠንን
ከብዞዎች ድርሻ ተሻምተን ተናጥቀን
ለአንድ ለእራሳችን በወርቅ ላይ አልማዝ በህንፃ ላይ ህንፃ ስንቆልል ስንከምር የማይሰቀጥጠን
የመንፈስ ድዊዎች የንዋይ ምርኮኞች
የወንበር ሱሰኞች የሆድ አምላኪዎች
ከሰውነት ወርደን በነፍስ የኮሰመንን የስጋ ቡኩኖች
የራሳችን ሀጢያት የራሳችንን ሲኦል እኛው ነን መርገምቶች
እኛው ነን።
🔘በጌትነት እንየው🔘

****ፍፃሜዉ****
የሚሽከረከሩ አለምን በገንዘብ
አድምቀው ያበዙ ተፈጥሮን በጥበብ ፣
-
ያገር ተወካዮች የአለማት መሪ ፣
ጎዳና የሚኖር በልቶ ፍርፋሪ ፣
-
ኑሮ ያቆሰለው ያገር ወንደላጤ፣
የተጎሳቆለ ምስኪን የኔ ቢጤ ፣
-
ጠቢብ ስአሊያን ድንቅ ሙዚቀኛ ፣
ሽጋ መልከ መልካም ታዋቂ ዝነኛ ፣
-
የኔ አይነት አመዳም ባሪያ መልከ ጥፉ ፣
እውቅ ባለሀብቶች
ሚሊዮን ተርቦ ቢሊዮን ያቀፉ ፣
አንቱ የተባሉ በስም የገዘፉ ፣
ይኖራሉ በአለም እንዲህ ተለያይተው ፣
ምድርና ሰማይ ቤታቸውን ሰርተው ።
-
ይሄ ሁሉ አዳም አንድ ሆኖ ደሙ ፣
ስጋው አፈር ሲለብስ
ሲለይ ከአለሙ ፣
መአረጉ ቀርቶ
ሁሉም በአንድ ላይ ሬሳ ነው ስሙ ።
ከቻናሉ ተከታታይ የተላከ አስተያየታችሁን አድርሱት 👉 @Sam2127
ከ🔘ሳሙኤል አዳነ🔘
11/10/08
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

#የአራዳ_ልጅ_ሽለላ
ጎራው...ና...ጎራው...ና...ጎራው...ና
ጎራው...ና...ጎራው...ና....ጎራው...ና
ጎራው...ና እያለ ማነዉ የሚጣራ
ጎራው...ና እያለ ማነዉ የሚጣራ በሉ እናተ ሂዱ
እኔስ ፀብን ፈራሁ ተዉኝ
ጎራው.. ተወኝ ጎራው
ዘራፍ !! አካኪ ዘራፍ ! ዘራፍ !! አካኪ ዘራፍ !
ቢገርፈኝ እንኳን ሱስ እንዳለጋ ኑሮ እንደ ጅራፍ ማልደራደር ባንዲት አገሬ
እንደ ፕሪም ዛፍ እንደ ፖም ፍሬ
መንግስትን ላወርድ ድንጋይ ወርዉሬ
አልሳካ ሲል ከሀዘኔ ላይ ሳቅ የምቀጥል
የመንግስትን ስም ባሽሙር በነገር የማብጠለጥል
ዘራፍ !! አካኪ ዘራፍ ! ዘራፍ !! አካኪ ዘራፍ !
አልሞ ተኳሽ አነጣጣሪ
የሚጨማደድ ሸሚዝ ወይ ሱሪ
በወፍ ወስፈንጥር ሰዉ አባራሪ
#ዘራፍ
በሰዉ ካዉያ በሰዉ እሳት
እንዴት መተኮስ አወቀበት
ብለዉ ለሚሉ አራዳ መልሱ
ሲለብስ ይታያል አተኳኮሱ
#ዘራፍ
በል በለዉና ይምጣ የመጣዉ
ከሀገር ቀድሞ ትግል የወጣዉ
በባዶ እጁ ታንክ የማረከ
ወያኔ ሌባ የሚለውን ስድብ የፈበረከ
ፀረ ዘረኛ ስመ ቅምጥል
በኮብል ስቶን ጠመንጃ የሚያስጥል
የቀበሌ አጥር የሚገነጥል
ከቻይና ጫማ ፍቅሩ የሚያቃጥል
#ዘራፍ
ቄሮና ፋኖ ዘርማ ሳይኖሩ
ተነስ እያለ ላንዲት አገሩ
ላንዲት ባንዲራ ሁሉ አንዲታገል
የቀሰቀሰክ ሳትመነገል
መሪ ኮከብክ ለሰባ ሰገል
ያዲሳባ ልጅ ስሙ ያራዳ
ቀለም ያልቀባ በመኪና አሰፋልት በሰዉ ግድግዳ
በመንጋ ስሜት የማይነዳ
ሰዉ ሀገር ነዉ ባይ ሰዉ የማይጎዳ
#ዘራፍ
ያዲሳባ ልጅ ያራዳ ልቡ ሰውን ከፍ አድርጎ ልክ አንደ ሰንደቅ የሚያዉለበልብ ቢያገኝ አካፋይ ቢያጣ የሚያዝን
ከሚዛን በላይ የሚያመዛዝን
ራሱን የማያኖር ሰዎችን ቀብሮ
ብይ የሚጫወት ጉድጓድ ቆፍሮ
ቀስት ባይኖረዉ ቀልዱን ወርዉሮ
ሺህ መሳይ ገዳይ በሙቀት ጥላ በብርድ ፀሀይ
መሆን የሚቻለዉ እንደ ሁኔታዉ
በሰዎች ቋንቋ አፉን የፈታዉ
ቃል የማይወጣዉ አፍ ለሚከፍቱ
አፍ የሚያዘጋ በመሀል ጣቱ
ቢያፈገፍግም ፈርቶ የማይሮጠዉ
ሲጨፍር ብቻ የሚንቀጠቀጠዉ
#ዘራፍ
🔘ከ በላይ 🔘

❤1
#እኔ_ደግሞ …."
ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……
፡
#እኔ_ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።
፡
ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ
፡
#እኔ_ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።
፡
ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።
፡
ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።
፡
ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ
፡
#እኔ_ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።
፡
ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።
፡
በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….
፡
#እኔ_ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።
፡
የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።
፡
እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!
🔘አሌክስ አብርሃም 🔘
ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……
፡
#እኔ_ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።
፡
ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ
፡
#እኔ_ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።
፡
ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።
፡
ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።
፡
ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ
፡
#እኔ_ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።
፡
ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።
፡
በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….
፡
#እኔ_ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።
፡
የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።
፡
እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!
🔘አሌክስ አብርሃም 🔘
#ውርሰ_ውበት
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን..
በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው
ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ
ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ
ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት
ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ
ፀባይሽ ግን ውዴ...
እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...
ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ
እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸዉ
🔘ልዑል ሀይሌ🔘
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን..
በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው
ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ
ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ
ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት
ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ
ፀባይሽ ግን ውዴ...
እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...
ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ
እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸዉ
🔘ልዑል ሀይሌ🔘
#ያሳፈርኩህ_እንዳታፍር_በመፈለጌ_ነው
‹‹ እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ያምሻል?›› ስል እናቴ ላይ በብስጭት ጮህኩባት ... አንድ ጥግ ላይ ኩርምት ብላ እና አንገቷን ደፍታ በቁጣ የምደነፋባትን ንግግር ሁሉ ስታዳምጠኝ ትልቅ ወንጀል ሰርቶ ዳኛ ፊት የቀረበ ወንጀለኛ እንጅ የሰባት አመት ልጇ የሚጮህባት እናት አትመስልም ነበር !
ብስጭቴ ልክ አልነበረውም እንዲያውም ከንዴቴና ከቁጣየ የተነሳ እናቴ አስጠላችኝ ‹‹አሁኑ ብትሞች ግልግል ነበር›› ስል ጮህኩባት እውነቴን ነበር እንዲህ ከምታሳፍረኝ ብትሞት እና ብገላገል በሰላም እኖር ነበር ! እንዴት እንዳስጠላችኝ እንደቀፈፈችኝ ! ደምስሬ ተገታትሯል እንባየ በአይኖቸ ሞልቶ በእልህና በጥላቻ አስቀያሚዋ እናቴ ፊት እየተንቀጠቀጥኩ ነበር ! አርሷ ግን አንገቷን ደፍታ አሮጌ ጫማወቿን አቀርቅራ እየተመለከተች በዝምታ የምላትን ሁሉ ታደምጥ ነበር !
እናቴ ካለአባት ብቻዋን ነበረ ያሳደገችኝ ….እኔን ለማሳደግ ብቸኛ የገቢ ምንጯ የነበረው በምማርበት ት/ቤት ውስጥ ለመምህራንና ተማሪወች ምግብ በማዘጋጀት የሚከፈላት አነስተኛ ክፍያ ነበር ! እንዲህም ሁኖ የምማርበት ትምህርት ቤት የሃብታም ልጆች መማሪያ ስለነበርና እኔም በልብስም ሆነ በመማሪያ ቁሳቁሶቸ ከማንም ስለማላንስ ስለእናቴ ማንነት ማንም አያዉቅም ነበር እኔም ስለእናቴ ተናግሬ አላውቅም !
በእናቴ የማፍረው ደሃ ስለሆነች ብቻ አልነበረም አንድ አይን ብቻ የነበራት ሴት ስለነበረች እንጅ ! በእውነትም እናቴ አስቀያሚ መልክ ነበራት ! የግራ አይኗ የነበረበት ቦታ ባዶ ጉድጓዱ ብቻ ቀርቶ አንዲት ትንሽ አይኗ ብቻ እየተቁለጨች ድንገት ለተመለከታት ከማስቀየም አልፎ ትቀፍ ነበር ! የብዙ ጓደኞቸ እናቶች አይኖቻቸው በኩል ተከበውና አምረው ስመለከት የእናቴ አንድ አይን ያሳፍረኛል ! ምንም ማድረግ አልችልም ‹‹ምንም ቢሆን እናቴ ናት ›› እያልኩ ነገሩን ለመቀበል ብሞክርም አልቻልኩም ! በእናቴ መልክ በጣም እሳቀቅና አፍር ነበር! በእርግጥም የእናቴ አንድ አይናነት ለእኔ የማልቋቋመው የሃፍረት ምንጭ ነበር !
ቢሆንም እናቴን ማንም ስለማያውቃትና ስለዚህም ጉዳይ ተናግሮኝ የሚያውቅ ተማሪ ስላልነበር እናቴን ሳያት ካልሆነ በስተቀር ትዝ አትለኝም ነበር ! በአንድ የተረገመ ቀን ታዲያ እማርበት ወደነበረው የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪወች ብቻ ወደሚገኙበት አጥር ውስጥ እናቴ ስትመጣ አየኋት ! ራሴን ልስት ምንም አልቀረኝም ... ተማሪወቹ የእናቴን አይን ሲመለከቱ በሳቅ አውካኩ አሾፉባት የእማማ ፊት ላይ ግን ምንም መከፋት ሳይታይ ወደእኔ ትራመድ ነበር …..ድንገት ወደኋላየ ሮጥኩ ‹አላውቃትም እችን ሴት ወዲያ በሉልኝ ›› እያልኩ ሮጥኩ ! ይሁንና ተማሪ ጓደኞቸ መዘባበቻ አደረጉኝ
‹‹አንተ እናትህ አይኗ የት ሂዶ ነው? ››
‹‹እናትህ 'ሆረር' ፊልም የምትሰራ ነው የምትመስለው ››
‹‹እናትህ በአንድ አይኗ ሽንኩርት ስትከትፍ እጇን አብራ አትከትፍም ?ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ›› ተማሪው አሽካካ ተውካካ ለዘላለሙ ልቤን የሚሰብር የእናቴ ድርጊት ሁኖ ተሰማኝ ! ከዛን ቀን በኋላ የትምህርት ቤት ጓደኞቸ የነበሩ ህፃናት የሚስቁት የማሾፍ ሳቅና የሚወረውሩብኝ ቃል የሚያሳፍርና አንገት የሚያስደፋ ነበር ! እድሜ ላሳፈረችኝ እናቴ ! እጠላታለሁ ! እቤቴ ማታ ስመለከታት እንኳ የጓደኞቸ ሳቅ ነው የሚታወሰኝ !
በዚህ ሁኔታ አብሪያት ልኖር ስላልቻልኩ ትንሽ ከፍ ስልና ነብስ ሳውቅ እናቴን ትቻት ወደሌላ ሩቅ አገር ትምህርት ቤቱ ባመቻቸው እድል ተጠቅሜ ተሰደድኩ ! እዛም ማንነቴን በማያውቁ ሰወች መሃል በደስታና በኩራት እኖር ጀመረ ! አድጌ ዩኒቨርስቲ ስገባ ስራ ስይዝ እና ሚስት አግብቸ ልጆች ስወልድ ሁሉ እናቴን አይቻትም ስለእርሷም ወሬ ሰምቸ አላውቅም ነበር ! ትልቅና የሚያምር የግሌ መኖሪያ ቤት ቆንጆ ሚስትና የሚያማምሩና ጎበዝ ልጆች አሉኝ !
ሚስቴም ሆነች ልጆቸ ትክክለኛውን ነገር አያውቁም ነበር ! ስለእናቴ ሲጠይቁኝ እንዲህ እላቸው ነበር ‹‹ እናቴ ውብ ነበረች... በተለይ አይኖቿ ጨረቃን የሚያስንቁ ከውስጣቸው ብርሃን የሚረጩ ውቦች ነበሩ የእናቴን አይን ተመልክቶ በፍቅሯ የማይማረክ የለም ግን ከብዙ አመታት በፊት ሙታለች ›› በቃ!! በዚህም የውሸት ታሪክ ታላቅ ኩራት ሰማኛል !
አንድ ቀን ግን ይህ ውብ ኑሮየን የሚያደፈረስ አሰቃቂ ነገር ተፈጠረ ! የቤቴ በር ተንኳኳ ….ትልቁ ልጀ በጉጉት በሩን ከከፈተው በኋላ በድንጋጤ እየጮኸ ወደቤት ተመለሰ ….ሁላችንም ያስደነገጠውን ነገር ለመመልከት በእኔ መሪነት ክፍቱን ወደተተወው በር ተንጋጋን ይህች አሰቃቂ እናቴ በር ላይ ቁማ ነበር ! ከበፊቱ የበለጠ ተጎሳቁላና የፊቷ አጥንት ቀርቶ የአይኗ ጉድጓድ የባሰ ሰፍቶ ይታያል አንድ አይኗ ሲቁለጨለጭ አንዳች አስፈሪ አውሬ ትመስል ነበር !
ድንጋጠየን ተቋቁሜ ‹‹ምን ልርዳሽ ሴትዮ›› አልኳት አጠያየቄ ግልምጫ የታከለበትና ፍፁም የማላውቃት ሴት መሆኗን የሚያሳይ ነበር
‹‹ የኔ ልጅ ላይህ ጓጉቸ ነበር ….›› ብላ መናገር ከጀመረች በኋላ ወደሚስቴና በድንጋጤ የእናታቸውን ቀሚስ ጨምድደው ወደቆሙት ልጆቸ በዛቹ አንድ አይኗ ተመልክታ እንዲህ አለች ‹‹ ይቅርታ አድራሻ ተሳስቶብኝ ነው ›› ከዛም ተመልሳ መንገድ ጀመረች ጀርባዋ ጎበጥ ብሏል ፀጉሯም ግማሽ በግማሽ ነጭ ሁኗል ! እውነቱን ለመናገር ምንም አላዘንኩም እንደውም በየሄድኩበት እየተከተለች ኑሮየን መበጥበጧ አበሳጨችኝ !!
ከአንድ አመት በኋላ ድሮ እማርበት የነበረው ትምህርት ቤት ያስተማራቸውን ተማሪወች ጠርቶ የምስረታ በአሉን ሲያከብር የክብር እንግዳ አድርጎ ስለጠራኝ ወደጥንት መንደሬ በአሉ ላይ ለመገኘት ሄድኩ ! እናቴ የነበረችበት የጥንት መንደር ምንም ሳይሻሻል ከነ ደሳሳ ቤቶቹ እዛው ነበር !
በአሉን ተሳትፌ ልመለስ ስዘጋጅ አንድ እንደእናቴ የተጎሳቆለ ሰው ወደእኔ እየተጣደፈ መጣና እንዲህ አለኝ
‹‹ እናትህ ሙታለች … !! ›› እውነት እላችኋለሁ ትልቅ እረፍት ተሰማኝ ካሁን በኋላ መሳቀቄ ሃፍረቴ ሁሉ አብሮ ሞተ ! የማፍርበት የኋላ ታሪኬ መቃብር ወረደ ! እፎይይይይይይይይይ! ይሄ መርዶ ሳይሆን ‹‹የምስራች›› ነበር!!
ይሁንና ‹የምስራቹን › ያበሰረኝ ሰው አንድ አሮጌ ፖስታ ከአሮጌ ኮቱ ኪስ አውጥቶ ሰጠኝና ‹‹እናትህ አደራ ስጥልኝ ብላኝ ነው ›› ብሎ ፖስታው ጋር ትቶኝ እየተጣደፈ ሄደ !ፊቱን ሲያዞርና ከእኔ ለመራቅ ሲጣደፍ አንዳች ቆሻሻ ነገር የሚሸሽ ነበር የሚመስለው ! ፖስታውን ከፍቸ ድሮ የማስታውሰው የእናቴ የእጅ ፅሁፍ ጋር ተፋጠጥኩ አጭር እና ግልፅ መልእክት ነበር !
‹‹ የምወድህ ልጀ እድሜ ልክህን ሳሳፍርህ እና ሳሳቅቅህ በመኖሬ ይቅር በለኝ …. ለትልቅ ደረጃ መድረስህን እቤትህ ድረስ መጥቸ በአንድ አይኔ በማየቴ ደስ ብሎኝ ቀሪ እድሜየን ኑሪያለሁ ! ውድ ልጀ ያሳፈርኩህ እንዳታፍር በመፈለጌ ነው ….በልጅነትህ አደጋ ደርሶብህ አንድ አይንህ ጠፍቶ ነበር እድሜ ልክህን በአንድ አይን እንድትኖር የእናት አንጀቴ ስላልቻለ የራሴን አንድ አይን ልለግስህና በቀሪው አንድ አይኔ ደስታህን ልመለከት ስለፈለኩ ይሄንኑ አድርጊያለሁ !! በዚህም እኮራለሁ ልጄ ! ………እናትህ ››
ከውስጥ የማይወጣ ፀፀት ተሰማኝ ያን ፊት እንደገና ማየት ተመኘሁ ግን😢😢

👍6
#ለግዜር_የተፃፈ_ደብዳቤ
,,,,,,,,,,
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሁሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሾመው ሁሉ "ፀሃይ ነኝ " እያለ
የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል "ዝናብ" ሁኖ እንደመፈጠር ........
ኧረ እግዜር በናትህ ...
በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርበዋ
ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን
ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና.......!

#በፍቅር_እንኑር
መነሻ ከሌለው ዝንተ ዓለም ወደ ማይደረስበት ዘላለም ተጓዥ ነን፡፡በሁለቱ መካከል ትንፋሽ መውሰጃ ጊዜ የለም፡፡ምን አልባትም ማይክሮሰከንድ አይኖርም ይሆናል፡፡ነገር ግን ሽርፍራፊዋም ብትሆን ያው የኛ ዕድሜ ነች፡፡በዚህ ዓለም አረፍ የምንልባት(የምንኖርባት እንዳልል ከመጣንበት ዝንት ዓለም እና ከምንሄድበት ዘላለም አንፃር የዕድሜያችን ርዝማኔ መለኪያው ስለማይነፃፀር እና ከዓይን ጥቅሻ ያነሰ በመሆኑ ነው)አንዳአንዴ ያንኑው የጥቅሻ ዕድሜ ያሰለቸናል፡፡ያነጫንጨናል፡፡ምክንያቱም እንደማረፊያ ሳይሆን እንደ ቋሚ መኖሪያ እናስባታለን፡፡እናም ቋም ነገሮችን ለመገንባት እንጣጣራለን...ወደ ውስጥ የሳብነውን አየር መልሰን ወደ ውጭ ሳንበትን የረፍት ጊዜያችን ይገባደድ እና እረጂም..በጣም እረጂም የፀጥታ እና የማይታወቅ ጉዦችንን እንጀምራለን፡፡
እና የዘላለም ተገጓዦች ነን፡፡በምድር ምንገነባው ህንፃ ማረፊያ ድንኳን እንጂ ቋሚ ሀውልት አይደለም፡፡ዘና ብሎ መሳቅ ...በፈገግታ መደሰት እንጂ ፊታችንን አጨማደን… ልባችንን አኮማትረን ..ስለ ኒዩኪሌር ቦንብ መጠበብ በህይወት ስለት ትርጉመ ቢስ ነው
ህይወት እኮ ምትሰለቸን እረፍታችን ምቸት ስለሌለው ነው...ለዚህ ነው የሚቀነቅነን፡፡የአብዛኞቻችን ኑሮ በችግር የታጠረበት ዋናው ምክንያት የጥቂተች ስግብግብነት ነው፡፡መቶ ሺ ዓመት በዚህች ምድር እንደሚኖር ..አንድ ሺ ሰዎች እድሜ ልክ ማኖር የሚችን ንብረት ብቻውን ታቅፎ እና ቀብሮ...እሱ በምቾት እና በስግብግብነት ቅዠት ውስጥ እየኖረ ..ሌሎች ሺ ዋችን በችግር እና በሰቀቀን ቅዠት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ትርፉ ምንድነው፡፡
እና እስቲ እንተሳሰብ፡፡ በፍቅር እንኑር፡፡ ጠብታ ጊዜያችንን በክፋት አናጨማልቃት፡፡በፈገግታ ጀምረን...በሳቅ አዋዝተን....በዜማ አጅበን...በደስታ ዘለን...በፍቅር ሰክረን..በእርካታ እንሰናበታት፡፤መጨረሻችን መድረሻ የሌለው ዘላለም አይደል፡፡
ስለዚህ መልካም አልመን ...መልካም ተግብረን...በመልካም ሁኔታ ኖረን..ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ፀፀት አልባ ሆነን እንድንገጓዝ ከፀለምተኛ አስተሳሰባችን...ከስግብግብ ባህሪያችን...ከመጠላለፍ ምግባራችን እንላቀቅ፡፡ትናንትን አክባሪ...ዛሬን አፍቃሪ...ነገን ናፋቂ እንደሆን ህይወትን ሳንሰለች ሩጫችንን በጥሩ አነሳስ ጀጀምረን በድንቅ አጨራረስ ማጠናቀቅ ይገባናል
#መልካም_ቀን
🔘ከዘሪሁን🔘

👍3
#ከኢንጅነር_ናዝራዊት_የተላከ
😥😥እናንተዉ ውለዱኝ😢
"በቅን አስተሳሰብ በገራገር ልቤ
የታሸገ ሻንጣ በስሜ አስመዝግቤ
እኔም እንደባሕራን የሞቴን ደብዳቤ
መልክቴን ለማድረስ ሳላየው አንብቤ
ተሰናበትኩና የሀገሬን ጓዳ
በእምነት ገሰገስኩ ወጣሁ በማለዳ
ከኢትዮጵያ አየር ከአፈሯ ስርቅ
ባየር ተሳፍሬ ስሔድ እሩቅ ምስራቅ
ምኞቴ ሊሳካ በደስታ ስቦርቅ
አውሮፕላን ወርዶ ከሀገረ ቻይና
በፍቅር ደርሼ በሰላም በጤና
ሀገሩን አፈሩን ባይኔ ሳላይ ገና
በኋላ በፊቴ ከበቡኝ መጡና
እጀግ ደነገጥኩኝ ሆዴም ተሸበረ
ከቶ ምን ወረደ ምንስ ተፈጠረ
በሴትነት መንፈስ በሰፍሳፋ አንጄቴ
ጨለማ ሲውጠኝ ጠፋኝ እኔነቴ
እራሴን ስፈልግ ራሴ ጠርጥሬ
ራሴን ስጠይቅ ራሴን መርምሬ
ናዝራዊት አይደለሁ ሌላ ሴት ነኝ እኔ
አደንዛዥ ዕፅ ሰቶ የላከኝ ወገኔ
መሞት መገደልን ካገሬ ሳላጣው
እንዴት ሞት ፍለጋ ወደቻይና መጣሁ?
እኔ ለመሆኔ ባይኖርም መረጃ
ለካስ እኔ ሳላውቅ ያገሬ ምድጃ
ውጭ ውጭ ብሎ ሸኝቶ የላከኝ
በሞት ብያኔ ነው ካገር ያሾለከኝ
እናማ ወገኔ የሀገሬ ዜጋ
እኔም ሳልሰቀል እንደ ፍየል ሥጋ
የታነቀችን ነብስ በብርቱ ፈልጉ
ድምጻችሁን ስጡኝ ሳትሳሱ ሳትነፍጉ
እኔ እንደባሕራን ነኝ ሞቴን ተሸካሚ
መላኩን ላኩልኝ ለህይወቴ ቋሚ
መላክ ፈልጉልኝ የሚታመን ቃሉ
ጦማር የሚለውጥ እፍ ብሎ በቃሉ
ሚካኤልን ጥሩት ገብርኤልን ላኩልኝ
የሞቴን ደብዳቤ የሠርግ ያድርጉልኝ
ዳንኤልን ጥሩት ባንድ ድምጽ ሁኑና
በረበናት ቅጣት እንዳትሞት ሶስና
ወገን ድምጽ ሰጠኝ ናፍቆቱ ከብዶኛል
ድምጽ ደምጽ የሚያሰኝ ስስት አድሮብኛል
እናቴ ብትወልደኝ ዘጠኝ ወር አርግዛ
ከናቴ ማሕጸን ወጥቼ እንደዋዛ
እንዳትቀር እናቴ ፎቶ ብቻ ይዛ
አዋቂ በእውቀቱ አማኝ በጸሎቱ
ሰው የሚፈጥርበት አሁን ነው ሰዐቱ
የሞት የልደቴን ቀን እየጠበኩኝ
ደግሞኛ ጽንስ ሁኜ ስለተረገዝኩኝ
ነብሴን ሳያጠፉት በጽንሴ ሳይጎዱኝ
እናንተ አምጣችሁ እናንተ ወለዱኝ"
15/7/2011
🔘በመምህር ኤፍሬም ተስፋ🔘
http://chng.it/YPY2Z4ZMfg
😥😥እናንተዉ ውለዱኝ😢
"በቅን አስተሳሰብ በገራገር ልቤ
የታሸገ ሻንጣ በስሜ አስመዝግቤ
እኔም እንደባሕራን የሞቴን ደብዳቤ
መልክቴን ለማድረስ ሳላየው አንብቤ
ተሰናበትኩና የሀገሬን ጓዳ
በእምነት ገሰገስኩ ወጣሁ በማለዳ
ከኢትዮጵያ አየር ከአፈሯ ስርቅ
ባየር ተሳፍሬ ስሔድ እሩቅ ምስራቅ
ምኞቴ ሊሳካ በደስታ ስቦርቅ
አውሮፕላን ወርዶ ከሀገረ ቻይና
በፍቅር ደርሼ በሰላም በጤና
ሀገሩን አፈሩን ባይኔ ሳላይ ገና
በኋላ በፊቴ ከበቡኝ መጡና
እጀግ ደነገጥኩኝ ሆዴም ተሸበረ
ከቶ ምን ወረደ ምንስ ተፈጠረ
በሴትነት መንፈስ በሰፍሳፋ አንጄቴ
ጨለማ ሲውጠኝ ጠፋኝ እኔነቴ
እራሴን ስፈልግ ራሴ ጠርጥሬ
ራሴን ስጠይቅ ራሴን መርምሬ
ናዝራዊት አይደለሁ ሌላ ሴት ነኝ እኔ
አደንዛዥ ዕፅ ሰቶ የላከኝ ወገኔ
መሞት መገደልን ካገሬ ሳላጣው
እንዴት ሞት ፍለጋ ወደቻይና መጣሁ?
እኔ ለመሆኔ ባይኖርም መረጃ
ለካስ እኔ ሳላውቅ ያገሬ ምድጃ
ውጭ ውጭ ብሎ ሸኝቶ የላከኝ
በሞት ብያኔ ነው ካገር ያሾለከኝ
እናማ ወገኔ የሀገሬ ዜጋ
እኔም ሳልሰቀል እንደ ፍየል ሥጋ
የታነቀችን ነብስ በብርቱ ፈልጉ
ድምጻችሁን ስጡኝ ሳትሳሱ ሳትነፍጉ
እኔ እንደባሕራን ነኝ ሞቴን ተሸካሚ
መላኩን ላኩልኝ ለህይወቴ ቋሚ
መላክ ፈልጉልኝ የሚታመን ቃሉ
ጦማር የሚለውጥ እፍ ብሎ በቃሉ
ሚካኤልን ጥሩት ገብርኤልን ላኩልኝ
የሞቴን ደብዳቤ የሠርግ ያድርጉልኝ
ዳንኤልን ጥሩት ባንድ ድምጽ ሁኑና
በረበናት ቅጣት እንዳትሞት ሶስና
ወገን ድምጽ ሰጠኝ ናፍቆቱ ከብዶኛል
ድምጽ ደምጽ የሚያሰኝ ስስት አድሮብኛል
እናቴ ብትወልደኝ ዘጠኝ ወር አርግዛ
ከናቴ ማሕጸን ወጥቼ እንደዋዛ
እንዳትቀር እናቴ ፎቶ ብቻ ይዛ
አዋቂ በእውቀቱ አማኝ በጸሎቱ
ሰው የሚፈጥርበት አሁን ነው ሰዐቱ
የሞት የልደቴን ቀን እየጠበኩኝ
ደግሞኛ ጽንስ ሁኜ ስለተረገዝኩኝ
ነብሴን ሳያጠፉት በጽንሴ ሳይጎዱኝ
እናንተ አምጣችሁ እናንተ ወለዱኝ"
15/7/2011
🔘በመምህር ኤፍሬም ተስፋ🔘
http://chng.it/YPY2Z4ZMfg
Change.org
Sign the Petition
Free Nazrawit Abera from Guangzhou Prison
👍2
#የሕይወት_አዙሪት
ሕይወት አዙሪት ናት፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም ነገር ግን የምትጨርሰው ከጀመ
ርክበት ነው፡፡ ልብ በል!
.
• ራቁትክን ትወለዳለህ፤ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ፡፡
• በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ።
• የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ፡፡
.......
ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡
መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል፤ ሠኞ ማክሠኞ ብለህ ተጉዘህ፤ እንደገና ሠኞ ትላለህ፡፡ እናም ሕይወት አዙሪት ናት!
.
መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው፡፡
.
ልብ በል! ባለማወቅ ትጀምራለህ፤ በመዘንጋት ትጨርሳህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም፡፡በለቅሶ ትጀምራለህ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡ በሠው እቅፍ ትጀምራለህ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል? ሕይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ ልብ በል! የዓለም # ከንቱነት ግን ውበትዋ ነው፡፡ ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን፤ ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!! ‹‹ርቀህ የሄድክ ቢመስልህም፤ ትልቅ ክብ ሰርተህ ተመልሰህ እዚህ ትመጣለህ፡፡ ዋናውን ተግባርክን ግን እስካሁን አልጀመርከውም፡፡››
ከመርበብት መጽሐፍ የተወሰደ