#እኛው #ነን...
እኛው ነን የገፋን እኛው ነን የከፋን
እኛው ነን ያጠፋን እኛው ነን የጠፋን
ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን ተስኖን
ሰፊ ሀገር ይዘን በሀሳብ አየጠበብን
በፍቅር ተሳስቦ አብሮ መራመድ አቀበት የሆነብን
ቂም እየቆጠርን ቂም እየመነዘርን
በዛሬ መንጋጋ የትላንት ድርቆሽ የምናመነዥክ
በዛሬ ምድጃ የትላንቱን አመድ ታቅፈን የምንሞቅ
በአንድ ላይ ከመጓዝ በየፊና ሩጫ አረፋ የምንደፍቅ።
እኛው ነን እኛው ነን
ከእምነት የተፋታን ከፈጣሪ የራቅን።
እኛው ተጋፊዎች እኛው ተገፊዎች
እኛው አሳዳጆች እኛው ተሳዳጆች
ካሳለፍነው ህይወት ካሳለፍነው መከራ መማር የተሳነን
ደመና ወራሾች።
በማስመሰል ጥበብ በአድርባይ አንደበት በሸፍጥ
የሰለጠንን
ከብዞዎች ድርሻ ተሻምተን ተናጥቀን
ለአንድ ለእራሳችን በወርቅ ላይ አልማዝ በህንፃ ላይ ህንፃ ስንቆልል ስንከምር የማይሰቀጥጠን
የመንፈስ ድዊዎች የንዋይ ምርኮኞች
የወንበር ሱሰኞች የሆድ አምላኪዎች
ከሰውነት ወርደን በነፍስ የኮሰመንን የስጋ ቡኩኖች
የራሳችን ሀጢያት የራሳችንን ሲኦል እኛው ነን መርገምቶች
እኛው ነን።
🔘በጌትነት እንየው🔘
እኛው ነን የገፋን እኛው ነን የከፋን
እኛው ነን ያጠፋን እኛው ነን የጠፋን
ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን ተስኖን
ሰፊ ሀገር ይዘን በሀሳብ አየጠበብን
በፍቅር ተሳስቦ አብሮ መራመድ አቀበት የሆነብን
ቂም እየቆጠርን ቂም እየመነዘርን
በዛሬ መንጋጋ የትላንት ድርቆሽ የምናመነዥክ
በዛሬ ምድጃ የትላንቱን አመድ ታቅፈን የምንሞቅ
በአንድ ላይ ከመጓዝ በየፊና ሩጫ አረፋ የምንደፍቅ።
እኛው ነን እኛው ነን
ከእምነት የተፋታን ከፈጣሪ የራቅን።
እኛው ተጋፊዎች እኛው ተገፊዎች
እኛው አሳዳጆች እኛው ተሳዳጆች
ካሳለፍነው ህይወት ካሳለፍነው መከራ መማር የተሳነን
ደመና ወራሾች።
በማስመሰል ጥበብ በአድርባይ አንደበት በሸፍጥ
የሰለጠንን
ከብዞዎች ድርሻ ተሻምተን ተናጥቀን
ለአንድ ለእራሳችን በወርቅ ላይ አልማዝ በህንፃ ላይ ህንፃ ስንቆልል ስንከምር የማይሰቀጥጠን
የመንፈስ ድዊዎች የንዋይ ምርኮኞች
የወንበር ሱሰኞች የሆድ አምላኪዎች
ከሰውነት ወርደን በነፍስ የኮሰመንን የስጋ ቡኩኖች
የራሳችን ሀጢያት የራሳችንን ሲኦል እኛው ነን መርገምቶች
እኛው ነን።
🔘በጌትነት እንየው🔘