ሚካኤል ስዩም /2/ ሊቀ መላእክት /2/
መዝገበ ርኅራሄ@ /3/ የዋህ /2/
ትርጉም:- የመላእክት አለቃ ሚካኤል
የዋህ የርኅራኄ መዝገብ ነው
~~~~~~~~~
የመልአኩ ምልጃና ፀሎት አይለየን
እንኳን አደረሳችሁ
@And_Haymanot
መዝገበ ርኅራሄ@ /3/ የዋህ /2/
ትርጉም:- የመላእክት አለቃ ሚካኤል
የዋህ የርኅራኄ መዝገብ ነው
~~~~~~~~~
የመልአኩ ምልጃና ፀሎት አይለየን
እንኳን አደረሳችሁ
@And_Haymanot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦርቶዶክስ ከጂንካ እስከ ሩዶልፍ (Rudolf) ኬንያ !
Share Share
¶ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጦር ሳትሰብቅ የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ብቻ ይዛ በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ኬንያ ሩዶልፍ
(Rudolf) ልጆቿን እያጠመቀች ትገኛለች ።
Join

ኦርቶዶክስ ከጂንካ እስከ ሩዶልፍ (Rudolf) ኬንያ ! Share it
@And_Haymanot
የቃል ሙሽራው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ #ከጂንካ እስከ #ሩዶልፍ
(Rudolf) ኬንያ !
¶ # ቃላችን #ቃል ነው ! #ቃልም በቃል ነው! #ቃልም ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!
¶ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጦር ሳትሰብቅ የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ብቻ ይዛ በአሁኑ ሰዓት ሰሜን ኬንያ ሩዶልፍ
(Rudolf) ትገኛለች ።
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/588
✦́✦́✦́
ይህንን የአምላኳን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ተሸክማ ገና አለምን ታካልላለች!
"እንግዲህ # ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆ እኔ እሰከ አለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ
፡፡የማቲዎስ ወንጌል 28፡20"
✦́✦́✦́
✢ በኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ እና በሰሜን ኬንያ በሩዶልፍ ግዛት የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች ወደ እናታቸው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤት ደርሰዋል፡፡ ብጽኡ አቡነ ፊሊጶስ የወንጌል አርበኛ ፤
ደቡብ ኦሞን ከኬንያ የሰሜን ግዛቶች ጋር በተዋህዶ ገመድ እያሰናሰሉት ነው፡፡
✦́✦́✦́
#ወጣት_የእምዬ_ተዋህዶ_ልጆች_እባካችሁ_ታሪክ_ስሩ በዚህ
ክርመት፡፡ ከዩኒቨርስቲዎች የግቢ ጉባኤያት ለእርፈት ወደ ቤተሰቦቻችሁ የተመለሳችሁ ፤የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቃሁ ጀግና የእምዬ ኦርቶዶክስ የተዋህዶ ወጣቶች ፤ታሪክን
በቃል ፃፉት። ቃላችሁም እራሱ ቃል መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ።
✦ በዬት በኩል እንሳተፍ ካላችሁኝ ✦
✢ በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ፤ በየአጥቢየው ባሉ ስብከተ ወንጌልና የፀረ ተሃድሶ ኮሚቴ በኩል :ግሪሳ ተሃድሶዎች ባልገቡባቸው በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ማሕበራት በኩል : በግቢ
ጉባኤያት እና ፤በሰንበት ትምህርት ቤት ስር ሆናችሁ በመሰባሰብ “”” ዘመቻ ተዋህዶን ” ለገጠሪቱ እና ለጠረፋማ ኢትዮጵያ አከባቢዎች አድርሱዋቸው ፡፡የእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝን
በመድኃኔ አለም ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት በያዝነው አመት እስኪ ከ53% ወደ 75% እናሳድገው ። በርቱ እንበርታ ! ጣረሞት
ሆነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ላለፉት 30 ዓመታት እንዳትንቀሳቀስ አላስኬድ አላላውስ ያሉትን የኢሊሙናቲ ተወካይ ባለስልጣናትን ጠሚዶ ዐቢያችን አባሮልና፡ ቀንዳቸውንም ሰባብሮታል፡፡ ከዕኛ የሚጠበቀው እንደ ደርግ ግዜ የወጣቶች የእድገት በህበረት
ዘመቻ ወደገጠሪቱ እና ጠረፋማ ኢትዮጵያ ግዛቶች #ዘመቻ
#ተዋህዶን ማድረግ ነው፡፡
✦́✦́✦́
✢ በአዲስ አበባ እና በሰሜን ኢትዮጵያ በታላላቅ መንፈሳዊ ጉባኤዎች ያላችሁ መምሀራን እባካችሁ እባካችሁ ፤
ለትክክለኛው ለኢየሱስ ክረስቶስ ወንጌለ መንግስተ ሰማያት ወደ ደቡብ: ወደ ምዕራብ እና ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ተበተኑ፡፡ በመናፍቅ አዚም ተይዘው የጠፉትን ምዕመናን ወደ መንጋው
መልሷቸው፡፡ ቆሎ ቆርጥማችሁ ፤መቃብር ቤት አድራችሁ ፤ከመቃብር በላይ የሆነ ታሪክ ስሩልን፡፡ ውዱ መምህራችን መምህር ምህረተ አብ አሰፋ ከሰሞኑን ዘመቻ ተዋህዶን "
ሐዋርያዊ ጉዞ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ " ብሎ ችቦዉን ለኩሶታል ፡፡ይሄንን ችቦ የማቀጣጠሉ ኃላፊነት የእናንተ ነው፡፡
✦́✦́✦́
✢ ቤቱ በመንጋው እየተጥለቀለቀ ነው፡፡ የጠፉትም ልጆቿ የአምላካቸው የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት አምነው
በመቀበል አማላጅ/ለማኝ ነው በማለት ክብሩን ላዋረዱበት ዘመን ንስሃ ገብተው እየተመለሱ ነው ።አንድ ይሁዳ ቢክድ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሺዎችን ከምስራቅ አፍሪካዊቷ ሐገር ኬንያ ሩዶልፍ ግዛት በፍቅር ስቦ በረድኤት አቅርቦ ከመንጋው ደምሯቿል ።
✦́✦́✦́
✢ ይህን ላደረገ ለአባቶቻችን አምላክ ለቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ለቸሩ መድኃኔ አለም ክብር ምስጋና ይድረሰው፡፡
ንስሄብሆ ንሴብሆ ንሴብሆ ለእግዚአብሔር ስቡሃ ዘተሰብሃ ።
by:- Ezra yekrstos barya
ሼር በማድረግ ሌሎችም ለቤተክርስቲያን እንዲቆሙ እናድርግ
፩ ኃይማኖት

Telegram
፩ ኃይማኖት
ኦርቶዶክስ ከጂንካ እስከ ሩዶልፍ (Rudolf) ኬንያ !
Share Share
¶ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጦር ሳትሰብቅ የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ብቻ ይዛ በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ኬንያ ሩዶልፍ
(Rudolf) ልጆቿን እያጠመቀች ትገኛለች ።
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
Share Share
¶ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጦር ሳትሰብቅ የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ብቻ ይዛ በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ኬንያ ሩዶልፍ
(Rudolf) ልጆቿን እያጠመቀች ትገኛለች ።
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
መጽሐፈ ጦቢት በተሐድሶ መናፍቃን
@And_Haymanot
"መጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 6
መልአኩም ዓሳውን እረደው ጉበቱንና ሀሞቱንም አጭስ ብሎታል ይሄ ደግሞ ሞራ ገላጭነት ይባላል የጠንቋይ ስራ ነው ይላሉ ይህ በቤተክርስቲያን እንዴት ይታያል?" በማለት በውስጥ ላደረሠን ወንድማችን የተሠጠ ምላሽ በዲ/ን ቴዎድሮስ

ከፕሮቴስታንት ፓስተር ጋር የተደረገ ውይይት ክፍል11‹‹ጥምቀት
ከመዳን ጋር ግኑኝነት አለው ወይስ የለውም?‹ያመነ የተጠመቀም ይድናል
ያላመነ ግን ይፈረድበታል › ማር 16፡16
ኦርቶዶክሳዊ ትርጋሜ. ከዚህ በፊት በነበረን የእህታችን ሐና እና የፕሮቴስታንቱ ፓስተር ተከታታይ ውይይት ኦርቶዶክሳዊ የመዳን አስተምሮቶች ከፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ያለውን ሰፊ ልዩነት በቅደም ተከተል ያየን ሲሆን እምነት ላይ የነበረውን ውይይት ያጠናቀቅን ስለሆን አሁን ‹‹ነገረ ጥምቀትን›› እንጀምራለን
Join
👉 @Tewahdo_Haymanote
@And_Haymanot
ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/Tewahdo_Haymanote/124

ተዋህዶ ሃይማኖቴ
ከፕሮቴስታንት ፓስተር ጋር የተደረገ ውይይት ክፍል11‹‹ጥምቀት
ከመዳን ጋር ግኑኝነት አለው ወይስ የለውም?‹ያመነ የተጠመቀም ይድናል
ያላመነ ግን ይፈረድበታል › ማር 16፡16
ኦርቶዶክሳዊ ትርጋሜ. ከዚህ በፊት በነበረን የእህታችን ሐና እና የፕሮቴስታንቱ ፓስተር ተከታታይ ውይይት ኦርቶዶክሳዊ የመዳን አስተምሮቶች ከፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ያለውን ሰፊ ልዩነት በቅደም ተከተል ያየን ሲሆን እምነት ላይ…

#ኢየሱስ_ክርስቶስ የቅዱሳን ሁሉ ንጉስ ነው።
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሚጠራው ስሙ የጣፈጠ።
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሚያዳምጠው ቃሉ የጣፈጠ።
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሚበላው ስጋው የጣፈጠ።
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሚጠጣው ደሙ የጣፈጠ።
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ዜናውን ለሚነግር መታሰቢያው የጣፈጠ።
#ኢየሱስ_ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ የሰውም ልጅ ነው።
#ኢየሱስ_ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ያለ።
እትራቶቹ ከእርሱ ጋር መስቀሉም በፊቱ ያለ።
የአንድነታችን አለቃ የትምክህታችን አስተማሪ የእረኞቻችን አለቃ
የካህናቶቻችንም አለቃ ነው።
እርሱ ከእኛ ጋር ከሰማያዊ አባቱና ሕይወትን ከሚሰጥ ከመንፈስ
ቅዱስም ጋር ይኖራል ለዘላለሙ አሜን ይሁን። ዮሐ 5፡29, 18፡36 ዕብ 3፡1
መጽሐፈ ምስጢር በቅዱስ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ

ሰበር ዜና - ቋሚ ሲኖዶስ: ጎይትኦም ያይኑ ታግዶ ማጣራቱ
እንዲካሔድ ወሰነ!
@And_Haymanot
• የፓትርያርኩን መመሪያ እየጣሰ ግድፈቱን ለመሸፈን መሞከሩ
ተጠቁሟል፤
• የመደባቸውን ደጋፊዎች ያደራጃል፤ ያሳድማል፤ ሰነድ ያሸሻል፤
ይሰርዛል፤
• ይታገድ ባይ ተቃዋሚዎችና አይታገድ ባይ ደጋፊዎች
በየፊናቸው ተንቀሳቅሰዋል፤
• የማጣራቱ ሒደት እስኪጠናቀቅ፣ ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ
ለመመደብ ታቅዷል፤
†††
ቋሚ ሲኖዶስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
ጎይትኦም ያይኑ፣ ከሓላፊነቱ ታግዶ በጽ/ቤቱ ላይ የተወሰነው
ማጣራት እንዲካሔድ ወሰነ፡፡
የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት፣ ትላንት በጉዳዩ ላይ በልዩና ፍጥጫም
በታከለበት ኹኔታ የጀመሩትን ውይይት፣ ሳምንታዊ መደበኛ
ስብሰባቸውን በሚያካሒዱበት ዛሬ፣ ዓርብ፣ ሰኔ 15 ቀን
ቀጥለው የዋሉ ሲኾን፤በመጨረሻም ሥራ አስኪያጁ ጎይትኦም
ያይኑ ታግዶ ማጣራቱ እንዲካሔድ ወስነዋል፡፡
ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
እንዲካሔድ ወሰነ!
@And_Haymanot
• የፓትርያርኩን መመሪያ እየጣሰ ግድፈቱን ለመሸፈን መሞከሩ
ተጠቁሟል፤
• የመደባቸውን ደጋፊዎች ያደራጃል፤ ያሳድማል፤ ሰነድ ያሸሻል፤
ይሰርዛል፤
• ይታገድ ባይ ተቃዋሚዎችና አይታገድ ባይ ደጋፊዎች
በየፊናቸው ተንቀሳቅሰዋል፤
• የማጣራቱ ሒደት እስኪጠናቀቅ፣ ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ
ለመመደብ ታቅዷል፤
†††
ቋሚ ሲኖዶስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
ጎይትኦም ያይኑ፣ ከሓላፊነቱ ታግዶ በጽ/ቤቱ ላይ የተወሰነው
ማጣራት እንዲካሔድ ወሰነ፡፡
የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት፣ ትላንት በጉዳዩ ላይ በልዩና ፍጥጫም
በታከለበት ኹኔታ የጀመሩትን ውይይት፣ ሳምንታዊ መደበኛ
ስብሰባቸውን በሚያካሒዱበት ዛሬ፣ ዓርብ፣ ሰኔ 15 ቀን
ቀጥለው የዋሉ ሲኾን፤በመጨረሻም ሥራ አስኪያጁ ጎይትኦም
ያይኑ ታግዶ ማጣራቱ እንዲካሔድ ወስነዋል፡፡
ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ደጅ ጠናሁ
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተጽናናሁኝ እረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሆኝኝ ቀሪው ዘመኔን
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የዓለምዋን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት
ባርያሽን ሰውረኝ ከአስጨናቂ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ልቤ በአንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላንን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ደጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክአቸው ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብላ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
Join
@And_Haymanot
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተጽናናሁኝ እረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሆኝኝ ቀሪው ዘመኔን
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የዓለምዋን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት
ባርያሽን ሰውረኝ ከአስጨናቂ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ልቤ በአንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላንን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ደጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክአቸው ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብላ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
Join
@And_Haymanot
አዎን አቤቱ አንተ ለዘላለም ልዑል ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ሁሉን የምትገዛ ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ሁሉን የምታድን ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ሁሉን የምትመግብ ነህ
አዎን አቤቱ አንተ የፍጥረታት ጌታ ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ በእውነት የምትፈቀር ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ሁሉን አሳልፈህ የምትኖር የዘላለም አምላክ
ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ አልፋ እና ኦሜጋ ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ አባታችን ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ የነፍስ የሥጋችን መመኪያ ነህ!
አዎን አቤቱ ፈጣሪያችን ነህ!
አዎን አቤቱ የምንገዛልህ የምናመልክህ የምንሰግድልህ
የምናመሰግንህ ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ንጉሰ ነገሥት ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ የጌቶች ጌታ ነህ!
"አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።
" (መጽሐፈ ነሀምያ 9:6)
"አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ጸሎት ይቀርባል።ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል። መዝ 65፡1-2
" በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 66:4)
ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው። የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ኃይልን ለእግዚአብሔር አምጡ። ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤ በቅድስናው ስፍራ
ለእግዚአብሔር ስገዱ። መፅ. ዜና. ቀዳማዊ 16፡27-29

የዛሬው ርዕሳችን በማታው መርሃ ግብር
መጽሐፍ ቅዱስ እና ሳይንስ
👉ዝግመተ ለውጥ
👉 የአለማችን እድሜ በሳይንስና
በኃይማኖት እንዴት ይታያል?
👉 ዳይኖሰር ነበር?
👉 መጽሐፈ ሔኖክ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት በፍጥረታት ያላቸው ማሥረጃ፡፡ እና ሌሎች
በመጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የተሠጠ ድንቅ ትምህርት በማታው መርሃ ግብራችን ይዘን እንቀርባለን ጠብቁን በ ፩ ኃይማኖት ቻናል
Share
@And_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት

Audio
መጽሐፍ ቅዱስ እና ሳይንስ
Share
👉 ዝግመተ ለውጥ
👉 የአለማችን እድሜ
👉 ዳይኖሰር ነበር?
👉 የቅዱሳት መጽሐፍት ማሥረጃ፡፡...
በመጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
Join:- @And_Haymanot
መጠኑ 7.3Mb ነውና ሁላችሁም አዳምጡት
Share
👉 ዝግመተ ለውጥ
👉 የአለማችን እድሜ
👉 ዳይኖሰር ነበር?
👉 የቅዱሳት መጽሐፍት ማሥረጃ፡፡...
በመጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
Join:- @And_Haymanot
መጠኑ 7.3Mb ነውና ሁላችሁም አዳምጡት
ከፕሮቴስታንት ፓስተር ጋር የተደረገ ውይይት ክፍል12… በማር
16፡16 ‹‹ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።›› የሚለው ጥቅስ በእርግጥ ሕጻናትን ማጥመቅን ይከለክላል? ከዚህ በፊት በነበረን
የእህታችን ሐና እና የፕሮቴስታንቱ ፓስተር ተከታታይ ውይይት በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት መካከል ስላለው
የመዳን አስተምሮ ልዩነቶች ማየት ከጀመርን ሰንብተናል በባለፈው በክፍል 11 የመጀመሪያውን እምነትን
መሰረት ያደረገውን ውይይት አጠናቀን ‹‹ነገረ ጥምቀትን›› ጀምረን ነበር ቀጣዩ
እነሆ ብለናል
ለማንበብ 👉 Open

አስደሳች ሰበር ዜናዎች {3}
ለመላው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን በሙሉ።
✞ የአዲስአበባው ቅዱስ ሲኖዶስ ልኡክ ሰሜን አሜሪካ ካለው ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ለአንድነት ውይይት ወደ ሐገረ
አሜሪካ ሊጓዝ ነው ፡፡
¶ የተሃድሶ መናፍቃን መከታ የሆነው አጽራረ ቤ/ያኑ ሚሊየነር አቶ ጎይቶም ያይኑ ከአ.አ ስራ አስኪያጅነት ተነሳ፡፡
✞ በአዲስ አበባ ሐገረስብከ ስር በቲም ጎይቶም ስትበዘበዝ የነበረችው ሰዓሊተ ምህረት አስገራሚው የአካውንት ብር
ጉዳይ ፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት
👉 .... See more

<... #ለዛቲ_ቤት_ሐነጻ_ወልድ >
፩ ኃይማኖት
( እስኪ ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ )
ቤተ ክርስቲያን ማለት ትርጉሙ
👉ክርስቲያን የሆነን ሰው (1ቆሮ
3፥16፤ገላ1፥13)
👉 2.የክርስቲያኖች ሕብረትና ጉባኤ (ማቴ 18፥17፤ የሐዋ 5፥11፤ ቆላ4፥15)
👉 3.ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡበት፥ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉበት
የከበረ የተወደደ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ማለት ነው(ማቴ 16፥16፣ የሐዋ11፥26) የሐዲስ ኪዳንዋ ቤ/ክ በብሉይ አስቀድማ በትንቢት የተነገረች በሐዲስም ራሱ ጌታ በቃሉና በእጁ የሰራት የአማናዊው/እውነተኛው መስዋዕት መሰውያ ናት:: አስቀድሞ
በነብዩ በሚልክያስ "ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ" (ሚልክ1፥11) ተብሎ ነበር:: በብሉይ ዘመን የኦሪት ቤተ መቅደስ፣ ዕጣንና ቁርባን በእስራኤላውያን ዘንድ እንጂ በአሕዛብ ዘንድ ፍጹም አልነበረም!
ስለዚህ ይህ የሚልክያስ ትንቢት በሐዲስ ኪዳን ስጋውና ደሙ ለሚሰጥበት፣ የቅዳሴው ዕጣንም ለሚቀርብበት ቤ/ክ የተነገረ መሆኑ ግልፅ ነው:: ነብዩ ኢሳይያስም "በዚያም ቀን እግዚአብሔር በግብጽ የታወቀ ይሆናል፥ ግብጻውያንም እግዚአብሔርን ያውቃሉ በመሥዋዕትና በቍርባን
ያመልካሉ"ኢሳ19፥21 አለ:: በብሉይ ኪዳን ጊዜ ግብፅ የአሕዛብ ከተማ የነበረች፣ እስራኤላውያን በግብፅ ምድር ሆነው መስዋዕት እንዳይሰው የተከለከለች ሀገር ነበረች:: (ዘፀ 8፥1,29) ስለዚህም ግብጽ ጌታን ያወቀችው በዓመተ ምሕረት ነውና
ኢሳይያስ በትንቢቱ የሚናገረው በዘመነ ሐዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን በቁርባኑና በመስዋዕቱ እንድናከብረው ጌታ
መውደዱን ይገለጥ ዘንድ ነው:: በትንቢት የተነገረው ይፈፅም ዘንድ መሰረትዋም ይመሰርት ዘንድ "አንተ ጴጥሮስ ነህ፥
በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም" በማለት ወልድ ዋሕድ በሚል እምነት እቺን ቤ/ክ ሰራ:: በማይናወፅ ምስክርነት የማትናወፅ ቤ/ክ አቆመ:: በክርስቶስም የማዕዘን ድንጋይነት፣ በጴጥሮስ ዓለትነት፣
በሐዋርያትና በነብያት መሰረትነት መቅደሱን መሰረተ::"በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥
የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" እንዲል(ኤፌ 2፥20 ፤ 5፥23)::የሐዲስ ኪዳንዋ ቤ/ክ ለሐዲስ ኪዳኑ መስዋዕት የመሰውያው ቦታ ሆና ተሾመች:: "መሰዊያ አለን" እንዳለው ቅዱስ ጳውሎስ (ዕብ13፥10)
...ይቀጥላል

....የቀጠለ በመጀመርያው ክ/ዘ ጌታ ካረገ ከ15 ዓመት ብኋላ እመበታችን አርፋ ካረገች ብኋላ 4 ዓመታት እንዳለፉ በ53ዓ.ም ቤተ
ክርስቲያን በጉባኤ መልክ እየሰፋ ሲሄድ ጳውሎስና በርናባስ ባስተማሩባት የፍልጵስዩስ ከተማ ቤ/ክ ይሰራ ዘንድ ግድ ነበር:: በዚህም ሐዋርያት ሱባዔ ይዘው ወደ ጌታ አመለከቱ:: ጌታም
በፊልጶስ ቂሳርያ ለጴጥሮስ በገባለት ቃል ኪዳን መሰረት ሐዋርያትን ለስብከት ከሄዱበት ሀገረ ስብከታቸው በደመና
እየጠራ ፊልጵስዩስ ከሰበሰባቸው ብኋላ አስቀድሞ በነብያት በየቦታው መቅደሱ ይሰራ ዘንድ ባዘዘው መሰረት 3 ድንጋዮችን አንስቶ በእጁ እየለመለሙለት የመጀመርያዋን ቤ/ክ መሰረትዋን
ግድግዳዋንና ጣራዋን ሰርቶ በእናቱ በእናታችን በወዳጁ በእመቤታችን ስም ሰይሞ ስጥቷቸዋል:: ሕንጸተ ቤታም
አከበሩ:: በነጋታው በሰኔ 21 ጌታ ራሱ በሰራት ቤ/ክ ቀድሶ የራሱን ስጋና ደም በማቁረብ ቅዳሴ ቤታን አክብሯል:: ቅዱስ ያሬድ ይህንን ዕለት በማስመልከት "ለዛቲ ቤት ሐነፃ ወልድ
ወፈፀማ መንፈስ ቅዱስ - ይህቺን ቤት ወልድ ሰራት መንፈስ ቅዱስም አጠናቀቃት"አለ:: ይህም ክርስቶስ እንደሰራት፣ መንፈስ ቅዱስም "የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ
ይመራችኋል"እንዲል (ዮሐ16፥13) አጠናቀቃት አለ! መራት ጠበቃት፥ ይመራታል ይጠብቃታል ሲል ነው::....ይቀጥላል

..... #ለዛቲ_ቤት_ሐነጻ_ወልድ_ወፈፀማ_መንፈስ_ቅዱስ ሰኔ 21
ዛሬ ይህንን የቤ/ክ የመሰራትና የቅዳሴዋ በዓል ስናከብር እቺን
ቤ/ክ ለመጠበቅ ደም የለበሱትን፥ ሊያኖርዋት የሞቱትን፥ ቅርሶችዋን ለመጠበቅ በየዱሩ የአውሬ እራት የሆኑትን በየገደሉም የተረሱትን አባቶች በማስታወስ ነው::ክርስቲያኖች
በድንጋይ ተወግረው ወደ ገደል ቢጣሉም፥ ቆዳቸው ተልጦ ጨው ቢጨመርባቸውም፥ አንገታቸው ተቀልቶ ቁልቁል ቢሰቀሉም ሞታቸው ብዙዎችን እየወለደ፥ ደማቸውም ለራሳቸውና ለብዙዎች ጥምቀት እየሆነ፥ እቺን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለኛ አስረክበዋል:: በእውነት ምስጋና ይገባቸዋል::
ምስጋና- በ9ኛው ክ/ዘ በዮዲት ጉዲት ጊዜ 40 ዓመት ሙሉ በየጫካው
ታቦታቱንና ንዋየ ቅድሳቱን ይዘው ለተሰደዱት አባቶች! ክብር- በ16ኛው ክ/ዘ በአሕመድ ግራኝ ጊዜ ማዕተባችንን አንበጥስም ላሉት ቅዱሳን! ውዳሴ- በ17ኛው ክ/ዘ በንጉስ ሱስንዮስ ለታወጀው ካቶሊካዊ አዋጅ አንቀበልም ብለው ለታረዱት 8000
ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን! ልዕልና- በዘመነ መሳፍንት ቅብዓትንና ጸጋን ተከራክረው በመርታት ተዋሕዶን ለመሰከሩ ሊቃውንት አባቶች! መወደድ- የዛሬዋን ቤ/ክ ለመጠበቅ በየገዳማቱ በጸሎት ለተጠመዱት አበው መነኮሳት፥ የጽድቅም አክሊል ቤ/ክንን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ መናፍቃንንና
ተሐድሶን ለሚቃወሙ መምህራን፥ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች! አምልኮና ስግደትም ይቺን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመሰረታት ለትንሳኤው ጌታ ለክርስቶስ ኢየሱስ
ይሁን!!
# ለዛቲ_ቤት_ሐነጻ_ወልድ_ወፈፀማ_መንፈስ_ቅዱስ !!
©Binyam ZeChristos ሰኔ 20 - 2010

[ቃየን አቤልን በሴት ቀንቶ ገደለው]
@And_Haymanot
"ኦርቶዶክስ መልስ ካላት እኛም ጥያቄ አለን" በሚል ርዕስ በተሐድሶ
መናፍቃን በ 2004 ዓ.ም ግንቦት 15 በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙት እነ
ጽጌ ስጦታው CD ማዘጋጀታቸው ይታወሳል፡፡ ለጥያቄያቸው በግዜው በቂ መልስ የተሠጣቸው ቢሆንም ባለማወቅ የሚፍጨረጨሩ ልጆቻቸው መልስ ይሆን ዘንድ አቅርበነዋል በዚህ CD የጠየቁት አንዱ ጥያቄ በ 81 መጽሐፍ ቅዱስ ላይ "ቃየን አቤልን በሴት ቀንቶ
ገደለው" የሚለውን የሚተች ነበርና በውኑ ትችታቸው ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር ሲመዘን ሚዛን ይደፋልን?
+++ "ቃየን አቤልን በሴት ቀንቶ ገደለው" ማለት ትክክል አይደለምን?
ነጩን ማጥቆር ጣፋጩን ማምረር የሚወዱ የተሐድሶ መናፍቃን
የሚያጠራጥሩበት ጥቅስ ነው:: "ወንድሙ የሚወድደው መስሎት
በየዋህነት የተከተለውን ወንድሙን በገደለው በቃየን መንገድ አትሂድ;
እርሱም በሴት ቀንቶ ወንድሙን ገደለው::" |1ኛ.መቃ.23:1-2; የ2000ዓ.ም ዕትም| የሚለውን በመጥቀስ ሳይሆን ለእኩይ ግብራቸው
በመንቀስ ይተቻሉ:: አርሲሳኑ|መናፍቃኑ| እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ሐዋርያው ዮሐንስም ቃየን አቤልን ስለገደለበት ሲናገር "ቃየን ስለምን ወንድሙን ገደለው? የእርሱ ስራ ክፉ የወንድሙ ጽድቅ ስለነበረ ነው::"
1ኛ.ዮሐ.3:12 በማለት በልቡ ክፋትና በአቤል መልካምነት የተነሳ እንጂ እንዴት በሴት ምክንያት ነው የገደለው ይባላል? ይላሉ::
መልስ:- አቤልና ቃየን ከአዳምና ከሔዋን ተለይተው ብቻቸውን ለምን
መሥዋዕት አቀረቡ? እግዚአብሔር የሚመለከው በፍጥረት ሁሉ ነው::
ታዲያ አዳምና ሔዋን ስለምን መሥዋዕት አላቀረቡም? እነዚህን ጥያቄዎች የሚመልሱልን መጽሐፈ መቃብያንና መጽሐፈ ኩፋሌ እንዲሁም አዋልድ መጻሕፍት ናቸው:: ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ያለ እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ምሉዕ ሊሆኑ አይችሉም ማለት ነው::
በዘፍ.4:17 ላይ "ቃየንም ሚስቱን አወቀ; ጸነሰችም ሄኖህንም ወለደች::" ይላል:: ይህች ሴት ከየት መጣች? ቀድሞ አዳምና ሔዋን የወለዱት ቃየንና አቤል ብቻ መሆናቸውን ገልጾ አልነበረምን? ይህች ሴት ከእነርሱ ጋር ከነበረች እንደ አቤልና እንደ ቃየን ለምን መሥዋዕት
አላቀረበችም? የሚል ጥያቄ ያስነሳል:: አሁን ለምን ቃየን አቤልን በሴት ቀንቶ ገደለው ተብሎ የተገለጸውን እንመልከት:: መጽሐፈ ኩፋሌ ሲገልጽ አባታቸው አዳም ከቃየንና ከአቤል ጋር ሌሎች ሁለት ሴቶች እንደ ተወለዱ ይናገራል:: "ሔዋንም በአምስተኛው ሱባኤ አዋንን ወለደቻት አዳምም በስድስተኛው ሱባኤ ልዋን ወለዳት::" |ኩፋ.5:8| ይላል:: እነዚህ ሴቶች ልጆች ከወንዶች ጋር መንትዮች ሆነው እንደተወለዱ የውዳሴና የቅዳሴ ማርያም አንድምታ እንዲሁም ገድለ
አዳምም|First Book of Adam and Eve Prologue; P.1| ይገልጻል:: መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ዘሮም እንዲህ ይላል:- "አዳምና ሔዋን ከደብር ቅዱስ ወርደው ከሱ በታች ተቀመጡ:: በዚሁ አዳም ሔዋንን ተገናኛት:: እሷም ፀነሰች:: የመውለጃዋ ጊዜም ደረሰ::
ቃየልንና ሉድንም መንታዎች ወለደች:: ዳግመኛም ሔዋን ፀነሰች:: የመውለጃዋም ጊዜ ደረሰ:: መንታዎቹን አቤልንና አቅሌምያንም ወለደች:: እነዚህ ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች የአዳም ልጆች አድገው:: ለጋብቻ ደረሱ:: አዳም ይህን ተመልክቶ ሔዋንን እነሆ
እግዚአብሔር እነዚህ ልጆቻችንን አሳደጋቸው:: ስለዚህ ቃየል የአቤልን
እህት አቅሌምያን ያግባት:: አቤል ደግሞ የቃየልን እህት ሉድን ያግባት አላት:: አዳምና ሔዋን በዚሁ ተስማሙ::" ይላል:: [መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ ምዕራፍ አንድ]. በዚህም ምክንያት በአንድነት ያደጉት መንትያ የሆኑት ማለት ከቃየን ጋር አብራ የምትውል|የተወለደች| ና
ከአቤል ጋር አብራ የምትውል|የተወለደች| በአንድነት እንደማይጋቡ አዳም በልቦናው ስላወቀና እግዚአብሔርም ስለ ገለጸለት ሁለቱም
ሴቶች ልጆች ተቀያይረው እንዲጋቡ ፈቀደ:: ገድለ አዳምም ስለዚህ
ሁናቴ ሲገልጽ Then Adam said to her|Eve|, "We will join Abel's sister in marriage to Cain, the Cain's sister to Abel."|Second Book of Adam and Eve; Chapter LXXVIII|. ይላል:: ነገር ግን ቃየን በአባቱ ሃሳብ ስላልተስማማና ስላዘነ
አዳም ወዲያውኑ ያደረገው አቤልና ቃየን በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ነገራቸው:: ይህን ያደረገበት ምክንያት ከአቤል ጋር ያልተወለደችውን መንትያ እግዚአብሔር መሥዋዕቱን ከተቀበለው ከእርሷ ጋር እንዲጋባ ነበር:: "But when Adam saw that the older brother hated the younger, he endeavor f to
soften their hearts, and said to Cain, "O my son, take of the fruits of your sowing and make an offering to God, so that He might forgive you for your wickedness and sin." He said also to Abel, "Take son of your sowing and make an offering and bring it to God, so that He might forgive you for your wickedness and sin."|Second Book of Adam and Eve; Chapter LXVII|. ቃየን
ግን ቀድሞውንም በዚህ ውሳኔ አዝኖ ነበርና ይበልጥ ክፋት ሠራ:: ይህም ለእግዚአብሔር ከፍሬው እንክርዳድ ያለበትን መሥዋዕት ሊቃጠል ነው እንጂ:: እግዚአብሔር ንስሐ እንዲገባ ምክር መከረው:: "ለምንስ ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ? መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚያበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅዋ
ታደባለች; ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው:: አንተ ግን በእርሷ ንገስባት::" |
ዘፍ.4:6-7| ያለው:: ይህም ማለት የአባትህ ሃሳብ የእኔ ነውና ተቀበለው በአባትህ ሃሳብ አትናደድ; አትዘን; የአባትህ ሃሳብ የእኔ ነውና:: ለዚህ ነው የአቤልን መሥዋዕት የተቀበልኩት ሲል ነው:: God would accept Abel's offering. Then God looked at Abel and accepted his offering. ... because of his good heart and pure body. |Second Book of Adam and Eve Chapter LXVII|. ቃየን ወንድሙን ለመግደል ያነሳሳው
የመጀመሪያው ምክንያት በሴት መሆኑን እንረዳለን ማለት ነው:: ለዚህም ነው ገድለ አዳም Cain becomes jealous of Abel because of his sisters. |Chapter LXXVI| ያለው:: ምክንያቱም እግዚአብሔር የአቤልን መሥዋዕት ከተቀበለ የአባቱ የአዳም ፈቃድ በማራራቅ ሊያጋባቸው እንደወሰነ ስላወቀ ይህችን የሚፈልጋት ሴት
ለማግባት ደግሞ ወንድሙን ለመግደል በቅናት ተነሳ:: ገድለ አዳምም
Jealousy overcomes Cain|Chapter LXXVIII| ይላል:: | ዘፍ.4:17; ኩፋ.5:8|. በ 1ኛ.ዮሐ.3:12 ላይ የተገለጸውን ከመቃብያንና ከዘፍጥረት ጋር ሃሳባቸው የተጋጨ አይደለም:: የአቤል ሥራው ወይም ጽድቁ ምን ነበር? የቃየንስ ክፉ ሥራ ምን ነበር? ብለን ብንጠይቅ የመጀመሪያው ምክንያት መሥዋዕት ማቅረባቸው ሊሆን አይችልም:: ነገር ግን ቃየን በአቤል በመቅናቱ ነው:: የቀናበት
ምክንያት ስንመለከት ደግሞ የመጀመሪያው የሚወዳት ሴቷን አቤል
እንደሚያገባት ሲያውቅና የእርሱ

ቃየን አቤልን በሴት ቀንቶ ገደለው?
....የቀጠለ...
እንደማትሆን ሲረዳ በቅናት ወንድሙን ገድሎታል:: ሐሰት በ 4 ደረጃዎች እንደሚሰራ ማለት ነው:: ይህም በመጀመሪያ ከልብ ይጸነሳል; ከዚያም በገጽታ; ከዚያም በቃላት ወይም
በአንደበት በመናገር በመጨረሻም በተግባር እንደምንፈጽመው ማለት
ነው:: ልክ እንደዚህ ሁሉ መጽሐፈ መቃብያን የመጀመሪያውን ምክንያት
የሆነውን በሴት እንደቀና ገለጸው; ቀጥሎ ያለው ደግሞ በኦሪት እንደተገለጸው በመሥዋዕቱ ምክንያት እንደሆነ ገልጾታል:: ሐዋርያው
ዮሐንስ ደግሞ የሦስተኛው የሆነውን የገደለበትን ምክንያትና ውጤቱን
ጽፎታል:: ከዚህም የምንረዳው በተለያየ ክፍሎች የአቤልና የቃየንን ጉዳይ ተካፍለው እንደጻፉት ነው:: እንዲህ ካልሆነማ ቃየን አቤልን የገደለበት ምክንያት በመሥዋዕቱ ነው? ወይስ ክፉ ስራ ስለሠራ ነው? ክፉ ሥራ ተብሎ የተገለጸው ምን ይሆን? ታዲያ መጽሐፈ መቃብያን የመጀመሪያው ምክንያት ወስዶ ቢጽፈው ስህተቱ ምኑ ላይ ነው???? ‹‹ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እያሳቱና እየሣቱ በክፋት
እየባሱ ይሄዳሉ፤ አንተ ግን በተማርክበትና በተረዳህበት ነገር
ፀንተህ ኑር ከማን እንደተማርከው ታውቃለህና ከህፃንነትም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጽሐፍትን አውቀሃል›› 2ኛ ጢሞ 3፥13-18)
ወሰብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ከክቡር!!!

ወዳጄ ሆይ ለነዳያን የምሰጠው የምመጸውተው ገንዘብ ይብዛልኝ ማለት አይገባህም፤ ልዑል እግዚአብሔር ከኛ ይልቅ የሚረባንን የሚጠቅመንን ያውቃልና፡፡ አንተ ግን ብዙ ገንዘብ ባገኘህ ጊዜ በመሳሳት አንዱን ሁለት ሁለቱን ሦስት ላድርግ ማለት ይመጣብህ እንደሆነ አታውቅምና፡፡ ነገር ግን አንተ ዛሬ የምትሰጥ የምትመጸውት ይመስልሀል፡፡ ሰጥቶ ቢፈትንህ ላኑር፤ ላብዛ አልስጥ፤ ላስቀምጥ በማለት አእምሮህ በተለወጠ ነበር፤ ልክ እንደ አውሎጊስ፤
ይህ አውሎጊስ ወፍጮ እየነጠለ እያለዘበ ያንን እየሸጠ ለልብስ፤ ለቀለብ እያስቀረ ይመጸውት ነበር፡፡ ዳንኤል የሚባል ባሕታዊ ወዳጅ ነበረው፤ ከቤቱ ሒዶ አድሮ እንዲህ ሲያደርግ አይቷል ዕለት ዕለት ይጠይቀው ነበርና፤ በዚህ
በጥቂት ገንዘብ እንዲህ ያደረገ ብዙ ገንዘብ ቢያገኝ ነዳያንን እንደምን በጠቀመ ነበር ብሎ ብዕል እንዲሰጠው ወደ ጌታ አመለከተ፡፡ አይሆንም ይበድለኛል አለው፤ እኔ እዋሰዋለው አይበድልህም አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ከዕለታት ባንድ ቀን ወፍጮ ሲነጥል ድስት ሙሉ ወርቅ አገኘ ወስዶ ለንጉሡ አበረከተ፡፡
በዚህ ምክንያት ራስ ቢትወደድነት ሹሞታል፤ ኋላ አውያተ ግፉኣንን/ የተገፉትን ጩኸት/፣ ፅራኀ ነዳያንን/ የነዳያንን ጩኸት/ የማይሰማ ሆነ፡፡ ጌታ፤ ሒዱ ዳንኤልን በምላሱ ስቀሉት ሲል እመቤታችን አማልዳ ስታድነው በራእይ አየ፡፡
ወደዚየሰው ያ ሰው በድሎ ይሆን እስኪ ልሒድና ልጠይቀው ብሎ ሔደ የማያገኘው ሆኖ ሦስት ቀን ያህል ከውጭ አደረ፤ በሦስተኛው ቀን ወደ ውጭ ሲወጣ አየው፡፡ አገኘሁትም አጣሁትም ዛሬ ነው ብሎ ሒዶ ዛቡን ያዘ አስገፍቶት አስደፍቶት ሔደ፡፡ ከዚህ በኋላ እሱ ባወቂ በሕርዩ ይበድላል
አይሆንም ቢለኝ እኔ ባላዋቂ ባሕር አይበድልም አልሁ ብሎ ሒዶ ከሥዕለ ማርያም ተማፅኖ አድናዋለችና እንዲህ አለ፡፡ ......... ተግሳጽ ዘዮሐንስ አፈወርቅ........
Zemaryam zeleke

እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ቤተሰብ
¶ ሕፃኑም ዮሐንስ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል። (ሉቃ ፩፥፲፭)
¶ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ
ሞላባት። (ሉቃ ፩፥፵፩)
¶ አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ።
(ሉቃ ፩፥፷፯)
መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን ታላቅ ቤተሰብ ታሪክ በሉቃስ ወንጌል ላይ ካህኑ ዘካርያስ እና ከካህኑ ከአሮን ወገን የሆነች ኤልሳቤጥ ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ
በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ በማለት ይገልፃል። የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ታሪክም እንዲህ በሚለው በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ይጀምራል፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ
ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤
ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው
ይመልሳል። እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል። (ሉቃ
፩፥፲፭-፲፯) የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሕግጋት እየጠበቀ በቅድስና ይኖር
የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣውን የቅዱስ ገብርኤል ቃል ባለመስማቱ ሕፃኑ እስከሚወለድ ድረስ
ድዳ እንደሚሆን በአብሳሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተነገረው። ይወለዳል የተባለው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ
ዮሐንስን የኤልሳቤጥ መፅነስ በቤተሰቡ መካከል ለረጅም ጊዜ ይፈለግ የነበረ ስለነበር ደስታ ሲፈጥር የካህኑ ዘካርያስ ድዳ መሆን ደግሞ ቤተሰቡን የሚያስጨንቅ ሌላ ክስተት ሆነ። ቅድስት
ኤልሳቤጥም ባለመውለዷ ምክንያት በአካባቢው ሰዎች ግን እግዚአብሔር እንዳዘነባትና ልጅ እንደከለከላት ይነገርባት ስለነበር የልምላሜዋ ዘመን ካለፈ በኋላ መፅነስ በመቻሏ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ
በተመለከተበት ወራት እንዲህ አድርጎልኛል (ሉቃ ፩፥፳፭) በማለት ደስታዋን ገልፃለች። አስቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስ የአዋጅ ነጋሪ ቃል ተብሎ
እንደተነገረው የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካክሉ በማለት ፊት አውራሪ ሆኖ የሚላከውን ቅዱስ ዮሐንስን የፀነሰችው ቅድስት ኤልሳቤጥ
በፀነሰች በስድስተኛው ወር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልትጠይቃት ወደ እርሷ በሔደች ጊዜ እጅግ የሚያስገርም ሁኔታ ተፈጠረ። ይኸውም ቅዱስ ዮሐንስ በማኅፀን ውስጥ ኾኖ ለቅድስት ድንግል ማርያም እና በማኅፀኗ ላለው ለዓለም መድኃኒት ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰግዷል (ሉቃ.፩፥፳፮-፵፩) ።
ሕፃኑም ከተወለደ በኋላ አባቱ ካህኑ ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንደዚህ አለ፦ ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፤
እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤ ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፤ ብርሃኑም
በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል። (ሉቃ ፩፥፸፮-፸፱)
በዚያም ዘመን ሄሮድስ የአምላካችን፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ ከሰብአ ሰገል ሲሰማ መንግሥቴን ይወስድብኛል ብሎ በመፍራቱ የቤተልሔም ሕፃናትን መግደል የመጀመርያ ውሳኔው ሆነ። (ማቴ. ፪፥፩-፲፮) ቅድስት ኤልሳቤጥም ልጇን ዮሐንስን ይዛ ወደ ምድረ በዳ ተሰደደች። የአዋጅ ነጋሪው ቃል ተብሎ የተነገረለት ቅዱስ ዮሐንስ ጊዜው
ሲደርስ ከነበረበት በረሐ ድምፁን እያሰማ መንግሥተ ሰማያት
ቀርባለችና ንስሐ ግቡ! እያለ እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለው አገር ሁሉ ወጣ። (ሉቃ. ፫፥፫-፮) ። በስብከቱም እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ኹሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል፤
ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፤ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ፤ ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ፤ በማንም ላይ ግፍ አትሥሩ፤ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፤ ደመወዛችሁም
ይብቃችሁ፤ ይል ነበር። (ሉቃ. ፫፥፯-፲፬) ። የትሕትና አባት የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ ጌታ ሊጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጣ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? በማለት የጌታችንን አምላክነት ፍጹም በሆነ
ትሕትና ተናግሯል (ማቴ. ፫፥፲፬) ። ብዙ ተከታይ የነበረውና በስብከቱ የብዙ ሰዎችን ቀልብ የገዛው ቅዱስ ዮሐንስ ስለ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል። (ዮሐ ፫፥፳-፱-፴) በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የሚገባውና ከሁሉ የበለጠ ሙሽራ መሆኑን ተናግሯል። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ካህን፣ መምህር፣ ሐዋርያ፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ እና ሰማዕት ነው። ሊቁም ከሰማይ
መላእክት ወገንም ሆነ በምድር ካሉ ቅዱሳን፣ ነቢያት፣ ካህናት፣ መምህራንና ሐዋርያት መካከል ማንም እንደ ቅዱስ ዮሐንስ መለኮትን ለማጥመቅ የተመረጠ አለመኖሩን በመጥቀስ ዮሐንስ ሆይ ራጉኤል በትጋቱ፣ ኢዮብም በጽድቁ ቢመኙም ሆነ ቢጨነቁ እንደ አንተ የሚነድ እሳትን (መለኮትን) ሊያጠምቁ
አልተቻላቸውም ሲል ተናግሮለታል። (መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ) ።
ሰኔ ፴ ቅዱስ ዮሐንስ የተወለደበትን ቀን ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴ እና ታቦት በማውጣት ታከብራለች። በጌታ የተወደደ እና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ሆኖ አምላክን ለማጥመቅ የታደለው
የቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት አይለየን፣ መንፈስ ቅዱስን ተሞልተው ድንቅ ያደረጉና ሕያው ምስክርነትን የሰጡት የመላው ቤተሰብ በረከትም ከሁላችን ጋር ይሁን።