፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
​​ለመሆኑ አስራ አራተኛው የሐዊረ ሕይወት ጉዞ ምን የተለዬ ነገር
ይዞ ተከሰተ ?

@And_Haymanot

የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ
👉 የኔ
👉 ያንተ
👉 ያንች
የሁላችን ጉዳይ ነው የምንለው በምክንያት ነው:: በአስራ አራተኛው የሐዊረ ሕይወት ጉዞ ልዩ ስጦታን ለህዝበ ክርስቲያኑ እንካችሁ ተብሏልና ደስ ይበላችሁ!!! ከዚህ ቀደም ነገረ ተሃድሶን የሚመለከት የአምስት ሰዓት
ውይይትን በድምፅና በምስል የያዘ vcd ለምዕመኑ መዳረሱ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ቢሆንም
👉 ይሔው ዛሬም የጠላት ወረዳን የሚያሸብር የሰባት ሰዓታት ነገረ ክርስቶስን የያዘ ምስልና ድምፅ ( vcd ) ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ በዛሬው ዕለት በአባቶቾ ተመርቆ ለምዕመኑ በነፃ ተበርክቷል::
ከዚህ በተጨማሪም በሰ/ሸዎ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ዳቤ ሰፈረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያንን ለማሰራት ባሰባሰቡት የገቢ ማሰባሰቢያ ከአምስት መቶ ሽ ብር በላይ ገቢ አስደርገዋል።
በ wendye ze tewahdo
ክፍል08 ወይይት..ክርስቶስ የዓለም
አዳኝ እንጂ የግል አዳኝ ተብሎ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጠርቶ አያውቅም ይልቁን ይህ አባባል አማኑኤል ከሚለው ስሙ ጋር ይጋጫል. ‹‹ክርስቶስን የግል
አዳኝ ብሎ መጠራት..አማኑኤል/እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው/ የሚለውን የጌታ ስም ፍጹም መቃወም ነው›› በክፍል ሰባት በነበረን ውይይት
ፕሮቴስታንቶች ለመዳን “Have you accepted Jesus Christ as your personal savior?” ብለው ስለሚያነሱት ተደጋጋሚ ጥያቄ... መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድም ቦታ
በሐዋርያቱ በእነቅዱስ ጴጥሮስ እና በእነቅዱስ ጳውሎስ አፍ ‹‹ጌታ ኢየሱስን እንደግል አዳኝ አድርጋችሁ ተቀበሉ›› ብለው እንዳላስተማሩ እንደዚህም ብሎ ያመነ ሕዝብ እንደሌለ አይተናል…..
በዛሬው ውይይታችን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም አዳኝ እንጂ
የግል አዳኝ እንዳልተባለ እናያለን
….መልካም ንባብ
ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/Tewahdo_Haymanote/113
~~~~~~~~~~
ለአስተያየት 👉 @AHati_Haymanot
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጌታችን መድሃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው ???
በሚል የመንደርደሪያ ሃሳብ ማሕበረ ቅዱሳን በነፃ የሚታደል የሰባት ሰዓታት VCD ለምዕመኑ እንዳዘጋጀ ሰምተዋልን??? የመርሃ ግብሩ ዋና ዋና አላማዎች

አንደኛ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የምታምነውን የምታስተምረውን እና የምትመሰክረውን ያለ የነበረና የሚኖር አስተምሮዎን መግለጥ ነው

ሁለተኛ አንዳንድ ወገኖኖች ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ክርስቶስን ከምታምነውና ከምታስተምረው ስለሱም ከምትመሰክረው ውጭ እንዲህ ትላለች በማለት ለስህተት ትምህርታቸው መንደርደሪያ ለማድረግ ስለሚሞክሩ እውነተኛውን መረጃ በመስጠት ግራ
የሚጋቡ ወገኖቻችንን መጠበቅ ነው
ሶስተኛው የዚህ መርሃ ግብር አላማ ከመፀሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ነገረ
ክርስቶስን በተመለከተ ጥያቄ ለሚነሳባቸው ገፀ ንባቦች ኦርቶዶክሳዊውን ማብራሪያ መስጠት ነው ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡት ደግሞ መምህር ገ/መድህን እንዬው ከደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት የቦሩ ሜዳ ደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ጉባዔ ቤት የሐዲሳት ተርጓሚ
መምህር, አባ ገ/ ኪዳን ግርማ የሐዲሳት ትርጓሜ መምህር የደቡብ
ጎንደር ሃገረ ስብከት ደብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ጉባኤ ቤት የብሉያት ትርጓሜ ደቀ መዝሙር እና በአስተምህሮው የብዙዎቹን ቀልብ መያዝ የቻለው ሰባኪ ወንጌል
መምህር ብርሃኑ አድማሴ ሲሆኑ
የቤተክርስቲያን ወዳጆች ብቻ ሳይሆን ጠላቶቿም የማህበሩ ቢሮ
በመሔድ በፍላሽ አለያም በሚሞሪ ካርድ ወይንም በስልክ
ማስጫን እንደሚቻል ማህበሩ አስተላልፏል።

እኛም እንደደረሠን የምንለቀው ይሆናል ቢሮው በአቅራቢያቸው ሆኖ መረጃው የሌላቸው ይኖራሉና ሼር አድርጉት ለማለት እንወዳለን የደረሣችሁም ካላችሁ
👉 @AHati_Haymanot ላኩልን እናደርሳለን
፩ ኃይማኖት
@And_Haymanot
በቀን እስኪሰለቸን ድረስ የቢራ ማስታወቂያ ሲያሳዩን የሚውሉት የቴሌቪዥን ቻናሎቻችንን የዚህን በጎ አድራጎት ማህበር አላማ በሳንምት 2 ቀን ለዛውም ለ1 ደቂቃ ለማስተላለፍ 150,000(አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ) ብር ሲጠይቁ እንደማየት የሚያም ነገር የለም

እኛ በቻልነው አቅም ፕሮፋይል በማድረግ ማህበሩን እንደግፍ
ከፕሮቴስታንት ፓስተር ጋር የተደረገ
ውይይት ክፍል09 ውይይቱ በእጅጉ ቀጥሏል ብዙዎቻችሁ እየተማራችሁበትና ሼር እያደረጋችሁት እንደሆነ ሥለምትነግሩን ደስ ብሎናል ሐና እህታችንን ለመምሠል የምትጥሩትም በርቱልን እንላለን ድጋፍ አሥተያየታችሁ አይለየን እንላለን ሀሳባችሁን በዚህ ላኩልን
👉 @AHati_Haymanot
ከፕሮቴስታንት ፓስተር ጋር የተደረገ
ውይይት ክፍል09 የጌታን ስጋ እና ደም
በግል መካፈል ሳይቻል…እሱን የግል
አምላክ..የግል አዳኝ ብሎ መቀበል እንዴት ይቻላል…? .....
ለማንበብ 👉 https://tttttt.me/Tewahdo_Haymanote/114
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞"ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል።" ራዕ.
22፥18-20።

@And_Haymanot

የዚህ ገጸ ንባብ ትርጉም ምንድን ነው?
የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የተጻፉት በልዩ ልዩ ዘመን በልዩ ልዩ ሰዎች በልዩ ልዩ ቦታ ነው። ለምሳሌ የሙሴ መጻሕፍት
ከጌታችን ልደት 1500 ዓመት በፊት ሲጻፉ የዮሐንስ ራዕይ ደግሞ በ 88 ዓ.ም አካባቢ ተጽፏል። በብሉይ መጻሕፍት
መካከል የኦሪት መጻሕፍት ከደብረ ሲና እስከ ከነዓን መግቢያ ባለው መንገድ ሲጻፉ ትንቢተ ዳንኤልና ትንቢተ ኤርምያስ
በባቢሎን ምርኮ ጊዜ በአሕዛብ ሀገር ተጽፈዋል። ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መካከል የማቴዎስ ወንጌል በፍልስጤም፥ የማርቆስ ወንጌል በግብፅ፥ የጳውሎስ መልእክታት ደግሞ በታናሽ እስያና የአውሮፓ ከተሞች፥ የዮሐንስ ራዕይ ደግሞ በፍጥሞ ደሴት
ተጽፈዋል። ምንም እንኳን በተለያዩ ሰዎች፥ በተለያዩ ቦታዎች የተጻፉ
ቢሆኑም ቅዱሳት መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በመጻፋቸው ሐሳባቸው ሁሉ አንድ ነው። 2ኛ.ጴጥ.1፥20።
ለምክርና ለተግሣጽ፥ ልብንም ለማቅናት ተጽፈዋል። ሮሜ 13፥4፤ 2ኛ.ጢሞ.3፥15-17። በእግዚአብሔር መንፈስ ስለተጻፉ እርስ በርሳቸው አይጋጩም። በውስጣቸው ከያዙት ትምህርት መካከልም አንዳች ስህተት የለም። ሆኖም ግን እያንዳንዱ መጽሐፍ ከጸሐፊው ማንነት፥ ከተጻፈበት ምክንያት፥ ከተጻፈበት ቋንቋና ባሕል፥ ከተጻፈላቸው ሰዎችና ከተጻፈበት ዘመን አንፃር የአገላለጽ ልዩነት ሊኖረው
ይችላል። ለምሳሌ የማቴዎስ ወንጌል ጸሐፊ ማቴዎስ ሲሆን የጻፈው በዕብራይስጥ ቋንቋ በዕብራውያን ልማድ መሠረት ነው። በመሆኑም አንዳንድ ቦታዎችን ሲገልጥ ተጨማሪ ማብራሪያ አላስፈለገውም። ዕብራውያን ትንቢተ ነብያትን በሚገባ ስለሚያውቁ ከሌሎች ወንጌላውያን በተለየ ብዙ የትንቢት ቃሎችን/ወደ 150 የሚሆኑ ጥቅሶችን/ ጠቅሷል። የመጽሐፉ
ዓላማ ትምህርተ ሙሴን ለሚያውቁ አይሁድ ትምህርተ ክርስቶስ
ምን እንደሆነ መግለጥ በመሆኑ በአብዛኛው የወንጌሉ ክፍል
ከሌሎች በተለየ የጌታን ትምህርቶች ይዟል። የማርቆስ ወንጌል የተጻፈው ለሮማውያን በመሆኑ አጻጻፉ
ከማቴዎስ የተለየ ነው። ወንጌሉ የተጻፈው በላቲን ቋንቋ የዕብራውያንን ባሕል ለማያውቁ በመሆኑ አንዳንድ ቦታዎችንሲገልጥ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷቸዋል። ለምሳሌ ማቴዎስ በምዕ. 3፥13-17 ስለ ጌታችን መጠመቅ
ሲገልጥ በዮርዳኖስ "ወንዝ" አይልም። "ዮርዳኖስ" እንጂ። ማርቆስ በዘመናቸው ኃያላን ነን ያሉ ለነበሩት ሮማውያን
የተጻፈ በመሆኑ የጌታችንን የተአምራትና የኃይል ሥራ በሰፊው በመጻፉ ለሮማውያን ከእነርሱ የበለጠ ኃያል መኖሩን ገልጦላቸዋል። በሌላም በኩል በሮማውያን ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ዓለምን የገዙ በንግድ፥ የሕንጻ ሥራ፥ በአስተዳደር፥ በውትድርና ወዘተ....የተጠመዱ ጊዜ የጠበባቸው በመሆናቸው ከወንጌሎች ሁሉ አጭሩና 16 ምዕራፎች ብቻ ያለውን ወንጌል
ጽፎላቸዋል። እነዚህ ሁሉ መጻሕፍት ከመጀመሪያው ጀምሮ አሁን ባለው
ሁናቴ መጽሐፍ ቅዱስ ተብለው በጥራዝ መልክ የተዘጋጁ አልነበሩም። አስቀድሞ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በብራና
በጥቅል መልክ የተቀመጡ ነበሩ። የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትም በተበታተነ መልክ ለየብቻቸው የተቀመጡ እንጂ በአንድነት የተጠረዙ አልነበሩም። ከ 2ኛው መቶ ክ/ዘመን ጀምሮ የተነሡ
መናፍቃን በሐዋርያት ስም የሐዋርያትን አስመስለው/የበርናባስ ወንጌል፥ የቶማስ ወንጌል... እያሉ/ እየጻፉ ሕዝቡን
በማወካቸው፥ አባቶች እውነተኛውን መጽሐፍ ከሐሰተኛው ለይተው ለሕዝቡ መግለጥ ግድ ሆኖባቸዋል። በመሆኑም በ 20ኛ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ በቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ በ 367 ዓ.ም በጥራዝ መልክ ተዘጋጁ። ከዚህ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን አሁን በምናየው መልክ
ማግኘት ተቻለ። ስለዚህ የዮሐንስ ወንጌላዊ "በዚህ መጽሐፍ"
ሲል በዚህ የራዕይ መጽሐፍ ማለቱ እንጂ በዚህ "የመጽሐፍ ቅዱስ" አጠቃላይ ጥራዝ ማለቱ አይደለም። ቅዱስ ዮሐንስ
ይህንንም ያለበት ምክንያት ማንም በገዛ ሥልጣኑ ትንቢትን ለመተርጎም፥ በትንቢት ላይ ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ
ሥልጣን ስለሌለው ነው። ወንጌላዊውም ከዚህ ቃል በላይ
"በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ" በማለት ቃሉ የሚመለከተው ትንቢቱን ብቻ እንደሆነ ገልጾታል። ራዕ. 22፥18።
እንደዚህ ዓይነት ቃል በኦሪት ዘዳግም ምዕ.4፥2 ላይም እናገኛለን። ይህ ቃል በኦሪት ዘዳግም የተጻፈው ሙሴ
ከእግዚአብሔር አግኝቶ በጻፋቸው ትእዛዛት ላይ መጨመርም
ሆነ መቀነስ ተገቢ እንዳልሆነ የሚያመለክት ነው። የመጽሐፍ
ቅዱስን አጠቃላይ ጥራዝ የሚመለከት አይደለም። ከሙሴ መጻሕፍት በኋላ የተጻፉትን መጻሕፍት በዚያ ዘመን ስላልተጻፉ ይመለከታቸዋል ማለትም አይቻልም።

#ኦርቶዶክሳዊት_የተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያናችን_በመጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ትጨምራለች ? አንዳች! አንዳንድ ሰዎች ከላይ የተገለጸውን ቃል ባለመረዳት ቤተ ክርስቲያን የተቀበለቻቸውን ቁጥር 81
በመሆናቸው ከ 66ቱ ላይ የጨመረች ይመስላቸዋል። ቤተ ክርስቲያን የተቀበለቻቸው መጻሕፍት ያሉና የነበሩ፥ የሚኖሩም እንጂ የተጨመሩ አይደሉም። ለዚህም የያዙት ሙሉውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዝ አለመሆኑን የሚገልጹ አንዳንድ ምሳሌዎችን መመልከት ይቻላል።
፩. በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 4 የቃየን ሚስት ከየት እንደመጣች አይነግረንም። በዓለም ላይ የነበሩት ሰዎች ሦስት ናቸው
ይለናል። አዳም፣ ሔዋን፣ ቃየን /አቤል በመሞቱ/ ቁጥር 16 ላይ ግን "ቃየንም ሚስቱን ዐወቀ፥ ፀነሰችም" ይላል። ከየት
መጣች? ለዚህ ሙሉ መልስ የምናገኘው መጽሐፈ ኩፋሌን
ስናነብ ነው። ኩፋሌ 5፥8።
፪. በማቴ. 27፥9 ማቴዎስ የጠቀሰው የኤርምያስ ትንቢት በ 66ቱ
ውስጥ በሚገኘው ትንቢተ ኤርምያስ የለም። ታድያ ማቴዎስ ከየት አመጣው? ይህ ትንቢት የሚገኘው ከተረፈ ኤርምያስ መጽሐፍ ነው። ተረፈ ኤርምያስ 7፥31።
፫. በይሁዳ መልእክት ቁጥር 14-15 የሚነበበው የሄኖክ ትንቢት
ከየት መጣ? የተገኘው ከመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 1፥9 ላይ ነው።
፠ እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። እናም የዮሐንስ ራእይ መልእክት ትርጉሙ ለጠቅላላው አይደለም። በዚያ ላይ ቤተ
ክርስቲያን ባለው ነገር ላይ የጨመረችው ወይም የቀነሰችው
ነገር የለም። እንዲያውም ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢሩን
ጠብቃ ለእኛም አቆይታልናለች።

#አዋልድ_መጻሕፍትን_መቀበላችን_መጽሐፍ_ቅዱሳዊ_አይደለምን?
የእግዚአብሔር ጸጋው አልተጓደለም። ጥበቡም አላለቀምና ሐዋርያትን እንዳስነሣ፥ ሊቃውንትንም እያስነሣ መጻሕፍትን አጽፏል፥ ያጽፋልም።
☞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያሉትን አዋልድ መጻሕፍት በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰለውን ምሳሌ ተርጉመው፥
የተጠቀሰውን ጥቅስ የበለጠ አብራርተው ብሉያትና ሐዲሳትን
አስማምተው የረቀቀውን አጉልተው መሠረቱን ሳይለቅ ለሰው እንደሚገባው በመተርጎም የተጻፉ ናቸው። በመሆኑም አዋልድ መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ እስከተጻፉ ትምህርታቸውም
ከመሠረታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ለትምህርትና ለተግሣጽ መጠቀም ከነቢያትም ከሐዋርያትም የተማርነው ትምህርት ነው።
፩. "ዳዊት ስለ ሳኦልና ስለ ልጁ ስለ ዮናታን ይህን የኀዘን ቅኔ ተቀኘ፥ የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፏል።" 2ኛ.ሳሙ.1፥17-18።
.....👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/565
✞"ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል።" ራዕ.
22፥18-20። ....

፪. "የቀረውም የሰሎሞን ነገር ያደረገውም ሁሉ፥ ጥበቡም፥
እነሆ፥ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፏል።" 1ኛ.ነገ.11፥41።
፫. "የቀረውም የኤላ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በእሥራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለም?" 1ኛ.ነገ.16፥14። እነዚህን ሁሉ መጻሕፍት እናነብ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ ይጋብዘናል። የቀረው ነገር ከዚያ ተመልከቱ እያለ ምክንያቱም
"ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።" ዮሐ.21፥25 ተብሏልና።
☞ በይሁዳ መልእክት ቁጥር 9 "የመላእክት አለቃ ቅዱስ
ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ
ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ቃል ሊናገረው አልደፈረም።" ይላል። ስለ ሙሴ አሟሟት በተጻፈው በኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 34 ላይ ይህን ቃል አናገኘውም። ከየት መጣ?
የተገኘው "ዜና ሙሴ" ከተባለው መጽሐፍ ነው።
፩. ሐዋርያት ሐዲስ ኪዳንን ሲጽፉ አዋልድ መጻሕፍትን ብቻ
ሳይሆን በቃል ሲተላለፍ የነበሩ ትውፊቶችንም ተጠቅመዋል። ለምሳሌ ራዕይ 2፥14 ባላቅን ያስተማረ የበለዓም ስህተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል። በለዓም ባላቅን ምን እንዳስተማረ ኦሪት ዘኁልቅ ምዕራፍ 23፥24 አይነግረንም።
ሐዋርያት ግን በትውፊት ያገኙትን ነግረውናል።
፪. ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ዔሣው መጨረሻ "በዕንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ሥፍራ አላገኘምና።" ሲል ጽፏል። ዕብ.
12፥16። ኦሪት ዘፍጥረት ግን ይህን አይለንም። ቅዱስ ጳውሎስ
በትውፊት ያገኘውን ነገረን እንጂ።

❖ በመሆኑም ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ.ቆሮ.1፥13 "በውኑ ጳውሎስ
ስለ እናንተ ተሰቀለን?" ያለውን ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ
ጳጳሳት "ከጌታችን ልደት በፊት ብዙ ነብያትና ጻድቃን ሞቱ፥ መሞታቸው ግን የጠቀመው የለም። ክርስቶስ ግን ዓለሙን ሁሉ አዳነ።" ማለቱ ምሥጢሩን ያጎላው እንደሆነ እንጂ የሚለይበት
ነገር አይኖርም። እንዲሁም በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 3 ላይ ቅዱስ ገብርኤል ሦስቱን ወጣቶች ከእሳት እንዳዳነ፥ በሐዲስ ኪዳን ዘመን በእምነት የእነርሱ ልጆች የሆኑት ቅዱስ ቂርቆስና
ቅድስት ኢየሉጣም በእግዚአብሔር ቸርነት፥ በቅዱስ ገብርኤል ረድኤት ከፈላ ውኃ ቢድኑ ምን ያስደንቃል? በዘመናችንስ የእግዚአብሔር ጸጋው ግድሏል እንዴ? እንግዲህ አዋልድ መጻሕፍት አሁንም የእግዚአብሔር ጸጋ
እንዳልጎደለ የሚያስረዱ የቅዱሳን መጻሕፍትን ትርጉም የሚያብራሩ የሥነ ምግባርና የሃይማኖት መመሪያ፥ ማስተማሪያ መመከሪያ ናቸው እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሌላ የተለየ ነገር
ለመጨመር የተዘጋጁ አይደሉም።
ስንጠቀልለው የዮሐንስ ራዕይ 22፥18-20 ትርጉም መናፍቃኑ እንደሚሉት ሳይሆን ከላይ እንዳየነው ነው። ኲላዊት ቤተ ክርስቲያናችንም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ አትጨምርም። ካለውም አታጎድልም። አዋልድ መጻሕፍትን
መቀበሏም አያስነቅፋትም።

፠፠፠ የአባቶቻችን አምላክ ምሥጢሩን ይግለጽልን። አሜን። ፠፠፠
ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
💗 "ቅድስት ድንግል ማርያምን መውደድ ከሚገባኝ መጠን በላይ አልፌ ወድጄያት ይሆን? ብለህ ሥጋት አይግባህ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከወደዳት በላይ ልትወዳት አትችልምና" 💗
ቅዱስ ማክሲሚሊያን ኮልብ
@And_Haymanot
💗 መልካም ዕለተ ሰንበት 💗
ተወዳጆች እንደምን ቆያችሁ እግዚአብሔር አምላክ ፈቅዶ 10 ሺህ አባላት ደርሰናል በውስጥ ስለምታደርሱን ጥሩ እና ደካማ ጎን ከልብ እያመሰገንን ዛሬ አንድ ስራ አብረን አንሰራለን ለምንለቃቸው ትምህርቶች እና መረጃዎች እንዲሁም አብዛኛውን ያማከለ ስራ ለመሥራት ይጠቅመን ዘንድ አገልግሎት ክፍላችሁን ግለጹልን ለአስተያየት @AHati_Haymanot ፩ ኃይማኖት በየትኛው የአገልግሎት ላይ
public poll

ግቢ ጉባኤ ተማሪ – 91
👍👍👍👍👍👍👍 29%

ሰንበት ተማሪ – 84
👍👍👍👍👍👍 27%

ዲያቆን – 58
👍👍👍👍 18%

ማህበረ ቅዱሳን አገልጋይ – 44
👍👍👍 14%

ሌላ – 39
👍👍👍 12%

👥 316 people voted so far.
አድርገህልኛልና

@And_Haymanot

አድርገህልኛልና በቸርነትህ አመሰግንሃለሁ እልል ለዓለም/2/ አማኑኤል እገዛልሃለሁ ለዘላለም
- - - - - -አዝ - - - - -
ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ ይችግር አረንቋ ፊቴ ተደቅኖ ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ ፈፅሞ አራክልኝ የልቤን ትካዘዜ
- - - - - -አዝ - - - - -
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ ካለኝ ነገር ሁሉ ባንተ ታምኛለሁ
- - - - - -አዝ- - - - - -
ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ የምመልስልህ በላገኝ ስጦታ በቀንም በለሊት ሁሌ የሚያበራ መንክር ለባህሪ እፁብ ያንተ ሥራ
- - - - - - አዝ - - - - - -
አምላክ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባሃል ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሃል ድሃ ነኝ አልልም ሐብቴ አንተ ነህና ማሰሮዬ ሞልቷል ላይጎል እንደገና
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
🎓 በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ በመሆን ለቅድስት ቤተክርስቲያን እንዲሁም ለሃገራችሁ የተመረቃችው የግቢ ገባኤ ፍሬዎች ሁላችሁ 🎓
🎓🎓🎓🎓
🎓እንኳን ደስስስስ አላችሁ!!🎓
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት pinned «ድኅነታችን ሂደታዊ ነው! (Our salvation is a process) @Konobyos ያኔ ካቶሊኪን ተቃውመውና ታደስን ብለው ሲወጡ ካህን አልነበራቸውም(ተቃውሞአቸው የተወሰነ እውነትነት ቢኖረውም)! ስለዚህ ሊኖራቸው የሚችለውን ሁለት አማራጭ ተጠቀሙ! አንድ ሁሉም ካህን ነው አሉ (ይህ ግማሽ እውነት ነው) በአንፃሩ ደሞ ሐዋርያዊ ክህነትን (አያይዞም ምስጢራት ፈፃሚነትንና የቤተ ክርስቲያን ስልጣንን…»
ድሮ ትከራከሩለት የነበራችሁ ሁሉ አሁን ምን ተሰማችሁ???
ዲያቆን ነኝ ብሎ በፓስተር ሲዳር አየን አሁን ደሞ እንዲህ ሆኖ መጣ ሌሎቹም ሩጫቸው ለባዶ አዳራሽ ነውና ዛሬም ኦርቶዶክስ ናቸው ብላችሁ የምትሸወዱ
ንቁ ንቁ ንቁ [[[[Share]]]]
Join @And_Haymanot
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
.
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!
በእግዚአብሔር ፍጹም ሰላም እንደ ምን ሰነበታችሁ? ዓለምን ከዳር እስከ ዳር ባስደመመው ልዩ ፍቅሩ የወደደን
እስከዚህም ሰዓት የጠበቀን የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ የኛም አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን!
አሜን!!!
.
የመታሰቢያ መጽሐፍ
ሚል.3:16
.
አሁን እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዚህ የትምህርት ርዕስ ለጥቂት
ደቂቃ አብረን ቆይታ እናድርግ!
. @And_Haymanot

በዚህ በሚል.3:16 ላይ
"የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤
እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ ☞እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ
ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ" ይላል
ቃሉ፡፡
.
ደግሞም እውነት ነው፡፡
እግዚአብሔርን በመፍራት ስለ ቅዱሳን የምንነጋገረውን ሁሉ እግዚአብሔር ያደምጣል ይሰማልም፡፡ ምክንያቱም እርሱን ያመኑ ቅዱሳን ሁሉ መታሰብያቸው ለዘለዓለም እንዲጠፋ እግዚአብሔር አይፈቅድምና፡፡
.
"እግዚአብሔርም ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች
በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ" ይላል፡፡ ኢሳ.56፡4-5
ስለዚህ፡-
👉 መጽሐፍ ቅዱሱ
👉 ገድሉ
👉 ተአምሩ
👉 ድርሳኑ
ስንክሳሩና የመሳሰሉት ሁሉ ክርስቶስን ስለማመን የከፈሉትን
መሥዋዕትነትና ክርስቶስን በማመን ያደረጉትን ተዓምራት የሚያመለክት ለዘላለም የቅዱሳን ሰዎች የመታሰብያ መጽሐፍ ነው፡፡
.
በእነዚህ ሁሉ የመታሰብያ መጻሕፍት የቅዱሳን የሕይወታቸው
ታሪክ ሲነበብ ከሕይወታቸው ሕይወትን እንማራለን፡፡ ከመልካም ሥነ ምግባራቸው ሥነ ምግባርን እንማራለን፡፡ ከቅድስናቸው ቅድስናን እንማራለን፡፡ ከሃይማኖታቸው ጽናት ትምህርተ ሃይማኖትን እንማራለን፡፡
ስለዚህ በጌታ ትዕዛዝ ለቅዱሳን ሰዎች የተጻፈላቸው ይህ የመታሰብያ መጽሐፍ ለእኛ ለተዋህዶ ልጆች ለትምህርትና
ለተግሣፅ በጽድቅ ስላለው ምክር ደግሞ በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡
.
ምክንያቱም፡-
"የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን
ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው
ምክር ደግሞ ይጠቅማል" ተብሎ ተጽፏልና፡፡ 2ጢሞ.3:16-17
.
መናፍቃን ግን ይህንን እውነት በእጅጉ ይኮንኑታል፡፡ ምክንያቱም ኅብረታቸው ከቅዱሳን ኅብረት አይደለምና የቅዱሳን
ታሪካቸው ለዘለዓለም ተቀብሮ እንዲቀር ቅዱሳንንና ስለ ቅዱሳን የተጻፈውን የመታሰብያ መጽሐፍ ለዘመናት ሲቃወሙ ይኖራሉ፡፡
.
"እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት
ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።
ዕብ.10:39 መናፍቃን ቅዱሳንን ለመቃወም ቅዱሳን ሞተው ከመቃብር በታች ስላሉ እነርሱ ሙታን ናቸው እንጂ ሕያዋን አይደሉም ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አመለካከታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳብ ያፈነገጠ በመሆኑ የሞቱት እነርሱ ናቸው እንጂ ቅዱሳን አይደሉም፡፡ ቅዱሳንን ሙታን ናቸው የሚል እርሱ ራሱ በቁመናው ሞቶ በክህደት የተገነዘ ንፍሮ ያልተቀቀለለት፡ ድንኳን ያለተተከለለት፡
ጥሩንባ ያልተነፋለት፡ ዘመዶቹም ያላለቀሱለት ተንቀሳቃሽ ሬሳ
ነው፡፡
.
በጌታ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይላል፡- "ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ ☞የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ
ሕያው ይሆናል፤" ዮሐ.11:25
.
ስለዚህ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን በማመን 562 ዓመት
ሙሉ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ መከራን ተቀብለው ያረፉ አባት ናቸው፡፡
.
አቡነ ተክለሃይማኖትም መላ ዘመናቸውን የተሰቀለውን ክርስቶስን በመስበክ አምልኮተ ጣዖትን እየደመሰሱ ከቁመት
ብዛት የተነሳ እግራቸው እስኪሰበር ድረስ እንደ ምሰሶ ተተክለው ያመኑበትን ክርስቶስን ሲያገለግሉና ለክርስቶስ ያላቸውን ልዩ ፍቅር በተግባር ሲያሳዩ የኖሩ አባት ናቸው፡፡
.
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራም ክርስቶስን በማመኗ የባህር
አራዊት ሆዷን ቀድዶ መመላለሻ እስኪያደርገው ድረስ በባህር
ውስጥ ተተክላ በመጸለይ በክርስቶስ ላይ ያላትን መተማመን ያስመሰከረች ቅድስት እናት ናት፡፡
.
ሰማዕቷ ቅድስ አርሴማም ቅድስናዋን ጠብቃ ስለ ክርስቶስ ልዩ ፍቅር በሰማዕትነት አርፋ እንደ እርሷ በክርስቶስ ላመኑት ክርስቶሳውያን ሁሉ ዘመን የማይሽረውን ሕያው ታሪክ በደሟ
ያስመዘገበች ቅድስት እናት ናት፡፡
.
ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስም ክርስቶስን በማመኑ በድንጋይ ተወግሮ በአስተሳሰባቸው ድንጋይ የሆኑትን ሰዎች ሁሉ ያስገረመ የክርስትናውን ልዕልናም በአደባባይ ላይ እንደ ፋና ያበራ ፍጹምና ቅዱስ የሆነ ሰማዕት ነው፡፡
.
ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስም ለሰባት አመታት ያህል ያለምንም ፍርሀት የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በዓደባባይ ላይ ሲስብክ የኖረና ክርስቶስን በማመኑም ለክርስቶስ ካለው
ታላቅ ፍቅር የተነሳ ደሙን ላፈሰሰለት ጌታ ደሙን አፍስሶ በሰማእትነት ያረፈ ታላቅ መስተጋድል ነው፡፡
.
በ70 ዓ.ም የተወለደው ታላቁ አባት ቅዱስ ፖሊካርፐስም በክርስትና ሕይወቱ እስታድየም ላይ በተሰበሰቡት ሕዝብ መካከል ወደ እሳት ተጥሎ ለክርስቶስ የነበረውን ልዩ ፍቅር በተግባር በማሳየት ምስክርነቱን የፈፀመ ሰማዕት ነው፡፡
.
ጌታ በመዋዕለ ሥጋዌው አቅፎ ተሸክሞ በወንጌል ላይ ለትልልቆች ምሳሌ አድርጎ ያቀረበው የዚያን ጊዜው ሕጻን የአሁኑ
አባትና ሰማዕት ቅዱስ አግናጥዮስም ሕዝብ በተሰበሰበበት እስታድየም ላይ ወደ እሳት ተጥሎ ለክርስቶስ ያለውን ልዩ ፍቅር በተግባር ያሳየ ድንቅ ሰማዕት ነው፡፡
.
በመሆኑም እነዚህ ሁሉ፡-
"ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ ☞የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ
ሕያው ይሆናል፤" ዮሐ.11:25
በሚለው በጌታ ቃል መሠረት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያረፉ በመሆናቸው ሕያዋን እንጂ ሙታን አይባሉም፡፡ ስለዚህ በክርስቶስ አምነው ያረፉትን ቅዱሳን ሙታን ናቸው ብሎ
ማለት ክርስቶስን የሙታን አምላክ ነው እንደ ማለት ነው፡፡ ያ ደግሞ ፍጹም ክህደት ነው፡፡ የሕይወታችን መመርያ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ
"ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። እንግዲህ
እጅግ ትስታላችሁ" ተብሎ ተጽፏል፡፡
ማር.12፡26-27 ክርስቶስ ደግሞ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ እርሱ የሕያዋን አምላክ ነው ከሆነ በእርሱ አምነው የረፉት ቅዱሳን የሕያዋን ናቸው እንጂ ሙታን አይደሉም ሙታንስ
ቅዱሳንን ሙታን የሚሉ መናፍቃን ናቸው፡፡
.
እንግዲህ ክርስቶስ በባሕርዩ ሕያው ነው፡፡ ቅዱሳንም ደግሞ በዕርሱ አምነው በማረፋቸው ሕያዋን ናቸው፡፡ ስለዚህ ሕይወት የሆነውን ክርስቶስን ስላመኑና ቅዱሳንም በእርሱ ሕያዋን በመሆናቸው ስለ እነርሱ የሚናገረው መጽሐፍ
ሁሉ ደግሞ ሕያው ሆኖ በሥጋ አስተሳሰብ ሳይሆን በመንፈስ
ሆነው የሚያነብቡትን ሁሉ ሕያዋን ያደርጋቸዋል፡፡ ይኸውም ደግሞ በፈቃደ እግዚአብሔር የተጻፈ ለቅዱሳን
ለዘለዓለም የመታሰብያ መጽሐፋቸው ነው፡፡
ልዑል እግዚአብሔር የቅዱሳኑን ረድኤትና በረከት ያሳድርብን!
አሜን!!!
▄ ▃ ▂ ▁✞▁ ▂ ▃ ▄
@And_Haymanot
▄ ▃ ▂ ▁✞▁ ▂ ▃ ▄
በሐዋሳ የተነሣውን ግጭት ሸሽተው ቤተ ክርስቲያን የተጠለሉ ወገኖቻችን አዎ ምንጊዜም የቤተ ክርስቲያን ገጽታዋ ለስዱዳን መጠጊያ ለግፉአን መጠለያ ላዘኑ መጽናኛ መኾን ነው፡፡
የአባትነት ወጉንም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ስላሳዩን ረዥም ዕድሜ ይስጥልን!

ቡራኬዎ ይድረሰን አባታችን!
@And_Haymanot
ጸልዩ ጸልዩ
"ወዳጄ፥ ሕይወት አጭር ናት። ዛሬን እንጂ ነገን ስለመኖርህ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ስለዚህ ዛሬን መልካም አስብ፤ ለሌሎች መልካም አድርግ። በሙሉ ልብህ እመን። ስላለህ ነገር አመስግን። ሰው አትበድል ነገር ግን ብትበድል ይቅርታን ጠይቅ፤ ቢበድሉህም ይቅርታ እስኪጠይቁህ ሳትጠብቅ ይቅርታን አድርግ። የዋህ ሁን ነገር ግን ይቅርታ ያደረክለት ሰው ዳግም ይበድልህ ዘንድ ሞኝ አትሁን።"
Join
@And_Haymanot
🌸መልካም ዕለተ ሰንበት🌸
@And_Haymanot
​​ሙስሊሞች ፕሮቴስታንቶች ሌሎችም ቅዱስ ገብርኤል እቅፍ ውስጥ...
ቤተክርስቲያን ግን አትገርማችሁም??
እነዚ የምታዩአቸው ሰሞኑን ሀዋሳ ላይ በተነሳው ብሄር ተኮር ግጭት ሸሽተው ወደ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የገቡና አሁንም እዛው ያሉ ሙስሊም ኦርቶዶክስ ፕሮቴስታንት የሆኑ
በብሄርም አማራ ጉራጌ ኦሮሞ ሲዳማ ትግሬ ሌላም ሌላም የሆኑ ወገኖቻችን ናቸው።


#ቤተክርስቲያን_ሰውን_ሰው_በመሆኑ_በክርስቶስ_ፍቅር_እንዲህ_ታኖራለች፡፡


ተወዳጆች ታድያ ቤተክርስቲያናችን ለሰው ልጅ ያላትን የፍቅር እያያችሁ ይህች ቤተክርስቲያን የዚህ ብሔር ናት የእከሌ ናት.... በማለት ለሚነቅፏት የእናት ጡት ነካሽ ሐራጥቃዎች
ጥግ ድረስ share አድርጋችሁ አታሳዩላትም??
፩ ኃይማኖት
@And_Haymanot
@And_Haymanot
🔊ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ
📖"እኛ ግን ለፀሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን" ሐዋ ፮:፬
በሚል መሪ ቃል ለ፫ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ታላቅ የፀረ ተሀድሶ ጉባኤ ⛪️🌈በናዝሬት ደ/ቀርሜሎስ ቅ/እስጢፋኖስ ቤ/ን አውደ ምህረት ተዘጋጅቷል 🌈
በጉባኤው👩‍👩‍👧‍👦👩‍👩‍👦‍👦👨‍👩‍👧‍👧ላይ
ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታ
የተሃድሶ ዶግማዎች
በተሃድሶ ለሚነሡ ጥያቄዎች መፅሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ
እንዲሁም ከእኛ ምን ይጠበቃል 🎤በሚሉ ጉዳዮች ላይ በታላላቅ መምህራነ ወንጌል ትምህርት📖 ይሠጣል...እርሶም በጉባኤው ላይ በመገኘት ርትዕት ስለሆነች ☁️ሃይማኖታችን☁️ ምስክር ይሁኑ፡፡
✔️የጉባዔው ሰዐት እና ቀን
አርብ በ15 ከ10 ሰዐት🕙 ጀምሮ
ቅዳሜ ጠዋት ከቅዳሴ በኃላ🕑
ማታ ከ10 ሰዐት🕙 ጀምሮ እሁድ ጠዋት ከቅዳሴ በኃላ 🕑
ማታ ከ10 ሰዐት🕙 ጀምሮ
🏵🎤ተነሳ ህዝቤ ተነሳ(፪)
ተነሳ ወገን ተነሳ
የጥንቱ እንዳይረሳ
የቀድሞ እንዳይረሳ🔊🏵

👉share share share
@And_Haymanot
​​#አስደሳች_የድል_ዜናዎች
ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕናን በሙሉ!

@And_Haymanot

✦́ # ድል # በድል ይሉሃል ይሄ ነው { 5 } #የድል ዜናዎች!
ክብሩ ይስፋ ለመድኃኔ አለም ሌላ ምን እንላለን፡፡
✦́ በል እንግዲህ # ጠላት ! # እሳቱን የለኮስከው አንተ በለኮስከው እሳት የተለበለብከውም አንተ ! የተዋህዶ ማዕበል በያቅጣጫው እየተፋፋመልክ ነው!
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
¶ የደቡብ ኦሞ ህዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የኦረቶዶክስ
ተዋህዶ መንጋ እየተቀላቀለ መምጣታቸው።
¶ በኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የአዲስ አበባው የፀረ
ተሃድሶ መናፍቃን ጉበኤ 2ቀናት ቀሩት ።
¶ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚደረገው ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ
የክርስቶስ ወንጌለ መንግስተ ሰማያት የማስፋፋቱ አገልግሎት
መበሰሩ ። ወጣት የተዋህዶ አናብስት ልጆችም በክርምቱ
የእርፍት ጊዜያችሁ “ዘመቻ ተዋህዶ” እንድተቀላቀሉ ጥሪ
መቅረቡ ። ዳይ ! ዳይ ! ወደስራ ! የምን መፍዘዝ ነው !
¶ በምዕራብ ኢትዮጵያ ኢሉባቡር እና በምስራቅ ኢትዮጵያ
በሐረር ከተማ የመሸገው የተሃድሶ መናፍቃን መንጋ
የመጨረሻዎቹ መሽጎች እየፈራረሱ መምጣታቸው ፡፡
¶ በናዝሬት ከተማ የተመሰረተው የአባታችን የአቡነ ገብረ
መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እናፈርሰዋለን ያሉት ፈራርሰው
፤ሐምሌ 5/2010 ዓ.ም ሊመረቅ መሆኑን፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 1ኛ ) #“እኛም # ጥምቀትን እና # ቤተክርስቲያንን #
እንፈልጋለን “ በሚል መርሃ ግብር ፡ በደቡብ ኦም ሐገረ ስብከት
ሊቀጳጳስ በብጹ አቡነ ዕንባቆም መሪነት ፡ በማኅበረ ቅዱሳን
ዋናው መእከል እና በአዲስ አበባ ሐገረ ስብከት ጥምረት ፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን : መላው የደቡብ
ኦሞን ማሕበረሰብ እያካለለች መታለች ፡፡በዚህ አመት መጨረሻ
የክርምት ወር ላይ ለሚደረገው በሺዎች ለሚቆጠሩ የአዳዲስ
ምዕመናን የጥምቀት እና የክርስቶስ ተክክለኛው የወንጌል
የማስፋፊያ አገልግሎት የሚውል ድጋፍ ለማሰባሰብ በሰሜን
አሜሪካ በሲያትል (Seattle , Washington ) ከተማ ታላቅ
መንፈሳዊ ጉባኤ እና የድጋፍ መርሃ ግብር በደቡብ ኦሞ ሐገረ
ስብከት ሊቀጳጳስ በብፁ አባታችን በአቡነ ዕንባቆም አስተባባሪነት
በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ማኀበረ ምዕመናን ተዘጋጅቷል ።
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
ምዕመኑም ለመንፈሳዊ አገልግሎቱ ጥሪ ቆርጦ ተነስተዋል፡፡
በሰሜን አሜሪካ የምትኖሩ የእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ምዕመናን በሙሉ፤ ለዚህ ሐዋርያዊ አገልግሎት የበኩላችሁን
አስተዋጾ እንድታደርጉ እና ጥምር ኮሚቴው ለሚያሰራው ከ42
በላይ አዳዲስ ሕንጻ ቤተክርስያናት ድጋፍ እንድታደረጉ
በእግዚአብሔር ፍቅር ተጠርታቿል፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 2ኛ ) ) በመምህር ምህረተአብ አሰፋ ጀማሪነት የሚደረገው
የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ትክክለኛው ሉተር ያልበረዘው ኦርቶዶክሳዊ
የሆነ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌለ መንግስተ ሰማያት
የማስፋፋት አግልግሎት በይፋ ተጀምሯል፡፡ለበርካታ ወራት
ከሀገር ውጭ የነበረው መምህራችን ፤ ወገቡን በአባቶች ልብስ
ታጥቆ ወንጌለ መንግስተ ሰማያትን ገጠር ላሉ ኢትዮጵያውያን
ለማዳረስ እና መንጋውን ወደቤቱ ለመመለስ ቆርጦ ተነስቷል ፡፡
በዚህም የተዋህዶ ማዕበል(ሐራ ተዋህዶ) የየሐገረስብከቱ
ስብከተ ወንጌል ሰራተኞች ፡ የማኀበረ ቅዱሳን አባላት እና
ወጣት የሰንበት ተምህርት ቤት ተማሪዎች ድጋፍ
እንደሚታከልበት ተጠቁሟል ።፡በአዲስ አበባ እና በሰሜን
ኢትዮጵያ ያላችሁ መምህራን ለ30 ዓመታት በሀገራችን ላይ
ተጋርዶባት የነበረውን ይሄንን የ ጨለማ የምንፍቅና አዚም
በትክክለኛው ወንጌል እንድታርቁት እና የገጠሪቱ ኢትዮጵያ
ምዕመናን እንድትታደጉ ጥሪ ቀርቦላቿል ።
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
በል እንግዲህ እንደ ፓስተር በግ ዋሻው የአንድ ዘመን ድሪቶ ፥
5 star ሆቴል ካልተያዘልኝ ብለክ እምቡር እምቡር በል አሉክ ፡፡
ለክርስቶስ ወንጌል ፡ ለተዋህዶ ጥሪ ና ከተባልክ! በቃ ና፡፡ቆሎ
ቆርጥምህ ፡መቃብር ቤት አድረህ ህዝቡን ወደመንጋው
መልሰው፡፡በየከተማው ያላችሁ ወጣት የተዋህዶ አናብስቶች
በኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ ማሕበራት ሆናችሁ የክርምት
ጊዜያችሁን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለሚደረገው የተዋህዶ ማዕበል
የማስፋፋት አገልግሎት እንድትሳተፉ ጥሪ ቀርቦላችኋል፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 3ኛ ) ከመሐል ሐገር እና ከደቡብ ኢትዮጵያ አከርካሪው
ተሰብሮ የተገነደሰው የፕሮቴስታንቱ አለም አዲሱ ታርጋ ፡
የተሃድሶ መናፍቃን “# እንደገና # ማንሰራራት” በሚል መርህ
በሰዶማዊው ፓስተር አገሰግድ ሳህሉ እየተመራ መዳረሻውን
በምዕራብ ኢትዮጵያ ኢሉባቡር ዞን በመቱ እና አከባቢው አድርጎ
የነበረ ሲሆን ይህንን ምሽግ ብርቅዬው የተዋህዶ ልጅ መምህር
ምህረተአብ አሰፋ " ወንጌልን ለገጠሪቱ ኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ
ባደረገው የተዋህዶ ዘመቻ ፤ግሪሳዎችን እንከትክታቸውን
በእግዚአብሔር ቃል መዶሻነት አውጥቷል ፡፡በመሆኑም እነ
ፓስትር አሰግድ መጦሪያችን ይሆናል ያሉት አዳራሽ በመቱ እና
አከባቢዋ ባሉ የተዋህዶ ወጣት አናብስት በትላንትናው እለት
ተዘግቷል፡፡በተሳሳተ ተምህርትም የተወሰዱ 73 ምእመናን ወደ
እናታቸው ቤት ተመልሰዋል፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
የመጨረሻው የፕሮቴስታንቱ አዲሱ ታርጋ የሆነው የተሃድሶ
መናፍቃን ምሽግ በሐርር እና በአከባቢዋ በሚገኙ ከተሞች ነበር
፡፡ይህንንም ምሽግ የማኀበረ ቅዱሳን ዋናው መዕከል መምህራን
ከምዕራብ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት ሊቃውንት እና ወጣት አናብስት
የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጋር በፈጠሩት አስደናቂ ጥምረት
ከሰሞኑን ባዘጋጁት የተዋህዶ የወንጌል አገልግሎት ግብአተ
ምድሩን እየፈጸሙ ነው፡፡ምጽ ምጽ የፕሮቴስታንት ተላላኪ
ተኩላዎች! እግዚአብሔርን ችላችሁ ልትዋጉት??? በማይሻር
ቃሉ እንክትክታችሁን አወጣልን !
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 4ኛ ) በናዝሬት ከተማ በመናፍቃን የወያኔ ቅጥርኛ ቡድን
በ2009 ዓ.ም ሊፈርስ የነበረው የጻድቁ አባታችን የአቡነ
ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ፡ በአከባቢው የተዋህዶ
አናብስት ተጋድሎ እና በክቡር የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በሊቀ
ዲያቆን በአቶ ለማ መገርሳ ቀጥተኛ ፍቃድ እነሆ ሐምሌ
5/2010 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ በታላቅ ድምቀት አዲስ ወደታነጸለት
ሕንጻ ቤክርስቲያን ይገባል፡፡የሚገርመው የአከባቢው ምዕመናን
ልጆቻቸውን ድቁንና በማስተማር ለነገይቱ የተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ሰራዊቶቿ እንዲሆኑ እያዘጋጇቸው ነው፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
# 5ኛ ) በአዲስ አበባ ሐገር ስብከት በሚገኙ የቦሌ ደብረ ሳህል
ቅዱስ ሚካኤል እና የጉለሌ እግዚአብሔር አብ ደብራት ከፊታችን
አርብ ከሰኔ 12/2010 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት
የሚቆይ የተሃድሶ መናፍቃንን ሴራ ሚያጋልጥ ታላቅ መንፈሳዊ
ጉባኤ አዘጋጅተዋል፡፡ አዲስ አበቤዎችዎች ይሰማችሁዋል!
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
የቦሌው የደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ጉባኤ በአይነቱ እስካሁን
በኢትዮጵያ ከተደረጉት ልዩ የሆነና በቀጥታ ስርጭት በyou tube
ለመላው አለም ይተላለፋል፡፡ በተለይ ለስደስት የአፍሪካ ሐገራት
የሚሆን የ ኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛው የመንግስቱ ወንጌል
በቀጥታ live streaming እንደሚተላለፍ የዝግጅቱ አስተባባሪ
ኮሚቴዎች ገልጸዋል፡፡
✢́✢✢ ✞✞✞ ✢́✢✢
ይህን ላደረገ ለአባቶቻችን አምላክ ለቅድስት ድንግል ማርያም
ልጅ ለቸሩ መድኃኔ አለም ክብር ምስጋና ይድረሰው፡፡
Share ፩ ኃይማኖት share
@And_Haymanot
@And_Haymanot