፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
<... #ለዛቲ_ቤት_ሐነጻ_ወልድ >

፩ ኃይማኖት

( እስኪ ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ )
ቤተ ክርስቲያን ማለት ትርጉሙ

👉ክርስቲያን የሆነን ሰው (1ቆሮ
3፥16፤ገላ1፥13)
👉 2.የክርስቲያኖች ሕብረትና ጉባኤ (ማቴ 18፥17፤ የሐዋ 5፥11፤ ቆላ4፥15)
👉 3.ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡበት፥ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉበት
የከበረ የተወደደ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ማለት ነው(ማቴ 16፥16፣ የሐዋ11፥26) የሐዲስ ኪዳንዋ ቤ/ክ በብሉይ አስቀድማ በትንቢት የተነገረች በሐዲስም ራሱ ጌታ በቃሉና በእጁ የሰራት የአማናዊው/እውነተኛው መስዋዕት መሰውያ ናት:: አስቀድሞ
በነብዩ በሚልክያስ "ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ" (ሚልክ1፥11) ተብሎ ነበር:: በብሉይ ዘመን የኦሪት ቤተ መቅደስ፣ ዕጣንና ቁርባን በእስራኤላውያን ዘንድ እንጂ በአሕዛብ ዘንድ ፍጹም አልነበረም!
ስለዚህ ይህ የሚልክያስ ትንቢት በሐዲስ ኪዳን ስጋውና ደሙ ለሚሰጥበት፣ የቅዳሴው ዕጣንም ለሚቀርብበት ቤ/ክ የተነገረ መሆኑ ግልፅ ነው:: ነብዩ ኢሳይያስም "በዚያም ቀን እግዚአብሔር በግብጽ የታወቀ ይሆናል፥ ግብጻውያንም እግዚአብሔርን ያውቃሉ በመሥዋዕትና በቍርባን
ያመልካሉ"ኢሳ19፥21 አለ:: በብሉይ ኪዳን ጊዜ ግብፅ የአሕዛብ ከተማ የነበረች፣ እስራኤላውያን በግብፅ ምድር ሆነው መስዋዕት እንዳይሰው የተከለከለች ሀገር ነበረች:: (ዘፀ 8፥1,29) ስለዚህም ግብጽ ጌታን ያወቀችው በዓመተ ምሕረት ነውና
ኢሳይያስ በትንቢቱ የሚናገረው በዘመነ ሐዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን በቁርባኑና በመስዋዕቱ እንድናከብረው ጌታ
መውደዱን ይገለጥ ዘንድ ነው:: በትንቢት የተነገረው ይፈፅም ዘንድ መሰረትዋም ይመሰርት ዘንድ "አንተ ጴጥሮስ ነህ፥
በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም" በማለት ወልድ ዋሕድ በሚል እምነት እቺን ቤ/ክ ሰራ:: በማይናወፅ ምስክርነት የማትናወፅ ቤ/ክ አቆመ:: በክርስቶስም የማዕዘን ድንጋይነት፣ በጴጥሮስ ዓለትነት፣
በሐዋርያትና በነብያት መሰረትነት መቅደሱን መሰረተ::"በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥
የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" እንዲል(ኤፌ 2፥20 ፤ 5፥23)::የሐዲስ ኪዳንዋ ቤ/ክ ለሐዲስ ኪዳኑ መስዋዕት የመሰውያው ቦታ ሆና ተሾመች:: "መሰዊያ አለን" እንዳለው ቅዱስ ጳውሎስ (ዕብ13፥10)
...ይቀጥላል
@And_Haymanot
@And_Haymanot
..... #ለዛቲ_ቤት_ሐነጻ_ወልድ_ወፈፀማ_መንፈስ_ቅዱስ ሰኔ 21

ዛሬ ይህንን የቤ/ክ የመሰራትና የቅዳሴዋ በዓል ስናከብር እቺን
ቤ/ክ ለመጠበቅ ደም የለበሱትን፥ ሊያኖርዋት የሞቱትን፥ ቅርሶችዋን ለመጠበቅ በየዱሩ የአውሬ እራት የሆኑትን በየገደሉም የተረሱትን አባቶች በማስታወስ ነው::ክርስቲያኖች
በድንጋይ ተወግረው ወደ ገደል ቢጣሉም፥ ቆዳቸው ተልጦ ጨው ቢጨመርባቸውም፥ አንገታቸው ተቀልቶ ቁልቁል ቢሰቀሉም ሞታቸው ብዙዎችን እየወለደ፥ ደማቸውም ለራሳቸውና ለብዙዎች ጥምቀት እየሆነ፥ እቺን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለኛ አስረክበዋል:: በእውነት ምስጋና ይገባቸዋል::
ምስጋና- በ9ኛው ክ/ዘ በዮዲት ጉዲት ጊዜ 40 ዓመት ሙሉ በየጫካው
ታቦታቱንና ንዋየ ቅድሳቱን ይዘው ለተሰደዱት አባቶች! ክብር- በ16ኛው ክ/ዘ በአሕመድ ግራኝ ጊዜ ማዕተባችንን አንበጥስም ላሉት ቅዱሳን! ውዳሴ- በ17ኛው ክ/ዘ በንጉስ ሱስንዮስ ለታወጀው ካቶሊካዊ አዋጅ አንቀበልም ብለው ለታረዱት 8000
ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን! ልዕልና- በዘመነ መሳፍንት ቅብዓትንና ጸጋን ተከራክረው በመርታት ተዋሕዶን ለመሰከሩ ሊቃውንት አባቶች! መወደድ- የዛሬዋን ቤ/ክ ለመጠበቅ በየገዳማቱ በጸሎት ለተጠመዱት አበው መነኮሳት፥ የጽድቅም አክሊል ቤ/ክንን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ መናፍቃንንና
ተሐድሶን ለሚቃወሙ መምህራን፥ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች! አምልኮና ስግደትም ይቺን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመሰረታት ለትንሳኤው ጌታ ለክርስቶስ ኢየሱስ
ይሁን!!
# ለዛቲ_ቤት_ሐነጻ_ወልድ_ወፈፀማ_መንፈስ_ቅዱስ !!
©Binyam ZeChristos ሰኔ 20 - 2010
@And_Haymanot
@And_Haymanot