፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
..... #ለዛቲ_ቤት_ሐነጻ_ወልድ_ወፈፀማ_መንፈስ_ቅዱስ ሰኔ 21

ዛሬ ይህንን የቤ/ክ የመሰራትና የቅዳሴዋ በዓል ስናከብር እቺን
ቤ/ክ ለመጠበቅ ደም የለበሱትን፥ ሊያኖርዋት የሞቱትን፥ ቅርሶችዋን ለመጠበቅ በየዱሩ የአውሬ እራት የሆኑትን በየገደሉም የተረሱትን አባቶች በማስታወስ ነው::ክርስቲያኖች
በድንጋይ ተወግረው ወደ ገደል ቢጣሉም፥ ቆዳቸው ተልጦ ጨው ቢጨመርባቸውም፥ አንገታቸው ተቀልቶ ቁልቁል ቢሰቀሉም ሞታቸው ብዙዎችን እየወለደ፥ ደማቸውም ለራሳቸውና ለብዙዎች ጥምቀት እየሆነ፥ እቺን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለኛ አስረክበዋል:: በእውነት ምስጋና ይገባቸዋል::
ምስጋና- በ9ኛው ክ/ዘ በዮዲት ጉዲት ጊዜ 40 ዓመት ሙሉ በየጫካው
ታቦታቱንና ንዋየ ቅድሳቱን ይዘው ለተሰደዱት አባቶች! ክብር- በ16ኛው ክ/ዘ በአሕመድ ግራኝ ጊዜ ማዕተባችንን አንበጥስም ላሉት ቅዱሳን! ውዳሴ- በ17ኛው ክ/ዘ በንጉስ ሱስንዮስ ለታወጀው ካቶሊካዊ አዋጅ አንቀበልም ብለው ለታረዱት 8000
ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን! ልዕልና- በዘመነ መሳፍንት ቅብዓትንና ጸጋን ተከራክረው በመርታት ተዋሕዶን ለመሰከሩ ሊቃውንት አባቶች! መወደድ- የዛሬዋን ቤ/ክ ለመጠበቅ በየገዳማቱ በጸሎት ለተጠመዱት አበው መነኮሳት፥ የጽድቅም አክሊል ቤ/ክንን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ መናፍቃንንና
ተሐድሶን ለሚቃወሙ መምህራን፥ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች! አምልኮና ስግደትም ይቺን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመሰረታት ለትንሳኤው ጌታ ለክርስቶስ ኢየሱስ
ይሁን!!
# ለዛቲ_ቤት_ሐነጻ_ወልድ_ወፈፀማ_መንፈስ_ቅዱስ !!
©Binyam ZeChristos ሰኔ 20 - 2010
@And_Haymanot
@And_Haymanot