ይህ ሳምንት ከሰርከ ሆሳዕና እስከ ትንሣኤ ያሉትን ቀናት ያካትታል
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
❖ የጌታን መከራ እንግልት መሰቀል መሞት መቀበር የምናስብበት ነው፤ ለእኛ ሲል የተቀበላቸውን 13ቱ ሕማማተ መስቀል በማሰብ በልቅሶ በስግደት በጸሎት ልናሳልፈው ይገባል
❖ በዚህ ሳምንት ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው፤ በመስቀል መባረክ ማማተብ መሳቅ መሳሳም ከሴት ጋር መገናኘት ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን የ5500ው የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ
❖ በዚህ ሳምንት ለሞተ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም፤ እግዚአብሔር ይፍታህ አይባልም ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው
❖ የግዝት በዓላት እንኳ ይሰገድባቸዋል፤ የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው፤ ምግቡም ቆሎ ዳቦ
የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው መጠጡም ንጹህ ውኃ ነው
❖ ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው፤ ጸሎቱ ውዳሴ ማርያም አንቀጸ ብርሃን መልክአ ሕማማት መዝሙረ ዳዊት ነው፤ የቅዱሳን መልክአ መልክእ ይጸለይም
❖ የጾሙ ሥርዓት ምን ይመስላል ካሉ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15
📌 ቁጥር 578
❖ በሊህ በስድስቱ ቀኖች (በሰሙነ ሕማማት) ከቂጣ ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፤ በሊህ ቀኖች ከወይን ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም
❖ ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፤ #የሚችል እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው ሰውየውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም
📌 ቁጥር 590
❖ ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፤ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ ስዑር በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር
📌 ቁጥር 593
❖ ከካህናት ወገን ማንም ቢሆን በአርባ ጾም
በዓርብና በረቡዕም ጾም ወይን መጠጣት አይገባውም ወደ መዋት (ውሽባ ቤት) አይግባ፤ በዐቢይ ጾም ወራት ሰው ከሚስቱ ጋር አይተኛ
📌 ቁጥር 597
❖ ሴቶችም ጌጣቸውን ይተው፤ ሁሉም ለእያንዳንዱ በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና የኃጢአታችን ሥርየት በእነርሱ ነውና
❖ ይኸውም ሥራ አንዱስ እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ
ሕግ የወጣ ነው
❖ ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን
ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፤ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ ?
📌 ቁጥር 599
❖ በተባሕትዎ በትሕትና አርባ ቀን ጾምን ይጹሙ፤ ከጥሉላት መከልከል ይገባል፤ አያግቡም
📌 ቁጥር 600
❖ በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት
መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም
❖ በእነዚህም ቀኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፤ በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጅ
📌 ቁጥር 601
❖ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)
❖ ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሐት ይፈታል፤ ከመሳለም በቀር ጸሎተ ዕጣንም ይጸለያል
❖ በዕለተ እሑድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ
ቀንም ማልቀስ አይገባም፤ ዳግመኛም በውስጧ በአርባ ጾም ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም
❖ መጋባት ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፤ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል
📌 የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ
፩. እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መባባል መሳሳም
፪. ሩካቤ ሥጋ ማድረግ
፫. መስቀል ማሳለም እና መሳለም
፬. ክርስትና ማስነሣት
፭. ለሙታን ፍትሐት ማድረግ
፮. ክህነት መስጠት
፯. የላመ የጣመ ምግብ መመገብ
፰. መሳቅ መጫዎት መጨፈር
፱. አብዝቶ ጠግቦ መመገብ
፲. መስከር ወዘተ ናቸው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን !!!
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
💚 @And_haymanot 💚
💛 @And_haymanot 💛
❤️ @And_haymanot ❤️

Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ሳልፆም ሊፈሰክ ነው
አይ የኔ ነገር !
እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ
ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ
መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ
ስዋሽ ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
ገላዬን_ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
አይ እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
ጌታ ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው
አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" 🙏
================
ከናንተው የተላከ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
አይ የኔ ነገር !
እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ
ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ
መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ
ስዋሽ ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
ገላዬን_ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
አይ እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
ጌታ ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው
አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" 🙏
================
ከናንተው የተላከ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
👍1
ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚባላ ንፍሮ ነው፡፡
የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር፤ አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ
እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበርና ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና
ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል፡፡
በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን
አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያም አብዛኛዎቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡
በዲ/ን ቤርዜሊ ተስፋዬ

+++ምን ሰጡህ ይሁዳ+++
ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ
ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ
ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ
ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ
ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ
ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ
ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
🔔 ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል
አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
🔔 ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
🔔 እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው
🔔 ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
🔔 ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው
🔔 ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው
🔔 አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ
መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
🔔 አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

ሁሉን የያዘውን ያዙት
ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት
በቁጣ ጎተቱት
በፍቅር ተከተላቸው
✥••┈┈┈••●◉✞◉●••┈┈┈••✥
መልካም የስቅለት በዓል ይሁንልህ/ሽ
_SHARE______
❤️ @And_haymanot ❤️
ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት
በቁጣ ጎተቱት
በፍቅር ተከተላቸው
✥••┈┈┈••●◉✞◉●••┈┈┈••✥
መልካም የስቅለት በዓል ይሁንልህ/ሽ
_SHARE______
❤️ @And_haymanot ❤️
ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም ። ሉቃ 24፥5
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም በጤና አደረሰን ።
****
@And_Haymanot
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም በጤና አደረሰን ።
****
@And_Haymanot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ለምን አንጾምም?
ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች?
ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም?
በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/።
"የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ
15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት
ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው።
በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ
እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም
ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም።

አደባባያችንን አትንኩ!
ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ። ብፁዕነታቸው ዛሬ ለአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላምና ደኅንነት፡ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ሙስሊም ወንድሞቻችን ከዚህ ቀደም አፍጥርን በስታዲየም ሲያከብሩ መቆየታቸው እየታወቀ ዛሬ
በመስቀል አደባባይ እንዲከበር መፍቀድ ተከባብሮ የኖረውን ክርስቲያኑን እና ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ወደ አላስፈላጊ ግጭት የሚገፋ ተግባር መሆኑን ፈቃድ ሰጭው አካል እንዲያጤነው አሳስበዋል። ሊቀ ጳጳሱ በደብዳቤያቸው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ ያላቸውን አክብሮት ገልጸው የአፍጥር ዝግጅቱም ሆነ ዒድ አልፈጥር በዓል ግን በተለመደው ስታዲዬም እንጂ በመስቀል
አደባባይ መከበር እንደሌለበት በአንክሮ አሳስበዋል።

፩ ሃይማኖት
Photo
ታፍኛለሁ!
#Ethiopia | የአረማውነት ሥራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት
ሞክሬ አልተሳካም! በምስጢር ተቀድቶ የወጣው የቪድዮ መልእክታቸው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ታፍኛለሁ አሉ።
«ስለ ትግራይ ስናገር ድምጼ ይታፍፈናል። በትግራይ ጭካኔ
የተሞላበት የአረመናዊነት ድርጊት እንዲቆም ብዙ ጊዜ ሞክሬ አልተሳካም። ሚያዝያ 7 ያደረኩት ኢንተርቪው ታግዷል። ስቃወም ድምጼ ይታፈናል። የአለም ሚዲያ እየተናገራው እኛ
እንዳንናገር ታፍነናል።» በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ብዙ ግፍ ተሠርቷል። በትግራይ ላይ የተደረገው ግን ይበልጣል በማለት ተናግረዋል።
ለዓለም መንግሥታት፣ ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት የተለየ የድጋፍ ጥያቄ ጠይቀዋል። "የአለም ሚዲያ እየተናገረው እኛ እንዳንናገር ታፍነላል"
"ባሁን ጊዜ በሀገራችን በኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው አረመኔያዊነት፣ የአረማውነት ስራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት ሞክሬ አልተሳካም ፤ ምክንያቱም ፍቃድ አልተሰጠም። እናገራለሁ ይመልሱታል፣ እናገራለሁ
ይመልሱታል፤ ይኸው እስካሁን ጊዜ ምንም አይነት ፍቃድ
አልተገኘም።
እናም ሁላችሁም ወገኖቻችን ማወቅ ያለባችሁ፣ እዚህ ያለውን ችግር፣ የኔን ችግር የማውቀው እኔ ነኝ።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ
ተክለሃይማኖት

✞ ግንቦት ፩ እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከኢያቄምና ከሐና ስትወለድ የሆነውን ነገር ሐዋርያው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊ መጽሐፍ ሲገልጽ፡፦
@And_Haymanot
"And Joachim(ኢያቄም) said: Now I know that the Lord has been gracious unto me, and has remitted all my sins . And he went down from the temple of the Lord justified,
and departed to his own house. And her months were fulfilled, and in the ninth month Anna(ሐና) brought forth. And she said to the midwife: What have I brought forth? And she said: A girl. And said Anna: My soul has been magnified this day. And she laid her down. And the days having been fulfilled, Anna was
purified, and gave the breast to the child, and called her name Mary." The Protoevangelium of James, 5
👉 @Konobyos
👉 @And_Haymanot

አስተካክለኝና ትክክል ልኹን
@And_Haymanot
“ተወዳጅ ሆይ! እግዚአብሔር አይሰማኝም አትበል፡፡ አንተ ተናገር
እንጂ ርሱ ይሰማኻል፤ ባትናገርም ያደምጥኻል፡፡ ኾኖም ርሱ አንተን ሲሰማኅ ችግሮችኅ ይስተካከላሉ፤ ርሱን ስትሰማው ደግሞ አንተ ትስተካከላለኅ፡፡
ያልተስተካከለን ችግር የተስተካከለ
ሰው ይሻገሯል፤ ያልተስተካከለ ሰው ግን የተስተካከለን ችግርም አይሻገርም፡፡ “እንዴት?” ብለኽ ከጠየቅከኝ ግን መልሴ
“አካሔድ የማያውቀውን የተነጠፈም ጐዳና ጠልፎ ይጥለዋል” የሚል ነው፡፡ ከችግሮች ኹሉ እኛ ችግሮች ስንኾን ቀኖች ይከብዳሉ፡፡ መሣሪያው ሲበላሽ ሥራው ይበላሻል፡፡ ስለዚኽ መሣሪያው ተሠርቶ ሥራው ይሠራል፡፡ አንተ ከተበላሸኽ የሚስተካከል ነገር የለም፡፡ አንተ ከተስተካከልክ ግን ሌላው
ቢበላሽ ራስኽን ታድናለኽ፡፡ “ከምንም ነገር አንድ ነገር” ይባላልና ይሔ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወዳጄ! እውነት
እውነት እልኻለኁ እመነኝ፤ አንተ ስትስተካከል ብቻኽን አትስተካከልም፡፡ በተስተካከለ የሚስተካከሉ፣ በዳነ የሚድኑ ብዙዎች ናቸውና፡፡ የአየር ንብረቱን ዐይቶ ልብስን ማስተካከል
ካለ የዘመንን መልክ ዐይቶ ልብን ማስተካከል ተገቢ ነው እልኻለኁ፡፡ ፀጉርን ለማስተካከል ከአስተካካዩ ጋር፣ የከበረ ልብስን ለማስተካከል ከአልባሹ ጋር፣ ዕውቀትን ለማስተካከል ከመምህሩ
ጋር፣ … ትገናኛለኅ፡፡
@And_Haymanot
ሕይወትን ለማስተካከል ግን ማንን አግኝተኅ ይኾን? አንተን ለሕይወት የሠራኅ እንጂ ሌላ ማንም አያስተካክልኽም፡፡ ሰው ኹሉ ከራስኅ በላይ የሚነፍስ ነፋስ ኾኖብኅ “ለእኔ እኔ - ከእኔ ወደ እኔ” ብለኅ ከራስኅ ጋር ቃል ኪዳን ተጋብተኽ አዲስ ኑሮ ዠምረኽ ነበር፡፡ ነገር ግን ለመስተካከል ዓቅም አጥተኽ የመስተካከልን በጐ ፈቃድ ብቻ
ይዘኅ ቀረኽ፡፡ ስንት ዘመን የራስኽ ጥበብ ስንፍና፣ የራስኽ ብርታት ድካም፣ የራስኽ ሙከራ መከራ እንደኾነብኅ ዐውቂያለኹ፡፡ ስለዚኽ ለፈጠረኽ ጌታ ራስኽን አሳልፈኅ ለመስጠት ወስን፡፡ በራስኽ ላይ እንደዚኽ ዓይነቱን ውሳኔ
እንደማስተላለፍ አስቸጋሪና እጅግ ውብ የኾነ ነገር በዚኽ ዓለም ላይ አታገኝም፡፡ ወደ ፈጠረኽ መምጣትኅ ዥማሬኅ ነው፤ ከርሱ ጋር ያለው ቈይታኅ ዕድገትኅ ነው፤ ርሱን አምነኅ እንደኖርኅ አምነኅ ስትሞትም ሕይወትኅ ነው፡፡ እውነት አንተስ ዕድለኛ ነኽ!!! እናም ምክሬን ስጠቀልልኅ፡- የእውነት ልመና “ጌታ ሆይ!
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን!” የሚል መኾኑን ደግሜ በማስታወስ ነው፡፡ “እንዳስተውል ርዳኝ፤ በሕይወትም አኑረኝ” / መዝ.118፡144/፡፡”
© ዲ/ን ቃለኣብ ካሣዬ

የእግዚአብሔርን ቅጣት ፈርቶ ንስሓ መግባትና የእግዚአብሔርን ቅድስና ፈልጎ ንስሐ መግባት ይለያያል።
☞ እውነተኛ ክርስቲያንም ንስሐ የሚገባው ገሃነመ እሳትን ፈርቶ
ሳይኾን የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም ስለሚናፍቅ ነው።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
☞ እውነተኛ ክርስቲያንም ንስሐ የሚገባው ገሃነመ እሳትን ፈርቶ
ሳይኾን የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም ስለሚናፍቅ ነው።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው ለሚለው ኑፋቄ የተሰጠ ምላሽ
📝 @And_Haymanot
ብዙ ጊዜ ፕሮቴስታንት ወገኖቻችን ይህንን ቃል ደጋግመው ሲያነሱ እና እውነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስመስለው ፌስ ቡክ ላይ ሲለቁት ተመልክታችሁ
ይሆናል፡፡ይህንንም የሚያደርጉበት ምክንያት ቤተክርስቲያንን ለመቃወም እና ምእመኑን ከእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ለማውጣት እና ለዲያብሎስ ለማስረከብ በማሰብ ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችን ዘወትር እግዚአብሔርን በልቧ በተግባርና በአምልኮ ስርአቷ ትቀድሰዋለች /
ታመሰግነዋለች/፡፡
✏️ ቅዳሴ ማለት “ቀደሰ አመሰገነ” ከሚለው የግዕዝ ቃል
የመጣ ሆኖ “ማመስገን፣ ማወደስ፣ ማገልገል” የሚል ትርጉም አለው፡፡ (ቅዳሴ ማለት ምስጋና ማለት ነው)፡፡ መናፍቃን ግን ለመተቸት ‹‹ክርስትና ማስቀደስ ሳይሆን መቀደስ ነው››እያሉ ሲፎክሩና ሲሸልሉ በሀይማኖት ያልበሰሉትንም ሲያደናግሩ እንመለከታለን መጽሐፍ ቅዱስ ስለቅዳሴ/ጌታን ስለመቀደስ ምን ይላል እስቲ እንመልከተው፡፡
@And_Haymanot
✍ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፥15 ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። ትንቢተ ኢሳይያስ 8፥13 ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን። የማቴዎስ ወንጌል
6፥10 ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
✍ ኦሪት ዘኍልቍ 20፥12 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና
ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው።
✍የሉቃስ ወንጌል 11፥2 አላቸውም። ስትጸልዩ እንዲህ በሉ። በሰማያትየምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ ታዲያ ቤተክርስቲያን ምን አጠፋች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባገኘችው ቃል ነው ቅዳሴ የምትቀድሰው/ ጌታን የምታመሰግነው።
ጌታ ለመናፍቃኑ ልቦና ይስጣቸው
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሼር ማድረግዎን አይርሱ

መልካምነት
አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል ያደርጉለታልም፡፡ አንድ ቀን አባቱ "ልጄ ጓደኞች አሉህ" አሉት "አዎ ሶስት ጓደኞች አሉኝ በጣም የሚወዱኝ የምወዳቸው" አላቸው፡፡ እርሳቸውም "ከእነዚህ ውሰጥ የልብ ጓደኛህ ማነው?" አሉት "ሁሉም" አለ "እርግጠኛ ነህ ልጄ" ሲሉት "አዎ" አለ፡፡ "እንደዚያ ከሆነ የሆነ ነገር እንፍጠርና እውነተኛ መሆናቸውን እናረጋግጥ" ይሉታና ጓደኞቹን እንዲፈትን ያደርጉታ፡፡ ልጁም አባቱ ባለው መሰረት ለአንዱ ጓደኛው ይደውልና "ያለጥፋቴ ሰው ገድለሃል ተብዪ ፍርድ ቤት ነኝ ድርሰልኝ" ይለዋል ጓደኛውም "አዝናለሁ አልችልም" ይለዋል፡፡ አሁንም ለሁለተኛው ይደውላል ሁለተኛ ጓደኛውም "ችግር የለውም እመጣለው እርዳታየም ካሰፈለገህ የምችለውን ሁሉ አደርግልሀለው ፍርድ ቤት ግን አብሬህ አልገባም አዝናለው" ይለዋል አሁንም ለሶሰተኛው ይደውላል ሶሰተኛውም "እንዴ ኧረ ችግር የለውም ደሞ ለአንተ አይደለም ፍርድ ቤት ሌላም ቦታ እመጣልሃለሁ" አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ በአባቱ ምክር እውነተኛ የህይወት ጓደኛው ማን እንደሆነ አረጋገጠ ።
ፍርድ ቤት የተባለው የሰው ልጅ ይችን ዓለም ተሰናብቶ የሚኖርባት የዘላለም ቤቱ ሲሆን
1-የመጀመሪያው አልችልም ያለው ገንዘብ ነው መቸም የሰው ልጅ በዚች ምድር ሲኖር ምን ያህል ሀብት ቢኖረው ከሞት አያሰጥለውም በሞት ጊዜ ተከትሎን አይመጣም ።
2-ሁለተኛው ፍርድ ቤቱ አመጣለው እረዳሃለሁ እንጅ አልገባም ያለው ዘመድ ወይም ጓደኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰው ምን ያህል ቢወድህ ያለቅሳል ያዝናል ወደ ቀብር ቦታህ አብሮህ ይመጣል እንጅ መቸም አንተ ሞተሀልና ልሙት አይልም።
3- ሶሰተኛው እሰከ መጨረሻው አንተ ጋ ነኝ ያለው በዚች አለም ሰትኖር የሰራናቸው ጥሩና መልካም ሰራዎች ናቸው፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምንሰራቸው ጥሩ ሰራወች የዘላለም ሰንቃችን ናቸው እስከ መጨረሻው ከአኛ ጋር ይከተሉናል፡፡
ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና።
✟🍀🌸 🌸🍀✟
💐 @And_Haymanot 💐
🌺🍂 @And_Haymanot 🍂🌺
💐 @And_Haymanot 💐
🍂🏜💒🏜🍂

ቅዱሳን ሥዕላት
✍ የተሃድሶ መናፍቃን ቅዱሳን ሥዕላትን አይቀበሉም፤ በሥዕል ፊትም አይጸልዩም፤ ጭራሽም ሥዕልን ማክበር ጣዖትን እንደ ማምለክ ይቆጥሩታል እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ቅዱሳት መጽሐፍትን መሠረት አድርገን ለቅዱሳት ሥዕላት ተገቢውን ክብር እንሰጣለን።
✞ በዘፀ 20፥3 ላይ የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸውም፣ አታምልካቸውም የሚለውን ትእዛዝ የሰጠው እግዚአብሔር አምላክ በዘፀ 25፥16 ላይ "ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ስራ" ብሎ ሙሴን አዝዟል ይህም ቅዱሳት ሥዕላት ቁጥራቸው ከጣዖት እንዳልሆነ የሚያመለክት ነው እግዚአብሔር አምላካችን የሰው ልጅን ጣዖት እንዲሰራ አያዝምና ከዚህም በተጨማሪ እስራኤል በኃጢአታቸው ምክንያት በእባብ መንጋ ሲነደፉ በዘኁ 21፥8 ላይ "እባብ ሰርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፣ የተነደፈውንም ሁሉ ሲያየው በሕይወት ይኖራል" ሲል አዝዞት ነበረ ነገር ግን ይህ እንደ ጣዖት አምልኮ አልተቆጠረም እንዲያውም በዘኁ 21፥9 ላይ "እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ" ተብሎ ተጽፏል ጌታችንም በዮሐ 3፥14 ላይ ሙሴ በምድረ በዳ የሰቀለው እባብ የእርሱ መሰቀል ምሳሌ መሆኑን አስተምሯል።
✞ ንጉሡ ሰሎሞንም የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ በሠራ ጊዜ በ1ኛ ነገ 6፥23 ላይ እንደምናነበው በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆኑ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ በዚህ የተነሳ እግዚአብሔር መምለኬ ጣዖት ነህ አላለውም እንዲያውም በሌሊት ተገለጠለት እንጂ ንጉሥ ሰሎሞንም የኪሩቤልን ሥዕል ብቻ ሳይሆን "የዘንባባ ዛፍ፣ የፈነዳም አበባ ምስል ቀርጾ" ነበር /1ኛ ነገ 6፥29-35/ ነገር ግን ይህ እንኳን የጣዖት ምስል አስቀረፀ አላስባለውም።
✍ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳት ሥዕላት ክብርና የአክብሮት ስግደት ይገባቸዋል እንላለን እንጂ አናመልካቸውም የአምልኮ መፈጸሚያዎች ናቸው እንላለን እንጂ የአምልኮ ስግደት አንሰግድላቸውም፤ ሥዕሎቹ በራሳቸው አንዳች ምስጢራዊ ኃይል ኖሯቸው ሳይሆን የሥዕሉ ባለቤት በሥዕሎቹ አማካኝነት ኃይሉን፣ ተአምሩን ይገልጣል ብለን ግን እናምናለን ሙሴ በበትሩ ባሕረ ኤርትራን ከፍሏል፣ ኤልሳዕ በኤልያስ ልብስ ዮርዳኖስን ከፍሎ ተሻግሯል፣ የቅዱስ ጳውሎስ ልብስ ድውያንን ፈውሷል፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ አጋንንትን አውጥቷል... እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን በራሳቸው አንዳች ኃይል ኖሯቸው ሳይሆን የባለቤቱን ቅድስና ያስገኘላቸው ጸጋ ነው።
✍ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስተምረን እመቤታችን ጌታን እንደታቀፈች አድርጎ የመጀመሪያውን ሥዕል የሳለው ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው ይህም ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ሥዕላት በቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ቦታ ያመለክተናል ከዚህም በላይ በኢየሩሳሌም፣ በባዛንታይን፣ በኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በሌሎችም ሀገሮች የጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሾች በቁፋሮ ሲገኝ ቅዱሳን ሥዕላትም ይገኛሉ ይህም ሥዕሎችን ለመንፈሳዊ አገልግሎት መጠቀም ከጥንት ክርስቲያኖች ጀምሮ የነበረ መሆኑን ያሳያል።
❖ በ7ኛው መ/ክ/ዘ ቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ አሁን የተሃድሶ መናፍቃን የያዙትን ሃሳብ ይዘው የተነሱ ሰዎች ነበሩ እነዚያኞቹ ከዚያም አልፈው ቅዱሳት መጻሕፍትን ከምድረ ገጽ ለማጥፋትም ተነስተው ነበር እነዚህ ጸላዕያነ ሥዕላት "ኢኮኖማኺያ" በመባል ይታወቁ ነበር ትርጉሙም "ሥዕላትን የሚጠሉ" ማለት ነው ይህ አስተሳሰብ በ720 ዓ/ም አካባቢ ተነስቶ እስከ 843 ዓ/ም ድረስ ለአንድ መቶ አመታት ያህል ቤተ ክርስቲያንን ሲያወዛግብ ቆየ፤ ጉዳዩ የበለጠ እንዲሰፋ ያደሰገው ደግሞ ሥዕሉን ከባለ ሥዕሉ በላይ የሚያከብሩና የሚያመልኩ ክርስቲያኖቼ/ኢኮኖላትሪያ/ መፈጠራቸው ነው።
✍ በዘመኑ የነበሩት ነገስታት የሥዕል አጥፊዎችን ሀሳብ በመደገፋቸው ለ700 ዓመታት የተሰበሰቡ አያሌ ጥንታውያን ሥዕሎች እንዲጠፉ ተደረገ ሁኔታው ግን ሊበርድ አልቻለም ሥዕሎች አማልክት አይደሉም፣ ነገር ግን ሊከበሩ ይገባቸዋል የሚለው ሃሳብ እያየለ መጣ በዚህም ምክንያት ችግሩ በተነሳበት በባዛንታይንና ሮሜ አካባቢ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በ787 ዓ/ም ጉባዔ አድርገው "ለቅዱሳት ሥዕላት ክብር እና ሰላምታ ይገባል፤ ለእነርሱ የሚደረግ ክብር እና ሰላምታ ሁሉ ለሥዕሉ ባለቤት የሚደረግ ነው እነርሱን የሚያከብር ሁሉ በሥዕሉ ላይ የተገለጠውን ነገር ማክበሩ ነው" በሚል ወሰኑ።
✍ ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን የአባቶቻችንን ስርአት ተከትላ ለቅዱሳት ሥዕላት ክብርና የአክብሮት ስግደት ትሰጣለች እንጂ የተሃድሶ መናፍቃኑ በሀሰት እንደሚሉት የጣዖት አምልኮ አይደለም ስለዚህ ከተሃድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርት መጠንቀቅና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለማንኛውም ጥያቄ ምላሽ ያላት መሆኑን ልናውቅ ይገባል።
አምላከ ቅዱሳን የቅዱሳን ሥዕላትን ረድኤት በረከት ያሳትፈን!!! አሜን።