፩ ሃይማኖት
8.99K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ጅማ ዩኒቨርሲቲ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ቅሬታቸውን ልከውልናል በተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ቢያቀርቡም ምላሽ ሰጪ አካል ባለመኖሩ በሶሻል ሚዲያ የሚሰማን ካለ በማለት ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል የሚመለከተው አካል ቢረዳቸው በማለት ልናቀርበው ወደናል
1ኛ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ቅዱስ የሆነው የጾም ወቅት ጾመን እንዳለፍን አይዘነጋም ሆኖም ግን ያሳለፍነውን የጾም ወቅት ተማሪዎች እንዳንጾም ተከልክለናል። በሳምንት ውስጥ ለ4 ቀን የምናቀርበውን ስጋ ብሉ አለዚያ ጦማችሁን እደሩ እየተባለ ነው ኮስትሼሪንግ በሚል የምንከፍለው እንዳለ ነው፣ እሱ አይደለም አሁን ላይ ያለው የተማሪ ጥያቄ ይሄ በሃይማኖት ጸንቶ የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ነው እስካሁን ድረስ ተማሪው ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እጅግ ቡዙ ነው፤ ሌላው ቀርቶ ጅማ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ #ነጠላ ማድረግ የትምህርት ሂደቱን ያውካል በማለት ትከሻ ላይ ሲደረግ እንኳን "አውልቁ እና በእጅ ያዙ" ነው ምንባለው እባካችሁ የእስካሁኑ ይበቃናል ቢያንስ ይሄን እውነት ለህዝበ ክርስቲያኑ አድርሱልን፣ አሁን አንደኛ ዓመት አዳዲስ ተማሪዎች ይመጣሉ እንደሚታወቀው ከፊታችን በፍቅር የምንናፍቃት ጾመ ፍልሰታ እየተቃረበች ነው ያኔስ እንዴት ነው ሚኮነው? እኔ አላውቅም አደራ አደራ አደራ ድምጽ የለንም እና ድምጽ ሁኑን ...
--------
ተወዳጆች ባላችሁበት የሚመለከተው አካል እንዲረዳቸው እየተማጸንን ሌሎቻችሁም በጸሎት እንድታስቧቸው ለማሳሰብ እንወዳለን የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
+ ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን?
+ ሰውነታች በበደል ለረከሰ ፣ በምኞት መቃብር ለተቀበርን ፣ በዝሙት ለተበላሸን ፣ በጥላቻ ለሸተትን ለእኛ ክርስቶስ ምንኛ ያለቅስ ይሆን?
+ የኃጢአት ድንጋይ ተጭኖን ፣ የፍትወት መግነዝ ተጠምጥሞብን ላለን ለእኛ የጌታ ዕንባ ምን ያህል ይፈስስልን ይሆን?
+ አልዓዛርስ ውጣ ቢባል ይወጣል ፣ ካለንበት ኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ
ይሆን?
+ የእኛ ሞት ከአልዓዛር ሞት በላይ ዘልቆ
የማይሰማው ይመስላችኋል?
+ እንዴት
አይሰማውም? ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰው ጌታ
ለእኛ እኮ ያፈሰሰው ደሙን ነው ። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ጅማ ዩኒቨርሲቲ

ተወዳጆች በቅርቡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚካሄደውን የእምነት ነጻነትን ማጣት እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊያኑ ላይ የሚደርሰውን በደል ማቅረባችን አይዘነጋም በውስጥ እያደረሳችሁን ያለውን ተመልክተናል
👉 መምህራኑን በእምነታቸው ከስራቸው ማፈናቀል
👉 ተማሪዎችን በጾም በነጠላ በትምህርታቸው ከሚሰሩት ፕሮጀክቶች አንስቶ ሌሎች በደሎችም እየደረሰባቸው መሆኑን በውስጥ እያደረሱን ነው
👉
👉 ስራ ላይ ላላችሁ መምህራን ክርስቲያናዊ ሃላፊነታኣችሁን እንድትወጡ ስንል በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን
👉
በተጨማሪም የሚመለከተው የቤተክርስቲያናችን አካል ይበልጥ ቢመለከተው ለማለት እንወዳለን🙏
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።

1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።

ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።

የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።

ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
በፈተና ጊዜ፥ ደካማው ሰው "እንደዚህ የደረሰብኝ'ኮ" እያለ የሚያመካኝበት ሌላ ሰውን ይፈልጋል፤ ብርቱው ሰው ግን በፈተናው ይጸና ዘንድ እግዚአብሔርን ይፈልጋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት:
ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ

@And_Haymanot

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡

ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)
@And_Haymanot
ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡

ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)

አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ "የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ አይሹትም ፣ አይደረግምም" የሚለውን በመጥቀስ የሐዲስ ኪዳነ ታቦትን ይቃወማሉ። ቃሉ የተነገረው ለእስራኤል ቤት ሲሆን እስራኤላውያን በእርግጥም የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይሹትም። በኦሪት ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃልኪዳን በአዲስ ኪዳን ተተክቷል። ይህ ከሐዲስ ኪዳን መሠዊያ ጋር የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ "አዎ እስራኤል አይሹትም" ብለን እንመልሳለን።
የአሁኑ ታቦት የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109)

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ.
1
2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያ

ከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡

የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡
@And_Haymanot
የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡

ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.

It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡
@And_Haymanot
‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) http://www.stmarkdc.org/coptic-sanctuary ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡

ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡
@And_Haymanot
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!
@And_Haymanot

....ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 10 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሃይማኖት አይወረስም? 🤔
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
👇👇👇👇👇👇
ሐይማኖት አይወረስም?

@And_Haymanot

ተወዳጆች የተሃድሶ መናፍቃን ሃይማኖት አያስፈልግም፤አያድንም፤አይወረስም በማለት ብዙዎችን ለማደናገር ይሞክራሉ ከዚህ በፊት በስፋት የዳሰስነው ርዕሳችን ቢሆንም በውስጥ ለጠየቀን ወንድማችን እነሆ ብለናል

ሐይማኖት አይወረስም ላልከን እንዲህ የምናምነውንም እንመሠክራለን! > እንግዲያውስ ከኃይማኖት በላይ ሊያወርሱት እና ሊወርሱት የተገባ የከበረ ነገር በዚች አለም የለም። ሰው መልካም መልካሙን ነገር ለልጆቹ ያወርሳል ከመልካም ስጦታዎች ሁሉ የሚልቀውን የዘላለም ሕይወት የሚገኝበትን ሐይማኖት ከማውረስ የበለጠ ታላቅ ውርስ እንዳውም በጭራሽ አይገኝም።

ሰው በምድር ላይ ለልጆቹ የሚሆን ታላቅ መኖሪያ ቢያወርስ ነገር ግን የዘላለም ሕይወት የሚያገኙበትን ሐይማኖቱን ግን ባያወርስ ምን ይረባቸዋል! ??
ሁለት ነገርን አደፈረስክ! መጀመሪያ ሐይማኖት ሊወረስ የተፈቀደ መሆኑን ካድክ ሲቀጥል ደግሞ በገዛ ድምዳሜክ ገባህና ሐዋርያት ከሀድያን ናቸው አልክ! እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።
አስቀድመህ በራስህ አላዋቂነት የደመደምከው ድምዳሜ ላይ የተመረጡትን ሁሉ አጋጭተሀል።
በመሰረቱ ሀይማኖት ለሰው ልጆች የተሰጠችው ልንጠብቃት እና ለትውልድም ልናወርሳት ነው።
አብርሃም አባታችን ለአይሁድም ሆነ ለሀዲስ ኪዳን ህዝቦች አባት ነው። ከህግ ለሆኑት የመገረዝ አባት ነበረ። ከእምነት ለሆንነው ደግሞ የእምነት አባት ነው። የፃድቅ አብርሃም
ሕይወት ለእኛ ምሳሌ ነው። አብርሃም እግዚአብሔር ን አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት ነገር ግን ይህ ብቻ አልነበረም ጉዳዩ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም ትዛዝን ሲሰጠው ልጆችህ ቃል ኪዳኔን እንዲጠብቁ አድርግ በሚል ጠንካራ
ማሰሪያም ጭምር ነው። አብርሃምም በቤቱ ለተወለዱት ልጆች ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ገና በተወለዱ በ8 ቀናቸው ጀምሮ ይፈፅምላቸው ነበር። የእርሱን ሐይማኖት ለልጆቹ ገና በስምንት ቀን ጨቅላነታቸው እያሉ ጀምሮ እንዲቀበሉ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ ነው። ልጆችም በአባቶቻቸው
ሐይማኖት ተወስነው እንዲኖሩ ነው የጌታ ትእዛዝ። ስለዚህ ሐይማኖት ይወረሳል። ከሐይማኖት የበለጠ ለልጅ ሊያወርሱት የሚገባ መተኪያ የሌለው ውድ ነገርስ ከየት ይገኛል???
ዘፍጥረት 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥
#ለአንተና_ከአንተ_በኋላ_ለዘርህ_አምላክ_እሆን_ዘንድ
⁸ በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ለዘላለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ አምላክም እሆናቸዋለሁ።
⁹ እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፥ አንተ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው።
¹⁰ በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
¹¹ የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ
መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
¹² #የስምንት_ቀን_ልጅ_ይገረዝ ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።
¹³ በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
¹⁴ የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ፥ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።//

ሮሜ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ
አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው።
¹³ የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው
የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም።
¹⁴ ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል
የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤
¹⁵ ሕጉ መቅሠፍትን ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።
¹⁶-¹⁷ ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ
ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት #የሁላችን #አባት #ነው
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
🙏🙏🙏ነገረ ማርያም 🙏🙏🙏

@And_Haymanot
ተከታተሉን
ጾሙን ዲያቢሎስን ድል መንሻ ያድርግልን
@And_Haymanot_bot
ሃገራችንንም ሰላም ያድርግልን
1
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ

@And_Haymanot

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን 
ተጽናናሁኝ እረሳሁ ሀዘኔን 
የአምላክ እናት እመቤታችን 
ሞገስ ሆኝኝ ቀሪው ዘመኔን 



የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ 
አንቺን ተጠግቼ የዓለምዋን ቤዛ 
የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት 
ባርያሽን ሰውረኝ ከአስጨናቂ ሞት 
እናቴ ስምሽን ስጠራ 
አለፈ ያሁሉ መከራ 
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ 
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ 
ሰላም ለኪ 

ልቤ በአንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ 
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ 
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል 
የኃያላንን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል 
እናቴ ስምሽን ስጠራ 
አለፈ ያሁሉ መከራ 
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ 
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ 
ሰላም ለኪ 

ደጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ 
በመርገም ምክአቸው ሊለያዩኝ ሲሹ 
እሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው 
እመቤቴ አለችኝ ብላ አሳፈርኳቸው 
እናቴ ስምሽን ስጠራ 
አለፈ ያሁሉ መከራ 
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ 
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ 
ሰላም ለኪ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
👍1
"አንቺ ከወደድሽኝ ልጅሽ አይጠላኝም"

🙏 አባ ጊዮርጊስን በወደደው ፍቅርሽ
🙏 አባ ኤፍሬምን በወደደው ፍቅርሽ
🙏አባ ሕርያቆስን በወደደው ፍቅርሽ
🙏አባ ሳሙኤልን በወደደው ፍቅርሽ
ብትወጅኝ ያን ጊዜ ልጅሽም ይወደኛል፡፡
አንቺ ጸሎቴን ስሚኝ እንጂ ልጅሽ ይሰማኛል ምንም እንኳን የፍቅርሽ ፍሙ ባይገባኝም ነበልባሉ; ባሕሩ ባይገባኝ እፍኙ በልቤ ላይ ቢወርድ ምንኛ በከበርኩ ... አንቺ አለሁልህ በይኝ እንጂ ልጅሽ ከደረትሽ ላይ ነው፡፡

የእኔን ነገር ንገሪው እንጂ እኔ በእቅፉ ላይ ነኝ፡፡ ሁልጊዜም ስዕልሽን ሳየው አቅፈሽውም ስመለከት ከአባይና ከጣና ከጠሩት ዓይኖችሽ ከሐርና ከጥጥ በለሰለሱ እጆሽ አቅፈሽው ሳይ እኔ ደግሞ በልጅሽ እቅፍ ተወዳጅ ልጁ በተባልኩ
እላለሁ፡፡
ዓይኖችሽ እርሱን ሲያዩ እርሱ ደግሞ እኔን ባየኝ እጆችሽ እርሱን ሲያቅፉ እርሱ ደግሞ እኔን ባቀፈኝ ክንዶችሽ እርሱን ሲያቅፉ እኔን ደግሞ የጠፋውን ልጄን አገኘሁት ብሎ ልጅሽ ባቀፈኝ፡፡
እናም....... አንቺ ውደጅኝ እንጂ ልጅሽ አይጠላኝም፡፡ምክንያቱም ልጅሽ ከፍጡር
እንዳንቺ የሚሰማው የለም፡፡እንዳንቺም ክርስቶስን የሚያውቀው የለም፡፡

*እንደ አብና መንፈስ ቅዱስ ወልድን የሚያውቀው የለም ምክንያቱም ዕውቀታቸው አንዲት ናት፡፡
*ከፍጡራን ደግሞ እንዳንቺ ወልድ ክርስቶስን የሚያውቀው የለም
*ከእመቤታችን በቀር ከፍጡራን ክርስቶስን “ልጄ” የሚለው የምትልና የማለትም ጸጋ የተሰጣት እመቤታችን ብቻ ናት ወደ ለምጻሙ ስምዖን ቤት ከመግባ አስቀድሞ የገባው ወደእመቤታችን ማሕጸን ነው፤በስምዖን አረጋዊም እጆች ከመታቀፉ አስቀድሞ በእመቤታችን ክንዶች ታቅፏል ስለዚህ ይህ ክብሯ በአምላክ ዘንድ ለምልጃ የቀረበ አደረጋት፡፡ጻድቃን ቅዱሳን መላእክት ክርስቶስን “አምላካችን ፈጣያችን ጌታችን” ይሉታል እመቤታችን ደግሞ ከዚህ በላይ ልጄ
የማለት ጸጋ ተሰቷታል ስለዚህ በዚህ ከመላእክት ትበልጣለች፡፡
ዛሬ እኛ “አባታችን ሆይ” ለምንለው አምላክ እመቤታችን “እናቱ” ናት ስለዚህ “ክርስቶስ
አባቴ” ያለ ሰው እመቤታችንን እናትነት ካልተቀበለ “አባቴ” ላለው ክርስቶስ እናቱ እንደሆነች ይወቀው፡፡ምክንያቱም ጌታ እመቤታችንን የሚያውቃት ጻድቃንን ካወቀበት ካከበረበት ጸጋ በላይ ነው ፤ልጅሽ 33ት ዓመት በዚህ ምድር ላይ ሲቆይ 30ውን ዓመት የኖረው ካንቺ ጋር ነው አስቀድሞ የሳሙት ያንቺ ከንፈሮች ናቸው አስቀድመው ያዘሉት ያንቺ እጆች ናቸው
እርሱ እንደ ልጅ ሲያድግ አንቺ እንደ እናት አሳደግሽው ገላዎቹን ያጠቡ የሳሙ ያንቺ አካላት ናቸው ፍጹምም ትሳሽለት ነበር፡፡ በልጅሽ ላይ ያለሽ ፍቅር ጥልቅ ነው አንቺንም ሳይሽ የኢትዮጵያ እናቶች ትዝ ይሉኛል እነዚህ እናቶች ስምሽንም እየጠሩ ባንቺ ተስለዋል፡፡ ልጆቻቸውም በእናት ፍቅር ይነድዱና ከጉያቸው አይጠፉም ፡፡
*እናም እናቴ እኔም ባንቺ ፍቅር ልንደድና ከጉያሽ አልጥፋ ፡ 🙏 ያንቺ ጉያ ጌታን የያዘ ጉያ ነው፡፡
እሳትም የተንተራሰበት ጉያ ነው... ያንጊዜ ቀና ብዬ በተኮላተፈ አንደበት የነገርኩሽን ለልጅሽ ንገሪው ምክንያቱም አንቺ ከወደድሽኝ ልጅሽ አይጠላኝም፡፡
አንቺ ካየሽኝ ልጅሽ አይተወኝም ብቻ አንቺ ውደጅኝ የሀገሬስ ሰው ሲተርት
"ከእናቱ ሆድ ውስጥ የዋለ እንቁላል አይሰበርም " አይደል.... እኔም ተሰብሬ የቀረሁት ያኔ ካንቺ ዕቅፍ በተለየሁ ጊዜ ነው ያኔ ቤትሽን ጥዬ በወጣሁ ጊዜ ያኔ በስምሽ ባፈርኩኝ ጊዜ ነው፡፡
* እናም ወደ እቅፍሽ መልሽኝና ያጣሁትን ያንቺና የልጅሽን መልክ ያጣሁትን ያንቺና የልጅሽን ፍቅር ሳይብኝኝኝ !!! "

"አንቺ ውደጅኝ እንጂ ልጅሽ አይጠላኝም"
© ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
​​ጾመ ፍልሰታ


ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገው ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት ኦርቶዶክሳዊያን የሚጾሙት ጾም ነው።

ፍልሰታ የግዕዝ ቃል ሆኖ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል።
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለሆነ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን 48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች።
ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት ወደ መኖሪያ ቤቷ (የዮሐንስ ቤት) መጥተው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች አስከሬኗን ገንዘውና ከፍነው ወስደው
ለመቅበር ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንም ማድረግ
የፈለጉት የሐዋርያት ትምህርት የጌታችን ከሞት መነሣትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ
እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። የፈሩት ይነግሣል የጠሉት ይወርሳል እንዲሉ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት
አይቀሬ ሆኗል።

አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፊኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ
ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነትና ክብር ለመመስከር በቅቷል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር ይቀመጥ እንጂ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር
ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ዮሐንስ ስለሥጋዋ ነግሯቸዋል።
ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ለስድስት ወራት ከአሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህ በኋላም ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው
ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን
አምጥቶ ስለሰጣቸው ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።

ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት
አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ ፪፥፲/።
እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ /ሕንድ/ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ
ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በስተቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት
እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን /የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።
ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ
ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት
አስረዱት። እርሱ ግን ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን
ለማሳመን መቃብሯን ለማሳየት ወሰዱት ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት
የነበረውን ጨርቅ/ የራሱን ድርሻ አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው ዛሬም ካህናቱ ከእጅ መስቀላቸው ጋር መሐረብ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ
ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት
በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለሁለተኛ ጊዜ ለሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ
ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

በአጠቃላይ የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ሐዋርያት ያገኙትን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በዶ/ር ሙሉጌታ ማርቆስ
@And\
Haymanot
@And_Haymanot_bot
ከፍጥረታት ሁሉ አምላክን ልጄ ብላ መጥራት የምትችል ብቸኛዋ ድንግል ማርያም ናት

ታድያ ማንም ቢሆን የሷን ክብር የሷን እናትነት አይታደልም

❤️የምናከብራት እና የምንወዳትም ቀድማ በአምላክ ስለተወደችና ስለተመረጠች ነው።

🙏ክብር አምላክን ለወለደችልን ለመዳናችን ምክንያት ለሆነች ልድንግል ማርያም ይሁን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ደብረ ታቦር👆👆

ስንክሳር። በዓለ ደብረ ታቦርን ስንማርም ሆነ ስናስተምር ምሥጢር ጠንቅቀን መሆን
አለበት። ሰላም ለታቦር መለኮተ ወልድ ዲቤሁ ዘአንበልበለ። አምሳለ ደመና መንፈስ ቅዱስ ጸለለ። እምሰማይ አብ ዘወሀበ ቃለ።
ወበእንተዝ ገጻት ሥላሴ ነአምን አካለ።
በአፈ ሊቃውንት መምህራን በከመ ተብህለ።
በዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ማርያም እና የመናፍቃን ተደጋጋሚ ጥያቄዎቻቸው


"ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ "1 ጴጥ 3:16

@And_Haymanot
👉 ጥያቄ 1
ከዚህም በኋላ እርሱም ፀሐየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ እየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም በግዜ ሞቷ ከመከራ ወደ ዕረፍት ከኀዘን ወደ ትፍሥሕት ትሔጂ ዘንድ ዘንድ ሙቺ አላት እርሷም እግዝእትነ ማርያም "ልጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ አንተን ወልጄ የአንተ እናት ሆኜ እኔ እንዴት ልሙት? " አለችው በሚለው አነጋገር ውስጥ የጌታ ከተባለው ንግግር ይልቅ የማርያም የተባለው ምላሽ በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃት የጌታ እናት ማርያም ምላሽ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ጌታ ተናገረ ለተባለው እርሷ በሰጠችው ምላሽ ይህን ኃላፊና ጠፊ ዓለም ከወዲያኛው ዘለአለማዊ ዓለም አስበልጣለች። ይህ ደግሞ የጌታ የሆኑ ሰዎች የማይመኙት ነው። ቅዱሳን የሚመጣውን ዓለም የሚናፍቁ እንጂ በዚህ ላይ ተስፋቸውን የሚጥሉ አይደሉም ሐዋርያው ጳውሎስ በዚህ አለም እያገለገለ ልሄድ ከክርስቶስ ጋር መኖር እናፍቃለው ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና እንዲል
👉 መልስ
እመቤታችን ሞትን መፍረቷ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል ጳውሎስ እንኳን ልሔድ እሻለው ብሏል የሚለው ጥያቄ ፈገግ ቢያሰኝም የድንግል ማርያምን ጠባይ ከሌሎች ሕይወት አንጻር justify ማድረግ መጀመሩ ግን በጣም ጥሩ ነው ጳውሎስ ሞትን ስላልፈራ እርሷም አትፈራም ያሉ ሰዎች ጳውሎስ እስጀሦስተኛ ሰማይመነጠቁን እያወቁ እርሷ አረገች ሲባል እደእብድ ሲያደርጋቸው ይታያል ።
ወደጉዳዪ ስንመጣ ሞትን መፍራትዋ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል የቅዱሳን ጠባይ አይደለም ላሉት !!
ከመሞቱ በፊት ስለፈራው የሞትን ጽዋ ከእኔ ውሰድልኝ ብሎ ስለተጨነቀው ጌታ ልናስታውሳቸው እንወዳለን ሉቃ 22:42 "በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደደም ነጠብጣብ ነበር "ሉቃ 22:44
"ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው "ሉቃ 22:43 የሚለውን ቃልስ ምን ሊሉት ነው? ክብር ይግባውና ጌታችን ሞትን የፈራው ከቅዱሳኑ አንሶ ነውን?? ኃላፊ ጠፊ የሆነውን አለም ከዘላለማዊ ሕይወት አስበልጦ ነውን ? በአጭሩ አይደለም። ለምን እንደፈራ እራሱ ተናግሯል " ስጋ ደካማ ነው"
ማቴ 26:41 ጌታ የፈራው በአምላክነቱ ሳይሆን በለበሰው ስጋ ነው። ሰው ሆኖ ሞትን መፍራት ከመንፈሳዊ ሕይወት ጉድለት ሳይሆን ከተፈጥሮ ነው።መለኮት የተዋሐደውን ሥጋ ለብሶ ከፈራ መለኮትነት የሌላት ድንግል ማርያም ብትፈራ ምን ያስደንቃል ።ጳውሎስስ " እናፍቃለው " አለ እንጂ አልፈራም አላለም የሞትን ፍርሃት አሸንፎ ሰማዕት ሆነጂ ፈርቷል " ብዙ ግዜ በመንገድ ሄድሁ በወንዝ ፍርሃት በወንበዴዎች ፍርሃት በወገኔ በኩል ፍርሃት በአሕዛብ በኩል ፍርሃት በከተማ ፍርሃት በምድረ በዳ ፍርሃት በባሕር ፍርሃት በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ "2 ቆሮ 11:26 "እኔም በድካምና በፍርሃት በመንቀጥቀጥም በእናተ ዘንድ ነበርሁ "1 ቂሮ 2:3 "በቅጥሩም ባለ መስኮት በቅርጫት አወረዱኝና ከእጁ አመለጥኩ "2 ቆሮ 11:33 በቅርጫት ያመለጠው አለም በልጦበት ነበርን?? አይደለም ።ስለዚህ ሞትን መፍራት የተፈጥሮ የማይለመድ ነገርም ነው
@And_Haymanot
👍21
ማርያም እና የመናፍቃን ተደጋጋሚ ጥያቄዎቻቸው

👉 ጥያቄ 2
ክርስቶስ ከሙታንመካከል ሲነሳና እንዲሁም ሲያርግ መግነዙን እዛው መቃብር ነበር የተወው ማርያም ግን ስታርግ መግነዟን ይዛ ነበር ለምንድነው?? ለቶማስ ልትሰጠው ነወ ከሚለው ሌላ የተሻለ መልስ አላችሁ
👉 መልስ
እመቤታችን ለቶማስ ልትሰጠው ሳይሆን መታጠቅያዋ ስለሆነ ነው ከነ መታጠቅያዋ ስለተነጠቀች ነው (Ascention በራስ ወደላይ መውጣት ሲሆን Assumption መወሰድ መነጠቅ ነው ።)
ለቶማስ መሥጠቷ ደግሞ የቅዱሳን ልማድ ነው ኤልያስ ሲያርግ መጎናፀፍያውን ትቶለት ሄዷል ለኤልሳ በዚህም መጎናፀፍያ ባሕር ከፍሎበታል ።2 ነገ 2:12
የእርሷ ልብስ ምን ያደርጋል? ቢሉ ከላይ እነሱ በሰጡን ፎርሙላ ተጠቅመን " እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎችም መናፍስት ይወጡ ነበር ።" ሐዋ 19: 22 ። ይህን ያሰነበበ የእመቤታችን ልብስ ምን እንደሚያደርግ አየይጠፋውም።ጌታ መግነዙን የተወው ትንሣኤውን የማያምኑ ሰዎች አውሬ በላው ሌባ ሰረቀው ብለው ያሶሩትን ወሬ ከንቱ ለማድረግ ነው አውሬ መግነዝ ፈቶ አይበላም ሌባም ውድ በፍታ ትቶ ሥጋ ብቻ አይሰርቅም በዚህ ጉዳይ የዲያቆን ኅብረት የሺጥላን "መግነዙን ትቶ ለምን ተነሣ? " የሚል ትምህርት google አድርጎ መመልከት ይቻላል ይህ መግነዝዋ ነው carbon dating አርኪዮሎጂስቶችም ለሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዘመኑን አረጋግጠው የምስክር ወረቀት ሰጥተዋታል።
@And_Haymanot
ማርያም እና የመናፍቃን ተደጋጋሚ ጥያቄዎቻቸው

"ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ "1 ጴጥ 3:16

@And_Haymanot

👉 ጥያቄ 3
ነገረ ማርያም ላይ ነፍሳት እንዲድኑ አንቺ ሙቺ ሲላት እንኳን አንዴ ሰባት ጊዜም ቢሆን ልሙት አለችው በምልጃዋ ሲገርመን እንዴት በሞቷ ልታድን ትችላለች??
👉 መልስ
ሰባት ጊዜ ልሙት ማለቷ በምልጃዋ እንጂ በሞቷ ታድናለች ? ለሚለው ሞትዋን የምልጃእጅ መንሻ አድርጋ ነው ያማለደችው እኛ እንዲህ ካደረክልን ብለን የምንሳለው ስእለት አይነትይህ ደግሞ የቅዱሳን ልማድ ነው " አሁን ይህን ኃጥያታቸው ይቅር በላቸው ያለዚያ ግን ከጻፍከው መፅሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ "ዘፀ 32:32 እመቤታችን ከተቀስናቸው ቅዱሳን ሁሉ ብትበልጥ እንጂ አታንስምና አምነን እንቀበላለን!!
©ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

👉 @And_Haymanot 👈
👉 @And_Haymanot_bot 👈
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
❖ "ለሚያምን(ለማመን) ይኼ የሚጸን(የሚከብድ) ነገር አይደለም/ To believe this is no doubtful matter/." [ዕርገተ ማርያም(Assumption of Mary)].
@Konobyos
@And_Haymanot
በዲ/ን ቴዎድሮስ

የተሐድሶ መናፍቃን የፍልሰታ ጾምን በእጅጉ ይተቹታል:: በቅርቡ ትዛታው ሳሙኤልን ዕርገተ ማርያምን ሲነቅፍም ሲሰማ በውኑ ዝም ካልን ስለ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተገቢው ያልተረዱትን አባግኣ ክርስቶስ(የክርስቶስ በጎች) ክርስቲያኖችን እንዳያስት ጥቂት ማለቱ አስፈልጓል። የተሐድሶ መናፍቃን ሐዋርያዊ ውርርስ የሌለው እንግዳ ትምህርት እንደሆነም ይናገራሉ:: ሲያልፍም እመቤታችን አርጋለች ማለት ስሕተትም ነው ይሉና፤ ይህንንም ያስተማረው በ 16ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ነው ይላሉ:: ያው አርሲሳን(መናፍቃን) ማሰብ የሚችሉትንና የሚያቁትን ብቻ እንጂ የእምነትና የእውቀት ባሕር ውስጥ መዋኘት ስለማይወዱም ስለማይችሉም ዘመናቸው ባለማወቅ በድንዙዝነት ይገፉታል:: ለመሆኑ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት (Assumption of Mary) ትምህርት በኢትዮጵያ ሊቃውንት ብቻ የታወቀ ነው? የድንግል ማርያምን ዕርገትን በስፋት የሚያትተው ጥንታዊ መጽሐፍ በ (C.400) የተጻፈው ዕርገተ ማርያም(Assumption of Mary(c.400) የተባለ መጽሐፍ ነው:: መጽሐፉ የሚጀምረው የነባቤ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ስለ ክብርት ወላዲተ አምላክ ዕረፍት የሰጠውን ምስክርነት(The Account of St. John the Theologian of the Falling Asleep of the Holy Mother of God). በማስረዳት ይጀምራል:: ተወዳጆች ሆይ! ይኼ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ሊቃውንት የጻፉት መጽሐፍ አለመሆኑና የተሐድሶ መናፍቃን እንደሚሉት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሳይሆን የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ እናት አባቱ፤ አያት ቅድመ አያት ሳይታሰቡ የተጻፈ ደገኛ ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ፍልሰት(ዕርገት) በስፋት የሚያትት በልሳነ አፍርንጅ(በእንግሊዘኛ) ልሳን የተጻፈ ጥንታዊ መጽሐፍ ነው:: [መቼስ እኛ በግዕዝ ከተጻፈው በእንግሊዘኛ የተጻፈ ፈረንጅ ያረጋገጠውን መቀበል እንደሚቀናን ይታወቃል! የልሳን ቀላዋጭ ከሆንን ከረምን!!] ዳግመኛም ይኼ ዕርገተ ማርያም(Assumption of Mary) የተባለው መጽሐፍ ፍልሰታ ለማርያም(The Passing of Mary) ብሎ በሁለት የላቲን ቅጅዎችን ማለትም First Latin Form & Second Latin Form በማለት ፍልሰታዋን ያትታል:: በቀዳማዊው የላቲን ገለጻ(First Latin Form) የሚጀምረው ስለ ብፅዕት ድንግል ማርያም ፍልሰት ነገር(Concerning the Passing of the Blessed Virgin Mary) በማለት ይጀምርና; ሐዋርያው ቶማስ እመቤታችን ስታርፍ እሱ በሕንድ እንደነበረና እመቤታችንም ባረፈች በሦስተኛ ቀን ስታርግ እሱም በደመና ተጭኖ ሲመጣ እንዳገኛትና ባርካው ሰበኗን እንደሰጠችው ይገልጻል:: እንዲህ በማለት Then the blessed Thomas told them how he was singing mass in India - he still had on his sacerdotal robes. He, not knowing the word of God, had been brought to the Mount of Oliver, and saw the most holy body of the blessed Mary going up into heaven, and prayed her to give him a blessing. She heard his prayer, and threw him her girdle which she had about her. ለሚያምን ይኼ የሚከብድ ነገር አይደለምም(To believe this is no doubtful matter) ይላል:: በመጨረሻም የእመቤታችን ዕርገት በዓለሙ ሁሉ እንደሚከበርም ይገልጻል(And her, whose assumption is at this day venerated and worshipped throughout the whole world). ሁለተኛው የላቲኑ ቅጂ(Second Latin Form) ደግሞ Here Begins the Passing of the Blessed Virgin Mary ብሎ ይጀምርና ክፉዎች አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋዋን እናቃጥለው እንዳሉም ይናገራል(Jews saying, let us burn her body with fire). በመጨረሻም ቅዱሳን ሐዋርያት ሱባዔ ይዘው እመቤታችንም እንደተገለጽላቸው እነርሱም ሐሴት እንዳደረጉ(The apostles then, having entered the house, found Mary, and saluted her, saying: Blessed are you by the Lord, who has made heaven & earth) ና ይህን ሁሉ ያደረገ ልዑል እግዚአብሔርንም እንዳመሰገኑ በመግለጽ ጽሑፉን ያሳርጋል(And the apostles being taken up in the clouds, returned each into the place allotted for his preaching, telling the great things of God, and praising our Lord Jesus Christ, who lives and reigns with the Father and the Holy Spirit, in perfect unity, and in one substance of Godhed, for ever and ever. Amen. [Ante- Nicene Fathers, Vol.8; Assumption of Mary (C. 400)]. ታዲያ የእመቤታችን ፍልሰት(ዕርገት) ልብ ወለድ ፈጠራ ነውን? የኢትዮጵያ ሊቃውንትስ ከዚህ የተለየ ምን አስተማሩን? ወይስ እያንዳንዷ የቤተ ክርስቲያናችን አስተምሕሮ በአፍርንጅ(በእንግሊዘኛ) የተጻፈ ማስረጃ የግድ ያስፈልግ ይሆን? ጾመ ፍልሰታ ወደ ጽድቅ ሕይወት የምንፈልስበትን ፍልሰተ ልቡና ያድርግልን፤ አሜን::
@Konobyos
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@Konobyos