፩ ሃይማኖት
8.99K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ይህ ሳምንት ከሰርከ ሆሳዕና እስከ ትንሣኤ ያሉትን ቀናት ያካትታል
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

❖ የጌታን መከራ እንግልት መሰቀል መሞት መቀበር የምናስብበት ነው፤ ለእኛ ሲል የተቀበላቸውን 13ቱ ሕማማተ መስቀል በማሰብ በልቅሶ በስግደት በጸሎት ልናሳልፈው ይገባል

❖ በዚህ ሳምንት ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው፤ በመስቀል መባረክ ማማተብ መሳቅ መሳሳም ከሴት ጋር መገናኘት ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን የ5500ው የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ

❖ በዚህ ሳምንት ለሞተ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም፤ እግዚአብሔር ይፍታህ አይባልም ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው

❖ የግዝት በዓላት እንኳ ይሰገድባቸዋል፤ የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው፤ ምግቡም ቆሎ ዳቦ
የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው መጠጡም ንጹህ ውኃ ነው

❖ ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው፤ ጸሎቱ ውዳሴ ማርያም አንቀጸ ብርሃን መልክአ ሕማማት መዝሙረ ዳዊት ነው፤ የቅዱሳን መልክአ መልክእ ይጸለይም

❖ የጾሙ ሥርዓት ምን ይመስላል ካሉ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15

📌 ቁጥር 578

❖ በሊህ በስድስቱ ቀኖች (በሰሙነ ሕማማት) ከቂጣ ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፤ በሊህ ቀኖች ከወይን ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም

❖ ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፤ #የሚችል እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው ሰውየውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም

📌 ቁጥር 590

❖ ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፤ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ ስዑር በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር

📌 ቁጥር 593

❖ ከካህናት ወገን ማንም ቢሆን በአርባ ጾም
በዓርብና በረቡዕም ጾም ወይን መጠጣት አይገባውም ወደ መዋት (ውሽባ ቤት) አይግባ፤ በዐቢይ ጾም ወራት ሰው ከሚስቱ ጋር አይተኛ

📌 ቁጥር 597

❖ ሴቶችም ጌጣቸውን ይተው፤ ሁሉም ለእያንዳንዱ በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና የኃጢአታችን ሥርየት በእነርሱ ነውና

❖ ይኸውም ሥራ አንዱስ እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ
ሕግ የወጣ ነው

❖ ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን
ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፤ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ ?

📌 ቁጥር 599

❖ በተባሕትዎ በትሕትና አርባ ቀን ጾምን ይጹሙ፤ ከጥሉላት መከልከል ይገባል፤ አያግቡም

📌 ቁጥር 600

❖ በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት
መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም

❖ በእነዚህም ቀኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፤ በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጅ

📌 ቁጥር 601

❖ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)

❖ ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሐት ይፈታል፤ ከመሳለም በቀር ጸሎተ ዕጣንም ይጸለያል

❖ በዕለተ እሑድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ
ቀንም ማልቀስ አይገባም፤ ዳግመኛም በውስጧ በአርባ ጾም ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም

❖ መጋባት ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፤ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል

📌 የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ

፩. እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መባባል መሳሳም
፪. ሩካቤ ሥጋ ማድረግ
፫. መስቀል ማሳለም እና መሳለም
፬. ክርስትና ማስነሣት
፭. ለሙታን ፍትሐት ማድረግ
፮. ክህነት መስጠት
፯. የላመ የጣመ ምግብ መመገብ
፰. መሳቅ መጫዎት መጨፈር
፱. አብዝቶ ጠግቦ መመገብ
፲. መስከር ወዘተ ናቸው።


               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን !!!
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

💚 @And_haymanot 💚
💛 @And_haymanot 💛
❤️ @And_haymanot ❤️