፩ ሃይማኖት
9K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ታቦተ ጽዮን

@And_Haymanot

✞ የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነው 2ኛ ዜና 8፥11 ✞


መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ጥንታውያን መዛግብት እንደሚሉት የቃል ኪዳኑ ታቦት በሚንቀለቀል ብርሃኑና እሳቱ በነቀርሳማ እባጭና በለምጽ የመምታት፣ የማቃጠል፣ ተራሮችን ወደሜዳማነት የመለወጥ፣ ወንዞችን የማድረቅ፣ ታላላቅ ሠራዊቶችን የመደምሰስ፣ ከተማዎችን የማፈራረስ ኃይል አለው።


እነዚህ ምንጮች አክለውም ታቦተ ህጉ የአይሁዶች የእምነት መሰረት እንደሆነና ንጉሥ ሰሎሞንም የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ያሰራው ይህንኑ ታቦት በክብር ለማኖር አስቦ እንደሆነ ይገልጻሉ ይሁንና ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአንድ ሺህና ስድስት መቶ አመታት መካከል በነበረው ጊዜ ይህ እጅግ ድንቅና ተአምራዊ ታቦት የትና ወዴት እንደሄደ ሳይታወቅ በመሰወሩ ጉዳዩ ለብዙ ሺህ ዓመታት እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቷል ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት በ587 ዓመተ ዓለም የናቡከደነጾር ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ባቃጠላት ጊዜ ታቦቱ በቦታው አልነበረም በጦርነቱ የተማረኩ እስራኤላውያን ከባቢሎን ወደሀገራቸው ኢየሩሳሌም በ538 ዓመተ ዓለም ተመልሰው ሁለተኛውን ቤተ መቅደስም በሠሩበት ወቅትም ታቦቱ በዚያ አልነበረም ይህም ቀደም ሲል ታቦቱ በባቢሎናውያን አለመዘረፉን ያረጋግጣል።

የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ኤሊየት ፍሬድማን በ1987 ይህን ጉዳይ አስመልክተው ሲጽፉ "የታቦቱ መጥፋት ከመጽሐፍ ቅዱስ አስደናቂ ምሥጢሮች እንደ አንዱ ይቆጠራል" ብለዋል።

❖ "ታቦቱ ወደሌላ ቦታ ስለመወሰዱ፣ ስለመውደሙ (መቃጠሉ) ወይም መደበቁ የተጻፈ ነገር የለም ከዚህ በኃላ ታቦቱ ጠፋ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለም አናውቅም ወይም የት እንዳለ ማንም አያውቅም የሚሉ አስተያየቶች እንኳን አልተጻፉም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዓለም ካሉ ነገሮች ሁሉ ትልቅ ሥፍራ የተሰጠው ክቡር ዕቃ፣ እንደዋዛ ይጠፋል"። [ ግራሃም ሐንኩክ፦ "The sign and the Seal" ወይም "ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ" ገጽ 4 ትርጉም፦በጌታቸው ተስፋዬ ጎጂ]

#የታቦተ_ጽዮን_መኖሪያ_ኢትዮጵያ


ታቦተ ጽዮንን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ይዞ የመጣው ልዑል ምኒልክ ይባላል ምኒልክ ማለት "የብልህ ሰው ልጅ" ማለት ነው እናቱ ንግስተ ሳባ የጠቢቡ ሰሎሞንን ጥበብ ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም በሄደችበት ወቅት ኢየሩሳሌም ውስጥ ከጠቢቡ ሰሎሞን ብትፀንሰውም ማርገዟን እንዳወቀች ወደሀገሯ ተመልሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የወለደችው ሃያ ዓመቱ ሲሞላ ምኒልክ ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ ከአባቱ ቤተ መንግስት እንደደረሰም የክብር አቀባበል ተደረገለት ይሁንና ለአንድ አመት ያህል ከቆየ በኃላ የእስራኤል ታላላቅ ሰዎች ንጉሱ ሰሎሞን ምኒልክን ከእኛ የበለጠ ያቀርበዋል፣ ይወደዋል በሚል በምቀኝነት ተነሳሱበት ወደሀገሩ ይመለስ ዘንድም አጥብቀው ጠየቁ ንጉሱ ሰሎሞንም የቀረበለትን አቤቱታ ካዳመጠ በኃላ ምኒልክ ወደሀገሩ የሚመለሰው የእስራኤል ታላላቅ ሰዎች የበኩር ልጆች ሁሉ በአጃቢነት አብረውት ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ከሆነ ብቻ መሆኑን ገለጸላቸው።

❖ በዚህም ተስማሙ ከነዚህም መካከል ከምኒልክ ጋር አብረውት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት መካከል የሊቀ ካህናቱ ሳዶቅ የበኩር ልጅ አዛርያስም ይገኝበታል የቃል ኪዳኑን ታቦት ከቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ደብቆ ያወጣውም እርሱ ነበር ምኒልክ ታቦቱ በድብቅ ወጥቶ ከእርሱ ጋር መምጣቱን ያወቀው ከኢየሩሳሌም ብዙ ርቆ ከተጓዘ በኃላ ነበር ስለሁኔታውም እንደነገሩት ድርጊቱ የተፈጸመው በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ተገንዝቦ ታቦተ ህጉ ከእነርሱ ጋር መሆን እንዳለበት አምኖ ተቀበለ በዚህ ሁኔታ ነበር ታቦተ ህጉ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው።

በአጠቃላይ ስለ ታቦተ ጽዮን አስር ዓመታት የፈጀ ምርምርና ጥናት በማድረግ የሚታወቀው ግራሃም ሐንኩክ የተባለ እንግሊዛዊ ጸሐፊ "The sign and the Seal" ወይም "ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ" በሚለው መጽሐፉ ገጽ 245 ላይ የታቦተ ጽዮን መኖሪያ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን አክሱም ጽዮን ቤተ መቅደስ ሆኖ ሲመሰክር፦ "...ከሲና ተራራ ግርጌ በወርቅ የተሰራው፥ በበረሃ የተጓዘውና የዮርዳኖስን ወንዝ የተሻገረው፥ ወደ ተስፊዪቱ ምድር ለመግባት እስራኤላውያን ያደረጉትን ትግል በድል ያጠናቀቀላቸው፥ በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግስት ወደ እስራኤል የተወሰደው፥ በ955 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ አካባቢ በንጉሥ ሰሎሞን በተሰራው ቤተ መቅደስ ተቀምጦ የነበረው ይህ የቃል ኪዳን ታቦት ነው..." በማለት ነበር የደመደመው።

☞ ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱት የዘመን አቆጣጠር በሙሉ እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነው።

✞ የእናታችን የአክሱም ጽዮን ረድኤት፣ በረከትንና ምልጃ አይለየን!!!! አሜን!!! ✞

ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
ከወቅታዊ መረጃ ጋር
የሚቀርቡበት፡፡
°ለተሃድሶዎች መልስ የሚሰጥበት°
👉"፩ ሃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እውነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፣ እውነተኛ ትህትናስ ትሩፋት መስራት ነው፡፡
🍃ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🍃
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ
ኢየሱስ_ከአዳም_ዘር_ዉጪ_ነዉ_የተወለደዉ!_ለፓስተር_ዳዊት_ድፍረትና_ስህተት_የተሰጠ_ምላሽ_@And_Haymanot.mkv
55.9 MB
"ኢየሱስ ከአዳም ዘር ዉጪ ነዉ የተወለደዉ!" ለፓስተር ዳዊት ድፍረትና ስህተት የተሰጠ ምላሽ
@And_Haymanot
ውርጃ


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምሮ

@And_Haymanot

ምድሪቱ (የሴቲቱ ማኅፀን) ዘር ከዘራንባት በኃላ ፍሬ እንዳታፈራ የምናደርገው ስለ ምንድን ነው? ውርጃን የምናካሒደው ስለ ምንድን ነው? እናንተ ዘማውያን ሆይ! ዝሙት መፈጸማችሁ ሳይበቃ ሰውን መግደል ትጨምሩበታላችሁን? እንግዲህ ስካር እንደ ምን ሴተኛ አዳሪን እንደሚያደርግ፣ ሴተኛ አዳሪነትም ዘማዊ፣ ዝሙትም እንደ ምን ነፍሰ ገዳይ እንደሚያደርግ ታስተውላላችሁን?

ይህን ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ምክንያቱም ይህን ሕፃን ከተወለደ በኃላ ከቤት አስወጥተን አይደለም ያባረርነው፤ እንዳይወለድ ከለከልነው እንጂ ወዮ! ስለምን የእግዚአብሔርን ስጦታ ታቃልላላችሁ? ስለምን ሕጉን ትተላለፋላችሁ? ስለምን ርጉም የሆነን ግብር እንደ በረከት ትቆጥሩታላችሁ? ስለምን እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያዘጋጀውን መንገድ መግደያ ታደርጉታላችሁ? ስለምን ልጅን አቅፋ እንድትስም የተፈጠረችውን ሴት ነፍሰ ገዳይ እንድትሆን ታደርጓታላችሁ? እህቴ ሆይ! ፍቅረ ንዋይ ዐይንሽን አሳውሮት፣ ዳግመኛም በፍትወት ከሚመስሉሽ ጋር ዝሙትን ለመሥራት ስትዪ ፍምን በራስሽ ላይ አታከማቺ ወንድሜ ሆይ! ምንም እንኳን ይህን አሰቃቂ ግድያ የምትፈጽመው እርሷ ብትሆንም አንተም ከእርሷ ጋር ተባባሪ ነህ። ✞

ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችው በገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገፅ 53
@And_Haymanot
@And_Haymanot
#ወዳጄ ሆይ!!!


የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

@And_Haynanot

🔔 አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#ይህ ጽሑፍ ለሌሎች እህት ወንድሞቻችን እንዲደርስ👉 Share ያድርጉ...

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haynanot
@And_Haynanot
@And_Haynanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
በብሉይ ኪዳን የመጀመሪያዋ የሴት ዘማርያት ምሳሌ ናት
Anonymous Quiz
17%
ሀ, ሣራ
21%
ለ, ራሄል
15%
ሐ, ማርያም እህተ አልአዛር
47%
መ, ማርያም እህተ ሙሴ
የቅዱስ ያሬድ የዜማ አይነቶች ስንት ናቸው
Anonymous Quiz
5%
ሀ, 1
3%
ለ, 2
60%
ሐ, 3
33%
መ, 4
+ ኢየሱስ ሆይ ከሀገራችን ሒድልን +


ሰዎች ኢየሱስን በብዙ ምክንያት ለምነውታል:: "ማረኝ" "ዓይኔን አብራልኝ" "ልጄን ፈውስልኝ" "ሙት አስነሣልኝ" ብለው የጮኹ ብዙዎች ናቸው:: የጌርጌሴኖን ሰዎች ግን ጌታን በአንድ ላይ ተሰብስበው "ከሀገራቸው እንዲሔድላቸው ለመኑት" ማቴ. 8:34
"ኢየሱስ ሆይ ውጣልን ! : ኢየሱስ ሆይ ሒድልን : ኢየሱስ ሆይ አትድረስብን : ኢየሱስ ሆይ አትምጣብን ! " የሚል ድምፅ እያሰሙ ተረባረቡበት::
ውጣልን ያሰኛቸው ሁለት ጋኔን የያዛቸውን ሰዎች ከላያቸው አጋንንቱን አውጥቶ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡ በፈቀደ ጊዜ አጋንንቱ አሳማዎቹን ወደ ገደል እንዲገቡ ስላደረጉ ነበር:: ጌታችን አጋንንቱ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡና ገደልም እንዲሰዱአቸው በመተዉ ትልቅ መልእክትን ለሰው ልጅ አስተላልፎ ነበር:: አጋንንቱ ወደ አሳማው ከመሔዳቸው በፊት ሁለት ሰዎች ላይ
ነበሩ:: እነዚያን ሰዎች ላይ ቢቆዩም ግን ሰዎቹን ወደ ገደል አልከተቱአቸውም:: ልክ አሳማዎቹ ላይ እንደሰፈሩ ግን ወደ ገደል ጨመሩአቸው:: ክርስቶስ በዚህ ያስረዳን "እኔ በቸርነቴ ባልከለክለው ሰይጣን በእያንዳንዳችሁ ላይ ያለው ዕቅድ በቅጽበት ወደ ገደል እስከ መጨመር የጨከነ ነው" የሚል
ነው:: ሰዎቹን ገደል እንዳይሰድ የከለከለው እሱ ነበር:: ዛሬም
እኛን ከአፋፉ ላይ ሆነን ወደ ገደል ያልወረድነው "ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው" በተጨማሪም ሰይጣንም እንኳን በሰው ልጅ ላይ ቀርቶ በአሳማ ላይ እንኳን እንደፈለገ የመስፈር ሥልጣን እንደሌለውም በዚህ ታሪክ ተረዳን::
የጌርጌሴኖን ሰዎች ግማሾቹ ጌታችንን ስለኃይሉ በትሕትና ፈርተውት ግማሾቹ ደግሞ በአሳማዎቹ መሞት ተበሳጭተው
ክርስቶስን ውጣልን አሉት:: ክርስቶስ የሰው ልጅ ከሚሰቃይ ጊዜያዊው ንብረት ቢጠፋ ይሻላል ብሎ ቅድሚያ ሲሠጥ ሰዎቹ ደግሞ ንብረታችን ከሚወድም ሁለቱ ሰዎች ጋኔን ቢጫወትባቸው
እንመርጣለን ብለው ውጣልን አሉት::
አሣማ ቆሻሻ እንስሳ ነው:: በግእዝ ሕሱም ሐሳማ ማለት አስቀያሚ ማለት ነው:: ቆሻሻ ወዳዱ ሰይጣን ወደ ማደሪያው ገብቶ ሕዝቡንም በጌታ ላይ አሳመፀ:: ሕዝቡም ኢየሱስ ሆይ
ሒድልን አሉት:: ጌታ ሆይ ከእኛ ጋር እደር ጌታ ሆይ ቶሎ ና ተብሎ ለሚዘመርለት
ጌታ ሒድልንን አዜሙለት:: አፍ አውጥተን አንበለው እንጂ እኛም ጌታችንን ብዙ ጊዜ "ሒድልን" ብለነው እናውቃለን:: ወዳጄ አንተስ “ክርስትና በአፍንጫዬ ይውጣ" ብለህ አታውቅም? ያም ባይሆን መንፈሳዊ ነገር ማሰብ ወይም መዝሙር መስማት የማትፈልግበት ቀን ወይም ቃሉን ማዳመጥ የምትሸሽበት ቀን የለም? ዛሬስ ይቅርብኝ ብለህ ከልብህ ሀገር
ኢየሱስን እንዲሔድልህ የለመንክበት ቀን : በቂም በቀል ልብህ ቆስሎ አኩርፈህ የይቅር ባዩን ጌታ ስሙን መስማት የጠላህበት ዕለት የለም?
ነጋዴው ከንግዱ ላይ ኢየሱስ ዘወር ቢልለት አይጠላም:: ኢየሱስ ከመጣ ገደል የሚጨምራቸው ብዙ ቆሻሻ ሥራዎች ያሉበት ሰው ጌታን ከሥራው ቦታ ዞር በልልኝ ይለዋል:: ሌብነት ማሟረት ጥንቆላ ዝሙት ሙስና የሚባሉ አሳማዎችን ገደል እንዳይገቡ ለመንከባከብ ስንል የናዝሬቱን መድኃኒት ዘወር በልልን ብለን የተማጸንን ብዙዎች ነን:: እንደፈለግን ለመኖር ከቆሸሸ አሳማ ጋር ለመዋል መርጠን በሀገራችን ላይ አጋንንት ሲጨፍሩ ሳያስከፋን የጌታችንን
መምጣት ግን ያልፈለግን ብዙዎች ነን:: ከእኛ መካከል እንደ አሳማ የከፋ ልማዱ እና ሱሱ ወደ ጥልቅ እንዳይወረወርበት
ፈርቶ የሚሸሽ ስንት አለ? የጌታችንን ቃል ለመስማት የማንፈልግ መንፈሳዊ ነገር ስንሰማ ጆሮአችንን የምንደፍን "ሒድልን
እባክህ" ብለን የምንለምን ስንቶች ነን::
ጌታ ሆይ ክፋትን መርጠን ከሀገራችን ሒድልን ከቀዬያችን ውጣልን ስላልንህ አትቀየመን:: በሽተኛ ሲነጫነጭ ክፉ
የሚያናግረው በሽታው ነው እንደሚባለው ክፉ የሚያናግረን
ኃጢአታችን ነውና አትቀየመን:: የኃጢአት ፍቅር እንደ አሣማ ፍቅር ከባድ ነው:: ሽታው ቢከረፋም እኛ ግን ለምደነዋልና
በቀላሉ መላቀቅ አቅቶናል:: አንተ ግን ሒድልን ብንልህም አትስማን:: አሳማ ኃጢአታችንን ከሚፈትኑን አጋንንት ጋር ወደ ጥልቁ ጣልልን:: ያን ጊዜ ነቢዩ
የተናገረው ቃል ይፈጸማል:-
"ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል" ሚክ 7:19
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 20 2013 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
#Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
እምነትህን በሥራ አሳይ

@And_Haymanot

ያዕ 2፥14-26

14 ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?

15 ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥

16 ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?

17 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።

18 ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።

19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።

20 አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?

21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

22 እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?

23 መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።

24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።

25 እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?

26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
ሀይማኖት ለቅዱሳን ፈጽማ የተሰጠችው ስንት ጊዜ ነው?
Anonymous Quiz
10%
ሀ/ በየጊዜው
77%
ለ/ አንድ ጊዜ
6%
ሐ/ ሶስት ጊዜ
7%
መ/ሁሉም
በምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል አድህኖ ከእመቤታችን በስተግራ የሚሳለው የማን ሥዕለ አድህኖ ነው
Anonymous Quiz
11%
ሀ, ቅዱስ ፋኑኤል
62%
ለ,ቅዱስ ገብርኤል
20%
ሐ, ቅዱስ ሚካኤል
8%
መ, ቅዱስ ሩፋኤል
✞በኢያሪኮ መንገድ✞

በኢያሪኮ መንገድ ጌታ እንተ ስታልፍ
ግፍያ ሆኖ ሳለ ስደነቃቀፍ
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ተማጸነኩኝ
ዓይኔንም ፈወስከኝ ዛሬ ማየት ቻልኩኝ

አንተን እንዳላይህ ቁመቴ አጠረብኝ
ከፊትህ እየሮጥኩኝ እዛፍ ላይ ወጣሁኝ
ጌታ ሆይ ጠራኸኝ ዘኬዎስ ሆይ አልከኝ
በቤቴ ልትገባ ፈቃድህ ሆነልኝ(፪)

ሐሴትም ሆነልኝ በጣምም ደስ አለኝ
አንተን በእንግድነት በቤቴ ተቀበልኩኝ
ኃጢአቴን ሁል በአንተ ፊት ጥያለሁ
ሐብቴን እከፍል ዘንድ እንዲገባ አውቃለሁ
ሐብቴን እሰጥህ ዘንድ እንዲገባ አውቃለሁ

የክፋትን ገንዘብ መሰብሰብን ትቼ
አንተን ልከተልህ ሁሉን ረስቼ
ኑሮዬንም ባርከው የሕይወት ዘመኔን
መርጫለሁ አንተን በቤትህ መኖሬን
መርጫለሁ አንተን በቤትህ ማደጌን

ዘማሪ
ቀሲስ ወንድወሰን በቀለ
ሉቃ፲፱፥፩-፲
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@And_Haymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
፩ ሃይማኖት የሁላችን ቻናል

እንደተለመደው በቅርቡ ጠንከር ባሉ ርእሶች ለመመለስ በዝግጅት ላይ ነው ከጎናችን በጸሎት እና በሃሳብ ላላችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነውና አሁንም ቀጥሉበት ለማለት እንወዳለን @And_Haymanot_bot ላይ
ሃሳባችሁን አድርሱ ቦቱ ላይ መፈሳዊ ጥያቄ የምጠይቁን ከብዛት አንጻር ነውና በዚህ አጋጣሚ ታገሱን ለማለት እንወዳለን

ኦርቶዶክስ መልስ አላት።
@And_Haymaot
ስለ ንጉሥ ቴዎድሮስ መምጣት

የመጀመርያው ክፍል

ጥንተ ነገሩ "ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም
መጨረሻው ይመጣል።" ማቴ.24፥14 የሚለው ገጸ ንባብ ሲኾን የመንግሥት ወንጌል ማለት ጌትነቱን የምትናገር ወንጌል በ፬ቱ ማዕዘን ትነገራለች። በእስላም ቤት ስንኳ ሳይቀር ትገኛለች
የሚል አንድምታ አለው። ትርጓሜውም ይኼን በታሪክ ሲያትተው፦ በሀገራችን ቴዎድሮስ በሀገራቸው ዮሐንስ የሚባል ይነግሣል፤ የእኛም ሂዶ ያም መጥቶ በእስክንድርያ ሦስት ቀን ይዋጋሉ።
አራቱ ሊቃነ ጳጳሳት የክርስቲያን ደም ለምን ይፈሳል? መሥዋዕት ሰውተን በመሥዋዕቱ ምልክት የታየለት ሃይማኖት ይጽና ይሏቸዋል። ኹሉም በያሉበት መሥዋዕት ያቀርባሉ። የእስክንድርያ
ሊቀ ጳጳሳት በሰዋው "አነ ውእቱ ክርስቶስ - እኔ ክርስቶስ ነኝ።" ብሎ በርግብ አምሳል ወርዶ ይመሰክራል። ከዚህ በኋላ በሃይማኖት አንድ ይኾናሉ፤ በግቢ ይገናኛሉ። እንደዚህ የሚል ከምን አለ ቢሉ ከገድለ ፊቅጦር ከራእየ ሲኖዳ።" [የማቴዎስ
ወንጌል 24፥14 አንድምታ]

➻ ይኽ ኾኖ ሳለ "ቴዎድሮስ" የሚለውን ስምም ለኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊያስተዋውቁ የሚሞክሩ አሉ። በቅዱሳት መጻሕፍት ከብዙ ጥቂቱን እንምዘዝ፦ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ ጻድቅ ባሕታዊ አባ
ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን ዘርዐ ያዕቆብ በድርሰቱ ሲመስለው ቴዎድሮስ ደግሞ በሕይወት መስሎታል። "ወበአሐቲ መዋዕል ተስዕሎ አሐዱ መስፍን ዘስሙ ቴዎድሮስ ዘይሰመይ ካዕበ ሊቀ ሐራ በእንተ ሃይማኖት ርትዕት ወደረሰ ሎቱ መጽሐፍ ዘይሰመይ ፍካሬ ሃይማኖት።" [ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ] እንዲል።

➾ ዐጼ ቴዎድሮስ አባ ጊዮርጊስን ከወኅኒ ቤት አውጥቶ በጥንቱ ቦታ አስቀምጦታል። ቴዎድሮስ የሚባል ሰማዕትም አለ። "የምሥራቃዊው
ቴዎድሮስና የሠራዊት አለቃ ቴዎድሮስ የገላውዴዎስ የፊቅጦር በረከት እንዲያርፍብኝ ለምኝልኝ።" [መጽሐፈ አርጋኖን ዘእሑድ ምዕራፍ ፰፥፮] ዳግመኛም "ሮማዊ ቴዎድሮስ የሚባል የሮም ሰው ነበር።" [ድርሳነ ገብርኤል፤ ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም 28] እንዳለ። ቴዎድሮስ የሚባልም ኤጲስ ቆጶስ አለ። "ኃጥእት ስለምትኾን ስለዚች ስለ እኅታቸው ያጥን ዘንድ የቸርነት መገኛ ወደምትኾን እመቤታችንም ይለምንላት ዘንድ ቴዎድሮስ ለሚባል
ኤጲስ ቆጶስ ሰጡት።" [ተኣምረ ማርያም፤ ተኣምር 53፥43]

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አባትም ቴዎድሮስ ነው የሚባለው።
ቴዎድሮስ የሚባል መነኵሴም አለ። "በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኵሴ ከእርሷ ዘንድ እንግድነት አደረ።" [ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም ፲] ቴዎድሮስ የሚባል ሊቀ ካህናትም አለ። "የዚህ አባት ወላጅ
አባቱ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ካህናት ነው፤ ስሙም ቴዎድሮስ ነው።" [ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር 29]

የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረ ቴዎድሮስ የተባለም አባት ነበረ። "በዚችም ዕለት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት ቴዎድሮስ አረፈ።"[ስንክሳር ዘወርኀ የካቲት ፯]
በቁሙ ቴዎድሮስ የሚባል ንጉሥም ይንገስ ወይም ቴዎድሮስ ማለት የስሙ ትርጓሜ ውኂብ እምእግዚአብሔር|
ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ| ማለት ነውና ከእግዚአብሔር ዘንድ የኾነ ለኢትዮጵያ የሰላም ጊዜ ይመጣ ይኾን? ብሎ በንስሓ በውዳሴ ማርያም፥ በመዝሙረ ዳዊት ደጊም በጸሎት ዘወትር
ተግተን ዘመነ ፍቅር ወሰላም እንዲመጣ ብንጸና እውነትም ቴዎድሮስ|ዘመነ ሰላም| ይመጣል። ድርጊት ትንቢትን
ይስበዋልና።

➸ ኹለት ዓይነት ትንቢት አለ፦...
፩. በነገሮች የሚወሰን
፪. በነገሮች የማይወሰን የግድ የሚፈጸም ትንቢት(Unconditio
nal Prophecy)
....
........ይቀጥላል
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ስለ ንጉሥ ቴዎድሮስ መምጣት
፨፨፨፨፨፨፨፨
.........የቀጠለ
➸ ኹለት ዓይነት ትንቢት አለ፦

፩. በነገሮች የሚወሰን ትንቢት(Conditional Prophecy)፦
ለምሳሌ፦ "እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።" ኢሳ.1፥19-20 የሚለው ተፈጻሚ የሚኾነው እኛ ተኣዛዚ ኾነን እሺ ካልን ብቻ በረከተ ምድር እንበላለን። ካልኾንን በረከተ ምድርን አንበላም።
የሚወሰነው በምንሰጠው ግብረ መልስ ነው። "አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።" ዘጸ. 20፥12 "ዕድሜ የሚረዝመው" እናት አባታችን ካከበርን ነው፤ ካላከበርን ያጥራል። ተፈጻሚነቱ የሚወሰነው በእኛ ድርጊት ነው።
፪. በነገሮች የማይወሰን የግድ የሚፈጸም ትንቢት(Unconditional Prophecy) ደግሞ አለ። ለምሳሌ፦ ምጽአት ክርስቶስ እኛ ጻድቅም ኾንን ኃጥእ የማይቀር የግድ የሚፈጸም ትንቢት ነው። ሊቁ አባ ገ/ኪዳን እንዳስተማሩንም ምጽኣተ ቴዎድሮስ
በተመለከተ የጥንት ብራና መጽሐፍ የሚለው "እኛ በንስሓ ከተመለስን ነው" ደገኛ ንጉሥ በሀገራችን የሚነግሠው
ብለዋል። ይኼ ማለት አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔር በፍጹም ንስሓ መመለሳችንን አይቶ ቴዎድሮስ
የሚባል ንጉሥ ሊነግሥ ይችላል አሊያም እንደ ስሙ ትርጓሜ ዘመነ ሰላም|ቴዎድሮስን| ያሳየናል ማለት ነው። በአጭር ቃል እንደ አባ ገ/ኪዳን ገለጻ ምጽኣተ ቴዎድሮስ በነገሮች የሚወሰን
ትንቢት(Conditional Prophecy) ውስጥ የሚመደብ ነው።

➻ ይኼን የመጻሕፍት አስረጅ አክብረን ሳንነቅፍ ዳሩ ግን የቴዎድሮስ መምጣት ብርቅም ድንቅም አርጎ አለመናገር
ይገባል። ከድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስ ይበልጣልና።
➾ በጠበል ከሥጋ በሽታችን ብንፈወስ መልካም ነው፤ባንፈወስም ንስሓ ገብተን ሕገ ወንጌለን ብንፈጽም በምሕረተ ክርስቶስ እንድናለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ነገር ግን በጠበል ከሥጋ በሽታ ተፈውሰን ዳሩ ግን ንስሓ ካልገባንና ሕገ ወንጌል ካለፈጸምን አንድንም። የሥጋ በሽታ ፈውስ ለምድራዊ ኑሯችን እንጂ ለሰማያዊ ሕይወታችን ዋስትና አይኾንም። ከምጽኣተ ቴዎድሮስ ይልቅ ምጽኣተ ክርስቶስን ነቅተን፥ ተገተን በእጅጉ መዘጋጀት ይጠቅማል። ምክንያቱም፦

፩. ንጉሥ ቴዎድሮስ ፍጡር፥ መድኅነ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የነገሥት ንጉሥ ፈጣሪ ነው።
፪. በቁሙ ቴዎድሮስ የሚባል ንጉሥ ላይመጣ ይችላል። መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እሱ ባወቀ ቀን መምጣቱ ግድ ነው። "ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ይመጣል።"[ጸሎተ ሃይማኖት] እንዲል።
፫. ቴዎድሮስ ቢመጣ ጊዜያዊ ዘመነ ሰላም ሊያመጣ ሊነግስ ነው፤ ጌታችን ሲመጣ ግን ዘላለማዊ ሰላም ሊሰጠን ለጻድቃን ሊፈርድላቸው ለኃጥኣን ሊፈርድባቸው ነው።
፬. ቴዎድሮስ ቢመጣ ዓለምን ሊያሳልፍ አይደለም። መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ሊያሳልፍ ነው።
፭. ቴዎድሮስ ቢመጣ ጊዜያዊ ንጉሠ ኀላፊት ምድር ቢኾን ነው፤ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ ንጉሠ ሰማይ ወምድር ነው። "እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።" ማቴ.12፥41 እንዲል።

➻ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራችን |የማርያም መቀነት| ሰንደቅ ዓላማችን ዓለምን ዳግም በንፍር ውሀ እንደማያጠፋት ለኖኅ ቃል ኪዳን መግባቱን የሚያሳይ ዓርማችን እንጂ ከዘላለም የሞት ፍርድ ግን አያድንም። በኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራት ነገሮች አሉ።

፩. ፈጽሞ እንዳንፈጽማቸው የተከለከሉ አሉ። ለምሳሌ፦ ኃጢኣትና ክፉ እኵያት ኹሉም።
፪. እንድንፈጽማቸው የታዘዙም አሉ። ለአብነትም ሕገ ወንጌልን
መፈጸም።
፫. ተፈቅደው ግን የማይበረታቱ አሉ። ለምሳሌ፦ የሚያሰክር መጠጥ ፈጽሞ አይከለክልም፥ ግና የሚያሰክር መጠጥ
አይበረታታም። የማይጠጣ የተሻለ አደረገ እንጂ።
፫. ብንፈጽማቸው፥ ባንፈጽማቸውም የማያስተቹ አሉ። ለምሳሌ፦ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነጠላ፥ አልባሳት ብንለብስም ባንለብስም ከወቀሳ ከከሰሳ አያደርስም። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ
እንጂ ዶግማም ሥርዐትም አይደለማ። ለዚህም ነው 'ንጉሥ ቴዎድሮስ ይመጣል በሚል አረንጓዴ ቢጫ ቀይ በሩ ላይ ያደረገ ይድናል' የሚል ፈጠራ እብለት ነው የምንል። የኢትዮጵያ ሰንደቅ
ዓለማ እንጂ በራሱ ሃይማኖት አይደለማ። ሰንደቅ ዓላማችን ክብራችን ነው እናክብረው ማለት እየተቻለ Code እየሰጡ፥ በሥዕለ ቅዱሳን ተሸፍነው፥ 'ባንዲራ ሰቅላችሁ ጠብቁ ድኅነታችሁ ነው' ማለቱ ለምን አስፈለገ? ትንቢተ ኢሳይያስ ላይ "ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፥ እናንተም በሩቅ ያላችሁ አሕዛብ፥ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ከማኅፀን
ጠርቶኛል፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን አንሥቶአል፤" ኢሳ.49፥1የሚለውኮ ስለ ቴዎድሮስ ሳይኾን ደሴት በውሀ፥ ውሀ
በደሴት እንዲከበብ ሰባ ዘመን በመከራ የተከበባችሁ እስራኤል ስሙኝ። አሕዛብ አድምጡኝ፤ በእናቴ ማኅፀን ስሜን ኢሳይያስ አለኝ፤ አንድም ከእናቴ ማኅፀን ከተወለድሁ በኋላ ኢሳይያስ ብሎ
ስም አወጣልኝ ለማለት ነው። "አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፥" ሲል አንደበቴ እንደ ተሳለ ምላጭ አደረገው ማለት ኦሪትን እንዳስተምር አደረገኝ ሲለን እንጂ ስለ ምጽኣተ ቴዎድሮስ
አይናገርም። "የተቀላቀለ እንዳይኾን እንለይ" እንዳለ ደራሲ [ቅዳሴ ማርያም]
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
​​አዎን አቤቱ አንተ ለዘላለም ልዑል ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ሁሉን የምትገዛ ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ሁሉን የምታድን ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ሁሉን የምትመግብ ነህ
አዎን አቤቱ አንተ የፍጥረታት ጌታ ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ በእውነት የምትፈቀር ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ሁሉን አሳልፈህ የምትኖር የዘላለም አምላክ
ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ አልፋ እና ኦሜጋ ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ አባታችን ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ የነፍስ የሥጋችን መመኪያ ነህ!
አዎን አቤቱ ፈጣሪያችን ነህ!
አዎን አቤቱ የምንገዛልህ የምናመልክህ የምንሰግድልህ
የምናመሰግንህ ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ ንጉሰ ነገሥት ነህ!
አዎን አቤቱ አንተ የጌቶች ጌታ ነህ!

"አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።

" (መጽሐፈ ነሀምያ 9:6)
"አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ጸሎት ይቀርባል።ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል። መዝ 65፡1-2
" በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 66:4)

ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው። የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ኃይልን ለእግዚአብሔር አምጡ። ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤ በቅድስናው ስፍራ
ለእግዚአብሔር ስገዱ። መፅ. ዜና. ቀዳማዊ 16፡27-29
፩ ኃይማኖት
@And_Haymanot
"ወዳጄ ሆይ ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን እራስ ላይ እሾህ እዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}

{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )
@And_Haymanot
[ ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሐ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር


... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሐ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሐ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን?
የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?
በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡
አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡
ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሐ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው?
ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡
እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሐ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡

"ሕማማት" ከተሰኘው ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጽሐፍ የተወሰደ



✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
👍1