፩ ሃይማኖት
8.99K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
"ሰይጣን የማይነካው ዕቃ "

በአንድ ሐገር ድንገት የአንድ" ጠንቋይ ዝና ከዳር ዳር ተሰማ ። ሰውዬው የማያሳየው ምትሐት የለም። አንበሳ ላለ አንበሳ፣ ነብር ላለ ነብር፣ የሞተ ዘመዴን ላለ የሞተ ዘመዱን፣ የጠፋብኝን ዕቃ
ከቤት ፈልገህ አምጣልኝ ላለ ዕቃውን ያመጣለታል። እንደሚታወቀው አጋንንት ከክብራቸው የተዋረዱ መላእክት ናቸው። መላእክት ደግሞ በፈለጉት ሁኔታ መገለጥ ይችላሉ። ይህ ጠንቋይ የሚሰጣቸውን ገጸ ባሕርይ ተቀብለው አንዴ አንበሳ፣ አንዴ ነብር፣ አንዴ ሰው እየሆኑ የሚተውኑት እንግዲህ አጋንንቱ ነበሩ። የበዚህ ጠንቋይ ዝና ወደ ንጉሱ ደረሰ። ንጉሱ ደግሞ ክርስቲያን
ቢሆንም ከመጸሐፍ ቅዱስ ይልቅ እንዲህ ያለ ተአምር እዚህ ቦታ ተፈጸመ ሲባል ለማየተት የሚሮጥ ሰው ነበር። ተአምር የሚወድ ሰው ደግሞ ክርስቲያንም ቢሆን ሰይጣን በሚሰራው ምትሐት
መታለሉ የማይቀር ነው። ስለዚህ ይህ ንጉስ የተማረውን መጽሐፍ ቅዱስ ዘንግቶ በጠንቋዩ ምትሐት አመነ።
ይህንን የሰሙ የንጉሱ ንስሐ አባት ነገሩን ሰምተው ወደ ቤተ መንግሥት ሲሮጡ ደረሱ። ሲደርሱ ንጉሡ ከቁም ነገር
አልቆጠራቸውም። እሱ የጠንቋይ ትርዒት ማየት ቀጠለ። "እስቲ አሁን ደግሞ እእእ ነጭ ፈረስ አምጣልኝ" ማለቱን ቀጠለ በነገሩ ያዘኑት "ኧረ ንጉሥ ሆይ ይተዉ፡ ይህ እኮ የሰይጣን ምትሐት ነው " ብለው ሊያስረዱት ሲሉ በቁጣ አስቆማቸው። ተአምር የሚከተል ሰው መቼስ ቢነግሩት አይሰማም። ጭራሽ
እንዲያው ለንስሐ አባቱ እንዲህ አላቸው። " የሰይጣን ስራ ነው አትበሉ፤ ቅናት ነው ይኼማ,,,, ይልቅ እርስዎም የሚፈልጉትን ነገር ይጠይቁት ያምጣልዎት!"አላቸው። ጠንቋዩ «የፈለጉትን ላምጣልውት,,,,,ምን ይፈልጋሉ,,,, " የሞተ ዘመድ አለዎት,,,,, ወይስ ከቤትዎ,,,, » አላቸው በኩራት። ካህኑ ውስጣቸው በመንፈሳዊ ቅናት ተቃጠለ። « እንግዲያውስ የፈለኩትን ማምጣት ከቻልህ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደህ ልብሰ ተክህኖዬ ውስጥ መስቀል አለ እርሱን ይዘህልኝ ና » አሉት።
ይህን ግዜ ጠንቋዩ ገና ድግምቱን ሲጀምር አጋንንቱ እላዩ ላይ ሰፍረው ጣሉት። በካህኑ ፊት ወደቀ። ሰይጣን ምንም ነገር ማምጣት ይችል ይሆናል። መስቀሉን ግን ማምጣት አይችልም።
አባቶቻችን ሰይጣን እንኳን መስቀል ቀርቶ መስቀለኛ መንገድም
አይወድም ይላሉ።
የጌታችን ቅዱስ መስቀል ሆይ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ «ብከ ንወግዖሙ ለኩሎሙ ጸርነ»
@And_Haymanot
«በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን!»
በዲ/ን ሔኖክ ሙላት
"ከሞት ባሻገር" የተወሰደ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
"ዐረገ በስባት ዐረገ በልልታ"
እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል (በዓለ አርብዓ) በሠላም አደረሳችሁ።

በእልልታ አረገ አረገ በእልልታ 
ሞትን ድል አድረጎ የሠራዊት ጌታ /2 
አረገ አረገ በእልልታ 

ከጌታ ዓበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው።
"ወረሲ ኀዋኅወ ቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት ርኅዋተ ለነ በምሕረት ወአሚን"
"የቅድስት ቤተ ክርስቲያንህንም ደጆች በምሕረትና በሃይማኖት እንዲከፈቱ አድርግልን።"
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ምንፍቅና በቅዱስ ቃሉ ሲፋቅ!
#ስግደት_ለመላእክት
👉ኢያሱ ለመልአኩ ሰገደ
👉ዮሀንስ ስለምን አትስገድልኝ ተባለ?

@And_Haymanot

መናፍቃን የሚያነሱትን ጥያቄ ቀለል ባለ
መንገድ ስንመልስ!!
👉1. የእስራኤል መስፍን የሆነው ኢያሱ “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን” ብሎ
እንዳላለ !!መጽ.ኢያሱ 5ቁ13“……እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኘ አሁን መጥቻለሁ አለ. ኢያሱም ‘ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና’ ጌታየ ለባሪያው
የሚነግረው ምንድር ነው አለው. የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን አውልቅ አለው” የምታመልኩትን ምረጡ ያለው ኢያሱ ለመልአኩ በስህተት ሰገደ ብለን አናምንም!!!ለመልአኩ በግንባሩ መደፋቱም መልአኩን ለማክበር እንጅ ለማምለክ እንዳልሆነ እናውቃለን!!!ዛሬም ኢያሱን ተከትለን እንዲሁ ስናደርግ አምላክን ከመልአክ ለይተን ነው!!!የአንዱን ላንዱ ሳንሰጥ፣ሳንቀላቅል!!

👉2. ወንጌላዊው ዮሐንስ፡በራእይ 19ቁ10 እና 22ቁ8 ….በመልአኩ እግር ፊት ሰገድኩለት እሱ ግን አትስገድልኝ፣ ሁለታችንም የእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን አለኝ….የሚለውን ጥሬ ንባብ ለመላእክት ስግደት እንደማይገባ ለማሳየት መናፍቃን ያቀርባሉ!!!ተሳስተዋል!!
✔️(ሀ)ወንጌሉን፣መልእክታቱን፣ራእዩን የጻፈው ዮሐንስ ለመልአኩ የሰገደው ባለማወቅ ነው ማለት ይሄን ሁሉ የጻፈውን ዮሐንስ ለማን መስገድ እንዳለበት እንኩዋ የማያውቅ አዲስ ምእመን ማስመሰል ነው!!!ዮሐንስ የሰገደው መስገድ ስለሚገባው ነው!!!
✔️(ለ)መልአኩ አትስገድልኝ ያለው ስግደት የበላይና የበታች መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ዮሐንስ በክብር እደተስተካከለው አውቆ ነው!!!ለትህትና!!!
✔️(ሐ)መልአኩ በምእራፍ 19 ቁ 10 እንደተገለጸው ዮሐንስን አትስገድልኝ ቢለውም ዮሐንስ ግን በምእራፍ 22 ቁ 8’ም ዳግመኛ ለመልአኩ ሲሰግድ እናገኘዋለን!!ዮሐንስን ያህል የጌታ
ወዳጅ(ፍቁረ-እግዚእ) ተብሎ የተነገረለትና በጰራቅሊጦስ
መንፈስቅዱስ የወረደበት አባት ለመልአክ መስገድ ስህተት
መሆኑ ጠፍቶ፣ እየተነገረው ጭምር ከአንዴም ሁለቴ ሰገደ ማለት ቅድስናውን መጠራጠር ይሆናል!!!ስለሆነም መልአኩ
አትስገድልኝ ያለው ለትህትና ነው ስንል እናምናለን!!!

👉3. የሞቱ ቅዱሳን ከእኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም የምትሉ ሰዎች አላችሁ!!!እሺ ቅዱሳኑስ ይሁኑ ታዲያ መላእክት እኮ አይሞቱም!!!ስለታናናሾች የአብን ፊት ያያሉ እንጅ-በማቴ 18ቁ 10 እንደተጻፈው!በዘካርያስ 1 ቁ 13 የመልአኩ ምልጃ እንዲህ
ተጽፉዋል “አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ እነዚህ 70 አመት የተቆጣሀቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተማዎች የማትምራቸው እስከመቼ ነው አለው እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው” ታዲያ ሳንለምነው እንዲህ የሚማልድልን መልአክ ብንለምነውማ ምን ያህል ይማልድልን?ሰአሉ ለነ ሚካኤል ወገብርኤል እንበላቸውማ!!!

👉4.የሞቱ ቅዱሳን በክርስቶስ ህያው ስለሆኑ ከእኛ ጋር በመንፈስ
እንደሚገናኙ ደግሞ ይሄው!!!የሞቱ ቅዱሳን “እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነሱ እንደማያፍር” በዕብ 11 ቁ 16 ተጽፉዋል!!!የሞቱ ቅዱሳን አላዋቂዎች ሳይሆኑ ወደፍጹምነት የተሸጋገሩ ‘ፍጹማን’ መሆናቸው በዕብ 12 ቁ 22 ሰፍሮልናል!!! ጌታም ከአመታት በፊት በሞት የተለዩትን አብርሃምን፣ይስሀቅንና
ያዕቆብን ጠቅሶ “የህያዋን አምላክ ነኝ” ሲል በማቴ 22 ቁ 32 ገልጹዋል!!!ጌታችን በስጋ ስለሞተው አብርሃም በዮሀንስ 8 ቁ56 ሲናገር፡ “አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴትን አደረገ፤አየም ደስ አለው” ይላል!!!በአጸደ ነፍስ ያለው አብርሃም የጌታን ቀን አይቶ የተደሰተው በሰማይ ያሉ ቅዱሳን በምድር ካለነው ጋር ህብረት ስላላቸው ነው!! ዮሐንስ በራዕዩ ምዕራፍ 8 ቁ 3 “የዕጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚብሔር ፊት ወጣ” ይለናል!!መላእክት ጸሎታችንን ያሳርጋሉ!!!አእርጉ ጸሎተነ የምንላቸውም ለዚሁ ነው-እንደ ቅ/ያሬድ-እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ!!ሙሴስ በዘጸአት 32 ቁ 13 “በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ይስሀቅንና እስራኤልን አስብ” ብሎ በአጸደነፍስ ነፍስ ባሉ ቅዱሳን ስም ጌታውን ሲማጸን ከሞቱ ቅዱሳን ህብረት ስላለን አይደለምን?ነው እንጅ!!!

👉5. ይሄን ሁሉ ስንል ባለቤቱን ረስተን አይደለም!!!በቀጥታም እሱን ማረን እንለዋለን-እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በምህላ- መሀረነ አብ በማስታኮት!!!ስማን፣ተማለደን፣ታረቀን እንለዋለን!!! ግን እንደሌሎቹ አማልደን አንለውም!!!ሌሎቹ የሚያማልደን ጌታ ነው እያሉ ቤዛነቱን እንደአማላጅነት ስለሚወስዱት ነው እኛ ቅዱሳንን አማልዱን ስንል አምላክ ያደረግናቸው የሚመስላቸው!!! አምላካችን አንድ ነው!!!የሃይማኖታችን መሰረትም እሱ-ለዚህም ነው ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን ስንል የሃይማኖት ጸሎታችንን የምንጀምረው!!!
ይቆየን
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
``የተፈጠረ እንጂ ያልተወለደ``
(ቢመርም ጠጣው)

ውኃ ያላረጠበው የበረሃ ተጓዥ ጥምቀት ያላራሰው; ጣዖት የለበለበው ተፈጣሪ ግን ያልተወለደ; አባት ያለው ግን ልጅ
ያልሆነ የተፈጠረ እንጂ ያልተወለደ አሕዛብ! ጸሎተ ሃይማኖታችን ላይ 318ቱ ሊቃውንት ወልድ የተወለደ እንጂ ያተፈጠረ` ብለውታል! ተወዳጆች! እኛ ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ``የተወለድንም የተፈጠርንም እንባላለን` የተፈጠርን-
መባሉ በአርአያ ሥላሴ ስለተፈጠርን ሲሆን ፤``የተወለድንም መባሉ በጥምቀት ተወልደናልና ነው፡፡ ልዩ የሆኑት አሕዛብ መናፍቃን ግን የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ`` ናቸው፡፡
አሕዛብ/መናፍቃን ``የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ከተባለለት አምላክ ያልተወለዱ ሆነው ቢገኙ `የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ አሰኘባቸው፡፡ መፈጠርን አግኝተዋል የነፍስ መወለድን ግን አላገኙም፤በሥጋ ተወልደዋል ከጥምቀት የሚገኝ መንፈሰ ልደት
ግን አላገኛቸውም፤በምጥ ተወልደዋል ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ በረቂቅ አልተወለዱም፤ተስዕሎተ መልክ አግኝተዋል ተሥዕሎተ ሥላሴን ግን አላገኙም ፤አካለ ሥጋን አግኝተዋል በሜሮን ግን አልከበረም፤መብለ ሥጋን ይበላሉ ቁርባኑ ግን አላሻተታቸውም፤ይጠጣሉ ጠበል ግን አልዳበሳቸውም ፤በከበረው ቤት ኖረዋል የከበረች ቤ/ክ ውስጥ ግን አልኖሩም፤ዓለምን ሁሉ ያውቃሉ ቤ/ክን ግን አያውቋትም፤ቤ/ክን ይጠሏታል እርሷ ግን ሥራቸውን እንጂ እነሱን አትጠላቸውም እነዚህም… እንደ ኦሪቱ ያልተገዘሩ ቆላፎች ሸለፈት ጌጣቸው
አንባር ዝናራቸው የሆነ በሐዲስ ኪዳኑ
የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ`` አሕዛብ ናቸው! ለማያውቁት ይሰግዳሉ የሚያውቃቸው ግን በሌላ አምላክ
ቀይረውታል እሱም ያዝንባቸዋል!
በአርአያው ፈጥሯቸው ሳለ አርአያውን ለማያውቁት ይሰግዳሉ! ከነፍስ መንጺያ ጥምቀት ይልቅ የሥጋ መንጸትን ይሻሉ!
ከክርስቶስም ሥጋና ደም ይልቅ የክርስቲያች ደም ያጸድቃቸዋል! ስለዚህ ተፈጥረዋል ግን አልተወለዱም ! ለአባትነቱ ሲል ፈጥሯቸዋል አባትነቱን ግን አላመኑለትም ምክንያቱም አልተወለዱምና! ለጌትነቱ ፈጥሯቸዋል እነሱ ግን አገልጋይነቱን አልፈለጉም! ለንጉሥነቱ ፈጥሯቸዋል ግን ስላልተወለዱ ሕዝብ መሆንን አላገኙም! በውኃ ውስጥም አልፈው ሥላሴን አላገኙም! ለፍቅሩ የሰጣቸውን ለልጅነት የሚሆን ሰውነታቸውን ለአላዊው
ዲያብሎስ ገበሩት እርሱም ለማያውቁት መስገድን ለሚያውቁት መገዳደርን አስተማራቸው! በጥምቀት መወለድን ትተው በመፈጠር ብቻ ቆሙ!
ስለዚህ ያልተወለዱት በተወለዱት ላይ አመጹ! መኖራቸው አነደዳቸው አመጹባቸውም! መኖሪያዎቻቸውን አነደዱ ስፍራዎቻቸውን ተቀራመቱ በስፍራዎቻቸውም ይጠጋሉ መሬት
ይከባሉ ጽነትን ያደርጋሉ ይቆረቁራሉ ያሰፋሉ ያስተጋባሉም የጥምቀት ውኃ ባላበረደው ሰውነት ያመኑትን ይጻረራሉ !
የተወለዱት ግን ያያሉ ይታዘቡማል ይመረምራሉ ይማጸናሉ ! አይጠሉም ይወዳሉ ሰውን ያይደለ ክፉ ግብርን ይጸየፋሉ! ስለዚህም አሕዛብ ተፈጥረው ቆሙ መወለድን ግን አልፈለጉም!
አሕዛቡ የማመናቸው መሠረት የተወለዱት ባለመኖራቸው ላይ ሆነ፤መኖራቸውን የሚያረጋግጡት የተወለዱትአለመኖራቸውን
ቅድሚያ አረጋግጠው ነው! ቢቻል ስፍራዎቻቸውን ማጥፋት ባይቻል መውረስ ባይቻል ተጠግቶ ቁር-ብትና(ብርዳም ጎረቤት፤አንድም ቁርበታም የሆነ ጎረቤት) ሆኖ መገኘት ነው! የተወለዱት ግን እንደ ልጅ ይኖራሉ - ምክንያቱም አባት አላቸውና! እንደ ባርያ ይኖራሉ -ምክንያቱም ጌታ አላቸውና !
እንደ አገልጋይም ይኖራሉ-ምክንያቱም ንጉሥ አላቸውና! በአንድነት ይኖራሉ ምክንያቱም - አንድ አምላክ አላቸውና!
ከሁሉም አስቀድሞ ደግሞ ጌታቸውን በ40/80 ቀን በውኃ ውስጥ ሦስት አካል ሆኖ አግኝተውታል! አባ አባ ማለትን አስለምዶ አንደበታቸው ሲፈታ አባታችን ሆይ ማለትን አስለምዷቸዋል! እነዚያ አሕዛብ ግን ``አባታችን ሆይ አይሉም
ምክንያቱም አባት ሳላቸው ልጅ አልሆኑለትምና! ምክንያቱም
`
የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ ናቸውና!
By:- ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
“ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡ አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡”

© ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፣ ገጽ 33
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
"12 የሆነው በምክንያት ነው"
# ቅዱሳን መላእክትን መታሰቢያቸውን መዘከራችን -በምክንያት
ነው
#ቅዱስ ሚካኤልን ማክበራችንም - በምክንያት ነው
#ቅዱስ ሚካኤል ዓይኑ ዘርግብ መባሉም - በምክንያት ነው
#ቅዱስ ሚካኤል እርዳን ማለታችን - በምክንያት ነው
# ቅዱስ ሚካኤል በ12 ማክበራችን - በምክንያት ነው
#ቅዱሳን መላእክትን መታሰቢያቸውን መዘከራችን -በምክንያት ነው...... በመጽሐፈ መሳፍንት የሶምሶን እናትና አባት መልአኩ ተገልጦ ልጅን እንደሚወልዱና እርሱም ናዝራዊ እንደሆነ በነገራቸው ጊዜ የሶምሶን አባት ማኑሄ ለመልአኩ " ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ ነገርህ በደረሰ ጊዜ መታሰቢያህን እንድናደርግ ስምህ
ማን ነው? አለው" (መጽሐፈ መሳፍንት 13:17) መልአኩም ስሜ ድንቅ
ነው ብሎታል፡፡ እንኳን በሐዲስ ኪዳን በብሉይ እንኳን መላእክት መታሰቢያቸው ይከበራል፡፡
*እስራኤላውያን ከቀሳፊው መልአክ የተረፋበትን ቀን " ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ"(ኦ.ዘጸ
12:14) እስራኤላውያን ከቀሳፊው መልአክ የተረፋባትን ቀን
ካከበሩ እኛማ ቅ/አፎምያ በቅ/ሚካኤል መትረፏን ብናከብር እኛም የቅ/
ሚካኤንም ውለታ እንዴት አናከብር !! ጠቢቡም " የጻድቅ መታሰቢያ
ለበረከት ነው፤ የኅጥኣን ስም ግን ይጠፋል። ምሳሌ 10:7)
እውነት ነው የቅ/ሚካኤል መታሰቢያ ለበረከት ነው፡፡
#ቅዱስ ሚካኤል ዓይኑ ዘርግብ መባሉም - በምክንያት ነው
*ለቅ/ሚካኤል የሰውና እንስሳ ዓይነት ዓይን ኖሮት "ዓይኑ ዘርግብ "
የተባለ አይደለም፡፡ይልቁንም የሰው ዓይን የሚያየው ነጩ ያይደለ
ጥቁሩ (ብሌን) ነው፡፡ ርግብ ግን ዓይኗ የሚያየው ነጩም ጥቁሩም
ነው፡ እንዲሁ ቅ/ሚካኤል ሆይ አንተም ያለፈውንም የሚመጣውንም
ማየት ይቻልሀል (በጸጋ ተሰጥቶሀል) ስንል ነው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ መልአኩ ነጫጭ ልብስ
የለበሱት ማናቸው ባለው ጊዜ ዮሐንስ ሲመልስ " እኔም ጌታ ሆይ፥ አንተ
ታውቃለህ አልሁት አለኝም እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ"ዮሐንስ ራእይ 7:14)
#ቅዱስ ሚካኤል በ12 ማክበራችን - በምክንያት ነው
*ቅ/ገብርኤል በ19 መታሰቡ በምክንያት እንደሆነው የቅ/ሚካኤልም
በ12 መሆኑ በምክንያት ነው፡፡ የቅ/ገብርኤል " መልአኩም መልሶ።
እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም
ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር "የሉቃስ ወንጌል
1:19 ........ ቁጥር "19" ይህ በምክንያት ነው፡፡ የቅ/ሚካኤል
" በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ
ሚካኤል ይነሣል " ትንቢተ ዳንኤል 12:1 ..... ምዕራፍ "12" ይህም በምክንያት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በዚህች ቀን
መታሰቢያውን እናደርጋለን ስሙንም ከፍከፍ እናደርጋለን ! ቅዱስ ሚካኤል
ያማልደን ዘንድ እንማጸነዋለን .... ምን ማማለድ ብቻ መልአክ አይደል
ደስ ያለውንም ያደርግልናል "እርሱም እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤
ደስም ያሰኘህን አድርግ " (መጽ.ሳሙ 19:27)
#ቅዱስ ሚካኤል ረዳትነቱንም ስንመሰክር በምክንያት ነው "
ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም" (ት.ዳን 10:21) .......እናም ከቅዱስ ሚካኤል በረከቱን ያድለን፡፡
(ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ ሰኔ 12/2012)
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ሐይማኖት አይወረስም?

@And_Haymanot

ተወዳጆች የተሃድሶ መናፍቃን ሃይማኖት አያስፈልግም፤አያድንም፤አይወረስም በማለት ብዙዎችን ለማደናገር ይሞክራሉ ከዚህ በፊት በስፋት የዳሰስነው ርዕሳችን ቢሆንም በውስጥ ለጠየቀን ወንድማችን እነሆ ብለናል

ሐይማኖት አይወረስም ላልከን እንዲህ የምናምነውንም እንመሠክራለን! > እንግዲያውስ ከኃይማኖት በላይ ሊያወርሱት እና ሊወርሱት የተገባ የከበረ ነገር በዚች አለም የለም። ሰው መልካም መልካሙን ነገር ለልጆቹ ያወርሳል ከመልካም ስጦታዎች ሁሉ የሚልቀውን የዘላለም ሕይወት የሚገኝበትን ሐይማኖት ከማውረስ የበለጠ ታላቅ ውርስ እንዳውም በጭራሽ አይገኝም።

ሰው በምድር ላይ ለልጆቹ የሚሆን ታላቅ መኖሪያ ቢያወርስ ነገር ግን የዘላለም ሕይወት የሚያገኙበትን ሐይማኖቱን ግን ባያወርስ ምን ይረባቸዋል! ??
ሁለት ነገርን አደፈረስክ! መጀመሪያ ሐይማኖት ሊወረስ የተፈቀደ መሆኑን ካድክ ሲቀጥል ደግሞ በገዛ ድምዳሜክ ገባህና ሐዋርያት ከሀድያን ናቸው አልክ! እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።
አስቀድመህ በራስህ አላዋቂነት የደመደምከው ድምዳሜ ላይ የተመረጡትን ሁሉ አጋጭተሀል።
በመሰረቱ ሀይማኖት ለሰው ልጆች የተሰጠችው ልንጠብቃት እና ለትውልድም ልናወርሳት ነው።
አብርሃም አባታችን ለአይሁድም ሆነ ለሀዲስ ኪዳን ህዝቦች አባት ነው። ከህግ ለሆኑት የመገረዝ አባት ነበረ። ከእምነት ለሆንነው ደግሞ የእምነት አባት ነው። የፃድቅ አብርሃም
ሕይወት ለእኛ ምሳሌ ነው። አብርሃም እግዚአብሔር ን አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት ነገር ግን ይህ ብቻ አልነበረም ጉዳዩ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም ትዛዝን ሲሰጠው ልጆችህ ቃል ኪዳኔን እንዲጠብቁ አድርግ በሚል ጠንካራ
ማሰሪያም ጭምር ነው። አብርሃምም በቤቱ ለተወለዱት ልጆች ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ገና በተወለዱ በ8 ቀናቸው ጀምሮ ይፈፅምላቸው ነበር። የእርሱን ሐይማኖት ለልጆቹ ገና በስምንት ቀን ጨቅላነታቸው እያሉ ጀምሮ እንዲቀበሉ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ ነው። ልጆችም በአባቶቻቸው
ሐይማኖት ተወስነው እንዲኖሩ ነው የጌታ ትእዛዝ። ስለዚህ ሐይማኖት ይወረሳል። ከሐይማኖት የበለጠ ለልጅ ሊያወርሱት የሚገባ መተኪያ የሌለው ውድ ነገርስ ከየት ይገኛል???
ዘፍጥረት 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥
#ለአንተና_ከአንተ_በኋላ_ለዘርህ_አምላክ_እሆን_ዘንድ
⁸ በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ለዘላለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ አምላክም እሆናቸዋለሁ።
⁹ እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፥ አንተ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው።
¹⁰ በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
¹¹ የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ
መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
¹² #የስምንት_ቀን_ልጅ_ይገረዝ ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።
¹³ በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
¹⁴ የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ፥ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።//

ሮሜ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ
አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው።
¹³ የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው
የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም።
¹⁴ ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል
የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤
¹⁵ ሕጉ መቅሠፍትን ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።
¹⁶-¹⁷ ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ
ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት #የሁላችን #አባት #ነው
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።

1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።

ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።

የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።

ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
❖ መልካም አዲስ አመት አትበሉን!!!!!!!

@And_Haymanot

የ ፳፻፲፩ (2011) ዓ.ም የመልካም ምኞት መግለጫ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያዎች 'መልካም አዲስ አመት' ሲሉ "መልካም አዲስ ገረድ' ማለታቸው መሆኑን ያውቃሉ......
"አመት" ተብሎ በአልፋው "አ" ሲጻፍ ሴት አገልጋይ ገረድን ይገልጻል። ለምሳሌ፦ "ተፈሥሒ ኦ አመት ወእም ድንግል ወሰማይ ሰማያዌ..." /ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ/ ሲል ገረድ(ሴት አገልጋይ) ና እናት፤ ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ ማለት ነው።

"ዓመት" ሲሆን ዘመን ይሆናል። "...ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ።..."/መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ፤ ለሥእርተ ርእስከ(ለራስ ጸጉርህ)/ ሲል ደግሞ "የመጥቅዕና የአበቅቴ መጀመሪያ ርእሰ ዓመት ዮሐንስ ሆይ..." ማለት ነው።

አመት የሚለው በብዙ ቁጥር አእማት ይሆናል። በዕብራይስጥ አማህ፤ በሱሪስት አምታ፤ በዐረብኛ ደግሞ አመት ይለዋል። ትርጓሜውም ሴት ባሪያ፤ ገረድ፤ ደንገጥር ማለት ነው። "...በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባሪያይቱ..." ዘፀ.11፥5 የሚለውን ግዕዙ "አመት እንተ ትነብር ዲበ ማሕረጽ።" ይለዋል። በዚህ አገባብ አማርኛው "ባሪያይቱ" የሚለውን ግዕዙ "አመት" ይላታል።
ወንዶች ባሪያዎችን "አግብርት" ሲላቸው ሴቶች ባሪያዎችን ደግሞ "አእማት" ይላቸዋል። [ዘፍ.32፥5 ግዕዙን ንባብ ተመልከት]
ዓመት የሚለው ደግሞ በብዙ ቁጥር "ዓመታት" ሲባል ዘመን፥ ዘመናት፥ ብዙ ቀን፥ የዕለታት ድምር ማለት ነው። "በባቢሎን ንጉሥ በብልጣሶር በመጀመሪያው ዓመት" ዳን.7፥1 የሚለውን ግዕዙ "በቀዳሚ ዓመተ መንግሥቱ።" ይለዋል። "የዕድሜህም ቁጥር ብዙ ነውና፥" ኢዮ.38፥21 የሚለውን ግዕዙ "ኊልቆ ዓመታቲከ፥" ይለዋል።

ስለሆነም አንድ ሰው 'እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰን' ሲል 'እንኳን ለአዲሷ ገረድ አደረሰን' አለ ማለት ነው። ይኼ ደሞ ጸያፍ ነው።
"እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን" ሲል "እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሰን ማለቱ ነው። ይኸውም የተገባ ነው።
መልካም ምኞታችሁን የገለጻችሁ መስሏችሁ 'መልካም አዲስ አመት' አትበሉን!!!!!
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ፍቅሯ ቢጸናብኝ !


* ተወዳጆች ሆይ ! ቅዱስ ኤፍሬም ሲመጸውት ዘወትር
በእመቤታችን ስም ነበር "ምነው ሌሎቹን ንቋቸው ዘንግቷቸው
ነውን"? ቢባል ... ዘንግቶ ንቆስ አይደለም የእሷ ፍቅር ቢጸናበት
ነው እንጂ ! ብለው ሊቃውንቱ መስክረውለታል! ጠቢቡ ሲራክ
"ብዙ ሰዎች ወዳጅ ይሁኑህ ነገር ግን ከብዙዎቹ አንዱ ምክርህን
የምትገልጥለት ይሁን " ሲራክ 6;6 እንዳለው ሁሉም ቅዱሳን
ወዳጅህ ይሁኑ ከሁሉ ግን የማን ፍቅር ጸናብህ? ለቅዱስ
ኤፍሬም እመቤታችን ወላዲተ አሞላክ;ለነቢዩ ኤልሳዕ ነቢዩ
ኤልያስ ፡ ለአፎምያ ቅ/ሚካኤል፡ ለአቡነ ቄርሎስ ቅዱስ ሚናስ፡
ለቅ/አትናቴዎስ አባ እንጦንስ፡ ፍቅር ጸንቶባቸው ነበር
አርአያቸውንም ተከትለዋል ! ወዳጄ አንተ የማን ፍቅር ጸናብህ?
የእመብርሃን? የአቡነ ተክለ ሃይማኖት? የአቡነ ገ/መንፈስ
ቅዱስ? የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ? የቅዱስ ጊዮርጊስ?
የወንጌላዊው ዮሐንስ? የየቱ ፍቅር ጸናብህ? ከጸናብህ ከቅዱሱ
ምን ተማርክ? ወር ጠብቀህ ትዘክረዋለህ? ምክንያቱም
ለወዳጆችህ ልደት እየታደምክ ደስታቸውን እየተካፈልክ የቅዱሱን
በዓል እንዴት አትሳተፍም? ለወዳጅህ ሠርጉን እያደመቅክ
እንዴት የእመብርሃንን የአቡዬን የተክልዬን የቅ/አርሴማን በዓል
ማክበር ማድመቅ ለምን ተሳነህ? ፍቅሩ ለጸናብህ ቅዱስ፡ ቀኑን
አስበህ ትጸልያለህ? ድርሳኑን መልኩን ታደርሳለህ? የዚያ ቅዱስ
ስብዕናና ቅድስና ሕይወት ባንተ ውስጥ እንዲሰራ ምን ያህል
ራስህን አዘጋጀከው? ተወዳጆች ለእኔ ግን የእመብርሀን ፍቅሯ
ጸንቶብኛል፡ የእናትነቷ መዳፍ የሳተው ልቡናዬን ሲያቀናው
ችግሬንም ስታቀለው ልመናዋም የሐጥያቴን ነዶ ሰንደው ፍቅሯ
አብዝቶ በልቤ ነደደ ! ሙሴ ስለ ሮቤል "ሮቤል አይሙትብኝ
እፈልገዋለሁ" ካለው በላይ ድንግል ስለእኔና ስለልጆቿ "ተክለ
አብን እሻዋለሁ ፍቅረ ማርያምን እወደዋለሁ ሰይፈ ሚካኤልን
እለመነዋለሁ ተክለ ማርያምም አይነቀልብኝ ብላ ስትለመን
ስትማልድ ፍቅሯ ጸናብኝ ! ፍቅሯን ያሳድርባችሁ!
(ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ)
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
Photo
እኛ ግን እያከበርን እናመሰግናቸዋለን። ይኼን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎች በብዛት እየተቀባበሉት ነው ፎቶውንም ሪፖርተር ላይ የሚሰራ አንድ መደዴ "ጋዜጠኛ" ለፌስቡክ ስላቅና መዘባበቻ ብሎ ያነሳው ፎቶ ነበር፤ ባይሳካለትም። እውነታው ግን ሰውየው የቤተክርስቲያን የጥበቃ ሠራተኛ ሲሆኑ
በፈረቃ ሰአታቸው እየተጠቀሙ ከመንገደኛ ምጽዋት ይሰበስቡና
በሰውኛ ለሚጠብቋት ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማደሻ ያስገባሉ። ሙሉ ታሪኩ ባጭሩ ይኼ ነው። ያለ ስማቸው ስም እየሰጠን ቤተ ክርስቲያንን በአቅማቸው የሚረዱትን ባንገፋቸው መልካም ነው፡፡
@And_Haymanot
እግዚአብሔርን የሚወድ እና በእግዚአብሔር የሚወደድ #መንፈሳዊ_ሰው ሁልጊዜ ደስተኛ ነው ። በምንም ሁኔታ ይሁን በምንም እግዚአብሔር በእርግጠኝነት እንደሚሰራለት ይሰማዋል በእርሱም ስራ ይደሰታል ። በእርግጥም እግዚአብሔር ሥራውን ባናየውም እንኳ ይሠራል ። ሥራውን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ልናየው እንችላለን በዚህም እንደሰታለን ። ይህን ደስታችንም ማንም አይወስድብንም ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች የሚደሰቱት በስጦታዎቹ ብቻ ሳይሆን በራሱ በጌታም ነው ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ አባታችን ሆይ ካላቹ በኋላ እመቤታችን
ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው
ስለዚህ መፀለይ የለበትም ለሚሉን ሁሉ፡፡
እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን የተወደደች
እናታችንን እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን እንጠራታለን
እንዲህም እንላለን፦

እመቤታችን ንፅህት ቅድስት ድንግል
(ማቴ1:23) ማሪያም ሆይ(2ቆሮ11:2) በመልአኩ በቅድስ
ገብሬል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28) በሀሳብሽ
ድንግል ነሽ (2ቆሮ11:2 ንፅህት )በስጋሽም ድንግል ነሽ
(ማቴ1:23) (ህዝ44:2) ያሸናፊ የልኡል እግዚአብሔር እናት ሆይ
(ሉቃ1:35)ሰላምታ ላንች ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ
አንች የተባረክሽ ነሽ (ሉቃ1:28 ናሉቃ1:32) የማህፀንሽ ፍሬ
የተባረከ ነው (ሉቃ1:32) ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ
ይበልሽ ልኡል እግዚአብሄር ካንች ጋር ነውና(ሉቃ1:28-30)
ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን ከመዳህኒታችን ከኢየሱስ
ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን በ1ቆሮ5:20 በፅድቅ
ስራ የኖሩት ይለምኑ ዘንድ ተሰጥቷቸዋልናሃጢአታችንም
ያስተሰርይ ዘንድ ለዘላለሙ አሜን።
እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡
ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተዋህዶን ሊተቹ የሚነሱትን
እግዚአብሄር ልቦና ይስጣቸው፡፡

ኦርቶዶክስ መልሥ አላት

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመሥቀሉ ክቡር
ለሌሎች ሼር ማድረጎን አይዘንጉ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ

@And_Haymanot

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡

ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)
@And_Haymanot
ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡

ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)

አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ "የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ አይሹትም ፣ አይደረግምም" የሚለውን በመጥቀስ የሐዲስ ኪዳነ ታቦትን ይቃወማሉ። ቃሉ የተነገረው ለእስራኤል ቤት ሲሆን እስራኤላውያን በእርግጥም የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይሹትም። በኦሪት ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃልኪዳን በአዲስ ኪዳን ተተክቷል። ይህ ከሐዲስ ኪዳን መሠዊያ ጋር የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ "አዎ እስራኤል አይሹትም" ብለን እንመልሳለን።
የአሁኑ ታቦት የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109)

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያ
ከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡

የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡
@And_Haymanot
የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡

ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.

It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡
@And_Haymanot
‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) http://www.stmarkdc.org/coptic-sanctuary ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡

ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡
@And_Haymanot
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!
@And_Haymanot
....ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 10 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot