፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ?
.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን ።
.
ወደዛሬው ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት አንድ ጥቅስን
በጥቂቱ
እንመልከት።
ማቴዎስ ምህራፍ 24: 4 ""ኢየሱስም መልሶ አንዲህ
አላቸው :-ምንም
እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ :: ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ
ብለው
በስሜ ይመጣሉና :: ብዙዎቹንም ያስታሉ :: ጦርንም
የጦርንም ወሬ
ትሰሙ ዘንድ አላችሁ:: ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ ""
ይህ
እንግዲህ ወገኖቼ ቅዱሳን ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ
ከማረጉ በፊት
የአለም መጨረሻ ምልክት ምን እንደሚመስል ሲጠይቁት
ኢየሱስ
የአለም መጨረሻ ምልክቱ ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ
ጦርነትም
የጦርነትም ወሬ ትሰማላችሁ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ይላል ::
.
የጦርነትም ዜና ስምተናል :: ይህም የሚያሳየን አለማችን
ወደ ፍጻሜዋ
መምጣቱዋ ነው :: ትንቢቱ እንደሚለው ብዙዎች በስሜ
ይመጣሉ
ይላል :: ዛሬ በአገራችን ነጮች የፈለሰፉዋቸው የእውሸት
ክርስትያኖች
በአገሪቱ ሰፍነዋል :: ሊሰብኩንም ሲፈልጉ ኢየሱስን ተቀበሉ ይሉናል ::
.
ይህ እንግዲህ ትንቢት የተነገረለት ጉዳይ ነው :: ወገኖቼ
ኢትዮጵያ
ከማንም አገር በፊት ክርስቶስን ተቀብላዋለች የ
""ሐዋርያት ስራ
ምህራፍ 8 ቁጥር 26-40 "" :: አሁን ግን ብዙዎች
በኢየሱስ ስም
ሰዎችን እያሳቱ ነው :: ለዚህም ደግሞ ብዙዎቹንም
ያስታሉ የሚለው
ትንቢትም እየትፈጸመ ነው :: ይህንን እራሱን በቻለ ርእስ
እንመለከተዋለን ::
ለዛሬ ግን እግዚአብሔር እንደፈቀደልን
የምንመለከተው ርእስ የሚሆነው
.
አንቺ_ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ
የሚለውን
ትምህርት ነው ::
ዉድ ክርስትያኖች ከላይ እንደገለጽኩት ዘመናችን አስከፊ
ነው ::
ይህ ያለንበት ዘመን እጅግ አሰቃቂ ወንጀሎች
የሚፈጸሙበት :
ሐይማኖት የሚካድበት :: ምንፍቅና የበዛበት : ሌባ
የበዛበት : ሆዳም
የበዛበት : ጉበኛ የበዛበት : ሰዎች ከተመሳሳይ ጾታ ጋር
የሚረክሱትበት
ፍቅር የቀዘቀዘበት ጊዜ ላይ ደርሰናል :: ከዚህም አልፈው
ደግሞ
መናፍቃን የእግዚአብሔር እናቱን ቅድስት ድንግል
ማርያምን
ቅዱሳኑንም ሁሉ እስከ መስደብ የደረሱበት ጊዜ ላይ
ደርሰናል ::
.
ወገኖቼ እንኳን በባህሪው ቅዱስ በአነዋወሩ ክቡር
የሆነው ልዑል
እግዚአብሔርን ይቅርነና ሰዎች እናትና አባትን አትስደቡ
አክብሩ ተብሎ
ታዟል ""ዘዳግም ምህራፍ 5 ቁጥር
16 "" እናትህንና አባትህን አክብር ይላል :: ይህ
እናትህንና አባትህን
አክብር ያለ እግዚአብሔር እንዴት እናቱን ይሳደባል ? ?
እረ እናስተውል ::
.
ለማንኛውም=> አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ማለት
ምን ማለት
ነው ? በውኑ
ይህ ስድብ ነውን ? አይደለም ::
ይህ በእስራኤላውያን ዘንድ # የትህትና አነጋገር ነው ::
ስለዚህ መጸሀፍቅዱስ
ስለዚህ ቃል ምን ይላል የሚለውን እንመለከታለን ::
,
መናፍቃኖች ብዙ
ጊዜ ይህ ስድብ ነው ይሉናል :: እኛ ግን እንደነሱ
(መናፍቃን)
በገዛፈቃዳችን ተረርገጉመን ሳይሆን # መጸሀፍቅዱስ
ምን ይላል ብለን አበው እንዳስተማሩን ይህን ቅዱስቃል
እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ እንመልከተው።
በውኑ መጸሀፍቅዱስ አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን
አለኝ ማለት ስደብ ነው ይላልን ???
አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ዮሐንስ 2 :1-12
ይህ አነጋገር በመጸሀፍቅዱስ ውስጥ የትህትና አነጋገር
ነው :: ይህንን
የሚያስረግጡልንን ጥቅሶች በጽል ሁኔታ እንመለከታለን ::
.
1ኛ . ኦሪት ዘፍጥረት ምህራፍ 2 ቁጥር 21-23 እንዲህ
ይላል
አስተውሉ "" እግዚብሄር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን
አጥንት ሴት
አድርጎ ሰራት : ወደ አዳምም አመጣት :: አዳምም አለ :-
ይህች
አጥንት ከአጥንቴ ስጋዋ ከስጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ
ተገኝታለችና ሴት
ትባል "" ይላል :: ተመልከቱ ሴት ማለት አጥንትዋ
ከአጥንቴ ስጋዋ
ከስጋዬ ነው ማለት ነው :: ስለዚህ ኢየሱስ አንቺ ሴት
ብሎ አናቱን
ሲጠራት "" አጥንትሽ ከአጥንቴ ስጋሽ ከስጋዬ ነው ""
ማለቱ ነው ::
ያልገባው ግን ብዙ ያወራል :: እግዚአብሔር ስጋን ደምን
የነሳው
ከቅድስት ድንግል ማርያም ነው :: ቅድስት ድንግል
ማርያም
የእግዚአብሔር እናቱ ናት ኢሳያስ 9:6, ዮሀንስ
1:1-14...:: ስለዚህ
አንቺ ሴት ማለት እራሱ አጥንትሽ ከአጥንቴ ስጋሽ ከስጋዬ
ማለት ነው::
.
አሁን ደግሞ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ማለት ምን ማለት
ነው
የሚለውን እንመለከታለን :: አሁንም መጸሀፍቅድስ ስለዚህ
ቃል ምን
ይላል እንመልከተው ::
.
እንዲህ ይላል "" እርስዋም ኤልያስን የእግዚአብሔር ሰው
ሆይ ከአንተ
ጋር ምን አለኝ ? ሐጢያቴን ታሳስበኝ ዘንድ ልጄንስ ትገድል
ዘንድ ወደ
እኔ ዘንድ መጥተሀልን ? አለችው :: ቅዱስ ኤልያስ ይህን
ባለችው
ጊዜ የሴትየውን ልጅ ከሞት አስነሳላት ይላል :: ሙሉን ስታነቡት ::
.
ታሪኩ እንዲህ ነው : አንድ ሴት ነበረች : ይህች ሴት
በእስራኤል አገር
ድርቅ በነበር ጊዜ ይህንን ቅዱስ ሰው ኤልያስን በቤትዋ
ውስጥ
ትመግበው ነበር :: ሰግነትም በኛ አገር ቆጥ ብለን
እንደምንሰራው
አይነት መተኛ ልብቻው ሰርታለት ነበር :: ይህች ሴት አንድ
ቀን ልጅዋ
ሞተባት :: ለሴትየዋ ብቸኛ ነበረ ልጁዋ :: በዚህን ጊዜ
ይችን ሴት
ልጅዋን እንዲያስነሳላት ወደ ተለያየ ቦታ አልሄደችም ::
ወደጠንቁዋይ
አልሄደችም ወደ መናፍቃንም አልሄደችም ይህች ሴት
የሄደችው ወደ
ቅዱስ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ቅድስ ኤልያስ ነበር ::
ሄደችናም
እንዲህ አለችው የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር
ምን አለኝ ?
ሐጢያታችንን ቆጥረህ ልጄን ሞተብኝን አለችው :: ይህ
አነጋገር
የትህትና አነጋገር ስለሆነ ቅዱስ ኤልያስ የሴትየዋን ልጅ
እቤቱዋ ድረስ
ሄዶ ከሞት አስነሳላት ::
አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ወይም አንተ ሰው ከአንተ
ጋር ምን
አለኝ ማለት : የትምህና አነጋገር ነው :: የትእቢት
አነጋገርማ ቢሆን
ኖሮ ቅዱስ ኤልያስ ቀናኢ ነው በእሳት ሴትየዋን ባቃጠላት
ልጅዋንም
ከሞት ባላስነሳላት ነበር :: ቅዱስ ኤልያስ ትእቢተኞችን
ክብር
የማይሰጡን ከሰማይ በእግዚአብሔር እሳት አቃጥሏቸው
አንድዷቸዋል
መጽሀፈ ነገስት ካልእ ምህራፍ 1 ቁጥር 9 - 13::
3ኛ . መጸሀፈ ነገስገስት ካልእ ምህራፍ 3 ቁጥር 13
-20:: እንዲህ
ይላል "" ኤልሳእም የእስራኤልን ንጉስ :- እኔ ከአንተ ጋር
ምን አለኝ
አለው "" ይላል ::
.
ታሪኩ እንዲህ ነው : እስራኤላውያን
ከሞአባውያን
ጋር ጦርነት ሊገጥሙ ነበር ::ይህን ጦርነት ሊያደርጉ
የነበሩት በበረሐ
ላይ ነው :: በዚያ በረሐ ውሀ ለፈረሶቹም ሆነ ሌሎቹ
የለም ነበር ::
በዚን ጊዜ የእስራኤል ንጉስ እንዲህ አለ : ውዮ
እግዚአብሔር
በሞአባውያን እጆ ሊጥለን ነው :: እነሆ እግዚአብሔርን
የምንጠይቅበት ነቢይ በዚህ አይገኝም እንዴ ? አለ
::ከእስራኤል ንጉስ
ባሪያዎች አንዱ እንዲህ አለ : በቅዱስ ኤልያስ እጅ ውሀ
ያፈስስ
የነበው የፋጥ ልጅ ኤልሳእ እዚህ አለ ብሎ ለንጉሱ
መለሰለት ::
የእስራኤሉ ንጉስ ኢየሳፍጥም :- እንዲህ አለ
የእግዚአብሔር ቃል
በእርሱ ይገኛል ( በቅዱሱ ነቢይ በኤልሳእ ) ከዚህ ቡሀላ
ንጉሱና
አሽከሮቹ ወደ ነቢዩ ኤልሳእ ጉዞ ጀመሩ :: ነቢዩ ኤልሳእም
መንፈስቅዱስ አለበትና ንጉሱ የሚለውን በሙሉ ባእቱ
(ገዳም ) ውስጥ
ሆን ያይ ነበረ :: በዚህን ጊዜ የእስራኤል ንጉስ ወደ እርሱ
መምጣቱን
ሲያውቅ ወዲያው ሊገናኘው ወጣና እንዲህ አለው
ለንጉሱ
""የእስራኤል ንጉስ ሆይ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ ""
አለው :: ይህንን
የትህትና ቃል ከተናገር ቡ
ሀላ ነቢዩ ቅዱስ ኤልሳእ ለንጉሱ
ጥሩ ዜና
ነገረው "" ንጉስ ሆይ ሞአባውያንን እግዚአብሔር
በእጃችሁ
ይጥልላቹሀል ብሎ ነገረው "" :: ተመልከቱ አንተ ሰው
ከአንተ ጋር ምን
አለኝ ማለት የትህትና ነው :: እንጂ ስድብ ቢሆን ኖሮ
የእግዚአብሔር
ታላቅ ነቢይ ቅዱስ ኤልሳእ እንዴት ይጠቀመዋል ? ከአንተ
ጋር ምን
አለኝ ማለት ግን የትህትና ስለሆነ ነቢዩ ቃሉን
ተጠቅሞታል ::
ንጉሱንም ከነበረበት ፍርሀት እና ጭንቀት እንዲወጣና
ደስታን በልቡ
ውስጥ አስርጾለታል ::
.
ስለዚህ እዚህም ጋር መጸሀፍቅዱስ
እንደሚነግረን አንተ ሰው ከአንተ ጋር ምን አለኝ ማለት
ንጉስ ሆይ
ከአንተ ጋር ምን ጸብ የለኝም የፈለግከውን አደርግልሀለው እታዘዝኻለሁ ማለት ነው ::
.
በአገራችንም እኮ ከአንት ጋር ምን አለኝ ? የጥያቄ
ምልክት ነው )
ካልን ከአንተ ጋር ጸብ የለኝም የፈለግከውን ጠይቀኝ
ማለት ነው ::ይህ
እንግዲህ በእኛም አገር የትህትና አነጋረት ነው ::
ጥቂቶች ግን
የአገራቸውንም ቁዋንቁዋ በአግባቡ ስለማያውቁት በዚህ
ቃል ይስታሉ
::
4ኛ . ሉቃስ ምህራፍ 4 ቁጥር 31 - 35 እንዲህ ይላል
"" ወደ
ገሊላም ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ :: በሰንበትም
ያስተምራቸው
ነበረ : ቃሉ በስልጣን ነበርና በትምህርቱ ተገረሙ ::
በምኩራብም
የርኩስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ነበረ በታላቅ ድምጽም
ጮሆ :-
የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለን ? ልታጠፋን
መጣህን ""
አሉት ይላል :: ተመልከቱ ወገኖቼ በሰዬው ላይ የነበሩት
አጋንንትም
የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለን ? አታጥፋን
እባክህን
ማለታቸው :: ከአንተ ጋር ምን ጸብ አለን ሲሉ ነው ::
ከአንተ ጋር ምን
አለን ማለታቸው ከአንተ ጋር ምንም ጸብ የለንም አታጥፋን ሂድ ወደምትለንኮ እንሄዳለን እንታዘዛለን
:: ሲሉት ነው ::
.
አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ማለት የትህትና
አነጋገር ነው
እንጂ የስድብ አይደልም ::
አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? (የጥያቄ ምልክት
ነው ) ማለት
የትህትና አነጋገር ነው ::
ሴት ማለት ደግሞ - ስጋሽ ከስጋዬ አጥንትሽ ከአጥንቴ
ማለት ነው
ኦሪት ዘፍጥረት ምህራፍ 2 ቁጥር 22 :: ስለዚህ ኢየሱስ
እርሱ
እግዚአብሔርም አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ብሎ
ቅድስት
ድንግል ማርያምን ሲጠይቃት እናቴ ሆይ ከአጥንትሽ
አጥንት ወስጃለሁ
(ነስቻለሁኝ ) ከስጋሽ ስጋን ነስቻለሁኝ
ከነፍስሽም ነፍስ ነስቻለሁ
እናቴሆይ ‹‹ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ››
ሉቃ 13÷9
ከአንቺ ጋር ምንም
ጠብ የለኝም ለአንቺማ የማላደርገው ምን አለ? የኔስ ጸብ ከኃጢአቶኖች ጋር ነው አንቺ ግን እንደቃልሽ ማድረግ ይቻልሻል እናቴሆይ አንቺ ከአዳም ዘሮች ዕዳ በደል ንጹህ ነሽና

የፈለግሸውን ጠይቂኝ ሲላት ነው ::
ለዚህም ነው
ልመናዋን ሰምቶ
አማላጅነትዋን ተቀብሎ ውሀውን ጣፋጭ የወይን ጠጅ
ያደረገው ::
እስቲ ለማንኛውም የዮሐንስ ወንጌል ምህራፍ 2 ከቁጥር
1- 12
ያለውን በግልጽ አስቀምጥላቹሀለውኝ :: ማስተዋሉን
የአብርሐም
የይስሐቅ የያእቅብ አምላክ እንደ እኔ ሐጢያትና ክፋት
ሳይሆን እንደ
ቸርነቱ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብሎ ይህንን
ለምታነቡ ወገኖቼ
ይግለጽላቹ ይግለጽልን አሜን ::
በተራ ቁጥር እንመልከተው ::
1ኛ . በሶስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበር ::
2ኛ . የኢየሱስም እናት ( ቅድስት ድንግል ማርያም )
በዚያ ነበረች ::
3ኛ . ኢየሱስም ደግሞ ደቀመዛሙርቱም ወደ ሰርጉ
ታደሙ ::
4ኛ . የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ : የኢየሱስ እናት
(ቅድስት ድንግል
ማርያም ) የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው ኢየሱስን
::
5ኛ . ኢየሱስም አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ጊዜዬ
ገና
አልደረሰም አላት ::
6ኛ . እናቱም ቅድስት ድንግል ማርያም ለአገልጋዮቹ
የሚላችሁን ሁሉ
አድርጉ አለቻቸው ::
7ኛ . ኢየሱስም ለአገልጋዮቹ 6 ጋን ውሀ ሙሉዋቸው
ብሎ ተናገረ ::
8ኛ . አይሁድም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ :;
9ኛ . ኢየሱስም አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት
አላቸው ::
10ኛ . አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሀ በቀመሰ
ጊዜ ከወዴት
እንደመጣ አላወቀም ::
11ኛ . አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ :- ሰው ሁሉ
አስቀድሞ
መልካውን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩ ቡሀላ
መናኛውን :: አንተስ
መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሀል አለው ::
12ኛ . ከዚህ ቡሀላ ኢየሱስ ከእናቱ እና
ከደቀመዛሙርቱም ጋር ወደ
ቅፍርናሆም ወረደ በዚያም ጥቂት ኖሩ :: ይላል ቃሉ ::
ቃል በቃል
ያደረግኩት ለሁላችንም በማያሻማ ሁኔታ ግልጽ እንዲሆን
ነው ::
እንግዲህ ወገኖቼ ኢየሱስ ክርስቶስ አንቺ ሴት ከአንቺ
ምን አለኝ ብሎ
የጥንያቄ ምልክት ሲያደርግ ? የጥያቄ ምልክቱ
የሚያሳየውን በጥሞና
መመልከት ይኖርብናል ::
እንደተመለከትነው ሴት ማለት ስጋሽ ከስጋዬ አጥንትሽ
ከአጥንቴ ነው
ማለት ነው ::
ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ሲል ደግሞ ከአንቺ ጋር ምን
ጠብ አለኝ ::
የፈለግሸውን አደርግልሻለሁኝ ማለቱ ነው :: ለዚህም ነው
አማላጅነትዋን ስለተቀበለ ነው ነጩን ውሀ ወደ ጣፋጭ
የወይን ጠጅ
የለወጠው :: አማላጅነቱዋን ባይቀበል ኖሮማ ውሀውን
ጠጅ ባላረገው
ነበር :: እንግዲህ እውነቱ ይህ ነው :: ቅድስት ድንግል
ማርያም
አማልጅ ናት :: አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ሲል
የትህትና
አነጋገር ነው ::
መናፍቃኑ እንደሚሉት አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ?
ማለት
ከሆነማ እነዚህን እስቲ ይመልሱልን :
1ኛ . መጸሀፈ ቀዳማዊ ምህራፍ 17 ቁጥር 17-24 አንድ
ሴት መጥታ
ቅዱሱን ባህታዊ ነቢይ ኤልያስን መጥታ አንተ
የእግዚአብሔር ሰው
ሆይ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ ? ብላ ጠየቀችው ::
ቅዱስ ኤልያስም
ይህን ባለችው ጊዜ የትህትና አነጋገር ነውና የሞተውን
ልጅዋን በጸሎቱ
አስነሳላት :: ይላል :: ታዲያ መናፍቃኑ እንደሚሉት
የትህቢት አነጋገር
ቢሆን ኖሮ ቅዱስ ኤልያስ እየተሰደበ የሞተውን ልጅዋን
አስነሳላት
ማለት ነውን ?
2ኛ . መጸሀፈ ነገስት ካልእ ምህራፍ 3 ቁጥር 13-20
ስትመለከቱ
የእስራኤሉ ንጉስ የሞአባውያን ንጉስ ሊወጋው ሰራዊቱን
መሳሪያ
አስታጥቆ ሲመጣ የእስራኤሉ ንጉስ ደግሞ የቅዱሱን
ነቢይ የኤልሳእን
እርዳታ ፈልጎ ወደ ቅዱስ ኤልሳእ በሄደ ጊዜ ቅዱስ
ኤልሳእ እንዲህ
ብሎ በትህትና ተናገረው :: የእስራኤል ንጉስ እኔ ከአንተ
ጋር ምን
አለኝ ? አለው :: ከዚያም ንጉሱን እረዳው :: ታዲያ ቅዱስ
ኤልሳእ
የእስራኤልን ንጉስ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ ? ስላለ ይህ
ስድብ
ነውን ? መንፈስቅዱስ ያለበት ይህ ታላቅ ነቢይ ተሳደበን ?
አንተ ሰው
ከአንተ ጋር ምን አለኝ የጥያቄ ምልክት ? ማለት ግን
የትህትና አነጋገር
ነው ::
3ኛ . ሉቃስ ምህራፍ 4 ቁጥር 31- 35 እርኩሳን
መናፍስት ኢየሱስን
አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ቅዱስ ኢየሱስ ሆይ ከአንተ ጋር
ምን አለን ?
ልታጠፋን መጣህን አለው :: ትያዲያ መናፍቃኑ እንደሚሉት
ከሆነ
ኢየሱስ በዚህ ቃል ላይ ተሰደበ ማለት ነዋ ! ስድብ ነው
እንዳይሉ
እንክዋን መጸህፍቅዱስ አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን
አለኝ ? ማለት
ስድብ ነው አይልም :: ማስተዋሉን ለሰጠን
ለእግዚአብሔር ክብር
ምስጋና ይግባው አሜን ::
ስለዚህ ወገኖቼ መጸሀፍቅድስ ስለዚህ ቃል መጸሀፍቅዱስ
ይህንን
የመሰለ መልስ ሰጥቷል :: ስለዚህ ይህን እውነት ይዘን
ለመሄድ
ያብቃን ::
"ማርያምን ለመዉሰድ
አትፍራ" ማቴ1፥20 ዮሀ19፥1
"መጽሐፍ ቅዱስ የብረት ቆሎ ነው የአበላሉን
ጥበ

ብ የማያውቅ ሰው ትርፉ ጥርሱን ማርገፉ ነው" እንዲሉ አበው በብሂላቸው ዛሬ ብዙዎቹ ጥርሳቸውን አርግፈው በድድ ቀርተዋል
የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል
ማርያም
አማላጅነት የቅዱሳንና የጻድቃን የሰማእታት ጸሎት እና
በረከት እና
ምልጃ እንዲሁም የቅዱሳን መላእክት እና ተራዳይነት እና
አማላጅነት
ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን ::
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ
መስቀሉ ክቡር ::

#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
https://telegram.me/And_Haymanot
✞ ✞ ✞ ✞ ነገረ ክርስቶስ ✞ ✞ ✞ ✞
(((((((((((ካለፈው የቀጠለ))))))))))))
#ስለ_እነርሱ_ሊያማልድ {ዕብ.፯፥፳፬}

@And_Haymanot

.....እርሱ ግን ለዘለዓለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ፤ ስለ እነርሱ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል ። ዕብ.፯፥፳፬

ስለ እነርሱ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል።

👉 ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመውሰድ አንዳንዶች ጌታችንን አሁንም አማላጅ አድርገው ሲናገሩ ይሰማሉ።
ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቱ ይህ አይደለም። ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው (ሰው ሆኖ በምድር ላይ) የማስታረቅን ሥራ ከራሱ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ፈጽሟል። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለ እውነታ ነው።
አሁንም አማላጅ ነው ማለት ግን ትልቅ ክህደት ነው። ለምሳሌ አምላካችን ጌታችን መድኀኒታችን ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ተርቧል ተጠምቷል ክብር ይግባውና በምድር ስለ ተራበ አሁንም ረሃብተኛ ስለ ተጠማ አሁንም ጥማተኛ ነው አንለውም። እንዲሁም በሥጋ የማስታረቅን ሥራ ስለ ሠራ አሁን አማላጅ አንለውም።

በመሠረቱ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከላይ ከዕብ.፯፥፲፩ ጀምሮ በደንብ ላስተዋለው ሰው አነጋገሩ በጣም ግልጽ ነው። ሐዋርያው የኦሪትና የሐዲስ ኪዳኑን ክህነት እያነጻጸረ ነው የጻፈው በሌዊ ክህነት ፍጹምነት እንዳልተገኘ የእነ አሮንም ሹመት እንዳለፈችና እንደ መልከ ጼዴቅ ሌላ ካህን ማስፈለጉን በዚህ ምክንያት በመልከ ጼዴቅ አምሳል ሌላ ካህን ከነገደ ይሁዳ መምጣቱንና ይህም በሊቀ ካህናችን በኢየሱስ ክርስቶስ መፈጸሙን ይናገራል።

ዕብ.፯፥፲፯ ላይም " እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘለዓለም ካህን አንተ ነህ " ሲል ያስምቀጠዋል ኦሪት ደካማ ስርዓት ስለነበረች ግዳጅዋን አልፈጸመችም ፍጹም የሰው ልጅ ድኅነት አልተገኘባትም ነበር ። ካህኑ ለኃጢአት ማስተስረያ እንስሳትን መስዋዕት አድርጎ የሚረጨው ደም የአዳምን የውርስ ኃጢዓት ሊያነጻ በፍጹም አልቻለም ነበርና በእሷ በኦሪት ፈንታ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት ተስፋ ገብቷል እያለ ነው ቅዱስ ጳውሎስ የሚያብራራው ።
ከታች ዝቅ ብሎ ዕብ.፯፥፳፬ ጀምሮ " እርሱ ግን ለዘለዓለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ስለ እነርሱ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና እርሱም እንደነዚያ(እንደ ኦሪቶቹ ) ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢዓት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢዓት ዕለት ዕለት መስዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጓልና " ( ዕብ.፯፥፳፯ ) ለነገሩ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መናፍቃኑ ለምንፍቅና ትምህርታቸው እንዲመቻቸው " ስለ እነርሱ ሊያማልድ ዘወትር ይኖራል " ብለው ያጣሙት እንጂ ቆየት ብሎ በታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ( 1960 ) ላይ ግን እንደዚህ አይደለም የተቀመጠው ትክክለኛው ቃል
"ክህነቱ አይሻርም ዘወትር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሊያድናቸው ይቻለዋል ለዘለዓለም ሕያው ነውና ያስታርቃቸዋል" ነው የሚለው ዕብ.፯፥፳፬-፳፭ ይህስ ቢሆን ምን ማለት ነው ?

👉 ጌታችን ራሱ መስዋዕት አቅራቢ ራሱ መስዋዕት ራሱ መስዋዕት ተቀባይ ሆኖ አንድ ጊዜ ብቻ ራሱን ባቀረበው ለዘለዓለም ኃጢዓታችንን ያስተሰርይልናል።
አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም ያለፈውንም ሆነ የሚመጣውን ትውልድ ለዘለዓለም ያስታርቀዋል እንጂ እንደ ኦሪቱ ስርዓት ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው " ዕለት ዕለት መስዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም " ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጓልና ስለዚህ እኛም ፍጹም ድኅነትን ያገኘነው አንድ ጊዜ በሠራልን የክህነት ሥራ ነው በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድራዊ ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷል ቆላ.፩፥፲፱ ተብሎ እንደ ተጻፈ።

ይህን የሠራልን የክህነቱ ሥራው ነው ዘወትር ሲያስታርቀን የሚኖረው አሁንም ያማልደናል ካልን ግን ክርስቶስ ዕለት ዕለት ኃጢዓት በሠራን ቁጥር መሞት አለበት ማለት ነው። ምክንያቱም ዓለም ፍጹም ድኅነት ያገኘችው በእርሱ ሞት ብቻ ነውና ወይም በሌላ አገላለፅ እንዲህ ማለት
ለምሳሌ ቅዱስ ጴጥሮስ አንካሳውን ሰውዬ " በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳና ተመላለሰ " ሲለው ተነሥቶ ተመላልሷል ጴጥሮስ " ተነሳና ተመላለሰ " ብሎ ሲናገር አንድ አንካሳ ብቻ ዳነ እንጂ ለዚህ አንካሳ የተነገረው ቃል በጴጥሮስ እጅ ለተፈወሱ ሌሎች ብዙ አንካሶች አልሠራም ማለትም ለሁሉም አንካሶች እንደገና ለእያንዳንዳቸው " ተነሳና ተመላለሰ " ተብሎ መነገር አለበት።

ይህ የሚያሳየው በፍጡራን አንድ ጊዜ የተነገረው ቃል ሥራ የሚሠራው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ማለት ነው።
የፈጣሪ ቃል ግን እንደዚህ አይደለም ፈጣሪ አንድ ጊዜ የተናገረው ቃል ለዘለዓለም ጸንቶ ነው የሚኖረው
ለምሳሌ እግዚአብሔር ዓለሙን ሲፈጥር ይሁን ይሁን እያለ ነው የፈጠረው ስለዚህ ፍጥረት ሁሉ ይኸው አንድ ጊዜ በተናገረው ቃል እስከ ዕለተ ምፅዓት ሁኑ እንዳላቸው ሆነው ተገኝተዋል "ቀንና ሌሊት ይለዩ " ዘፍ.፩፥፲፬ ብሎ አንድ ጊዜ ብቻ በተናገረው ቃሉ ይኸው ቀንና ሌሊት እየተፈራረቁ ነው ይህም በፈጣሪ አንድ ጊዜ የተነገረው ቃል ዘለዓለማዊ ሥራ እንደሚሠራ ነው የሚያሳየን።

እናም " ለዘለዓለም ሕያው ነውና ያስታርቃቸዋል " ወይም መናፍቃኑ እንደሚሉት " ሲያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል " ተብሎ ቢነገርም እንኳን ትርጉሙ ከዚህ ከላይ ካየነው የተለየ አይደለም " ራሱን መስዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ ፈጽሞ አድርጓልና " እንደተባለው ጌታችንም " የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው " ብሎ ማስታረቅን ያጠቃለለበት ያው አንዴ የተናገረው የምልጃ ቃል ክርስቶስ ደጋግሞ ሳያማልድ የሚመጣውንም ሁሉንም ትውልድ የሚያስታርቅ ነው።

ተፈጸመ ያለውም ይህንኑ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታረቀበትን ሥራ ነው ያው አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ የተነገረ ቃል የአምላክ ቃል ነውና ለዘወትር ይጸናል።
ልክ እግዚአብሔር " ቀንና ሌሊት ይለዩ " ብሎ አንዴ በተናገረው ቃል መሠረት ቀንና ሌሊት እየተፈራረቁ እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ እንደሚቆዩ ማለት ነው። ከዚህ ውጪ ግን ክርስቶስ ያን በሞቱ አንድ ጊዜ የፈጸመውን የማዳን የማስታረቅ ሥራ አሁንም ይሠራል ብሎ ማመን ከኑፋቄም በላይ ክህደት ነው የእግዚአብሔርንም ፍቅሩን አለማወቅም እኛም አልዳንም ክርስቶስም እንደ ገና መጥቶ መሞት አለበት ማለት ነው።

👉 በአጠቃላይ ሐዋርያት የክርስቶስን ስም ከምልጃ ጋር ቢጠቅሱም እንኳን እስካሁን ባየነው መልኩ ነው መታየት ያለበት ከዚህ ውጪ ግን ራሱ ጌታችን ለሐዋርያት በዚያች ቀን ( ከትንሳኤ በኋላ)

ዮሐ.፲፮፥፳፮ በስሜ ትለምናላችሁ እኔም ስለ እናንተ አብን አለምንም ብሏቸው እያለ " አይ አንተ ከትንሳኤ በኋላ ታማልዳለህ " ብለው አይቃወሙትም " ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ " ያላቸውን አምላክ ጠንቅቀው ያውቁታል ደግሞስ ቅዱስ ጳውሎስ

፪ቆሮ.፭፥፲፮-፲፰ " ክርስቶስ ከትንሳኤው በኋላ በሥጋው ወራት እንደምናውቀው ከእንግዲህ ወዲያ እኛም ሐዋርያቱ ብንሆን በሥጋ እንዳወቅነው አናውቀውም "በማለት ነው የጻፈው እንዲያውም እዚያው ላይ ቁጥር ፲፱ ጀምሮ " በእኛም የማስታረቅን ቃል አኖረ የማያስታርቅን ሥልጣን ለእኛ ሰጠን እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ዕወቁ
" ነው ያለው።

👉 በመሆኑም የክርስቶስ የማያስታርቅ ሥራ የማማለድ አገልግሎት በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙ በመስዋዕትነት ተፈጽሟል ።
" ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን ( ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ) ጋር በሥልጣን በአገዛዝ በሕልውና አንድ ስለ መሆኑ ( የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ( የሦስትነት እና የአንድነት ስማቸው ) ነው።

👉 አንድም ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ( ሥጋን ለብሶ ሰው ሆኖ ) ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር። (ኀላፊ ቃል) በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር። በእኛም የማያስታርቅን ቃል አኖረ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን እናማልዳለን ፪ቆሮ.፪፥፲፰-፳፩

በሌላ አገላለጽ ቅዱስ ጳውሎስ ለምን እንዲህ ጻፈ ብንል በምድር ላይ አንድ ጊዜ የፈጸመውን የማያስታርቅ ተግባርን ለመግለፅ ነው። እንዴት ብንል መጽሐፍት ምስጢርን እንጂ የአፃፃፍ ዘይቤን ጠብቀው ስላልተፃፉ ነው።
ይህም ያለፉና የተፈፀሙ ድርጊቶችን ወደ ፊት የሚፈፀሙ አስመስለው ይፅፋሉ። እንዲሁም አንድ ጊዜ የተፈፀሙትን ወደ ፊት ቀጣይነት ያላቸው አስመስሎ መፃፍ የመፅሐፍት ባሕሪ ነው። በምሳሌ እንመልከት

ኢሳ.፷፭፥፲፯ እነሆ አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር እፈጥራለው።
ይህ ቃል እግዚአብሔር ፈጥሮ ያዘጋጃትን አዲስ ሰማይና ምድር የተባለችውን መንግስተ ሰማይን ወደ ፊት እንደሚፈጥር አስመስሎ ይናገራል።

ኢሳ.፶፫፥፩ ላይ ጌታችን ሳይወለድ 700 ዓመት በፊት መከራን ሳይቀበል መከራን እንደተቀበለ አድርጎ ፅፎታል። እንዲሁም

ኢሳ.፱፥፮ ላይ ክርስቶስ ሳይወለድ እንደተወለደ አድርጎ ይናገራል።

ይሁዳ.፩፥፯ እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶም እና ገሞራ በዙሪያቸው የነበሩ ከተሞች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል። ሰዶም እና ገሞራ አንድ ጊዜ ተቀጥተው እንደጠፋ በዘፍ.፲፱ ተፅፏል። ነገር ግን ይህ ተግባር ቀጣይነት ያለው ተግባር በሚመስል መልኩ ተፅፏል። እየተቀጡ ብሎ

ስለዚህ በዚህ መሠረት በዕብ.፯፥፳፭ ላይም አንድ ጊዜ የተፈፀመን የማማለድ ተግባር ቀጣይነት ያለው አስመስሎ ተፅፏል። ፈጥሮ እፈጥራለው ፣ ሳይወለድ ተወለደ ፣ ተቀጥተው እየተቀጡ ካለ አማልዶም ሊያማልድ ቢል ይህ የመፅሐፍ የአፃፃፍ ባሕሪ ነው ። ወስብሀት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞_✞_✞
በነገረ ክርስቶስ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተከታታይ ትምህርት እየሰጠን ነው
፩ ሃይማኖት
@And_Haymanot
@And_Haymanot

~ ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው(፩&፪)
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/241
@And_Haymanot

~ጌታን እንደ ግል አዳኝህ ተቀበል
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/250

@And_Haymanot

~መዳን በኢየሱስ ነው
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/250

@And_Haymanot

~ ከእኔ አብ ይበልጣል
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/256

@And_Haymanot

~በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/260

@And_Haymanot

~ስለኛ የሚማልደው
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/264

@And_Haymanot

~ስለ እነርሱ ሊያማልድ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/273

@And_Haymanot
@And_Haymanot

ሌሎች ጥያቄዎችም በስፋት ይቀጥላሉ
@And_Haymanot
ምላሾቹ የሚያሥፈልጋቸው አሉና ያጋሩ
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞_✞_✞
✞ ✞ ✞ ✞ ነገረ ክርስቶስ ✞ ✞ ✞ ✞

‹‹በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ››ማቴዎስ 10፡34

@And_Haymanot

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ብዙ ጊዜ ከላይ እንደመነሻ ያደረኩትን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ንግግር ሙስሊም ወገኖቻችን ከወንጌል እየጠቀሱ ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ የመጣው ሰላምን ለማምጣት ሳይሆን ሁከትን ሽብርን መለያየትን እና በሰይፍ ክርስቲያኖች ሌሎች እምነት አማኞችን እንዲያርዱ እንዲገሉ ነው በማለት በራሳቸው መንገድ በጌታ ቃል ላይ ሲፈላሰፉ እንመለከታለን ፡፡
👉 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ የመጣው ሰላምን አንድነትን ህብረትን ሊመሰርት እንጂ ጠብን መለያየትን ሊያመጣ እንዳልሆነ በመፅሐፍቅዱስ ላይ የሰፈረ እውነትም ሆኖ በምድራችን ላይ በተግባር ያየነው ሀቅ ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ገነፍሷ ነፍስን ነስቶ በመጣ ጊዜ በልደቱ መላእክት ከብቶቻቸውን ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች ‹‹እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና አትፍሩ›› ሉቃ 2፡10 በሚል በሚያሳርፍ የምስራች መልካም ቃል አዋጅን ካወጁ በኋላ መላእክቱ በጌታ መወለድ ከእረኞች ጋር አዜሙ ‹‹ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ››ሉቃ2፡14፡፡

👉 ይህም ሰላም ከሰማያት የመጣ ምስጋናውም አርያም ደርሶ ለሰው ልጆች በልደቱ አማካኝነት ጌታ ሰላም አጥተው የነበሩትን ህዝቦች በሰላም ዝናብ ሊያረሰርስ ተለያይተው የነበሩትን አንድ ሊያደርግ በልደቱም ሰላምን እናደረገ በወንጌል ሰፍሯል ይህ ሰላም አለም እንደሚሰጠው ያለ ሰላም አይደለም የአለም ሰላም ስናገኝ ሲኖረን ስናጣ ከኛ የሚርቅ ጊዜያዊ በጤዛ የተመሰለ ስሙ ሰላም ተብሎ ተሰይሞ ሰላምን የማይወክል ከቃላት ያላለፈ ሰላም ነው የምትሰጠን የጌታ ሰላም ግን እንዲህ አይደለም ለዘለአለም ከእኛ ጋር ታትሞ ገንዘባችን ሆኖ የልባችንን መሻት በደስታ እና በሀሴት የሚሞላ ከስሜታችን በላይ የሆነ ሰላም ነው ፡፡

👉‹‹ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።››ዮሐ 14፡27 መፅሐፍ ቅዱስ ስለሰላም“ያለ ሰላም እግዚአብሔርን ማየት የሚችል የለም” ይላል /ዕብ. 12፥14 /ሰው ያለ ሰላም ማየት የማይችለው እግዚአብሔርን ብቻ አይደለም። ባልንጀራውንም ያለሰላም ማየት አይችልም። ሰላም የሌላቸው ወገኖች ሊተያዩና ሊነጋገሩ አይችሉም።
ሰውን ከሁሉ ነገር ማስቀደምና ማፍቀር የሚገባው ፈጣሪውን እግዚአብሔርን እንደሆነ ተጽፎአል። እንዲሁም ከሆነ ከሁሉ ነገር በላይ ለሰላም ቅድሚያ መስጠት ያስፈልገዋል። “እግዚአብሔር ሰላም ነው” “ክርስቶስ ሰላማችን ነው።” ተብሎአልና። መሳ. 6፥24፣ ኤፌ .2፥14
ይህ ሁሉ ሰላም በክርስቶስ ከክርስቶስ የሚገኝ ውስጣዊ በውጭ ልንገልፀው የማንችለው ለጠላቶቻችን እንድንራራ እንድናዝን እንድናፈቅር የሚያነሳሳን ሰላም ነው፡፡ጌታ ሰላምን ለማምጣት ከመጣ መፅሐፍ ቅዱስም ስለሰላም አጥብቆ ከሰበከን እና ከተናገረን ታድያ ስለምን ጌታ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም አለ?ስለሰይፍስ ተናገረ?
ከማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 10 ከቁጥር አንድ ጀምሮ አውዱን ስናነበው ጌታችን ኢየሱስ ቅዱሳን ሐዋርያቱን ጠርቶ በአጋንንት እና በአጋንንት ሀይላት ደዌያት ላይ ስልጣን ከሰጣቸው ስማቸውንም በመንፈሳዊ ግብር ከቃኘላቸው በኋላ ስለሱ የሚደርስባቸውን መከራ ችግር ስቃይ ስለስሙ መነቀፍ እንደሚያገኛቸው ያ መነቀፋቸው ምድራዊ እንጂ ሰማያዊ እንዳልሆነ ሰማያዊው የሆነ ዘላለማዊ ህይወት ከአባታቸው ዘንድ እንደተዘጋጀላቸው ያለ ፍርሀት ስለስሙ እንዲመሰክሩ በስሙም የሀጢያት ስርየት እንዳለ ስሙ አጋንንት የሚፈሩት ምእመናን የሚወዱት አህዛብ የሚጠሉት ስለስሙ በአህዛብ በአላውያን ነገስታት እና በአይሁድ ዘንድ ተላልፈው ለእስር ለእንግልት እንደሚሰጡ በሰይፍ እንደሚቀሉ በሸንጎ እንደሚዳኙ በድንጋይ እንደሚወገሩ ነጓሯቸው በዚህ ሁሉ ግን እሱ ከእነሱ ጋር እንዳለና በመከራቸው መንፈስ ቅዱስ እንደሚረዳቸው ሰማያዊ ተስፋቸውን ሰጥቷቸው እንዳይፈሩ ነግሯቸው ስለስሙ የሚመሰክሩትን በሰማዩ በአባቱ ፊት እና በመላእክቱ ፊት ለፍርድ ሲቀርቡ መስክሮ እንደሚፈርድላቸው አረጋግጦ ነግሮ የሚክደውን እንደሚክደው አሳስቦአል ፡፡

👉 ከዚህ በኋላ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም ሲል በአማኞቹ የሚደርሰውን መከራ ስቃይ ስደት በትንቢት መልክ ተናግሯል ማለትም ከላይ ሙሉ ምእራፉን እንዳየነው በሱ የሚያምኑ በአላውያን ነገስታት መናፍቃን እና አህዛብ ዘንድ መከራ ስለሚደርስባቸው ምድራዊ የሆነ ሰላም አማኞቹ በክርስቶስ በማመናቸው ምክንያት እንደሚያጡ በተለይም ከአንደኛው መቶ ክፍለዘምን አንስቶ እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ባሉት አመታት ክርስትያኖች ይደርስባቸው የነበረውን መከራ እና ስደት በታሪክ እና በሐዋርያት ስራ መፅሐፍ እንደምናነበው ከበከራው ብዛት የተነሳ እኔና እናንተ ሰላም ብለን ከምናስበው ምድራዊ ኑሮ ርቀው ከአንዱ አገር አንዱ አገር ተሰደው በመከራ እና በስደት በጭንቀት እንደኖሩ ይህ ውጫዊ ሰላም ማጣት እንደሚደርስባቸው ስሙን በማመናቸው ሰላምን ለማምጣት የመጣው እንዳይመስላቹ ብሎ ጌታችን ክርስቲያኖች እሱን በማመናቸው ምክንያት ስለሚደርስባቸው መከራ ተናገረ፡፡ሰይፍን እንጂ ማለቱም እሱን በማመናቸው ምክንያት ክርስቲያኖች የሚደርስባቸውን መከራ ችግር ስቃይ በሰይፍ መቀላት እና ስለሱ ሰማእት ሆኖ መሞትን መናገሩ ነው ፡፡ አንድም ሰይፍ አንድን ነገር ከአንድ ነገር እንደሚለይ ሁሉ በክርስቶስ በማመናቸው ከሀገራቸው በስሙ ካላመኑ ቤተሰቦቻቸው እንደሚለዩ ሀብት ንብረታቸውን ስለስሙ ጥለው እሱን ብቻ አምነው እንደሚከተሉት መከራ የተባለ መስቀሉን ተሸክመው አሰረ ፍኖቱን ይዘው እንደሚያምኑት የተናገረበት የወንጌል ክፍል ነው ፡፡ስናጠቃልል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ የወንጌል ክፍል ሙሉ ምእራፍ እያስተማረ እያሳሰበ ያለው ስለስሙ ስለሚነቀፉ ስለሚሰደዱ ስለሚታረዱ ክርስቲያኖች እንጂ በተቃራኒው ስለሚያርዱ ስለሚያሳድዱ ሰላም ስለሚያሳጡ ክርስቲያኖች የተናገረው አይደለም ፡፡ ምክንያቱም በመፅሀፍ ቅዱስም ሆነ በታሪክ በቅዱሳን ገድላት ጨምሮ እስካሁኑ ዘመን ድረስ ክርስቲያኖች ሲሳደዱ እንጂ ሲሰደዱ አላየንም ምድራዊ ሰላም ሲያጡ እንጂ ሲያሳጡ አልተመለከትንም ሲታረዱ እንጂ ሲያርዱ አልሰማንም ይልቁንስ ሰላም ያጣውን ህዝብ በወንጌል አማካኝነት ሰላም ሲሰጡ የሚረግሟቸውን ሲመርቁ ለሚያሳድዷቸው ስፀልዩ ጠላቶቻቸውን ሲወዱ ነው ያየነው ይህም ከመምህረ ትህትና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበሉት እና ገንዘብ ያደረጉት ዘላለማዊ የሆነ በሰላም የተቃኘ እውነት ነው ፡፡፡

👉 ስለክርስቲያኖች ስደትና መከራ ተጨማሪ የሚጠኑ ጥቅሶች፡- 2ቆሮ 6፡5 ፤ 4፡17-18 ፤ 7፡4-6 ፤ 8፡2 ፤ ገላ3፡4 ፤ ኤፌ 3፡13 ፤ ፊል 1፡17 ፤ 1፡29 ፤ 3፡10 ፤ 4፡14 ፤ ቆላ 12፡14 ፤1ጴጥ2፡20 ………ሐዋርያት ስራ ሙሉውን እና የሐዋርያቱን መልእክታት ማየት መመልከት ያስፈልጋል፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
በክርስቶስ ኢየሱስ የተከፈለልን ቤዛነት እና የቅዱሳን ምልጃ!

@And_Haymanot
ክፍል ፩
በኦርቶዶክስውያንና በፕሮቴስታንት በካከል ካሉ የእምነት ልዩነቶች አንዱና ዋነኛው የምልጃ ትምህርት ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ አላማም ስለምልጃ ማብራሪያ ለመስጠት ሳይሆን ልዩነቶቻችንን ነቅሶ ለማውጣትና ከልዩነቶቻችን በመነሳት ለፕሮቴስታንት ወገኖቻችንን መልስ የሚሻ ጥያቄ ማንሳት ነው፡፡

👉 1. አማላጃችን ማነው?

ኦርቶዶክስ፡- በምድርም በሰማይም ያሉ ቅዱሳን!
ፕሮቴስታንት፡- አንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ!
ጥያቄ ለፕሮቴስታንቶች
1.1) አማላጅነት በምድርም በሰማይም አለ፤ በምድር በሕይወት ያሉ የሰው ልጆች /ቅዱሳን/ ያማልዳሉ፤ በሰማይ ደግሞ ኢየሱስ ያማልዳል በሚለው አስተሳሰብ ብዙ ፕሮቴስታንት ይስማማሉ፡፡ ጥቂቶች ባይስማሙም /አማላጃችን አንድ ኢየሱስ ብቻ ነው ቢሉም/፡፡ አማላጅ አንድ ኢየሱስ ብቻ ነው? ወይስ ምልጃ በምድርም በሰማይም ይሰራል?

1.2) ምልጃ በሁለቱም ካለ በምድር ያሉ የሰው ልጆች /ቅዱሳን/ ምልጃ እና በሰማይ በኢየሱስ የሚደረግ ምልጃ አንድነት ወይም ልዩነት እንዴት ሊብራራ ይችላል? ማለትም የቅዱሳም ምልጃ ልመና ነው፤ የኢየሱስም ምልጃ ልመና ነው፤ ስለዚህ ተመሳሳይ ነው፤? አሊያም የቅዱሳኑ ምልጃ ልመና ነው፤ የኢየሱስ ምልጃ ግን ከዛ በላይ ነው፤ ይለያያል ብሎ ማብራራት ይቻል ይሆን?

👉 2. አማላጅነት ምን ማለት ነው?

ኦርቶዶክስ፡- አማላጅነት በሁለት ይከፈላል፡፡ የልመናና የተገብኦ በመባል፡፡
#የተገብኦ_ልመና ማለት ክርስቶስ በስጋው ወራት የፈጸመው ምልጃ ነው፡፡ ይህ ምልጃ የሰው ልጆችን ከማዳን ስራው ጋር የሚጠቃለል ነው፡፡ በጸሎት /ልመና/ ብቻ ሳይሆን በመከራ ጭምር የተፈጸመ ፣ በቤዛነት የተዋጀ፣ በሞት የተቋጨ ነው፡፡ በንጹሕ ደሙም መፍሰስ የኃጢያት ስርየት ያገኘንበት ነው፡፡ ቤዛነት ማለት ስለሌላው /ስለአዳምና ልጆቹ የተከፈለ ዋጋ ማለት ሲሆን መዋጀት ስንል መልሶ መግዛት ወይም ወደቀደመ ክብር መመለስ ማለታችን ነው/፡፡ ይህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የተፈጸመና ቅዱሳኑን ጨምሮ ሁላችንም የሰው ልጆች ድህነት ያገኘንበት ነው፡፡ ይህን በክርስቶስ በተገብኦ የተፈጸመ ምልጃ ከቅዱሳን ምልጃ ጋራ በንጽጽርና በምርጫ የማይቀርብ የመዳናችን ምስጢር ነው፡፡

#የቅዱሳን_ምልጃ፡- አንዱ ስለሌላው የሚያደርገው ጸሎት ነው፡፡ “ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ስለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በስራዋ እጅግ ኃይልን ታደርጋለች“ ያዕ.5፣16፡፡ ይህ ጸሎት ሁላችንም ዕለት ዕለት አንዳችን ስለሌላው በመጸለይ የምንፈጽመው ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው፡፡ ለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ የጥቅስ ማስረጃ መደርደር ጊዜ ማጥፋት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ምድር ላይ ስለሌላው የማይለምን፣ እኔን ብቻ ማረኝ ስለሌላው አያገባኝም ያለ ክርስቲያን ኖሮ አያውቅም፤ የለምም፡፡ ለዚህ ምስክሮች እኛ ሁላችን ነንና! ሁላችንም አንዳችን ስለሌላው የምናደርገው ጸሎት /ልመና/ ምልጃ ይባላል፡፡ ታዲያ ይህ ጸሎት ማንም ሰው የሚያደርገው ከሆነ ኦርቶዶክሳውያን በቅዱሳን ጸሎት መታመናችን አማልዱን ማለታችን ለምን ይሆን ቢሉ፤-
የጻድቅ ጸሎት በስራዋ እጅግ ኃይልን ታደርጋለችና ነው! ጸሎት ሁሉ እኩል መልስ አያመጣም፡፡ እኩል ኃይል የለውምም፡፡ የጻድቃን ጸሎት ግዳጅ ትፈጽማለች በስራዋም እጅግ ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ያዕ.5፤16 ፡፡ ይህ ልዩነት እግዚአብሔር አድሎ ያለበት ሆኖ ሳይሆን የቅዱሳን የእምነታቸውና የጽድቃችው ኃይል ነው፡፡
ስለቃልኪዳናቸው ነው፡፡ እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር የሚፈጽመው ቃልኪዳን ለትውልድ የሚሰራ ነውና፡፡ እግዚአብሔር ከወደደው ጋር ቃልኪዳን ይፈጽማል፡፡ ቃልኪዳኑም ይጠብቃል፤ በቃልኪዳኑ ይታመናል፤ ይምራልም፡፡ ስለሆነም በድፍረት ሳይሆን በትህትና፤ በብልጠት ሳይሆን በየዋህነትና በእምነት በቅዱሳን ቃልኪዳን ብንታመን ከቃልኪዳኑ ባለቤት ከእግዚአብሔር ምህረት እናገኛለንና ነው፡፡
ፕሮቴስታንት፡- በፕሮቴስታንት ዘንድ ግልጽ ያለ አስተምህሮ አይታይም፡፡ ምልጃን ከድህነት ጋር የሚያያይዙ ፕሮቴስታንቶች አማላጃችን ኢየሱስ ብቻ ነው ሲሉ፤ ምልጃን ከልመና ጋር የሚያያይዙና ለራሳቸው የምልጃ ጻሎት መልስ መስጠት የሚፈልጉ ፕሮቴስታንቶች ምልጃ በምድርም በሰማይም አለ ይላሉ፡፡ በምድር በስጋ ያሉ ሰዎች /እኛ/ ፤ በሰማይ ደግሞ በኢየሱስ ይፈጸማል ይላሉ፡፡ በዚህም የምልጃን ሰንሰለት ያረዝማሉ፡፡ ለአማኞቻቸው አገልጋዮቹ ወደኢየሱስ ያማልዳሉ፤ ኢየሱስ ወደአብ ያማልዳል፡፡ ምንም እንኳን ፕሮቴስታንት ወገኖቼ ብዙ ጊዜ ስለምልጃ ሲነሳ ምን ዙሪያ ጥምጥም አስኬደኝ፤ በቀጥታ ኢየሱስ ጋር መቅረብ እየቻልኩ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ነገር ግን በተግባር ሲታይ የፕሮቴስታንት የምልጃ ሰንሰለት ከኦርቶዶክሳውያን ይረዝማል፡፡ ምክንያቱም በኦርቶዶክስ ልመና ሁሉ ክርስቶስ ጋር ይቆማል፡፡ ለአብ ያለው ሁሉ የወልድ ነውና! በፕሮቴስታንት ግን ኢየሱስ የአማላጅነት ሚና ይኖረውና ልመናን ወደ አብ ያደርሳል፡፡ ምልጃን በሚመለከት በፕሮቴስታንቱ ዘንድ ግልጽ ያለ ዶክትሪንና አስተምህሮ እንደሚያስፈልግ ክፍተቱ ያመላክታል፡፡ በዝርዝር ከታች ተመልክቷል፡፡

👉 3. ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው ወራት አማልዷንል? ዛሬስ ያማልዳል?
3.1. ኦርቶዶክስ፡- በርግጥም ክርቶስ በስጋው ወራት ምልጃን ፈጽሟል፡፡ ይህ የተገብኦ ምልጃ የክርስቶስ የማዳን ስራው አንዱ አካል ነው፡፡ በስጋው ወራት የፈጸመውም ምልጃ የአማላጅነት ሚና ብቻ ካላቸው ከቅዱሳን ምልጃ ይለያል፡፡ ስለኃጢያት ይቅርታ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የቆሙ ብዙ ነቢያት ነበሩ፡፡ የነርሱ ልመና ጊዜያዊ እርቅ እንጂ ፍጹም መዳንን አላመጣም፡፡ የክርስቶስ ምልጃ የተገብኦ ነው ሲባል የነቢያትን፤ የኦሪት ካህናትን ልመና ሁሉ የሚወክልና የሚጠቀልል ነው፡፡ ጌታ ስለነቢያቱ ተገብቶ የፈጸመውና በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ፍጹም እርቅን ያስገኘ ነው፡፡ ይህ ምልጃ ከርሱ በፊት ሲለምኑ ስለበሩት ስለነቢያት ተገብቶ የፈጸመው ካሳ ነው፡፡ የክርስቶስ የማዳን ተግባሩ ልመና ብቻ ሳይሆን የመስቀልን መከራ በተገብኦ /በኃጢያተኛው ምትክ ስለኃጢያተኛው/ መከራ በመቀበል የተፈጸመበትና በሞት የተቋጨ ነው፡፡ ለዚህ ነው ጌታ በመስቀል ላይ ተፈጸመ ያለው፤ ዮሐ.19፤30፡፡
ማንም በክርስቶስ ድኛለሁ የሚል መዳኑ ስለነቢያቱ ተገብቶ በፈጸመው የካሳ ምልጃ ብቻ ሳይሆን፣ በቤዛነቱ፣ በመከራውና በሞቱም ጭምር ነው ብሎ ሊያምን ይገባዋል፡፡ ክርስቶስ በስጋው ወራት የፈጸመውን ምልጃ ከማዳን ስራው መነጠል አይቻልም፡፡ መዳን በክርስቶስ ምልጃ ብቻም አይባልም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ንጹሕ ደሙን ማፍሰስ መሞት ሳያስፈልገው በምልጃው ብቻ ባዳነን፡፡ ይህ ምልጃ የተፈጸመው ክርስቶስ የአማላጅነት ሚና ብቻ እንዳላቸው እንደቅዱሳን በመሆኑ አይደለም፡፡ የእርሱ ሚና መለመን የአብ ሚና ማለት ስለሆነም አይደለም፡፡ ክርስቶስ ጸለየ፤ ለመነ ብለን ይቅር አለም እንላለንና፡፡ አርሱ የለመነው ይቅር ማለት የማይችል ሆኖ ሳይሆን ይህ እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን የተጓዘበት መንገድ ነው፡፡
በሰው ልጅ የመዳን ጉዞ ድህነት የተፈጸመው ስለአዳም ኃጢያት ፍጹም ካሳ በመክፈልና፤ በፍርድ ነው፡፡ በአዳም ኃጢያት እግዚብሔር ተበድሏል፣ አዳም በድሏል፡፡ ድህነት ይፈጸም ዘንድ የበደለው አዳም ስለኃጢያቱ ካሳ መክፈልና ፍርድን መቀበል ነበረበት፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ሐጢያትን ምን ያህል እንደሚጸየፍና ከሐጢያት ፍጹም የራቀ ቅዱስ መሆኑን ተረጋገጠ፤
👍1
ኢየሱስ ክርቶስ ከቤተልሔም እስከቀራንዮ ያደረገው ጉዞ ስለአዳም ኃጢያት የተከፈለ ዋጋ ነውና፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር በጽድቅ የሚፈርድ መሆኑን አረጋገጠልን፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ኃጢያት ቅጣት አለው፡፡ አዳም ስለበደለው ኃጢያት ይቅርታ እንዲያገኝ ቅጣት ይገባዋል፡፡ እግዚአብሔር የአዳምን ኃጢያት ያለቅጣት ይቅር ብሎ ቢሆን ኖሮ፤ በኃጢያቱ የተበየነበት ፍርድና በይቅርታ ያገኘው ጽድቅ በእኩል ሁኔታ ከእግዚአብሔር ተገኙ ያስብላል፡፡ አምላክ ሰው በመሆኑ፤ ስለኃጢያት ፍርድን በመቀበሉና ካሳ በመክፈሉ የእግዚአብሔር ፍትሐዊነቱንና ቅድስናው ተረጋገጠ፡፡ ዳግማዊው አዳም ኢየስስ ክርስቶስ የአዳምን ኃጢያት ተሸክሞ በቀራንዮ ፍርድን ተቀበለ፡፡ የነቢያቱን አንደበት አንደበቱ አድርጎ ስለርሳቸው ተገብቶ ልመና አቀረበ፤ ምልጃን ፈጸመ፤ ቤዛም ሆነን፤ ተራበ፤ ተጠማ፤ ታመመ፤ ሞተም፡፡ በንጹሕ ደሙ መፍሰስ ኃጢያታችንን አጠበ፤ በሞቱ ሞትን ሻረ፡፡ በዚህም ፍጹም ድህነት ተገኘ፡፡ አዳም በኃጢያቱ ምክንያት ያጣውን ጸጋ በዳግማዊው አዳም በክርስቶስ ተመለሰንል፡፡
ይህም የማዳን ተግባሩ አንድ ጊዜ የተፈጸመና ለዘለዓለም የሚሰራ ነው፡፡ አንድ ጊዜ የፈሰሰው ደሙ ኃጢያትን ፈጽሞ የማስወገድ ኃይል አለውና! በስጋው ወራት የፈጸመው ይህ የተገብኦ ምልጃ እስከዘለዓለም ህያው ሆኖ በእርሱ ያመኑትን ሁሉ ሲያድን ይኖራልና! አንድ ጊዜ ለዘለዓለም በፈጸመው በዚህ ማዳኑ ሕይወት ካገኘን በኋላ ክርስቶስ ዛሬ ያማልዳል ማለት ስህተት ብቻ ሳይሆን ክህደትም ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ስርስቶስ ፍጹም የሆነ ሊቀካህናት ነውና፡፡ ፍጹምነት እንደሚጎድላቸው እንደ ብሉይ ኪዳን ካህናት ዛሬም ዕለት ዕለት የምልጃ መስዋዕት ማቅረብ የማያስፈልገውና ራሱን አንድ ጊዜ ለዘለዓለም መስዋዕት በማቅረብ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ሊቀካህናት ነውና! ያቀረበውም መስዋዕት ፍጹምና አንድ ጊዜ ለዘለዓለም የሚሰራ ነው! ስለሆነም ዛሬም ድረስ ዕለት ዕለት የምልጃ መስዋዕት መሰዋት አላስፈለገውም፡፡ ዛሬም በስጋው ወራት እንደነበረ በሰማይ አባት ሆይ እያለ አይለምንም፡፡ ይህን አንድ ጊዜ ለዘለዓለም ፈጽሟልና!
በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ያማልዳል ማለት በስጋው ወራት የተፈጸመው ምልጃ ዛሬም አልተቋጨም ማለት ነው፤ ክርስቶስ በስጋው ወራት ያደረገው ምልጃ ዛሬም በሰማይ ዕለት ዕለት እየደጋገመ ይፈጽማል ማለት ነው፡፡ እንዲህ ብሎ ማመን በዕለተአርብ የፈጸመውን የማዳን ስራ ከንቱ ማድረግ ነው፡፡ ይህንን ስህተት ብቻ ሳይሆን ክህደትም ነው፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ ስጋው ወራት የፈጸመውን የተገብኦ ምልጃ ፍጹምነት የጎደለው ያደርገዋልና ነው፡፡ ክርስቶስንም ፍጹምነት እንደጎደላቸው እንደ ብሉይ ኪዳን ካህናት ዕለት ዕለት የምልጃ መስዋዕት የሚያቀርብ ያደርገዋልና፡፡
በስጋው ወራት የተፈጸመው ይህ የተገብኦ ምልጃ፤ የተፈጸመው እርቅ ፍጹም በመሆኑ አይደገምም፣ አይከለስም፡፡ ክርስቶስ ልመናቸውና መስዋዕታቸው ፍጹምነት እንደጎደለው እንደ ብሉይ ኪዳን ካህናት አንድ ጊዜ መስዋዕት ከሆነ በኋላ ለሁለተኛ፤ ለሶስተኛ፤ ለአራተኛ…ጊዜ ዕለት ዕለት ለምልጃ አይቆምም፡፡ በዕለተ አርብ አንድ ጊዜ ለዘለዓለም የፈጸመው የተገብኦ ምልጃና መስዋዕት እስከዓለም ፍጻሜ ህያው ሆኖ ሲያድን ይኖራል!
ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ያማልዳል የሚሉ በክስርስቶስ ድኛለሁ ሊሉ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም እነሱን ለማዳን ጌታ ዛሬም በምልጃ ስራ ተጠምዷልና፡፡ ነገም በምልጃ ላይ ይሆናልና፡፡ እንዲህ ለሚያምኑ መዳን አንድ ጊዜ የተፈጸመ ሳይሆን ዕለት ዕለት የሚፈጸም ነው፡፡ ታዲያ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ያማልዳል ብሎ የሚያምን እንዴት በጌታ አንድ ጊዜ ድኛለሁ ሊል ይችላል? በጌታ አንድ ጊዜ ድኛለሁ ሳይሉ ጌታ ኢየሱስ አዳኝ ነው ብሎ መመስከርስ እንዴት ይቻላል? ጌታ ኢየሱስ አዳነኝ ነው ያለ አንደበትስ እንዴት ዛሬም ዕለት ዕለት ያማልደኛል፣ ስለኔ ኃጢያት በአብ ፊት ይለምናል ማለት ይቻላል? ሁልጊዜ የሚያማልድ እንዴት አንድ ጊዜ ሊያድን ይችላል? አንድ ጊዜ ያዳነስ እንዴት ሁል ጊዜ ለማዳን እየደጋገመ ያማልዳል? ምልጃን በተመለከተ ይህ መሰረታዊው የኦርቶዶክሳውያንና የፕሮቴስታንት ልዩነት ነው፡፡
👉 3.2. ፕሮቴስታንት፡- በርግጥ በፕሮቴስታንቱ ዓለም አብዛኛዎቹ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ያማልዳል ብለው የሚያምኑ ሲሆኑ ከፊሎቹ ደግሞ ዛሬ አያማልድም ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ ዛሬ ያማልዳል ከሚሉት ወገኖች ገሚሶቹ ደግሞ ማብራሪያቸው ዛሬ የማያማልድ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በውኑ ዛሬም እያማለደ ነው? ይህ ጥያቄ ለብዙ ፕሮቴስታንት ወገኖች አስጨናቂ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ለብዙ ዓመታት ሲያስጨንቃት የኖረችና በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን እስከነቢይነት ማዕረግ ደርሳ እረፍት የነሳትን የዚህን ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ስታገኝ ወደ ኦርቶዶክሳዊት እናት ቤተክርስቲያን የተመለሰች እህት እናውቃለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈስ ካልተረጎምነውና ፊደሉን ብቻ ተከትለን ከሔድን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ያማልዳልም ወይም አያማልድም ከሚሉ ከሁለቱም ድምዳሜ ልንደርስ እንችላለን፡፡ ለዚህ ይመስላል የዚህ ጥያቄ መልስ በብዙ ፕሮቴስታንቶች ዘንድ ብዥታና የተዘበራረቀ እምነትና አስተምህሮ የፈጠረው፡፡ ምድነው ብዥታው? የተዘበራረቀው? የሚል ቢኖር ፤ ይኸው፡- ኢየሱስ ክስርስቶስ በውኑ ዛሬ ያማልዳልን? የሚለው አንዱ ምክንያት ነው - ..... ይቀጥላል
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞_✞_✞
1
ኢየሱስ ክስርስቶስ በውኑ.pdf
318.9 KB
ኢየሱስ ክስርስቶስ በውኑ ዛሬ ያማልዳልን?
@And_Haymanot
ካለፈው የቀጠለውን በpdf አዘጋጅተነዋል ያንብቡት
❖መልካም ዜና
‘ዘማሪት’ ምርትነሽ ጥላሁን የይቅርታ ጥያቄ አቀረበች፤

@And_Haymanot

የማኅበራት ኅብረቱ የፀረ ተሐድሶ ኑፋቄ ፊርማ ማሰባሰብ ተጠናክሮ ቀጥሏል
• የይቅርታ ጥያቄዋ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል፣ በጥንቃቄ እየታየ ነው
• ከውጹዓን እና ውጉዛን ቡድኑ ጋራ ስለነበራት ግንኙነት መግለጫ ትሰጣለች
• በቡድኑ ኢ-ቀኖናዊ አካሔዶች ልዩነት እንጅ አንድነት እንዳልነበራት ጠቅሳለች
• እነዳግማዊ ደርቤና ሀብታሙ ሽብሩ፣“የይቅርታ መንገዱን አሳዩን” እያሉ ነው
• በፀረ ተሐድሶ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ፣ እስከ 1 ሚሊዮን ድጋፍ ይጠበቃል
†††
የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመከፋፈልና ማንነቷን ለማጥፋት፣ በኅቡእና በገሃድ የሚንቀሳቀሱ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ቡድኖችን እየተከተሉ ያሉ ምእመናን ወደ ከፋ ስሕተት እንዳይገቡና እንዲመለሱ ሲኖዶሳዊ ጥሪ እየተላለፈ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት፤ የኑፋቄው መንፀባረቂያና መተላለፊያ ከነበሩት ውጹዓንና ውጉዛን ቡድን ጋራ ስትንቀሳቀስ የቆየችው ‘ዘማሪት’ ምርትነሽ ጥላሁን፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የይቅርታ ጥያቄ ማቅረቧ ተጠቆመ፡፡
‘ዘማሪት’ ምርትነሽ፣ ከሕገ ወጥ ቡድኑ የኑፋቄና የክሕደት እንቅስቃሴ ራሷን አግልላና ከተሳትፎ ታቅባ እንደቆየች የተጠቀሰ ሲኾን፤ ወደ ቀደመ ሃይማኖታዊ ማንነቷ በቀኖናዊ መንገድና በይፋ ለመመለስ እንደምትፈልግ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ማስታወቋን ተከትሎ ጥያቄዋ በጥንቃቄ እየታየ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡
ካለፈው ዓመት መጨረሻ አንሥቶ፣ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ዘንድ እየቀረበች፣ የጥያቄዋን መነሻዎች ስታብራራና ከስሕተት አካሔድዋ ለመመለስ መወሰኗን ስታስረግጥ ሰንብታለች፡፡ ጉዳዩም፣ በሦስት ዙሮች ውይይት ምርመራና ምክክር ከተደረገበት በኋላ፣ ትላንት ዓርብ፣ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሔደው የቋሚ ሲኖዶስ ሳምንታዊ ስብሰባ ቀርቦ የአፈጻጸም መመሪያ እንደተሰጠበት ታውቋል፡፡
ቋሚ ሲኖዶሱ በሰጠው መመሪያ መሠረት፣ የ‘ዘማሪት’ ምርትነሽ የመመለስ ጥያቄና ተያይዘው መታየት ያለባቸው ጉዳዮች፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ደረጃ ታይተው ውሳኔ እንዲያገኙ ስምምነት ተደርሶበታል፡፡
በመኾኑም፣ በመጪው ጥቅምት 12 ቀን በሚከፈተው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ፣ ‘ዘማሪት’ ምርትነሽ፣ ስለ ሕገ ወጥ ቡድኑና በእንቅስቃሴው ስለነበራት ተሳትፎ በዝርዝር ታስረዳለች፤ ተብሏል፡፡ በጽሑፍ ያቀረበችው የይቅርታ ጥያቄም፣ ለምልአተ ጉባኤው በንባብ ተሰምቶ ከአስፈላጊው ምክርና ተግሣጽ ጋራ የአቀባበልና የይቅርታ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ተገልጿል፡፡ ከዚሁ ጋራ በተያያዘ፣ የኢ.ኦ.ተ.ቤክ ቴሌቭዥንን ጨምሮ ለተለያዩ ሚዲያዎች መግለጫ ለመስጠት ዝግጁ እንደኾነችም ታውቋል፡፡
በሐዋሳ ሀገረ ስብከት የይርጋለም ቅዱስ ሚካኤል ሰንበት ት/ቤት አባል የነበረችው ‘ዘማሪት’ ምርትነሽ፣ ከ1990ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ በኋላ ከሕገ ወጥ ቡድኑ ጋራ ግልጽ የተግባር ተሳትፎ ስታደርግ ቆይታለች፡፡ በይቅርታ ጥያቄዋም ይህንኑ ብታምንም፣ “ያሳደገችኝ” ያለቻትን ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እና ታሪክ በሚፃረረው ሥራቸው ኹሉ ግን እንዳልተባበረችና ለወደፊቱም አክብራና ጠብቃ እንደምትኖር ማረጋገጧ ተነግሯል፡፡
ምርትነሽ፣ “መዝሙር ላሳትም” ብላ ከሰንበት ት/ቤት ከወጣች በኋላ፣ በዋናነት በበጋሻው ደሳለኝ እና ትዝታው ሳሙኤል በተወሰነ መልኩም በአሸናፊ ገብረ ማርያም ስም የሚዘጋጁ ግጥምና ዜማዎችን እየተቀበለች በማሳተም፣ በዐውደ ምሕረትና የቤተ ክርስቲያንን ፈቃድ ሳያገኙ በቤተ ክርስቲያን ስም ይተላለፉ በነበሩ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ስታስተጋባ ቆይታለች፡፡
በሕገ ወጥ ቡድኑ ጋራ ያላት ልዩነት በግልጽ የታየው፣ ጥራዝ ነጠቁ በጋሻው ደሳለኝ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዞ ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በተባረረው በግርማ በቀለ በሚመራው “የእውነት ቃል አገልግሎት” የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ድርጅት አስተምህሮ ከ‘ተዘፈቀ’ በኋላ “የዘይት ፈውስና ልሳን” ሲጀምር እንደነበር ተጠቅሷል፤ በቅርቡም፣ ሃይማኖትንና ሃይማኖተኝነትን በማንኳሰስ ቤተ ክርስቲያንን በዐደባባይ መገዳደሩ፣ ከጥፋት ቡድኑ በግልጽ ተለይታ ለመውጣት ጠንካራ መግፍኤ እንደኾናት ተገልጿል፡፡
ቀድሞም በእነበጋሻው፣ “ወደ ትራዲሽን ታደያለሽ፤” እየተባለች ትገለል እንደነበርና እርሷም፣ “ከናንተ ወገን አይደለሁም፤ አቋማችሁን አልደግፍም፤” በማለት መሳተፏን ካቆመች ሁለት ዓመት እንዳስቆጠረች ተነግሯል፤ የአሰግድ ሣህሉን፣ የስቱዲዮና የአዳራሽ ፕሮግራሞች በመቅረፅ ከፍተኛ ክፍያ ያገኝ ነበር የተባለው ባለቤቷም፣ ከግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት በኋላ ራሱን እንደለየ ተዘግቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በተከራየችው ሱቅ፣ በከፈተችው መዝሙር ቤት፣ መጻሕፍትንና የስጦታ ዕቃዎችን ማከፋፈልና ሽያጭ ንግድ ላይ በመሰማራት ኑሯዋን እየመራች እንደምትገኝ ተጠቅሷል፡፡
ባለፈው ዓመት ግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ አሰግድ ሣህሉን አውግዞ ከለየና የበጋሻው ደሳለኝ የጥፋት ተልእኮ ግልጽ ከወጣ በኋላ፣ የኑፋቄው አቀንቃኝ የኾነው ሕገ ወጥ ቡድን፣ እርስ በርሱ እየተዘላለፈና አንዱ ቡድን የሌላውን ተከታይ እያስኮበለለ በመናቆር ላይ ይገኛል፡፡ ጥቂት የማይባሉትም ራሳቸውን በማግለልና እንደ ምርትነሽ ተለይተው በመውጣት በይቅርታ ለመመለስ ማኮብኮባቸው ተጠቁሟል - የደብረ ፍሥሓ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ውሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት አባል የነበረው ዳግማዊ ደርቤ እና የደብረ ብርሃኑ ሀብታሙ ሽብሩ ተጠቅሰዋል፡፡
“በይፋ ይቅርታ ጠይቀው ከተመለሱ ያስመቱናል፤” በሚል ቀድሞ በስም ማጥፋት ለማሸማቀቅ፣ በተለይ የአሰግድ አንጃ በማኅበራዊ ሚዲያ መንቀሳቀስ መጀመሩ ተስተውሏል፡፡ ለጊዜው፣ በምርትነሽ ጥላሁንና በዳግማዊ ደርቤ ላይ ያነጣጠረው የማሸማቀቅ ሙከራው፣ ከሦስት ዓመት በፊት ተዘጋጅቶ ሳይታተም የቀረን የዳግማዊ ደርቤን ‘መዝሙር’፣ “ለቃል ዓዋዲ ድጋፍ ለማሰባሰብ” በሚል በፌስቡክ ገጽ በመልቀቅ መጀመሩንና ዳግማዊም፣ “አላምንበትም” ሲል ምላሽ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
ሀብታሙ ሽብሩ፥ በአሰግድ ሣህሉ ተፈጽሞበታል በተባለው የአደራ ገንዘብ ክሕደት፣ ወደ አሸናፊ መኰንን በመኮብለል ኩርፊያውን ቢገልጽም፤ አሸናፊም በመወገዙና በግብረ ሰዶማዊነት በመታማቱ ከበጋሻው ደሳለኝ ጋራ ተጠግቶ ቆይቷል፡፡ ይኹንና በጋሻው፣ በጥራዝ ነጠቅነት የሸመተውን የኑፋቄ አስተሳሰብና ድርጊት በዐደባባይ መግለጡን ተከትሎ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፤ “የቤተ ክርስቲያኔን ጣዕም ሳላውቅ እንዲሁ ልቀር ነው፤ የማንም ደጋፊ አልኾንም፤” ሲል ምሬቱን ገልጿል፤ “መንገዱን አሳዩኝ፤ ይቅርታ ልጠይቅ” እያለም እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡
ሐራ ተዋህዶ
@And_Haymanot
ምንጫችን 👉 https://haratewahido.wordpress.com/
በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
‹‹ ገንዘብን በከንቱ አትበትን ገንዘብን በቃኝ አልቸገርም አትበል›› (ሲራክ 5፡1፡ 11፡24)

@And_Haymanot

መጽሐፈ ሲራክ ትክክለኛነት ከመሰሎቹ መጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊያን ጋር ሲፈተሸ
የተሃድሶ መናፍቃን ሰማንያ አሃዱ መፅሐፋችንን የተሳሳተ አድርገው ከሚያቀርቡት የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል አንዱ መፅሑፈ ሲራክ ላይ የተጠቀሰውን ቃል በመጥቀስ ነው

ገንዘብን በከንቱ አትበትን ገንዘብን በቃኝ አልቸገርም አትበል....
በከንቱ የሚለው ለማይጠቅም ነገር ለምሳሌ ለስካር ለዘፈን ለኃጢአት አትበትን አታባክን ነው፡፡ ባለፈው የሠራሁትና ያገኘሁት ገንዘብ ይበቃኛል አልቸገርም ብለህ ገንዘብ አላቂ ስለሆነ አልሥራም አትበል ነው፡፡ (መዝ61፡10)፡፤ ገንዘብን ለሚበትኑ ሲናገር ‹‹ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ›› (ሉቃ15፡13)
ይልና ለሚጠቅም ለምጽዋት ደግ ‹‹በተነ ለችግረኞችም ሰጠ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል (መዝ111 (112))9) ይላል፡፡
ለመመጽወትም ሆነ ለሕይወታችን ሠርተን ባለጠጋ መሆንን አንከላከልም ‹‹ የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች›› (ምሳ 10፡4) ይህን አምላክ ፈቅዶታል ‹‹
እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ ከእርስዋም ይበላና
እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ (መክብብ 5፡19) ስለዚህ ሰው ሰርቶ
በደከመበት ሲያከማች እንጂ ቶሎ ለመበልጸግ በሙስና ከሆነ ‹‹ በችኮላ የምትከማች ሀብት ትጎላለች ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች
(ምሳሌ 13፡11) ይላል፡፡ ሀብት እንድናከማች ተነግሯል (ዘዳ 8፡18) ወላጆችም ለልጆች ገንዘብን
በቃኝ ሳይሉ ማከማቸት አለባቸው ‹‹ ወላጆች ለልጆች እንጂ ልጆች ለወላጆች ገንዘብ ሊያገማቹ አይገባቸውም፡፡ (2ኛ ቆሮ 12፡14) ነገር ግን ባከማቹት ሀብት ሊመኩ አይገባም፡፡ ገንዘቡ አንዳይገዛቸው ይጠንቀቁ ‹‹ ጥበብን አግኝ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ›› (ምሳ 4፡7)
እንዳለ #ሀብታቸውን_ወደ_ማምለክ_መቀየር_የለበትም፡፡ እየመጸወቱ ወዳጅ ሊያፈሩበት (ሉቃ 16፡9)፤ ሰው
ሲቸገር በቃኝ ሳይሉ በሠሩበት ገንዘብ ሊረዱበት ‹‹የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆንን የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት
ይኖራል›› (1ኛ ዮሐ 3፡17) እንዳለ ገንዘብ ያለው ለሌለው ሊደርስለት በቃኝ ብሎ ያቆመውማ ከየት አምጥቶ ይረዳል ሥራ ሳላቆም ያለውም ያልቀብኛል
ብሎ ስስታም ይሆናልና፣ አንድም አያስፈልገኝም ሳይል ይሥራ ሲል ነው፡፡

‹‹ ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም እንኳ አያስፈልገኝም ሳይል ይሥራ ሲል ነው፡፡ ‹‹ ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ ጎስቋላና ምስኪንም ድሀም እውርም የተራቆትህም መሆንህን ስማታውቅ›› (ራዕይ 3፡17) የሚላቸው ገንዘብን በቃኝ ብለው ባላቸው ብቻ የተኩራሩትን መሆኑን ተገንዝበን ዋናው ‹‹አካሄዳችን ገንዘብ ያለመውደድ ይሁን›› (ዕብራ 13፡5) እንጂ መጽ. ሲራክ ላይ ያለው ቃል ባለፈው ባገኘነው በቃኝ ሳንል ሰርተን ሀብትን ማከማቸት እንደሚገባ የሚናገር ነው፡፡ ለዚህ መጽሀፍ ቅዱስን እርስ በርሱ ለማጋጨት መሞከር ለጥፋት ስለሚሆን፣ ንሰሐ ገብታችሁ ወደ ኦርቶዶክሳዊት (ቀጥተኛዋ) እምነታችሁ ተመለሱ፡፡ ‹‹ ኢትሰቄቀ ለነዋየ አመፃ እስመ አይከል አድኀኖተካ አመ ምንዳቤከ (ለኃላፊ ገንዘብ አትሳሳ በመከራህ ጊዜ አያድንህምና) (ሲራክ 5፡8) የአመጻ ገንዘብ የሚባለው አራጣ በማበደር በቅድሚያ የሚመጣ በማታለል ያገኘኸው ለጌታ ባለመታዘዝ
በአመፃ ያገኘኸው ነውና ለኃላፊ ገንዘብ
አትሳሳ አያድንህም ነው፡፡ (መጽሐፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ንባቡና ትርጓሜው 1988) ‹‹ አትስረቅ›› ዘዳ 20፡15) ከሚለው ጋር አንድ ነው፡፡

ይህን ሕግ በዐመፃ ገንዘብ የምትሰበስበው ይጠቅመኛል ያድነኛል ብለህ እየሳሳህ አታስቀምጥ፡፡ የዐመፃን ገንዘብ እየሰበሰብክ ከምታስቀምጥ ሳትሳሳ ስጥና ንሰሐ ገብተህ ይህን ግብር ትተል ለድሃ በመስጠት ኃጢአትህን አስቀር ሲል ነው (ዳን 4፡27 ሉቃ 18፡22) ለጥፋት የተዘጋጁ አሕዛብ በአንድ ወቅት ሐረግ እየመዘዙ መጽሐፍ ቅዱስን እርስ በርሱ ለማጋጨት መሞከራቸው የቅርብ ቀን ትውስታ ነው፡፡ አሁን ደግሞ 66ቱን መጽሐፍ ቅዱስ እንቀበላለን 81ዱን አንቀበልም የሚሉ ደግሞ ለማጋጨት መነሣታቸው በግብር መመሳሰላቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የሚጋጭ የሚመስል ዐረፍተ ነገር በ66ቱም መጽሐፍ
ውስጥም አለ፡፡ ‹‹ የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኸል›› (ያዕ 5፡4)
‹‹ በአራጣ ብዛትና በቅሚያ ሀብቱን የሚያበዛ ለድሃ ለሚራራ ያከማችለታል›› (ምሳሌ 28፡8) አትስረቅ ከሚለው ጋር ይጣላል ብንል ጤነኛ አስተሳሰብ ይሆናልን?
አይሆንም፡፡
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
Channel photo updated
በቅዱሳን ስም መጸለይ ለምን አስፈለገ?
=========================

@And_Haymanot

ለምን ራሳችን በቀጥታ አንጸልይም ፤ኢየሱስ ብቻ አይበቃንም ወይ? አማላጅ
መፈለግ መንገድ ማብዛት አይሆንም ወይ?
አይሆንም!!!
ለምን? ምክንያቱም መፅሐፍ ቅዱስ ስለማይል። አራት ነጥብ። እኛ ደሞ
መፅሐፍ ቅዱስን ስለምንከተል! ለምሳሌ ምን ብሎ?
ልዑል እግዚአብሔር የቅዱሳንን አማላጅነት ይወድዳል። “ፃድቅ ስለኃጥአን
ቤት ያስባል” እንዲል ምሳ21÷12 ላይ
ለእግዚአብሔር ባለቸው ቅርበት በጸሎትና በቃል ኪዳን ያማልዳሉ
ዘፍ20÷1-18 ት.ዳን12÷3 ት.ኤርም42÷2
እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ
ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ
ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥
ዋጋው አይጠፋበትም። ማቴ 10፥40
እኔ በጣም ይገርመኛል መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እርስ በእርስ እንደሚስማማ።
ትዝ ይላችኃል አይደል ጌታችን ምን እንዳለ? እኔ በር ነኝ! ብሎ ነበር። እውነት
ነው እናምናለን በሩ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ጴጥሮስ ግን ቁልፉን እንዲሸለም ያደረገው ያ ምርጥ መልስ አምላክን
ያስደሰተ ያ ግሩም መልስ ምን ነበር?
ጌታችን በሌላ ጊዜ ሐዋርያቱን ሰብስቦ ምን ብሏል? እኔ ማን እንደሆንኩ
ትላላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ ፈጠን ብሎ
"አንተማ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" አለው አባቶች ይህን ሲያመሰጥሩት
የወረድክ የተወለድ ግን ያልተፈጠርክ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ ድህረ
ዓለም ያለ አባት ከድንግል ማርያም የተወለድክ የእግዚአብሔር ልጅ እራስህ
እግዚአብሔር ነህ አለው። በዚህ ጊዜ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጅግ
ደስ ብሎት ቅዱስ ጴጥሮስን ሽልማት በሽልማት አደረገው። በስመአብ ምን
ያላለው ነገር አለ? ታድሎ እንደው አባታችን ቅዱስ ጴጥሮስ!
የመንግስተ ሰማያትን ቁ....ል...ፍ ሰጠው። አዎ እኔ ሳልሆን መፅሐፍ ቅዱስ
ነው ሚለው ሃራጥቃ ስለዚህ ቁልፍ አውርታን አታውቅም እንዲወራም
አትፈልግም።ሆዷን ይቆርጣታላ! ስልጣነ ክህነትን አጎናፀፈው በምድር
ያሰርከው በሰማይ ይታሰራል በምድር የፈታኸው በሰማይ ይፈታል ብሎ
ይኸው እስከ ዛሬ ስልጣኑ እጅ በመጫን እየወረደ ካህናት አባቶቻችን ድረስ
መጥቶ ይባርከናል የመፍታት የማሰረ ስልጣን አላቸው። አምላካችን እራሱ
ያለው እናንብበው እስቲ እንደወረደ
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው
አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን
እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም
መ...ክ...ፈ...ቻ...ዎ...ች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት
የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።
ማቴ 16፥17-19
በሩ እኮ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና መድኃኒታችንና ጌታችን
መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ጥያቄ የለውም። ነገር ግን
ሐራጥቃዎች አስተውሉ ቅዱሳን የመንግስተሰማያት መክፈቻና መዝጊያ ቁልፍ
አላቸው። የመፍረድና የማ ማለድ ጸጋም ተሰጥቷቸዋል።
ለቅዱሳን ማማለድ ትንሹ ስልጣናቸው ነው ወዳጄ። ሃራጥቃ ሆይ
እንዳይገርምህ እንጂ እንኳን ማማለድ ባንተ ላይ የ..መ..ፍ..ረ..ድ ስልጣን
ሁላ ተሰጥቷቸዋል ። ይገለጣ መፅሐፍ ቅዱስ! ይነበባ! ምን ይላል? በ1ኛ
ቆሮንቶስ ም6፥ቁ2 ላይ
ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? ይላል እኮ ይሄን ይሄን ስታነቡ
ትዘሉታላችሁ ወይስ ገጹን ገንጥላችሁታል?
አሁን በእኛ ላይ መፍረድ ሁላ እንደሚችሉ ይህን ጥቅስ ስነገርህ አትገረም
እዛው ወረድ ብሎ ቁጥር 3 ላይ ምን ቢል ጥሩ ነው? "በመላእክት እንኳ
እንድንፈርድ አታውቁምን?" በስመአብ ከዚህ በላይ የሚያሳርፍ መረጃ ከየት
ይምጣ?
በመላእክት እንኳ ይፈርዳሉ ቅዱሳን። ይቁረጥልህ። እኔና አንተ ያማልዳሉ
አያማልዱም ብለን ስንታገል ለካ ቅዱሳን እየፈረዱ ነው። እንግዲህ መናፍቃን
ምንም ልንረዳችሁ አንችልም እኛ ሳንሆን እራሱ ባለቤቱ ነው የሰጣቸው።
እንዴት ይሄ ይሆናል? እንዴት ትሰጠቸዋለህ አንተ ብቻ በቂ እኮ ነህ ኢየሱስ
ብቻ በቂ ነህ አሄሄ ምትል ከሆነ ደሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዩሀንስ
ወንጌል ምዕራፍ21 ቁጥር22 ላይ ይወስድህና "እኔ ብ...ወ...ድ...ስ!" ብሎ
ያረጋጋሃል ። እኔ ብወድስ! እሱ ከፈለገ ከወደደ አንተ ምን ታመጣለህ??
እንዴት ደስ እንደሚለኝ ይሄ የጌታችን መልስ! እኔ ብወድስ!!! አፍ የሚያዘጋ
መልስ ነው።
ለመሆኑ ከመፍረድ እና ከማማለድ የትኛው ይልቃል?
--------------------------------------------------------------------
ለዛውም ከእኛም አልፎ በመላእክት ላይ ከመፍረድ በላይ ምን ስልጣን አለ?
እኛም ኦርቶዶክሳውያን ከሃራጥቃ ጋር ይፈርዳሉ አይፈርዱም በሚል
ጭቅጭቅ ውስጥ ተውጠን የቅዱሳን የላቀው ስልጣናቸውና በረከታቸው
እንዳንዘነጋ ልንጠነቀቅ ይገባል።
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የገሀነም ደጆች
አያናውጧትም ቤተክርስቲያን አትታደስም!
ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት
ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት
ቤተክርስቲያን ጸልዩ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን-
ይቆየን።

#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
@ መናፍቁ አሰግድ ሣህሉ በግብር የወለዳቸው አሰግዳውያን በተደጋጋሚ
በልብ መታሰቡ፥ በቃል መነገሩ፥ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ
ይበልና የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን 'አማላጅ' ለማስባል
ከሚጠቅሱት ጥቅሶች አንዱ "እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች
አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።" ሮሜ
1፥8 የሚለውን ይዘው እየደጋገሙ 'በተወደደ ልጅህ እናመሰግንሃለን፥
በኢየሱስ ክርስቶስ እናመሰግንሃለን' ሲሉ በውኑ ትርጉሙን ያውቁታል?

@And_Haymanot


"በኢየሱስ ክርስቶስ" የምትለውን ለገዛ ፈቃዳቸው ይነቅሷታል። ለመሆኑ የዚህ
ጥቅስ ትርጉም ምንድነው?
፩. ለሐዋርያት በምስጋና መጀመር ልማዳቸው ስለሆነ ነው። ብርሃነ ዓለም
ቅዱስ ጳውሎስ "እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለተሰማች አስቀድሜ ስለ
ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።" ሮሜ 1፥8 ያለው።
አቀድም አዕኲቶቶ ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በእንተ ኲልክሙ።
ለሐዋርያት በምስጋና መጀመር ልማዳቸው ነው። ይኸውም፦
☞ ከዚያ በቅዳሴ አንድ ሁነው(በቅዳሴ ሐዋርያት ማለት ነው) "አቤቱ
በተወደደ ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናመሰግንሃለን።" ማለት
ጌታችን ልጅህ ወዳጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምሥጋናው አብነት ሁኖን(ጌታችን
አርአያ ሆኖ እንዳስተማረን እንደማለት ነው) "አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ
አመሰግንሃለሁ" ዮሐ.11፥41 እንዳለ ነአኲተከ በፍቁር ወልድከ/አቤቱ
በተወደደ ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናመሰግንሃለን/ ብለን ልጅህ
ወዳጅህ ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት አድርገን እናመሰግንሃለን ማለት ነው።
☞ ቅዱስ ጴጥሮስም በመልእክቱ በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ "ለማያልፍም
ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
አምላክና አባት ይባረክ" 1ኛ ጴጥ.1፥3-5 የሚለውን ግዑዙ "ይትባረክ
እግዚአብሔር አቡሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ"/በቸርነቱ ብዛት የወለደን
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አባቱ እግዚአብሔር አብ ይክበር
ይመስገን ማለት ነው/ እንዳለ።
☞ቅዱስ ጳውሎስም "...አስቀድሜ ስለሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ
አመሰግናለሁ።" አለ። እስራኤልን ከኦሪት ወደ ወንጌል፥ ከገቢረ ኃጢአት ወደ
ገቢረ ጽድቅ፤ አሕዛብን ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፥
ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ስለመመለሳችሁ እስራኤልን ከመልፈፍ፥
አሕዛብን ከመዝለፍ አስቀድሜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ማለቱ ነው።
፪. ሐራሴ ወንጌል(የወንጌል ገበሬ) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "...አስቀድሜ
ስለሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።" ማለቱ
እግዚአብሔር አብን፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም አመሰግናለሁ ሲል ነው።
፫. አንድም ጌታችን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግነዋለሁ ሲል
ነው።
፬. አንድም ልጁን ሰዶ ሐዋርያው ስለአሰኘኝ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ
ማለቱ ነው።
❖ የወርቃማው ዘመን ወርቃማ ደራሲ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም
በመጽሐፈ አርጋኖን ዘረቡዕ ላይ ሲጀምር "ስለጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ
አስቀድሜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።" (ሮሜ 1፥8) እመቤታችን
ስላንቺም የውዳሴሽ ዜና በዓለም ሁሉ ተሰምቷልና በመንፈስ ቅዱስ
እንደተናገርሽ እንዲህ ስትይ፦ እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት
ይሉኛል። በዕውነት ብፅነት ይገባሻል። ሉቃ.1፥8።" ብሏል። በመሆኑም ሮሜ
1፥ 8 መጋብያነ ምሥጢር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሚያፍታቱት፥ በዚያም
የሚያመሰጥሩት ገጸ ንባብ መሆኑን ልብ ይሏል።
"በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እንግዲያስ
እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ፥ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ እገዛለሁ።"
ሮሜ 7፥25 የሚለውን ሲተረጉሙም ነገር ግን የባሕርይ ልጁ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስን ሰዶ አዳነኝ፥ ያዳነኝ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን። እኔስ
በልቡናዬም በሕሊናዬም ለሕገ እግዚአብሔር እገዛለሁ፤ በሰውነቴ ግን ለሕገ
ኃጢአት እገዛለሁ ማለት ነው።
❖ ሮሜ 16፥27 "ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ
እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን አሜን።" ሲልም ክብር ጌትነት ገንዘቡ የሚኾን
እግዚአብሔርን ያውቁት ዘንድ ለዘለዓለሙ አዋቂ የሚኾን፦ አብን ጠቢብ
አለው፤ አሕዛብ እንጨት ጠርበው ደንጊያ አለዝበው ጣዖት ቢያመልኩ ግዙፍ
አምላክ ካሹ(ከፈለጉ) በግዘፍ ይታይላቸው ብሎ ልጁን በሥጋ ሰዶላቸዋልና
ጠቢብ አለው። አንድም ጠቢብ ብሎ ለወልድ ቀጠለ ዲያብሎስ ከሥጋ ከይሲ
ተሠውሮ ቢያስት እሱም በሥጋ ብእሲ ሥግው ኾኖ አድኖበታልና ጠቢብ አለው።
❖ "ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።" 1ኛ ቆሮ.15፥57 ሲል ነገር ግን በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ካሣ በወንጌል ኦሪትን፥ በትንሣኤ ሞትን፥ በጽድቅ ኃጢአትን
ድል እንነሣ ዘንድ ድል መንሣቱን የሰጠን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ማለቱ
ነው።
❖ኤፌ. 5፥20 "ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
አምላካችንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።" ማለቱ ደግሞ በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለተደረገላችሁ ነገር ኹሉ ኹል ጊዜ እግዚአብሔር
አብን አመስግኑት ሲል ነው።
ለዚህም ነው በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻሕፍት በመጽሐፈ
ቅዳሴ፥ በሊጦን፥ በመስተበቁዕ....ሁሉ ማብቂያ ላይ "በአንድ ልጅህ በርሱ ያለ
ክብር ጽንዕ ለአንተ ይገባል፤ ከርሱ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም
ዘወትርም ለዘላለሙ።" የሚለው። ይኸውም በቅድስት ሥላሴ ዘንድ የምስጋና፥
የክብር፥ የኃይል ተዋረድ የሚባል ነገር ፈጽሞ አለመኖሩንና ለባሕርዩ ልጁ
ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለን አምልኮ፥ ውዳሴ፥ ክብር ለባሕርይ አባቱና ለባሕርይ
ሕይወቱ ለመንፈስ ቅዱስ ከምንሰጠው አምልኮ፥ ውዳሴ፥ ክብር ጋር ፍጹም
ዕሩይ(የተካከለ) ነው ሲል ነው።
ስለሆነም በቅዱሳት መጻሕፍት "በኢየሱስ ክርስቶስ" የሚል ስናነብ
የቅድስት ሥላሴን የሥልጣን አንድነት የሚያፋልስ እንዳይመስለን። ይኼ ሲባል
ክብር ይግባውና 'በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና
ማቅረብ እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ማቅረብ አይቻልም' ማለት
አይደለም!!! መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነውና ከባሕርይ
አባቱ ከእግዚአብሔር አብ፥ ከባሕርይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
እኩል የአምልኮ፥ የፈጣሪነት ምስጋና ይገባዋል። "ነገር ግን በጌታችንና
በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ
ዘላለም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።" 2ኛ ጴጥ.3፥18 በማለት ቀጥታ ሊቀ
ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት
በሚገልጥ ሁናቴ "ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤
አሜን።" ብሏል።
አንዳንድ አብዳን(ሰነፎች) የመድኅነ ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን
ሥራ አዛብተው በመተርጎም በጎ ምግባር ለመዳን አያስፈልግም ሲሉ ይሰማሉ።
እንዳውም የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች
ማጠቃለያው እኮ በበጎ ምግባር አስፈላጊነት ላይ ነው። ያውም "ፈቃዱን ታደርጉ
ዘንድ፥" በማለት በጎ ምግባር ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑንም በማውሳት
"በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን
ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያደርጋችሁ፥ ለእርሱ እስከ ዘላለም
ድረስ ክብር ይሁን፥ አሜን።" ዕብ.13፥21 በማለት መልካም ሥራ ሥሩ ብቻ
ሳይሆን
"በመልካም ሥራ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤" ብሎ "አሜን" የሚያሰኝ ቃለ
ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ያስተላለፈው።
ተወዳጆች ሆይ እኛም ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ክርስቲያኖች ጠንቅቀን
የቅዱሳት መጻሕፍት ይትበሃል መረዳት አለብን። 'የመናፍቅ' የሚባል ጥቅስ
የለም። በቅዱሳት መጻሕፍት እስካለ ድረስ የምንሸሸው ጥቅስ የለም። በአንድ
ጥቅስም አንደናበር። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሶ ማቅረቡ ብቻ መንፈሳዊ
አያሰኝም። ከነ ደገኛ ትርጉሙ ሲገልጥ እንጂ። 'መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ
ይላልኮ' ከሚሉ ይልቅ "መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለው እንዲህ ለማለት ነው።"
በማለት ሐዋርያዊ የሆነች ደረቅ ሐቋን(Crystal Truth) ከሚያሳውቁን ጋር
እንወዳጅ። ርትዕት የተዋሕዶ እምነታችንን የሚያሳፍር፥ ልጆቿን አንገት
የሚያስደፋ ጥቅስ በቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የለም። ለመረዳት የሚጸን
(የሚከብድ) ኃይለ ቃል፥ ገጸ ንባብ ስናገኝ ከላይ አርእስቱን ከሥር ኅዳጉን
በማየት ማመላለስ፥ ሊቃውንቱን መጠየቅ እንጂ በግል ዕውቀታችን የግል ውሳኔ
ከማስቀመጥ መቆጠብ። ቅዱሳት መጻሕፍት ለማለት የፈለጉትን መረዳት እንጂ
'እኛ የምንፈልገውን እንዲሉልን ብለን አናንብብ!' የ Protestant መሠረታዊ
ችግር መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይለናል? ሳይሆን 'መጽሐፍ ቅዱስ እኛን በመደገፍ
የቱ ጋ ምን ይላል?' በሚል ማየታቸው ነው። የተሐድሶ መናፍቃንም እንዲሁ
ናቸው። በተለይ የዘመናችን የተሐድሶ መናፍቃን አሰግድ ካለ፥ አለ ነው። አሰግድ
ከሚነግረን የተለየ ሌላ እውነት የለም? እውን መጽሐፍ ቅዱስ የሚተረጎመው
በአሰግድ እውቀት ልክ ነው? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ደቀ
መዛሙርቱ ሂዱ ለዓለም ስበኩ ያላት ወንጌል ናት አሰግድ የሚሰብካት? እውን
በአሰግድ ኑፋቄ አልተመረዘችም? እውን በክህደቱ አላዛጋትም? አልጨመረም?
አልቀነሰም? ንጽሕት ወንጌልን አላሳደፋትም? ቅዱሳን ሐዋርያት የሰበኳትን
ርትዕት እምነት አሁን አሰግድ ከሚያስተምረን ጋር አንድ ነው? እስቲ ላንብብ፥
ቅዱሳት መጻሕፍትን ላገላብጥ፥....የሚል የለም። በስሜት ብቻ የሚላቸውን
እንጂ ለማለት የፈለገው ሳይገባቸው፥ በ TV መታየት መጽደቅ መስሏቸው፥
ጉዞውን እንጂ መጨረሻውን የማያውቁ፥ መንግሥተ ሰማያት የሚገባው ስብከተ
ሐዋርያትን የተከተለ ሳይሆን ክህደተ አሰግድን የተቀበለ አድርገው የሚቆጥሩ፥
የሚታዘንላቸው ሆነው ሳለ የተቀናባቸው የሚመስላቸው፥ 'እረ ባካችሁ ኦሽ'
ሲባሉ 'አካኪ ዘራፍ' የሚሉ፥ እረ ተመልከቱ ሲባሉ ዓይናቸውን የሚጨፍኑ
ጨቅላዎች ናቸው። ነፍስ ይማር።

#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
ፈያታዊ ዘየማን አጭር ገለጻ


@And_Haymanot


ተወዳጆች ሆይ!ብዙ ጊዜ ከሚያስገርሙኝ ታሪኮች መካከል አንዱ የዚህ ታላቅ
ሰማዕት ታሪክ ነው።የተሐድሶ መናፍቃን ልባቸውን በክሕደት አጥረው የዚህን
ሰማዕት መከራ የሚያዩበትን ዓይነ ልቦናቸውን ዘግተው በእምነት ብቻ ዳነ
ብለው ሲሞግቱ ይሰማሉ ግን ተወዳጆቼ ሆይ!እንዲያ ነውን?ቅዱሳን
አባቶቻችን ስለዚህ ሰው በመደመም ተናግረውለታልና ትንሽ
እናብራራው።ቅዱስ ጄሮም ፈያታዊ ዘየማን ሰማዕት ነው ይለዋል ለምን ትሉ
እንደኾን ሰማዕትነት ከክርስቶስ ጋር ኾኑው የሚቀበሉት መከራ ሰቃይ ግድያ
ስቅላት ነው አንድም የራስን ሕማም ረስቶ መከራ ክርስቶስን ማሰብ ነውና
ፈያታዊ ዘየማንም ያደረገው ይህን አይደለምን?ተወዳጆች ሆይ በትሑት
ስብእና በንጹህ ልቦና ኾናችሁ ተመልከቱት በእውን አይሁድ ጌታን ሲያንገላቱት
መከራ ሲያጸኑበት አምላክነቱን ክደው በመስቀል ሲሰቅሉት የጌታን ንጹህነት
የመሰከረው ብቸኛው ሰው ጥጦስ ወይም ፈያታዊ ዘየማን አልነበረምን?
በሉቃስ 23፥41 "ይህ ግን ምንም የሠራው ክፉ ሥራ የለም"በማለት ነበር
የገለጸው።ክርስቶሳዊያን ኾይ! ክርስቶስ ንጹሀ ባሕርይ መኾኑን ማን ነግሮት
ይኾን?መምህራነ ወንጌል አስተምረውት ይኾንን?ወይንስ የኦሪትን መጽሐፍ
አንብቦ?ታዲያስ ማን ይኾን የነገረው?እስኪ እናንተ የተሐድሶ መናፍቃኖች
ሆይ ንገሩን እንጠይቃችሁ?እስከ ዛሬ ድረስ እናንተ አልገባ ያላችሁን ነገር
እንዴት እርሱ ወዲያው ሊረዳ ቻለ?በእውን ፈያታዊ ዘየማን ይህንን ቃል
ሲናገር አምላከ ቅዱሳን ምን እንዳለው አላነበባችሁምን?ቅዱስ ጳውሎስ ራሱ
የፈያታዊንን ክብር በመንፈሳዊው ቅናት የቀና ይመስላል! ምክንያቱም
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ብሎ ገላ 2፥20 ላይ ተናግሯልና!ተወዳጆቼ
ክርስቲያኖች ሆይ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አበው አባቶቻችን በምስጢር
እንዲህ ይሉናል ሰባቱ ተአምራቶች ናቸው አንድም የጌታ ጥላው ቢያርፍበት
ከታወረበት ዓይነ ልቦና ተመልሷል በማለት ይደነቃሉ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ደግሞ በታላቅ ፍቅር የተሞላው የጌታ ንግግር ነው "አባት ሆይ የሚያደርጉትን
አያውቁምና ይቅር በላቸው" የሚለው የጌታ ቃል የተዘጋውን የጥጦስን ልብ
ሰብሮ ገብቶ ከሽፍታነት አስወጥቶ ለታላቅ ሰማዕትነት አድርሶታልና! ተወዳጆቼ
ይህቺ ቃል ሽፍታ ለነበረው ጥጦስ ሕይወት ስትኾን የሃይማኖት ሽፍቶች
ለኾኑት የተሐድሶ መናፍቃን ግን ጥፋት ኾናባቸዋለች!!ዳግመኛም የጴጥሮስ
ጥላው ድውያንን ከፈወሰ የጌታ ጥላማ እንዴት ይልቅ!!ተወዳጆች ሆይ!
ሌላም ድንቅ ነገር ተናግሯል እንዲህም ብሏል"አንተ በዚህ ፍርድ ውስጥ
ሳለህ እግዚአብሔር አምላክህን አትፈራምን?" ሉቃ 23፥40 በማለት
ተናግሯል።የጥንቱ ሊቃውንት ይህንን ቃል ፈያታዊ ዘየማን ወንድሙን ለማዳን
ምን ያህል እየተጋ እንደኾ የሚገልጽ ነው፤ለጓደኛው ያለውን እውነተኛ ፍቅር
እርሱን ለመመለስ ባደረገው ትግል አሳይቷል።በሽፍታ ለሽፍታ ትምህርት
ቢቀርብም ክፉው አስተሳሰብ ከልቡ አልወጣ ያለው ያ በግራ በኩል ያለው
ሽፍታ ሊመለስ አልቻለም።እኔ ግን ይህ በግራ ያለው ሽፍታ እኛን የሚመስል
ይመስለኛል።በእውን ብዙ ድንቅ ነገር ተደርጎልን ሳለ ፍቅረ እግዚአብሔር
አልገባ ብሎን ከበጎ ምግበረራት የሸፈትን የለንምን?ተወዳጆቼ ሆይ ይህ
እንዴት ያለ ድንቅ ቃል ነው!ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የእግዚአብሔር ልጅ
ነህ በማለቱ ከተመሰገነ ጥጦስስ እንዴት ይበልጥ ሊመሰገን ይገባው ይኾን?
የቀደመው የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ዐይቷል ፈያታዊው ግን
መስቀል ላይ መከራ ሲቀበል ያለ በደሉም ሲሞት ነው ያየው እጅግ ድንቅ እኮ
ነው የፀሐይን ያለ ወትሮዋ መጽለም፣የከዋክብትንም መርገፍ የጨረቃን ደም
መምሰል የዓለት መሰንጠቅ የሙታን መነሣት ለፈያታዊ ዘየማን በቂ
መምህራን ነበሩ!እንዲያውም ፖፕ ሺኖዳ እንዲህ በማለት ይጠይቃሉ ይህ
ሰው እንዴት አመነ?እንዴትስ የመመለስ ዝንባሌ ታየበት?የቀኙ ወንበዴ ፊቱን
ወደክርስቶስ ያዞረው በምን ዓይነት ኹኔታ ውስጥ ነበር?ክርስቶስ በብዙ
ሕዝብ ታጅቦ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች በታየበት ልዩ አጋጣሚ ወይስ መከራ
መስቀልን በሚቀበልበት የቀራንዮ አደባባይ!በትክክልም!ወቅቱ በበሽተኞች
ተከቦ ፈውስ በሚያድልበት የምሥጋ የሙገሳ ዕለት ሳይኾን ከሳሽ ካህናትና
ሰቃይ ጭፍሮች ተባብረው ያፌዙበትበነበረበት አስጨናቂ ሰዓት ነው።ይህ
የሚያሳየው የክርሰቶስ የመስቀል ላይ ቆይታ በተለይም ደግሞ ለሰቃዮቹ
ያሳየው ርኅራኄ በቀኝ በኩል በተሰቀለው ወንበዴ ደንዳና ልቡና ላይ ታላቅ
ተጽእኖ ማሳደር መቻሉ ነው።ኹል ጊዜም ቢኾን የእግዚአብሔር ፍቅርና
ደግነት ከሰዎች አረመኔያዊ ተግባር ና የጭካኔ ሥራ በላይ ጉልበት አለው"
በማለት ያደንቃል!የተሐድሶ መናፍቃን ሆይ ኢየሱስ ማን እንደኾነ ማወቅ
ትፈልጋላችሁን?በሉ ኦርቶዶክሳዊውን ፈያታዊ ዘየማንን ጠይቁት መልሱን
ይንገራችሁ!!!አማላጅ አላለም እግዚአብሔር አምላክ ነው አለ እንጂ!
ተወዳጆቼ ሆይ!እግዚአብሔርንስ አማላጅ የሚሉ የተሐድሶ መናፍቃን
መጨረሻቸው እንዴት ይከፋ ይኾን?አንድ ሊቅማ ሮሜ 10፥9-10 ያለው ቃል
በፈያታዊ ዘየማን ተፈጸመ በማለት ይደነቃል።በልቡም የኢየሱስ ክርስቶስን
አምላክነት አመነ በአፉም መሰከረ በሰውነቱም የሞትን መከራ ታገሰ!ተወዳጆቼ
ሆይ እንዴት ግን ፈየታዊ ዘየማን የራሱ ሕማም ምንም ሳይሰማው ቀረ?
አይደንቅምን?የራሱን ትቶ ስለጌታው ሲያወራ ስትሰሙ ምን ይሰማችሁ
ይኾን? ይህን የፈያታዊ መከራ ወይም እምነቱን በሥራ መግለጥን
አለመረዳታችን ያስገረመው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህም ይላል
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደሥራው ይሰጠዋል በጌታ ቀኝ የተሰቀለው
ወንበዴ እምነቱን የገለጠው በሥራ ነው ኹሉም ሰው ፈጣሪውን በረሳበት
በዚያ የጨለማ ቅጽበት በመስቀል ላይ በተሰቀለው በክርስቶስ ሳያፍር በሰው
ኹሉ ፊት መሰከለት መከራን በመቀበሉ ያለማጉረምረም ፈጣሪውን አመሰገነ
ይህ በውኑ ሥራ አልመስል አለንን? በማለት ተገርሟል።ሌላው ነገር ደግሞ
ራሱን መውቀሱ የተፈረደበትም ፍርድ ተገቢ መኾኑን ተናገረ።አንድ ሊቅ
ፈያታዊው ዘየማን ወድያውኑ ኃጢአቱን ጠላ ጌታም ምን ያህል ኃጥአን
ሲመለሱ እንደሚደሰት ይገልጥ ዘንድ ወዲያው ተቀበለው!በማለት
ይመሰጣል። ተወዳጆች ሆይ ጌታችን በወዳጅነት መንፈስ ወንበዴውን ማቅረቡ
ምንኛ ድንቅ ነው!ይህ ሰው የክርስቶስ ጥሩ የመስቀል ላይ ወዳጅ መኾን
ችሏል፤ጌታችንም የዚህ ሰው ወዳጅነት በመስቀል ላይ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር
አልፈለገም።ለዚህ ዋስትና እንዲኾን ከእኔ ጋር ትኾናለህ በማለት የማይታጠፍ
ቃል ገባለት።አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው!ሲደንቅ ይህቺ
ቃል ብዙ ምስጢራት አሏት ሌላ ጊዜ በደንብ እናብራራታለን ኾኖም ኢየሱስ
ክርስቶስ መንግሥተ ሰማያት የሚያገባ የመንግሥተ ሰማያት ባለቤት መኾኑን
ማመኑን የሚያስረዳ እስካሁንም በቤተክርስቲያናችን በጸሎተ ቅዳሴ ላይ
የሚታወጅ ዕጹብ ድንቀ ቃል ነው!!!አንድ ሊቅ የሚለውን እንስማ ፈያታዊ
ዘየማን በቀኝ በኩል የተሰቀለ ወንበዴ ነው ሌላኛው ደግሞ በግራ ነው
የተሰቀለው ጌታ ያለው ደግሞ በመሀል ነው ይህ የሚያስረዳው የጌታን ዳኛነት
ወይም ፈራጅነት ፈያታዊ ዘየማንን ዛሬ በገት ከኔ ጋር ትኖራለህ እንዳለው
በዳግም ምጽአት ጻድቃንንም የአባቴ ብሩካን ኑ ዓለም ሳይፈጠር በፊት
የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ ብሎ የሚሰጥ መኾኑን ያሳያል በግራ
ያሉትን ግን በግራ ያለውን አላውቅህም እንዳለው አላውቃችሁም ይላቸዋል
በማለት ገልጸዋል።ብዙ ትርጓሜያት አሉት ለጊዜው ይቆየን!
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
@And_Haymanot
ኢየሱስ ጌታ ነው


@And_Haymanot


⇨በዘመናችን አንዳንድ ሰዎች አብዝተው በንግግራቸውና በስብከታቸው
መሀል ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ሲናገሩ እሰማለው። የኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነትና
አምላክነት ምንም አይነት ጥያቄ የለኝም። ነገር ግን ስሙን በእውነትና
በመንፈስ፣ ደግሞም በማስተዋል የምንጠራው እንጂ፣ በከንቱና በልማድ፣
ለንግግር ማጣፈጫ፣ ወይም ለጉባኤ ማድመቂያ የምንናገረው ወይም እኛ
ተስማምተን ጌትነትን የምንሰጠው ወይም የምንነሳው ስም አይደለም።
ክርስቶስ እኛ አውቀነው አላወቅነው እርሱ ለዘልአለም የተከበረ አምላክ ነው።
ስናውቀው ስሙን ጠርተን እናመሠግናለን፣ የተወሰነ ሰው ጌታ ነው ስላለ
ጌትነቱ የሚፀና፣ የተወሰነ ሰው ደግሞ ጌታ አይደለም ስላለ ጌትነቱ የሚቀር
አይደለም። ጌትነቱ የመቀበልና ያለመቀበል የሰዎች ድርሻ ቢሆንም እርሱ ግን
"የጌቶች ሁሉ ጌታ የነገስታት ሁሉ ንጉስ ሆኖ ለዘልአለም
ይኖራል።"ራዕ19:16..ሰዎች ሁሉ አምነው ይድኑበት ዘንድ ለሰዎች ሁሉ
የተሰጠ ስም ነው። ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው። ከዚህ የተነሳ
"መድኃኒታችን እግዚአብሔር ነው" ማለት ነው። ስለዚ ጌትነቱ የስብከታችን
ማጣፈጫ ወይም ፉከራ ሳይሆን የነፍስም የስጋም መድኃኒት መሆኑን
ተገንዝበን መመሥከር ይገባናል። ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል፦
√ ኢየሱስ በስጋ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው
√ ኢየሱስ አምላክ ነው
√ ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነው
√ ኢየሱስ ብርሀን ነው ማለት ነው። ስለዚ ኢየሱስ ጌታ ነው የሚል ሰው ከልቡ
አምላክነቱ ያመነ፣ አምላክነቱን የተቀበለ፣ በመድኃኒነቱን የተማመነ፣
ሕይወቱንና ሁለንተናውን ለጌትነቱ ያስገዛ፣ የእርሱ ባሪያ ለመሆን የፈቀደ፣ ስለ
ስሙ የሚመሠክርና ትእዛዙን የሚጠብቅ ሰው ነው ማለት ነው።ሀዋርያ ቅዱስ
ጳውሎስ ኢየሱስን በጌትነቱ ማወቅና "ኢየሱስ ጌታ ነው" ብሎ መመሥከር
በሰው ጥበብና ዕውቀት እንደማይከናወን ሲያስረዳ "በመንፈስ ቅዱስም
ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይቻል
አስታውቃችኋለሁ" 1ኛ ቆሮ 12:3 ይለናል። ይህ ማለት ሰዎች የኢየሱስ
ክርስቶስን ጌትነት ዐውቀው ራሳቸውን የሚያስገዙት፣ መንፈስ ቅዱስ
ሲገልጥላቸው ነው ለማለት እንጂ ኢየሱስ ጌታና አምላክ እንደ ሆነ ርኩሳን
መናፍስትም ያውቁታል፣ አይተውም ይንቀጠቀጡለታል። ጌታ ኢየሱስ ርኩሳን
መናፍስቱን ከሰውየው ውስጥ እንዲወጡ ሲያዛቸው፣ እንዲህ ብለዋል፦
"የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን
እንደ ሆንህ # አውቄአለሁ ፣ # የእግዚአብሔር_ቅዱሱ ብሎ
ጮኸ" (ማር1:24፣ ማቴ8:14–18፣ ሉቃ4:38–41)፣"ኢየሱስ ሆይ
የእግዚአብሔር ልጅ ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሣቅየን
መጣህን? እያሉ ጮኸ" ማቴ8:29..2) "የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ
ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳትሣቅየኝ በእግዚአብሔር አምልሀለሁ"
ማር5:7..በማለት ጌትነቱንና የእግዚአብሔር ልጅነቱን ዐውቀው
እንዳያጠፋቸው ሲማፀኑት እናያለን። ይህ ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ብለው
የጠሩት በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ወይም አምነውበት ሊድኑ ሳይሆን፣
ጌትነቱንና ፈጣሪነቱን ዐውቀው ነው። ስለዚ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ በሰማይም
በምድርም ያሉ ፍጥረቱ ሁሉ ጌትነቱን ዐውቀው ይሰግዱለታል
ይንበረከኩለታል። ፊል2:8–103
·
⇨ይሁን እንጂ "በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር" የተባለው ሰዎች በመንፈስ
ቅዱስ ወቃሽነት ኃጢአተኝነታቸውን ተረድተው፣ ጌታ ኢየሱስ ያለበደሉና
ያለኃጢአቱ ስለሰዎች ኃጢአት ሲል ምትክ ሆኖ እንደ ሞተና እንደተነሣ፣
በስሙ እንዲያድነን ስንማፀነው ንስሓ ገብተን ራሳችንን ለእርሱ ፈቃድ
ስናስገዛና ስንጠራው ነው ማለት ነው። ከዚህ የተነሳ አንድ ሰው ኢየሱስ ጌታ
ነው ሲል፣ እኔ ባሪያህ ነኝ ያለ አንተ አዳኝነት አልድንም፣ አንተ ወደዚህ ምድር
የመጣሀው እኔን ልታድን ነው ብሎ ንስሓ በመግባት ጌትነቱን ማወቅ ማለት
ነው እንጂ ለንግግር ወይም ለስብከት ማጣፈጫ ኢየሱስ ጌታ ነው እየተባለ
የሚነገርበት አይደለም። ስለዚህ ሐዋርያቱና ደቀ መዛሙርቱ ለአይሁድም ሆነ
ለአሕዛብ የምስራቹን ወንጌል በሚናገሩበት ጊዜ የመልእክታቸው ፍሬ ነገር
የሚያጠነጥነው # በኢየሱስ_ሰውነት_ላይ_አምላክነት እንዳለ በማሳወቅ
ነበር። መልእክታቸውን ለሚቀበሉት ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ(አምላክ)
ነው ብለው እንዲያምኑና እንዲቀበሉ በአፅንዖት ያስተምሩ ነበር። "ኢየሱስ ጌታ
ነው" ብለህ በአፍህ ብትመሠክር እግዚአብሔርም ከሞት እንዳስነሣው
በልብህ ብታምን ትድናለህ" ማለትም ኢየሱስን ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ
ነው፣ ሰው በመሆኑ ተጨማሪ አምላክም ጭምር ነው(አሕዛብን የካዱት
ሚስጥር) ብሎ ማመን በተግባር የሚገለጥ በፍቅርም የሚሠራ እንጂ የሞተ
ወይም የማይሠራ እምነት አይደለም። ከተግባር የተለየ እምነት የሞተ
እንደሆነ ሁሉ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት አምናለው የሚል ነገር ግን ራሱን
ለእግዚአብሔር ፈቃድ የማያስገዛ፣ እርሱ እንደተመላለሰ የማይመላለስ፣
ትእዛዛቱን የማያከብር፣ በአጠቃላይ የማይታዘዝ ሰው እምነቱም ሆነ ዐዋጁ
(ኢየሱስ ጌታ ነው ማለቱ) ሐሰት ከዛም ባለፈ የከንቱ ከንቱ ነው። ስለዚህ
ክርስትና "ኢየሱስ ጌታ ነው" ብሎ ከመናገርና ጌቱነቱን ከማወጅ እጅግ የላቀና
ዕለት ዕለት የክርስቶስ ጌትነት በእያንዳንዱ መእመን ሕይወት በግብር ሊታይ
የሚገባው ጉዳይ ነው። ሐዋርያቱ ሲያስተምሩ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ
ከአመፃ ይራቅ፣ በማለት ሰዎች የጌታ ኢየሱስን ስም እየጠሩ በእግዚአብሔር
ላይ እንዳያምፁ፣ ማለትም ኃጢአትን እንዳይሠሩ በ2ተኛ ጢሞ2:19 ላይ
አሳስበዋል። ምክንያቱም የጌታ ኢየሱስን ስም የሚጠራና ጌትነቱን የተቀበለ
ሰው በቅድስና እየኖረ በስራውና በንግግሩ ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር
ማድረግ ስላለበት ነው።
⇨በሐዋርያት ዘመንና ከዚያም በኃላ በነበሩበት ዘመነ ሰማዕታት ክርስትያኖች
የኢየሱስ ጌትነት በአደባባይ እንዲክዱና ቄሳር ወይም ጣዖታት ጌቶች እንደ
ሆነ እንዲመሠክሩ ይገደዱ ነበር። እውነተኞቹና በመንፈስ ቅዱስ የተረዱ
ምእመናን የኢየሱስን ጌትነትና አዳኝነት ከእርሱ ሌላ ጌታም ሆነ አምላክ
እንደሌለ በመመስከር ሰማዕት ሆነዋል። ለአንበሳ ተሰጥተዋል፣ በእሳት
ተቃጥሏል፣ በዘይት ተቀቅለዋል፣ በሰይፍ ተሰይፈዋል በአጠቃላይ እስከ ሞት
ድረስ ፀንቷል። የኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት በልብ አምኖ በአፍ መሥክሮ
የሚዳንበት መንገዱ ይህ ነው። በሊቢያ በISIS የሰይጣን ባለሟሎች
ሀይማኖታቸውን እንዲክዱ ማለትም ኢየሱስ አምላክና ሰው እንዳልሆነ
እንዲናገሩ ለኦርቶዶክስ ምእመን ለቀረበላቸው የሞትና የሕይወት ጥያቄ ስጋን
እንጂ ነፍስን መግደል በማይችሉ ከሓዲዎች ፊት በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው
ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ መሥክረው አንገታቸው ለሰይፍ ሰጥተው ሰማእትነት
ተቀብለዋል። ለዚ ነው ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በቃል ብቻ ሳይሆን በኑሮአችንና
በሕይወታችን መሆን ይጠበቅብናል። ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ቢሰርቁ፣
ቢዘምቱ፣ በቂም በጥላቻ በዘረኝነት በጉቦኛነት ፍርድ እያዛቡ በቃሉ እየካዱ
ለጥቅምና ለከንቱ ፍላጎት ማዋል የሞት ቅጣት ያመጣ እንደነበረ ዛሬም
የክርስቶስ ስም በከንቱ መጥራት በመንፈስ ሙትነት ያሳያል። በከንቱ ስሙን
ከመጥራት፣ ከመማልና ከመገዘት ልንቆጠብ ያስፈልገናል።
⇨ስብሐት ለእግዚአብሔር⇦
⇨28/01/2010 ዓ·ም⇦


#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
@And_Haymanot