፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ድንግል ማርያምን እመቤት ማለት የይገባል?

@And_Haymanot

የተሃድሶ መናፍቃን በነገረ ድንግል ማርያም ላይ ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል ቅድስተ ቅዱሳን እናታችንን እመቤት ማለታችን ኢ-መፅሐፍ ቅዱሳዊ አድርገው ይቃወማሉ፡፡ እናት ቤተክርስቲያናችን መፅሐፍ ቅዱስን አብነት አድርጋ ታስተምራለች፡፡

ሲጀምር " እመቤት " ማለት በአንድ ቤተሰብ መካከል አስተዳዳሪና ኃላፊ የሆነች የታላቅ ሴት መጠሪያ መሆኑን
መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት ፍፁም ስህተት የሆነ ሴቶች የማይጠሩበት ስም አይደለም ፤እንኳን ጸጋን ሁሉ ለተመላች ፣ ከሴቶች ሁሉ ለተለየች ፣ አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ይቅርና ብዙ ሴቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደምናነበው እመቤት ተብለው ተጠርተዋል ።

እስቲ ለአብነት ከመጽሐፉ እየጠቀስን እንይ ፦
፨ የአብርሃም ሚስት ሣራ እመቤት ተብላለች" እርሱም ወደ አጋር ገባ፥ አረገዘችም እንዳረገዘችም
ባየች ጊዜ እመቤትዋን በዓይንዋ አቃለለች።" እንዲል ዘፍ 16 : 4
አጋር ከሣራ ተለይታ በኮበለለች ጊዜ
" የእግዚአብሔር መልአክም ወደ እመቤትሽ ተመለሺ፥ ከእጅዋም በታች ሆነሽ ተገዥ አላት።"ይላል ዘፍ 16 : 9
ወዳጄ የእግዚአብሔር መልአክ የሰው
ልጅ እመቤት ተብሎ ባይጠራ ኖሮ ወደ እመቤትሽ ይል ነበር ?
፨ ወዳጄ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ ቀጥራ የምታሰራዋን ሴት ምን ብሎ ነው የሚጠራት ?
° የንእማንን ሚስት ታገለግል የነበረችው ብላቴና " [ እመቤትዋንም ] ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር አለቻት። " 2ኛ. ነገ5 : 3
፨ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ያገልጋይቱ ዓይን ወደ እመቤቷ ነው ይለናል ።
° " እነሆ፥ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ የባሪያይቱም ዓይን ወደ [ እመቤትዋ ] እጅ እንደ
ሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው። " መዝ 124 :2
፨ ጠቢቡ ሰለሞንም እንዲህ ይላል ፦
° " በሦስት ነገር ምድር ትናወጣለች፥ አራተኛውንም
ትሸከም ዘንድ አይቻላትም።
፨ ባሪያ በነገሠ ጊዜ ፣
፨ ሰነፍም እንጀራ በጠገበ ጊዜ፥
፨ የተጠላች ሴት ባል ባገኘች ጊዜ፥
፨ ሴት ባሪያም [ እመቤቷን ] በወረሰች ጊዜ። "መ. ምሳ 30 : 21 - 23
ወዳጄ ይሄ ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ተጽፎ ሳለ ፤ ወይ ሳያነቡ ወይ ሳይጠይቁ ገና ለገና እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያምን ለመቃወም ሲባል ብቻ "ለወንድ ጌታ ለሴት እመቤት እንላለን ይሄ አባባል ፍጹም ስህተት ነው " የሚለውን የአጋንንት ስብከት ከየት
አመጣችሁት ? እውነት እናንተ እንደምትሉት ቢሆን ኖሮ እነሣራ ፣ የንእማን ሚስት እና ሌሎቹም ሴቶች ለምን እመቤት ተባሉ ? እመቤት ማለት የማይገባ ከሆነ የእግዚአብሔር መልአክ ፣ ቅዱስ ዳዊት ፣ ጠቢቡ ሰለሞን
ሴቶቹን ለምን እመቤት ብለው ጠሯቸው ? ነው መጽሐፉ ተሳስቶ ይሆን ?
መቼም ምክንያት እየፈጠሩ ለመካድ ለማስካድ እንጂ ለማመን አልተፈጠራችሁምና ይሄ በብሉይ ኪዳን እንጂ በአዲስ ኪዳን አይባልም ካላችሁ ማስረጃ ልስጥ ፤ ወዳጄ ፍቁረ እግዚ ቅዱስ ዮሐንስ 2ኛ የዮሐንስ መልእክቱን የጻፈው ለማነው ? አታቀውቁትም እንጂ ሲጀመር ብታውቁት ቃሉን እንደዚህ አንጋዳችሁ አወላግዳችሁ ባልጻፋችሁም
ነበር ፤ ታሪኩ ሰፊ ሲሆን ነገር ላለማርዘምና ቀጥታ ለጥያቄው
መልስ ለመስጠት ያህል ብቻ ቅዱስ ዮሐንስ ይቺን ሁለተኛ መልእክቱን የጻፈው ጣኦት ያመልኩ የነበሩ የነገሥታቱንና
የመኳንንቱን ልጆች ሞግዚት ሆና ታሳድግ ለነበረችው ሮምና ለምትባል ሴት ነው ።
ቅዱስ ዮሐንስና አብሮኮሮስ አስተምረው አሳምነው አጥምቀው ከአምልኮ ጣኦት ወደ ወገኛይቱ ወደ ክርስትና እምነት ከመለሷት በኃላ ለስብከት ወደ ሌላ አገር ይሄዳሉ፤ ከሄዱም በኃላ ግን በእምነቷ እንድትጸና እና እንድትበረታ ሲል ይቺን ሁለተኛይቱ የተባለችውን የዮሐንስ መልእክቱን የጻፈላት ። ወዳጄ ቅዱስ ዮሐንስ ለዚህች በነገሥታቱና በመኮንንቱ ቤት በሰራተኝነት ፣ በሞግዚትነት ለምታገለግለው ሮምና
ለተባለችው መልእክቱን ሲጽፍ ምን እንዳላት ታውቃለህ ? [ እመቤት ሆይ ] እያለ ነበር አክብሮ ይጠራት የነበረው ።
እስቲ የጻፈውን ቃል በቃል እንየው ፦
" በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ
ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ "ይላል 2ኛ.ዮሐ 1 : 1 - 2
ወዳጄ እመቤት ብቻ አይደለም ያላት
" የተመረጠች እመቤት " ማለቱን አስተውል ። ሲቀጥል ቁ. 5 ላይ
" አሁንም፥ እመቤት ሆይ፥ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች
ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም። "ይላታል 2ኛ. ዮሐ 1 : 5 ወዳጄ የሕግ ፍጻሜና የምትበልጠው ጸጋ የተባለች ፍቅር
ይኖራቸው ዘንድ ሲጽፍላት
" እመቤት ሆይ ... እለምንሻለሁ " ብሎ ሲማጸናት ታያለህ ?
ታዲያ እንደ እናንተ አገላለጽ የሰው ልጅ ጌታና እመቤት ተብሎ የማይጠራ ፍጹም የሆነ ስህተት ከሆነ ቅዱስ ዮሐንስ ሮምናን ለምን እመቤት ሆይ እያለ ጠራት ? እናንተ ከዮሐንስ ትበልጣላችሁ?
አናንተ ናችሁ እኛ ነን በመጽሐፍ ቅዱስ የማናምነው? ከላይ ያየናቸው የብዙ ሴቶች እና የሮምና እመቤት መባል
ፍጹም ስህተት ያልሆነ ፤ የሰማይና የምድር ንጉሥ እናት የሆነች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እመቤት መባል እንዴት ሆኖ ነው ፍጹም ስህተት የሚሆነው ?

በአዳምና በሔዋን አማካኝነት ወደ ዓለም የገባውን መርገም የሻረ ጌታ እግዚአብሔር ከእርሷ በመወለዱ እመቤታችንን እግዝእተ በዙኃን [ የብዙኅን እመቤት ]
ትባላለች ። እንዲሁም ዓለም ሁሉ በዳነበት በክርስቶስ የማዳን ሥራ ያመንን ክርስቲያኖች ሁሉ በክርስቶስ አንድ
ቤተሰብ በመሆናችን ቅድስት እናቱ ድንግል ማርያምእመቤታችን ናት ።
ወዳጄ ፦ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ እመቤታችን እንደ ሌሎቹ ሴቶች እመቤት ብቻ አላላትም ንግስት
እንጂ !" በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ
ትቆማለች ......
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ ( ይለምናሉ ይማጸናሉ )......
በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ ...... ......
[ ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ ] " ይላታል መዝ 45 : 9 - 17
ወዳጄ የትንቢቱ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ራሷ እመቤታችን ምን እንዳለች እንይ
" እነሆም ከዛሬ ጀምሮ [ ትውልድ ሁሉ ] ብፅዕት ይሉኛል " ሉቃ 1 : 48
ይቺ በንጉሡ ቀን የምትቆም ፣ የምድር አሕዛብ ሁሉ በፊቷ የሚማጸኗት ፣ በአባቶሽች ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ
የተባለች ፣ ገዢ አርጋ የመሾም ስልጣን የተሰጣት ፣ ትውልድ ሁሉ ስሟን የሚጠሯት የሚያመሰግኗት ንግስት
ማነች ? ለስም አጠራሯ ክብር ምስጋና ይግባትና የንጉሡ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል አይደለችምን ?
ልበ አምላክ የተባለ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ ሰው ሁሉ እናታችን እንደሚላትም ተናግሯል
"ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤
እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።"
ሲል መዝ 88 : 5 ጌታም በእለተ አርብ ተሰቅሎ ሳለ እመቤታችንን ለዮሐንስ
" እናትህ እነኋት " በማለት በሱ አንጻር ለዓለም ሁሉ እናትና እመቤት እርጎ ሰቶናል ዮሐ19 : 27
ፍቁረ እግዚ ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዮ ያያት ፦ " ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፣
ፀሐይን ተጐናጽፋ
👍1
፣ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት ፣ በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት
አንዲት ሴት ነበረች......
እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች......
ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ። አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን
ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች "ራዕ 12 : 1-5
ሲል የገለጻት የከበረች ሴት ማነች ?
ከንግስቲቱ ከእመቤታችን ውጭ ፀሐይን የተጎናጸፈች ፣ ጨረቃን ከእግሯ በታች ያደረገች ፣ በራሷ ላይ አሥራ
ሁለት አክሊል የደፋች ፣ አሕዛብን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛውን ጌታ የወለደች ማናት ? ወዳጄ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥረው ግሩምና ድንቅ አርጎ ፣ የዚህ ዓለም ገዢ ( ጌታ ) አርጎ እንደፈጠረው ሳታውቁ ነው ፤ ወንድ ጌታ ሴት እመቤት ልትባል አይገባም ፍጹም ስህተት ነው የምትሉት ? የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ
ተፈጠረ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ? እግዚአብሔር የሰማይና የምድር ገዢ ( ጌታ ) እንደሆነ ሁሉ ሰውም የዚህ ዓለም ገዢ ( ጌታ ) ሆኖ ተፈጠረ ማለት ነው ።
" እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ
የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።"
እንዲል ዘፍ 1 : 26 በተለይ " ይግዙ " የምትለዋ ቃል የወንዱን ጌትነት የሴቷን እመቤትነት የሚያሳይ ቃል ነው ።
አንተ ሰነፍ እንኳን የከበረው የሰው ልጅ አይደለም ሰይጣን ዲያቢሎስ የዚህ የጨለማው ዓለም ገዢ እንደሚባል
እንኳን አታውቅም ? " አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደርሶአል፤ አሁን የዚህ ዓለም
ገዥ ወደ ውጭ ይጣላል " እንዲል
ዮሐንስ 12 : 31 , 2ኛ. ቆሮ 4 : 4
መቼም ይሄንን የማታውቅ ደካማ ሰይጣን ዲያቢሎስ ለምን የዚህ የጨለማው ዓለም ገዢ ተባለ ? ተብለህ
ብትጠየቅ የባጥ የቋጡን እየቀባጠርክ ሰው ስታደክም ትውላለህ እንጂ መልስ የለህም ፤ የጸጋው ዙፋን የምስጢሩ ግምጃ ቤት ከሆነች ከተዋህዶ ተማር ፦
ሰይጣን ዲያቢሎስ የዚህ የጨለማው ዓለም ገዢ የተባለው ፤ የዚህች ዓለም ገዢ የሰው ልጅ የፈጣሪውን ትዕዛዝ አፍርሶና ኃጢአት ሰርቶ ስለበደለ ራሱን ለሰይጣን ከማስገዛቱም በላይ የሚገዛትን ዓለም ይዞ በሰይጣን
ቁጥጥር ሥር በመዋሉ ዓለማችን ከጌታዋ [ ከሰው ልጅ ] ጋር ለሰይጣን ተገዢ በመሆኗ ነው ሰይጣን ዲያቢሎስ
የዚህ ዓለም ገዢ ለመባል የበቃው ።
መቼም አናንተ አይታክቴ ሰው ናችሁና ሌላ ሰይጣናዊ ምክንያት እንደምትፈጥሩ አብሬ ስለኖርኩ ፀባያችሁን ልቅም አርጌ አቀዋለሁ ፣
የማታውቁትን ቢነግሯችሁ አትቀበሉም እሺ ተናገሩ ብትባሉ መልስ የላችሁም ፤ አሁንም እኔ ቤተ ክርስቲያን ያስተማረችኝን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘሁትን እውነተኛውን ነገርኳችሁ ልክ አይደለም የምትሉ ከሆነ እሺ እስቲ
አስተምሩን ቅዱስ ዮሐንስ ሁለተኛ መልእክቱን ለማነው የጻፈው ?

ለምን እመቤት ሆይ አላት ? ንግሥት የተባለች ማናት ? ለምን ንግስት ተባለች ? የልጅ ልጅ ስሟን የሚጠራው
ትውልድ ሁሉ ብጽእት የሚሏት ? በንጉሱ ቀኝ ያለችው የምድር አህዛብ በፊቷ የሚማልሉላት ? ፀሐይን የተጎናጸፈች ፣ ጨረቃን የተጫማች ፣ አሥራ ሁለቱን
ከዋክብት እንደ አክሊል የደፋች ይቺ የከበረች ሴት ማናት ?
ይቆየን
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
ቅዱሳን ስዕላት.pdf
1.6 MB
👆👆👆
ቅዱሳት ስዕላት
@And_Haymanot
👉መንፈሳዊ ስዕልና መጽሐፍ ቅዱስ
👉ስዕልና ጣዖት
👉ስዕልና የፕሮቴስታንት መንትያ አቋም
👉በስዕል ፊት ጸሎት ማድረግና መስገድ
👉ስዕልና ክርስትና
ሁሉንም በዚህ pdf አዘጋጅተናል
ይጠቀሙት(ለሌሎችም share)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
#ምክረ_አበው

«ምን እናድርግ?» (ሉቃ ፫፥፲፬)

ልጆቼ ሆይ «ምን እናድርግ?» ብላችሁ ራሳችሁን ስትጠይቁ በመጽፍ ቅዱስ ላይ በመጥምቀ ቅዱስ ዮሐንስ የተነገረውን ቃል አስቡ! ይህን ኃይለ ቃልም ታገኛላችሁ፦ «ጭፍሮችም ደግሞ፥ እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ» እንደተባሉ ልብ በሉ!።

ልጆቼ ሆይ፦ ምን እንደምታደርጉ ልንገራችሁ? ይህ እውነተኛና የታመነ ቃል ነው የምነግራችሁ! በማንም ላይ ግፍ አለመሥራት፣ በማንም ላይ በሐሰት አለመመስከርና አለመክሰስ፣ በማንም ላይ ያልተገባ ጉቦና የተለየ ጥቅማ-ጥቅም አለመጠየቅ፣ በማንም ላይ በሥልጣንህ ተመክተህ ፍርድ አለማጓደል፣ በማንም ላይ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደህ ራስህንም ሌሎች ሠዎችንም በገንዘብ አለመደለል፤ ለሀገርህና ከአንተ አገልግሎት ለሚጠብቅህ ሕዝብ ታማኝ መሆንን አለመዘንጋት፤ በላብህ ዋጋ ሕይወትህን ማጣጣም እንዳለብህም ተረዳ፤ ግፍን፣ ተንኮል፣ ሸርን፣ አሻጥርን፣ ሤራን፣ ምቀኝነትን፣ ከሕይወትህ አስወግድ፤ ትህትናን፣ ፍቅርን፣ የዋህነትን፣ መልካምነትን፣ ሠናይ ምግባርን፣ አርቆ አሳቢነትን፣ ልበ ሠፊነትን፣ ገርነትን፤ ገንዘብህ አድርግ።

ልጆቼ ሆይ፦ ምን እንደምታደርጉ ልንገራችሁ? ከትንሹ እስከ ትልቁ፣ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ከሕግ አውጪ እስከ ሕግ አርቃቂ፣ ከወታደር እስከ ባለሥልጣናት ድረስ፤ ከቀራጮች እስከ ጭፍሮች፣ አጠቃላይ ሕዝቡ ሁሉ ይሄ አማናዊ ቃል ለራሱ ገንዘብ ሊያደር ይገባል፤ ከላይ የተጠቀሱ እኒህን ነገሮች ስትፈፅሙ የመጥምቀ ቅዱስ ዮሐንስ ቃል ሕይወታችሁን በሐሴት ያረሰርሰዋል፤ እናንተም «ምን እናድርግ?» ብላችሁ ለጠየቃችሁት ጥያቄም የእግዚአብሔር ምላሽ ይሄ ነው።

መልካም ቀን
@And_Hayamanot
"ሁላችሁም እንድታነቡት በክርስቶስ ፍቅር
እለምናችኋለው"
✞ ✞ ✞
@And_Haymanot

†††“ #የመድኃኔዓለም_ጥሪ” ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ መልእክተ ጳውሎስ /ሮሜ.8፡31-39/ ሲተረጕም ከተናገረው
†††

† “ልጆቼ! በድህነቴ ላይ ቸርነትን አድርጉልኝ፡፡ በዚህስ አልችልም ካላችሁ እሺ በቁስሌ ላይ ዘይትን አፍሱልኝ፡፡ አሁንም ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ እኔ ጠጋ በሉና አናግሩኝ፡፡ እናንተን ማየት፣ ከእናንተ ጋር መጨዋወት ይናፍቀኛልና፡፡ በገዛ ደሜ የገዛኋችሁ ልጆቼ! ከባድ ነገር እኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እኔ የምፈልገው ትንሽ ዳቦ፣ ጊዜአዊ ማደርያ፣ እንዲሁም የሚያጽናኑ ቃላትን ብቻ ነው፡፡ “ይህ ሁሉ
ማድረጌ ምን ይጠቅመኛል?” ካላችሁ ስለ ምሰጣችሁን ርስት መንግሥተ ሰማያት ብላችሁ አድርጉት፡፡ አሁንም ልባችሁ አልተነካምን? ስለ መንግሥተ ሰማያት አታድርጉት፤ ግን ደግሞ ስለ ሰብአዊ ርኅራኄ ይህን አድርጉልኝ፡፡ የእኔን መራቆት የሚያሳዝናችሁ በቀራንዮ አደባባይ ስለ እናንተ ብዬ የተራቆትኩት
ብቻ ነውን? ታድያ አሁንም ‘ኮ በደጃችሁ ላይ ተጥዬ ዕራቁቴን ነኝ፡፡ ለምን አላዘናችሁልኝም? የታሰርኩት በቀራንዮ ብቻ ነውን? አይደለም፡፡ ታድያ እንደምን አታዝኑልኝም? የማፈቅራችሁ ልጆቼ?

† በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሳለሁ “ተጠማሁ” እንዳለኩ ዛሬስ ስለ እናንተ ብዬ ደጋግሜ ይህን ቃል አልተናገርኩምን? ጕሮሮዬ ደርቆ ስለምን ትንሽ እንኳ አላሳዝናችሁም? ስለምንስ ይህ ሁሉ ፍቅር ስለ እናንተ መሆኑን
ትዘነጉብኛላችሁ? የምለምናችሁ እናንተን ባለጸጋ ለማድረግ አይደለምን? ይህችን ትንሽ ቸርነት ስላደረጋችሁልኝ በዐይን
ያልታየች፣ በጀሮ ያልተሰማች፣ በሰውም አእምሮ ያልታሰበች ርስት መንግሥተ ሰማያት እንድታገኙ ብዬ አይደለምን? ስለ እናንተ ብዬ ደሀ የሆንኩት ያኔ በመዋዕለ ሥጋዌዬ ብቻ እንደሆነ
አታስቡ ልጆቼ! ዛሬም ቢሆን በደጃችሁ የተጣልኩት ስለ እናንተ ጥቅም እንደሆነ ተረዱልኝ፡፡ ከባድ ነገር ‘ኮ አልለመንኳችሁም፡፡

† እስር ቤት መጥታችሁ ጠይቁኝ እንጂ አስፈቱኝ አላልኳችሁም፡፡ ታምሜ ጠይቁኝ እንጂ ፈውሱኝ አላልኳችሁም፡፡ ከጠየቃችሁኝ ብቻ በቂዬ ነው፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ!
በዚያ በአስፈሪው ቀን ስመጣ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” የሚለውን ቃሌ መስማት አትፈልጉምን? ዛሬ የሰጣችሁኝ ሁሉ የምረሳ ይመስላችኋልን? ያኔ በክብር ስመጣ ከእልፍ ወለዱ ጋር
እንድሰጣችሁ አትሹምን? የማፈቅራችሁ ልጆቼ! ከደጃችሁ ተጥዬ የምለምናችሁ፣
ከበራችሁ ላይ ቆሜ ማደርያን የምጠይቃችሁ፣ እጄን ዘርግቼ
እናንተን እናንተን የማየው ያኔ ትሉ ወደማይጠፋው እሳቱ ወደማያንቀላፋው እሳት እንዳትሄዱብኝ ብዬ ነው፡፡ ታድያ ይህን ለምን አትረዱልኝ ልጆቼ? ስለምን እንዳስቸገርኳችሁ ታስባላችሁ? ለእናንተ ጥቅም እንደሆነ እንዳትረዱ አዚም
ያደረገባችሁ ማን ነው? ከእናንተ ጋር ቁጭ ብዬ ልብላ ስላችሁ ስለምን ትገፈትሩኛለችሁ? ይህን ያህል ቸርነት አድርጌላችሁ ሳለሁስ ስለምን በግልምጫ አያችሁኝ? ይህን ያህል መውደድ ወድጃችሁ ሳለሁ ስለምን በቅጡ ልታነጋገግሩኝ አልወደዳችሁም? ከአዳም ጀምሮ ዓለም እስኪያልፍ ድረስ ያለው ሕዝብ ሁሉ በአንድ አደባባይ ላይ ቆሞ፣ እልፍ አእላፍ መላእክት
በዙርያዬ ረበው “ይህ/ ይህቺ ልጅ ወዳጄ ነው/ ናት፤ በመሆኑም
በታላቅ ክብርና ዕልልታ አጅባችሁ ወደ ዘለዓለም ደስታዋ አግቡት/ አግቧት” የሚለውን ፍርዴ አትናፍቁምን?

† ልጆቼ! እኔን ላለማየት ስለምን ፊታችሁን ትሸፍናላችሁ? ስለምን ታፍራላችሁ? እኔ ሳላፍርባችሁ ስለምን እናንተ አፈራችሁ?
ልጆቼ! ልባችሁ እንደተነካ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት ብቻ አይሁን፡፡ ከንፈራችሁን ብቻ አትምጠጡብኝ፡፡ ከእናንተ የምፈልገው አንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ ከላይ የጠየቅኳችሁን
ነገሮች ወደ ተግባር ቀይሯቸው፡፡ ለማይጠቅማችሁ ነገር አብዝታችሁ እየሮጣችሁ ለሚጠቅማችሁ ነገር አትስነፉ፡፡ “እኔኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ ይህን እንደምን እችላለሁ?” አትበሉኝ፡፡
አውቃለሁ! ነገር ግን ፈቃዳችሁን ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ራሴ አደርግላችኋለሁ፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብዬ ያስተማርኳችሁን ቃል ረሳችሁትን? /ዮሐ.15፡5/፡፡ እንግዲያውስ ከእናንተ የምፈልገው ፈቃዳችሁን ነው፡፡ አሁን ካላችሁበት ቦታ ተንቀሳቅሳችሁ ወጣ ስትሉ ታገኙኛላችሁ፡፡ አናግሩኝ! አፍቃሪያችሁ መድኃኔዓለም ነኝ፡፡” እንመለስ ፣እንመለስ፣እንመለስ........
ይህ የመዳናችን አንዱ መንገድ ነውና
ፍፁም ፍቅሩን ለሌሎች አጋሩት
https://tttttt.me/And_Haymanot/17
መልካም ቀን ተመኘን
👇Join👇
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"መናፍቅስ አይደለሁም"

@And_Haymanot

አንድ ጊዜ ስለ አባ አጋቶን ትህትና የሰሙ መነኮሳት ሊያዩት መጥተው፡፡ ቁጡ ነበርና የቀድሞው የቁጣ ስሜቱን መተው፤ አለመተውን ለማረጋገጥ ፈልገው "አመንዝራውና፣ ትዕቢተኛው አጋቶን ማለት አንተ ነህ?" አሉት፡፡ አባ አጋቶንም፦"አዎን ትክክል ነው፡፡" አላቸው፡፡ ቀጥለውም "ፍሬ የሌለው ነገር ዘወትር የምታወራ አጋቶን ማለት አንተ ነህ?" አሉት፡፡ አሁንም "አዎ ነኝ" አላቸው፡፡ በመጨረሻም "መናፍቁ አጋቶን ማለትስ አንተ አይደለህምን?" ሲሉት ያን ጊዜ "መናፍቅስ አይደለሁም" ሲል መለሰላቸው፡፡ "እስካሁን የተናገርንብህን ሁሉ ተቀብለህ፤ የመጨረሻውን ግን ለምን ተቃወምክ?" ሲሉት አባ አጋቶንም ፦ "የመጀመሪያዎቹ ወቀሳዎች ለነፍሴ ተስማሚዎች ናቸውና ተቀበልኳቸው፡፡
ኑፋቄ ግን ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡ እናም እኔ ከፈጣሪዬ መለየት አልፈልግም፡፡" አላቸው፡፡ እነርሱም ከዚህ ፅኑ የህይወት አቋሙ ተምረው ተመለሱ፡፡
የአበው በረከት አይለየን
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ምርትነሽን ቅዱስ ሲኖዶስ በይቅርታ ተቀበላት፤ በቡራኬ
አሰናበታት!

@And_Haymanot

የዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሎ ሐራ እንዲህ ዘገበችው፦
ለይቅርታ ያመለከተችው ‘ዘማሪት’ ምርትነሽ ጥላሁን: በምልአተ
ጉባኤው ፊት ቀርባ አስረዳች፤ በይቅርታ ተቀበላት፤ በቡራኬ
አሰናበታት!
• በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የሚዲያ መግለጫ
ትሰጣለች፤
• ለሌሎችም መመለስ ጥረት እንድታድርግ ብፁዓን አባቶች
አሳሰቧት፤
• “ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ቤት ናት፤ጥፋታቸውን አምነው
ከመጡ እንቀበላቸዋለን፤” /ብፁዓን አባቶች/
†††
የቅዱስ ሲኖዶስን የምሕረት ጥሪ በመቀበል፣ የቤተ ክርስቲያንን
አስተምህሮና ሥርዓት ከሚገዳደረው የእነበጋሻው ደሳለኝ ሕገ ወጥ ቡድን፤ ራሷን ለይታ፣ ይፋዊ የይቅርታ ጥያቄ ያቀረበችው ‘ዘማሪት’ ምርትነሽ ጥላሁን፣ የምልአተ ጉባኤውን ይቅርታ
አገኘች፡፡ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችን በተመለከተ፣ ለጥፋተኞችና
ለበደለኞች እንደጥፋታቸው መጠን ምሕረት የመስጠት፣ ይቅርታ
የማድረግና አስፈላጊ ከኾነም በቀኖና የመቅጣት ሥልጣን ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በዛሬ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የቀትር በኋላ ውሎው፣ የ‘ዘማሪት’ ምርትነሽን
ማመልከቻ ተቀብሎ ይቅርታ አድርጎላታል፡፡ የይቅርታ ማመልከቻዋ፣ በምልአተ ጉባኤው ፊት በንባብ ሲሰማ፣
ከሕገ ወጥ ቡድኑ ጋራ በአባሪነት ትንቀሳቀስ እንደነበር የጠቀሰችው ‘ዘማሪት’ ምርትነሽ፣ ጥፋት መፈጸሟን አምና ይቅርታ እንዲደረግላት ጠይቃለች፡፡ “ከእነርሱ ጋራ የነበርኩ ቢኾንም፣ የዓላማቸው ተከታይ
አይደለሁም፤” ያለችው ‘ዘማሪት’ ምርትነሽ፣ ሕገ ወጡ ቡድኑ
ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ እንቅስቃሴ በማድረጉ ለመለየት መወሰኗን ገልጻለች፡፡ “እነርሱ ወደ ሌላ እምነት ቢሔዱም የእኔ እምነቴ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነው፤ ወዳሳደገችኝ ቤተ ክርስቲያኔ ተመልሻለሁ፤ አስተምህሮዋንና ሥርዓቷን ጠብቄ እኖራለሁ፤” በማለት ውሳኔዋን ለምልአተ ጉባኤው አረጋግጣለች፡፡ በይፋ ለመመለስ መወሰኗን አድንቀው ምክር የሰጡ ብፁዓን አባቶች፣ “ተቀብለንሻል” ብለዋታል፡፡ እንደ እርሷ፣ ጥፋታቸውን
አምነው የሚመለሱ ሌሎችም ካሉ፣ የይቅርታ ቤት የኾነችው ቤተ ክርስቲያን እጆቿን ዘርግታ እንደምትቀበላቸው አስታውቀዋል፤ የበኩሏን ጥረት እንድታደርግም አበረታተዋታል፡፡
በመጨረሻም፣ ቡራኬ እንድትቀበል የታዘዘችው ምርትነሽ ጥላሁን፣ ከርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ
ማትያስ ፊት ወድቃ መስቀል ከተሳለመች በኋላ በይቅርታና ቡራኬ መሰናበቷ ተገልጿል፡፡ በቅርቡም፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤቱ አስተባባሪነት፣ የጠቅላይ
ጽ/ቤቱን ጨምሮ ለብዙኃን መገናኛዎች መግለጫ እንደምትሰጥ ተጠቁሟል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤው፣ የምርትነሽ ጥላሁንን የይቅርታ ጥያቄ ተቀብሎ ምሕረት ያደረገላትና በቡራኬ
ያሰናበታት፣ አጉራ ዘለሉን የተሐድሶ ኑፋቄ ተላላኪ በጋሻው ደሳለኝን አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን በለየበት ማግሥት መኾኑ
ትኩረት ያሰጠዋል፡፡ ከሕገ ወጥ ቡድኑ ተለይታና የምሕረት ጥሪውን ተቀብላ
ለመመለስ ለወሰነችው ምርትነሽ ጥላሁን፣ በዛሬው ዕለት የተደረገላት ሲኖዶሳዊ ይቅርታና አቀባበል፣ ብዙዎች፣ ራሳቸውን ከኑፋቄው ተጽዕኖ ቶሎ በማላቀቅ፣ ዛሬ ነገ ሳይሉ ወደ እናት ቤተ
ክርስቲያናቸው እንዲመለሱ የሚያበረታታ አብነታዊ እንደ ኾነ አያጠያይቅም፡፡
@And_Haymanot
"ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች፤ ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች።"ምሳሌ 14:1

@And_Haymanot
@And_Haymanot
አባ ይፍቱኝ!!

@And_Haymanot

ጥንታዊያን ክርስቲያኖች የሆኑት ኦርቶዶክሶች (ካቶሊክንም
ይጨምራል) ከአዲሶቹ ፕሮቲስታንት የዕምነት ክፍሎች እንዲሁም የነሱ ስራ አሥፈፃሚ ተሃድሶዎች ከሚለዩበት መካከል አንዱ ስልጣነ ክህነት ነው……ፕሮቴስታንቱ በካህናት ተልኮ እና ምስጢረ ክህነት አያምኑም መጽሐፍ ቅዱስ ግን ምን ይላል? በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው ኦሪታዊ ክህነት በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ሲተካ (በነገራችን ክርስቶስ ሊቀካህን ነው የተባለው ፤የካህናት አለቃ ማለት ነው ፡፡ሊቀካህን ከሆነ ከስሩ ካህናት አሉ ማለት ይሆናል) ጌታችን የይቅርታ ምንጭ ሆነ፡፡በአገልግሎት ዘመኑ
<<ተሰረየችልህ ›› እያለ ያውጅ ነበር፡፡ (ሉቃ 5፡20) ነገር ግን ‹‹ ጻፎችና ፈሪሳውያንም። ይህ የሚሳደብ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?
ብለው ያስቡ ጀመር።›› ኢየሱስም አሳባቸውን እወቆ አዎ ኃጢዓትን የሚያስተሰርይው እግዚአብሔር ብቻ ነው ብሎ አልመለሰም እሱ ራሱ እግዚአብሔር ቢሆንም ሰውነቱን
አጉልቶ‹‹ በልባችሁ ምን ታስባላችሁ? ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ። ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል? ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአት
ሊያስተሰርይ ለሰው ልጅ ሥልጣን
እንዳለው እንድታውቁ ብሎ፥ ሽባውን። አንተን እልሃለሁ፥ ነተሣ፥ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ አለው›› ሉቃ 5፡21 ስለሆነም የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው የሰው ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢዓትን ያስተሰርያል…..ነገር ግን ይህን የማስተሰርይ ስልጣን እሱ ከምድር ሊያርግ ሲል ለሰው ልጆች ለሐዋርያት ስልጣኑን ሰጥቷል .. አስቀድሞም ከትንሳዔው በፊት አሰራሩን ገልጦ ነበር…..በማቴ 16፡16
‹‹እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥
በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ
ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።›› ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንዳረጋገጠው ቤ/ክ የተመሰረተችው በካህናት/በጴጥሮስ/ መሰረት ላይ ነው
ስለሆነም የቤ/ክ መሰረት ካህናት ናቸው/ይህን የማይቀበል የጌታ ቃል አይቀበለም ማለት ነው../ ካህናት ሐዋርያትን ጌታ መሰረት ናችሁ ያለው ጥምቀት ፤ቁርባን፤ንስሀ፤ ያለ እነሱ
መፈጸም ስለማይቻል ነው፡፡

ጌታ ‹‹በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።›› ያለው በስልጣነ ክህነት በኩል የሚገኘው የኃጢዓት ስርየት መሆኑን የምናረጋግጠው ዮሐ 20፡22 ስናነብ ነው ‹‹ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና። መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው።›› ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን በምልዓት የተቀበሉት በበዓለ ኀምሳ መሆኑ እርግጥ ሆኖ ጌታ አስቀድሞ ለምን መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ አላቸው? ብለን ብንጠይቅ ኃጢዓትን ይቅር የማስባል ‹‹ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል።›› ያለውን የማስፈጽም ስልጣነ ክህነት ወይም ምስጢረ ክህነት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ እንዴት ይሆናል ?? ‹‹ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?›› ሉቃ 5 ፡22 የሚል ፈሪሳዊ ጠያቂ ካለ እኛ መልሳችን የጌታ ቃል ነው
‹‹ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአት ሊያስተሰርይ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ ›› ሉቃ 5፡22 ‹‹ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና። መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤
የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው።››በዮሐ 20፡22 እናማ መመሪያችን የጌታ ቃል እንጂ የእናንተ የጥርጥር ጥያቄ አይሆንም መልሳችን ነው፡፡

በነገራችን ላይ ጌታ ለሐዋርያቱ የሰጠው ስልጣነ ክህነት ለተከታዮቹ የሚደርሰው ልክ ጌታ እንደሰጠው እፍ ተብሎ
በአንብሮተ እድ/ እጅ መጫን / ስርዓት ነው እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ>> የሐዋርያት ሥራ8፡18
‹‹በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።››1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ‹‹ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ
ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።››ወደ ዕብራውያን 6፡1-2 እንግዲህ የክርስትና ቃለ ወንጌል በጽሁፍ /መጽሐፍ ቅዱስ/ ቢደርሰንም ሕዮታዊ ክህነቱ ግን ቀድመው ከተሾሙት እጅ በመጫን በመንፈስ ቅዱስ አሰራር ነው የደረሰን ስለሆነም
የመጻፍ ደረቅ ንባብ የቃል ተንጠልጣዮች ሕዮቱን አጥተው
ስልጣነ ክህነትን ቢክዱ አይደንቅም አላገኙትማ የካህናት አሰራር አገልግሎቱስ በጽሁፍ ስላላነበብነው የት ነው ለሚሉ እንደክህነቱ በሕይወት አግኝተነዋል ምክንያቱም እንኳን ጌታ የዚህ ዓለም አስተማሪ ሳያስተምር አይሾምም/አይመርቅምና/ ሐዋርያት
ያገኙትን ትምህርተ ክህነት ሹመቱን በሚሰጡበት ባልተጻፈ አሰራር አድርሰውናል እዚህ ላይ የዓለም ጥንታዊያን ክርስቲያኖች
መስዋዕተ ቅዳሴ መመሳሰልን ያጠይቋል..

እኛ ግን ካህናት በተሰጣቸው የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ መንፈሳዊ ስልጣን የኃጢዓት ይቅርታ ሰጪ እሱ እግዚአብሔር መሆኑን በማወጅ እግዚአብሔር ይፍታቹ ሲሉን መልሳችን ይፍቱን ነው ጌታ ራሱስ ‹‹ የመንግሥተ
ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ
በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም
የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።›› (ማቴ16፤6)
አይደል ያለው፡፡
ይፍቱኝ አባቴ!!!!
ምንጭ ዲያቆን ሸዋፈራው አለነ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
____ክርስትና________

@And_Haymanot

+ ክርስትናን እሳት የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ ድምጥያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ በተሳካላቸው ነበር፡፡ ክርስትናን መግደል
የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ አይሁድና ሮማውያን፣ ኮሙኒስቶችና ማኦኢስቶች ድል በነሡት ነበር፡፡ ክርስትና በቤተ ክርስቲያኖች መቃጠል፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መቆነጻጸል የሚያበቃለት
ቢሆን ኖሮ ኔሮንና ትራጃን፤ ዮዲት ጉዲትና ግራኝ ባስቆሙት ነበር፡፡

ክርስትና እሳት ሆኖ በእሳት ውስጥ ማለፍ ነው፡፡ ክርስትና እሳትን እሳት ሆኖ ድል መንሣት ነው፡፡ እዚህ እሳት ላይ ሦስቱ ሕጻናት ተጥለው ነበር፣ እዚህ እሳት ውስጥ ቂርቆስና እየሉጣ ተወርውረው ነበር፡፡ ይኼ እሳት ቅዱስ ፖሊካርፐስን በልቶት ነበር፡፡ ክርስትና ግን ይኼው አለ፡፡ ሊያጠፉት የተነሡት ሁሉ ተረት ሆነዋል፡፡ ክርስትና ግን ህያው ሆኖ አለ፡፡ የሠራነውን ቤተ ክርስቲያን ያቃጥሉ ይሆናል፣ የሠራነውን ሰማያዊ ቤት ግን
አይደርሱበትም፡፡ ንብረታችንን ይወስዳሉ፣ እምነታችንን አያገኙትም፤ እኛን ይገድላሉ፤ ነፍሳችን ግን ከዐቅማቸው በላይ ናት፡፡ ይህንን መከራ አስቀድመን የማናውቀው ቢሆን ኖሮ በደነገጥን ነበር፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን ስንሆን ይህ እንደሚመጣ እናውቅ ነበር፡፡
‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› ተብለናልና ተዘጋጅተን ነበር፡፡ እኛ ቆንጨራና ቦንብ፣ መትረዪስና አዳፍኔ አንይዝም፡፡ እኛ በጠጠር ጎልያድን የሚረታውን ይዘናል፡፡ በጩኸት ሳይሆን በዝምታ ኢያሪኮን የሚንደውን ይዘናል፡፡ በሁካታ ሳይሆን በእርጋታ የሚሠራውን ይዘናል፡፡ እነርሱ ሲጮኹ ከአጋንንት ጋር ያውካሉ፤ እኛ ግን ዝም ስንል ከፈጣሪያችን ጋር እንነጋገራልን፡፡

ዛሬ በምድር ላይ የለኮሱትን እሳት ብዙዎች በሰማይ እነርሱው ይቀበሉታል፡፡ አይቀርም፤ አምላካችንም ዝም አይልም፡፡ እንገደላለን፤ ግን እናሸንፋለን፤ እንቃጠላለን፤ ግን እንለመልማለን፡፡ እናጣለን፤ ግን እናገኛለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠሉት ሕንጻዎቿ በላይ ናትና፡፡
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ
//ዲያቆን ዳንኤል ክብረት//
join us
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
በመምህር #ምህረታብ_አሠፋ

#ሁለት_ነገር_ያስፈራኛል_አንድ_ነገር_ያስተምረኛል ከሚለው VCD ላይ፡፡ መቼም የማረሳት አንድ አባብሉ በአይምሮዬ ውስጥ ተቀርጻ ቁጭ ብላለች #ብዙ_ሠው_ሊያደንቀኝ_ይችላል_ግን_አደራ_የምላችሁ_ነገር_ቢኖር_ሠይጣን_አሳስቶኝ_ብወድቅ_እኔ_ምህረታብ_እንጂ_ኦርቶዶክስ_ቤተክርስታያኗ_አደለም_የወደቀችው፡፡ ስለዚህ እኔን የምታደንቁ ከእኔ በፊት ቤተክርስቲያኗን ጠብቁ[ተከተሉ] አለ በእውነት መቼም ከአይምሮዬ አይጠፍም፡፡ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፡፡ ብዙ ነገሮችን እያየሁ ግርም ይለኛል ከሳሽ እኛ ፈራጅ እኛ እረ ተዉ በእግዚአብሔር ስራ አንግባ አሁን ግን
የእግዚአብሔር ዝምታ እጅጉን አስፈራኝ አምላኬ ፈጥረህ ለፍጡር አትስጠን እኛ ባሪያወችክ ነን በቃችሁ መለያየቱ በለን
አንድ አድርገን ድንግል ሆይ ተዋህዶ አይሜኖታችንን ጠብቂልን
ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ለዘለአለም አለም ፀንታ ትኑርልን ጸልዩ
በእንተ ሰላመ ቤተክርስትያን!!!

ረጅም የአገልግሎት ዘመን ለመምህራችን እንመኛለን

@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ክርስቶስ አምላክ ነው
<unknown>
ሰላም ተወዳጆች እንደምን ቆያችሁን ዛሬ ለየት ባለ መልኩ ሙስሊሞች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች በመምህር ዲ/ን ሸዋፈራው የሰጠውን ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ እነሆ ብለናል
ብዙዎችም በተኩላ መሃል ናቸውና Share አድርጉት እንላለን፡፡
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሰበር ዜና

@And_Haymanot

ፍኖተ አበው የቅዱሳን ኅብረት የሚባል ዐዲስ የተሐድሶ ቡድን (አንጃ) ተፈጠረ፡፡ ቡድኑ ከስሙ ውጪ የተለየ ነገር የለውም፤ ቀድሞ የምናውቃቸው ተሐድሶ መናፍቃን የተሰባሰቡበት ነው፡፡ ይህን የግሪሳው አባል የሆነው ሃዋዝም በዚሁ በ #Telegram ገፁ እያስተዋወቀ ነውና ተጠንቀቁ፡፡ ምናልባት የተለየ ነው ከተባለ መምህር አእመረ አሸብር የዚህ ቡድን ግልጽ ደጋፊ መሆኑ ብቻ ነው፡፡ Aemere A.Alemayehu
በሚለው የፌስቡክ ገጹ የዚህን ቡድን “መርሐ ግብራት” በመለጠፍ ያስተዋውቃል፡፡ የቡድኑ ዋና ዋና አስተባባሪዎች በአሰግድ ሣህሉ ቃለ ዐዋዲ ቴሌቪዥን ላይ “በሰባኪነት” እና
“በዘማሪነት” የምናውቃቸው ዐዲስ ይርጋለም፣ መኳንንት ተገኝ፣ ሰሎሞን አቡበከር፣ ዳዊት በቀለ፣ ወዘተ ናቸው፡፡ በተለይ ዐዲስ ይርጋለምና መኳንንት ተገኝ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከተወገዘው
ገበየሁ ይስማው ጋር “የነገረ መለኮታውያን ጉባኤ” የሚባል
የተሐድሶ ድርጅትም እንደሚያስተባብሩ ይታወቃል፡፡ እሑድ ጥቅምት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. “ጉባኤ” እንዳላቸው በማህበራዊ ድህረ ገፅ ማስታወቂያ የለቀቁ ሲሆን ይህን የተሐድሶ መናፍቃን ጉባኤ ማሳገድ የሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ግዴታ ነው፡፡ ሼር ሼር ሼር
ምነው ጩኸት በዛ
@And_Haymanot
በመርከቧ መሃል ምነው ጩኸት በዛ
እያለ በውስጧ የአለም ሁሉ ቤዛ
በፍቅር እያለ ህይወትና ሰላም
የምን ማዕበል ነው የሚሰማው ከአለም
ውስጧ ምን እንዳለ በቅን ላላወቁ
ግራ ለተጋቡ በቅን ለጠየቁ
ያሻል ሊመከሩ ቶሎ እንዲመለሱ
የማይሆን ከሆነ ድምፅ እንዲቀንሱ
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ወዳጆቼ ሁሉም የእምነት አራማጆች ተዋህዶን ሲቃወሙ እንጂ ስለ ልዩነታቸው ሲወያዩ አይታዩም... የዛሬው መረጃችን ደሞ “ሉተራን” አለም አቀፍ ቤተክርስትያን እና “ሮማ ካቶሊክ” ቤተክርስትያን ለመዋሀድ ተስማሙ ይለናል፡፡
https://binjaminia.wordpress.com/2015/01/02/luteran/

#አስታውስ:- ተሃድሶም ቢሆን ደግሞ ነፍሳትን ወደ መናፍቃኑ አዳራሽ የሚወስድ ገባር ወንዝ ነውና አትሸወድ
👉 " አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤"
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:14)

፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot


እግዚአብሔር ከቤቱ አያርቀን ለሳቱትም ልብ ይስጥልን እንላለን
«ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡»

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
@And_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት
@And_Haymanot
👍1