ሳልፆም ሊፈሰክ ነው
አይ የኔ ነገር !
እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ
ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ
መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ
ስዋሽ ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
ገላዬን_ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
አይ እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
ጌታ ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው
አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" 🙏
================
ከናንተው የተላከ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
አይ የኔ ነገር !
እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ
ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ
መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ
ስዋሽ ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
ገላዬን_ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
አይ እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
ጌታ ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው
አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር" 🙏
================
ከናንተው የተላከ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ኪዳነ ምህረት
@And_Haymanot
ቢዘገይም… ብዙዎች ድንግል እናቱን ኪዳነ ምህረት ስንል ግራ ሲጋቡ አስተውላለሁ። በእርግጥም ግራ ቢጋቡ አይደንቅም ምክንያቱም ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስን ጠንቅቆ መረዳትና የመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ይፈልጋልና። በብሉይ አማናዊው መሥዋት ከመሰዋቱ
በፊት “የሥርየት መክደኛ” በእንግሊዘኛው ደግሞ “mercy seat` እንዲህም ሲባል “የምህረት ዙፋን" የሚባል ክፍል ያለው የቃል ኪዳኑ ታቦት ነበር። እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን በማድረጉ በታቦቱ ላይ ተገልጦ ሙሴን ያነጋገረው ካህናቱን መሥዋዕታቸውን ይቀበል ነበር። ይህ መገለጥ ግን ከሰዎች ልጆች ጋር ፍጹም እርቅ መፈጸሙን የሚያሳይ አልነበረም። ነገር ግን በዚህ ሕዝቡ ይጽናና ራሱንም ለበለጠ የትንሣኤ ሕይወት ያዘጋጀው ነበር። ምክንያቱም ለአባታቸው ለአብርሃም የገባውን ቃል ኪዳን እንደማያጥፍ ያምኑ ነበርና። በሠውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የወረደው ግን ድንግል እናቱን የቃል ኪዳኑ ታቦት አድርጎ ሥጋና ደም ተካፍሎ ሰው ሲሆን ነው። ያኔ በሰውና በእግዚአብሔር በሰውና በመላእክት በሰውና በሰው መካከል የነበረው ጠብ ፍጻሜ አገኘ። እርቅን ከሰው ጋር በተዋሕዶ ከፈጸመ በኋላ በሰው ልጆች ላይ ሰልጥኖ
የነበረውን ዲያብሎስ ከድንግል እናቱ በተካፈለው ሰውነት በመስቀሉ ድል ነሳው። ድል መንሳትንም ለእኛ ሰጠን። ስለዚህ እርቅ የወረደልን ተስፋ መንግሥተ ሰማያት የተሰጠን እርሷንና
ሥጋዋን ለራሱ የቃልኪዳን ታቦቱ በማደረግ ስለሆነ ድንግል እናቱን ኪዳነ ምህረት እንላታለን። ምክንያቱም ምህረትና እርቅ ለሰው ልጆች ሁሉ ሆኖአልና። እርሱ እግዚአብሔር ቃል ከእርሷ ከድንግል እናቱ ሥጋና ነፍስ
ነስቶ ባሕርያችንን ለብሶ በእርሱም ለፍጥረቱ ተገልጦ በእኛ ላይ የተፈረደውን ፍርድ በራሱ ተቀብሎ ዲያብሎስን ድል ነስቶ በእርሱ ያመኑትን እርሱን ተስፋ የሚያደርጉትን ከቅዱሳን
መላእክት ጉባኤ ደመራቸው፡፡ ያመኑትንም በጥምቀት እርሱን
ለብሰን እንድንነሣ በማድረግ ከቅዱሳን ጉባኤ እንድንደመር አደረገን፡፡ ሰውነታችንን መቅደሱ በማድረግ ሕጉንም በመንፈስ ቅዱስ በልቡናችን ሰሌዳ ላይ ጻፈልን፡፡ እነዚህንና ሌሎች
በረከቶችን ሊሰጠን የወደደው ከድንግል እናቱ በነሣው ሥጋና ነፍስ ነበር፡፡ ስለዚህም ድንግል እናቱ መንፈስ ቅዱስ አናግሩዋት “በእኔ ታላቅ ሥራን አድርጎአልና እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል” ብላ ከፍ አድርጋ ተናገረች፡፡ ስለዚህ ነው ኪዳነ ምሕረት መባልዋ፤ በእርሷ እርቅ ወርዶአልና።
በነቢዩም “ ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው
ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔ አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፡፡”(ዕብ.8፡10) የሚለው ቃል በእኛ የተፈጸመው በድንግል ማርያም ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ ጳውሎስ
“እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት
ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው”ብሎ ጽፎልናል፡፡ (2ቆሮ.3፡3)ይህን በማን አገኘነው ብንባል በክርስቶስ ነው፡፡ እርሱ የድንግል እናቱን ሥጋና ደም ሳይካፈል ባይወለድ ኖሮ ይህ የምህረት ቃል ኪዳን በእኛና በክርስቶስ መካከል ባልተፈጸመ ነበር፡፡ እናም አጥርቶ ለመረደት የሚፈለግ ቅድስት እናቱን ኪዳነ ምህረት የማለታችን ዋናው
ምክንያት ሰውነቷን የምህረት ቃል ኪዳን ታቦት በማደረግ ከርሷ በነሣው ሥጋ ዓለሙ መዳኑ ነው።... ይቆየን
በመምህር ሽመልስ

Forwarded from ፩ ሃይማኖት
Forwarded from መሠረተ ያሬድ ሰ/ት/ቤት ዘአሣሣ
✝የማይቀርበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ✝
"ያልተሟሸ ሸክላና ሰንበት ትምህርት ቤት ያልገባ ወጣት አንድ ናቸው።" ብፁዕ አቡነ ሰላማ
✍ እነሆ የአሳሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል #መሠረት_ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት #የ40ኛ_ዓመት_የልደት_በዓልን ምክንያት በማድረግ ከጳጉሜ 1-3 2011 ዓ/ም ድረስ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ተዘጋጅቷል እርሶም ወዳጅ ዘመዶን በመጋበዝ የእግዚአብሔር ቃል ይሰሙ ዘንድ ተጋብዘዋል በእለቱም፦
☞ መጋቢ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
☞ ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ
☞ ዘማሪ ቶማስ {መሰንቆ}... ተጋብዘዋል በመሆኑም የነፍሶን ማዕድ ተመግበው የሰንበት ትምህርት ቤታችንን ልደት አብረን እናከብር ዘንድ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናሳስባለን።
#አሳድገሽኛል_ቤቴና_ውበቴ
#አልለይም_ካንቺ_እስከ_እለተ_ሞቴ
#የፀጋው_ግምጃ_ቤት_ክብሬና_ማዕረጌ
#ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የዘላለም_ቤቴ
#ሰንበት_ትምህርት_ቤት_ክብሬና_ውበቴ
✞ የአባቶቻችንን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤታችንን ይጠብቅልን!!!✞ አሜን!!! ✞✞✞

❤1
ወዳጄ! ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን የምታውቃት አልመሰለኝም።
(በአርበው ልጅ ዳግም)
ሒድ እና አፅሙን አስነስተህ መሐመድ ግራኝን ጠይቀው ይነግርሀል። ዮዲት ጉዲትን ብትጠይቃት ምን ልትልህ እንደምትችል አስበው። ጣሊያኖችን ጠይቅ ገና የቤክርስትያኗ ስም ሲነሳ ፈርጥጠው ገደል ሊገቡ ነው የሚደርሱት ከዛ ምን ሊሉህ እንደሚችሉ ታውቃለህ "ጊዮርጊስን አንተ አታውቀም ሒድልን ነው የሚሉህ።"
:
ድርቡሾችን ሀሎ ብትላቸው ቁጭ አርገው ያስረዱሀል። ግብፆችን ኧረ እንዴት ነው ነገሩ እንበትናቸው ብለህ ልታማክራቸው ደጃቸው ብትጠና ኧረ ዞርበልልን ብለው በራቸውን ይዘጉብሀል ።
፡
ካቶሊኮችን ቫቲካን ድረስ ሔደህ ኧረ እርዱን እናጥፋቸው ብትላቸው። እናንተ በየገዳማቱ እና በየዋሻው የሚፀልይሉትን ስውራን አባቶች ፀሎት ስለማንችለው ቀጥ ብለህ በመጣ እግርህ ውጣልን ብለው አንተኑ እዛው ሊገሉህ ይችላሉ።
ስለዚህ ወዳጄ ሆይ ቤተክርስትያን እና ፖለቲካ ለየቅል ናቸው ቤተክርስትያኔን ለቀቅ አድርገህ ያቦካሀውን ፖለቲካ እዛው ተጨማለቅበት።
ታፍራና ተክብራ በዓለም መድረክ ገናና ሆኖ ለብዙ ሺህ አመታት የኖረችን እስከዛሬም ያለችን ቤተክርስትያን አንተ መንደርተኛው ጊዜ ያመጣውን ተራ የፖለቲካ ቁማርህን እዛው የጀመርክበት ጨርስ።
:
ባሻዬ! ቤተክርትያኗ አገልግሎቷ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው። አንድ ትንሽዬ ክልል ሳይሆን ዘላለማዊ መኖሪህን ገነትን ነው የምታሰጠህ። ገነት እኮ ታዲያ ባሻዬ! መራብ የለ መጠማት የለ! ዘርህን አትጠየቅ! ብሔርህን አትጠየቅ!ጭቅጭቅ የለ!መናቆር የለ! ምስጋና ብቻ።
በመጨረሻ!
“ኢትዮጵያ ሥጋችን ቤተ ክርስቲያን ነፍሳችን ናት፤ ነፍስ እና ሥጋ ደግሞ አንድ ነው፡፡ አገር ያለሃይማኖት፣ ሃይማኖት ያለ አገር የለም፤ ኢትዮጵያን ያህል አገር ማጣት እግዚአብሔርን ከሚያህል ጌታ መለየት ሞት ነው፡፡ ሃይማኖትን እና ነጻነትን ማጣት ሽንፈት ነው፤ ስለ አገር፣ ሃይማኖት እና ነጻነት መሞት ደግሞ ክብር ነው፡፡” (የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ)

ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መንግሥትን ወክለው
እየተሳተፉ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚደንት
"የኦሮምያ ቤተ ክህነት የሚባለው የማይታሰብ ጉዳይ ነውና
እኛም አንፈቅድም የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ
እንደመንግስት መቸውኑ ተቀባይነት አይኖረውም" ማለታቸውን
የEOTC TV ጋዜጠኛው ዲ/ን ኃይሉ ገልጾልናል።
ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ በላይ ናት።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
እየተሳተፉ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚደንት
"የኦሮምያ ቤተ ክህነት የሚባለው የማይታሰብ ጉዳይ ነውና
እኛም አንፈቅድም የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ
እንደመንግስት መቸውኑ ተቀባይነት አይኖረውም" ማለታቸውን
የEOTC TV ጋዜጠኛው ዲ/ን ኃይሉ ገልጾልናል።
ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ በላይ ናት።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
EOTCMK TV
ማህበረ ቅዱሳን የሙከራ ሥርጭቱ ተጀመረ አዲሱ የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥን የሙከራ ሥርጭት እነሆ ተጀመረ። ሥርጭቱንም ከዛሬ ጀምሮ መከታተል
ትችላላችሁ።
SATELITE: NILESA TKU ወይም EUTELSA W3
FREQUENC: 11555
SYMBOL RATE: 27500
POLARIZATION: V

እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን እስከ ዛሬ ጠዋት 3:00 ይቅርታ እንዲጠይቁ ቅዱስ ሲኖዶስ ገደብ ሰጠ፤ ጥያቄአቸው በተጀመረው የመሪ ዕቅድ ትግበራ ማሕቀፍ እንደሚፈታ ገለጸ የጥያቄአቸው መነሻ በኾኑት በኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት፥ የስብከተ ወንጌል፣ የዕቅበተ እምነት እና የአገልጋዮች እጥረት… ወዘተ. ችግሮች ላይ ከምልአተ ጉባኤው ጋራ መግባባት ላይ ቢደረስም፣ ቀደም ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሰጠበት ጉዳይ እንደኾነ እያወቁ፣ “የክልል ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እናደራጃለን፤” ማለታቸውና የቋሚ ሲኖዶሱን ክልከላ ተላልፈው የሚዲያ
መግለጫ መስጠታቸው ስሕተት እንደኾነ ተገልጾላቸዋል፡፡ የክልል ጠቅላይ ጽ/ቤትም ኾነ የክልል ሲኖዶስ የማቋቋም
ዓላማ እንደሌላቸው የገለጹት እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በበኩላቸው፣ በክልል ደረጃ የአህጉረ ስብከትን ጉዳይ
የሚከታተልና የሚያስፈጽም፣ ከክልላዊ መንግሥታዊ አካላት ጋራ የሚያገናኝ፣ የሚያጋጥማቸውን መጓተትና እንግልት
የሚያስወግድ ተጠሪ እንዲሠየም ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፤ በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይኾን፣ በሌሎችም ክልሎች ለሚገኙ አህጉረ ስብከትም እንደኾነ ጠቅሰዋል፤ “በአንዲት ቤተ ክርስቲያንና በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ እናምናለን፤ አንከፋፍልም፤ አንገነጥልም፤” ያሉት በጉባኤው ፊት የቀረቡት አምስት
የኮሚቴው አባላት፣ “በክልሉ እየተባባሰ የመጣው የምእመናን ፍልሰት እና የመናፍቃን ወረራ ያሳስበናል፤” ብለዋል፡፡
በቤተ ክርስቲያን ሕግ እና የቃለ ዐዋዲ ደንብ ውስጥ የሚታዩ የአደረጃጀትና የአሠራር ክፍተቶችን ጨምሮ ለጥያቄአቸው መነሻ የኾኑት ችግሮች፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሥር በተጀመረው የመሪ ዕቅድ ትግበራ ማሕቀፍ እንዲመለስ በግንቦቱ የርክበ ካህናት
ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መውሰኑን ቅዱስ ሲኖዶሱ የውሳኔውን ቃለ ጉባኤ በመጥቀስ አስታውሷል፤ በመኾኑም፣
የኮሚቴው አባላት በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሥር በተቋቋመው “የመሪ ዕቅድ አመራር እና ትግበራ ዐቢይ ኮሚቴ” ውስጥ እንደሞያቸው መሳተፍ እንደሚችሉም አስታውቋል፡፡
ከዚህ በቀር፣ በሥራ ላይ በሚገኘው ሕገ ቤተ ክርስቲያንና የቃለ ዐዋዲ መተዳደርያ ደንብ መሠረት፣ የአህጉረ ስብከት ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶስ እና ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በመኾኑ፣ የተለየ ተጠሪ ይሠየም መባሉ፣ ሲኖዶሳዊ
መዋቅሯን እንደሚጥስና ተገቢም እንዳልኾነ የምልአተ ጉባኤው
አባላት አስረድተዋቸዋል፡፡ እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በማስከተል፣ “ጥያቄአችን በእናንተ በብፁዓን አባቶች ዘንድ ትክክለኛ ግንዛቤና ተቀባይነት እንዳያገኝ
ለማበላሸት ተንቀሳቅሰዋል፤” ያሏቸውን መንፈሳውያን የአገልግሎት ማኅበራት ለመክሠሥ ቢሞክሩም፣ “ከዚህ ጋራ
መያያዝ የለበትም፤” በሚል በምልአተ ጉባኤው ውድቅ ተደርጎባቸዋል፤ “የአንድን ብሔር መጠሪያ የክርስትና፣ ሌላውን የአረሚ ያደርጋል፤” ያሏቸውን መጻሕፍት ቢጠቅሱም፣ “የግለሰቦች ነው፤ ቤተ ክርስቲያንን አይወክልም፤” በማለት ተመልሶላቸዋል፡፡ በመጨረሻም፣ “ጉዳያችኹ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ተይዞ እየታየና መግለጫ እንዳትሰጡ ተከልክላችኹ እያለ ለምን ወደ ሚዲያ ለመውጣት ቸኮላችኹ፤ ለምን ሕዝቡን አሳዘናችኹ?” በማለት
ምልአተ ጉባኤው ጠይቋቸዋል፤ “ጥያቄአችን በግንቦቱ መደበኛ
ስብሰባ ራሱን ችሎ ያታያል ብለን ጠብቀን ስለነበረ ነው፤ አልታየልንም፤” በማለት መልሰዋል፡፡ የአደረጃጀትና የአሠራር ጥያቄአቸው በሲኖዶሳዊት ቤተ
ክርስቲያን ሕግ እና ደንብ መሠረት ምላሽ እንደሚሰጠውና ለዚህም ከመካከላቸው ምሁራንና ባለሞያዎች የኾኑት በመሪ
ዕቅድ ትግበራ ዐቢይ ኮሚቴ ውስጥ ተካትተው ሥራውን ማገዝና ማቀላጠፍ እንደሚችሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አቋሙን ገልጾላቸዋል፡፡ አያይዞም፣ “ሕግ ተላልፋችኋል፤ ቸኩላችኋል፤
ወደ ሚዲያ መውጣት አልነበረባችኹም፤ ይቅርታ ጠይቁ፤”
በማለትም አዟቸዋል፡፡ ጉዳዩ ከጠበቁት በላይና ውጭ መጮኹን እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ለምልአተ ጉባኤው አባላት ማመናቸው ተነግሯል፤ ነገር ግን፣ የኮሚቴው አባላት ጠቅላላ ቁጥር 13 በመኾኑ፣ ይቅርታ ለመጠየቅ ከኹሉም ጋራ መማከር እንዳለባቸው በመግለጻቸው፣ እስከ ዛሬ ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠዋት 3፡00 ድረስ በምልአተ ጉባኤው ገደብ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ አካባቢዎች በቀጣይነት
እየደረሰባት በሚገኘው ተጽዕኖና ጥቃት ጉዳይ ወሳኝ አቋም
በመያዝ አገልጋዮችንና ምእመናንን በነቂስ ለማነቃነቅ በጠራው
በዚሁ አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ የሚደርስበትን የጋራ
ውሳኔ ለማሳወቅ፣ ለዛሬ ረፋድ 4፡00 ብዙኀን መገናኛዎችን
መጥራቱ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ ሐራ ዘተዋህዶ

💢💢💢💢ይነበብ💢💢 💢💢
አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆዩልንን እምነት እኛም ደምና አጥንታችንን እኛነታችንን ገብረን እናስቀጥላለን። እኛ ብናልፍም ተዋህዶ ግን ለዘልአለም አለሞች ትቀጥላለች። ስጋዊ የሆነ ሁሉም ነገር ይቀራል እንጂ በአንዲት እምነት በተዋህዶ ምንም ድርድር የለም። ያገሬ ሰው ባንዲት እምነቱ ባንዲት ርስቱ ባንዲት እናቱ ድርድር አያውቅም። ማህተብ በአንገትታችን ያደረግንበት ሚስጥር አንገታችንን ለሃይማኖታችን እንሰጣለን ስንል ነው። "#የምሞትለት_ሃይማኖት_እንጂ_የምሞትለት_ብሔር_የለኝም!"
#ይህ_የኦርቶዶክሳውያን_ጉዳይ_ብቻ_አይደለም_የሁላችንም_ነው። እኔ ክርስቲያን ብሆንም መስኪድ ሲቃጠል እያየው ዝም የሚል ህሊና የለኝም ቸርች ሲፈርስ ፓስተር ሲታረድ እያየው ምን አገባኝ የሚል እሳቤ የለኝም ይህ የሰብአዊነት ጉዳይ ነው ሁላችንንም ይመለከተናል አንዳችን ስለሌላችን ያገባናል እኔ በወገኔ ላይ በሃይማኖቴ ላይ ለሚፈፀም በደል ዝም አልልም ያገባኛል። የወዳጄ ቤት ሲቃጠል እያየው ዝም ብል ትንሽ ቆይቶ ወደኔ ቤት እንደሚመጣ አላውቅም ማለት ነው። ይህንን መልእክት ሃይማኖት ሳትለዩ ለሁሉም ታካፍሉ ዘንድ አሳስባለው ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ሃገራዊ ግዴታችን ነው!። 04-01-2012 መስቀል አደባባይ
#ሁላችንም እንገናኝ! #Share

❖ መልካም አዲስ አመት አትበሉን!!!!!!!
@And_Haymanot
የ ፳፻፲፩ (2011) ዓ.ም የመልካም ምኞት መግለጫ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያዎች 'መልካም አዲስ አመት' ሲሉ "መልካም አዲስ ገረድ' ማለታቸው መሆኑን ያውቃሉ......
♦ "አመት" ተብሎ በአልፋው "አ" ሲጻፍ ሴት አገልጋይ ገረድን ይገልጻል። ለምሳሌ፦ "ተፈሥሒ ኦ አመት ወእም ድንግል ወሰማይ ሰማያዌ..." /ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ/ ሲል ገረድ(ሴት አገልጋይ) ና እናት፤ ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ ማለት ነው።
♦ "ዓመት" ሲሆን ዘመን ይሆናል። "...ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ።..."/መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ፤ ለሥእርተ ርእስከ(ለራስ ጸጉርህ)/ ሲል ደግሞ "የመጥቅዕና የአበቅቴ መጀመሪያ ርእሰ ዓመት ዮሐንስ ሆይ..." ማለት ነው።
✍ አመት የሚለው በብዙ ቁጥር አእማት ይሆናል። በዕብራይስጥ አማህ፤ በሱሪስት አምታ፤ በዐረብኛ ደግሞ አመት ይለዋል። ትርጓሜውም ሴት ባሪያ፤ ገረድ፤ ደንገጥር ማለት ነው። "...በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባሪያይቱ..." ዘፀ.11፥5 የሚለውን ግዕዙ "አመት እንተ ትነብር ዲበ ማሕረጽ።" ይለዋል። በዚህ አገባብ አማርኛው "ባሪያይቱ" የሚለውን ግዕዙ "አመት" ይላታል።
✔ ወንዶች ባሪያዎችን "አግብርት" ሲላቸው ሴቶች ባሪያዎችን ደግሞ "አእማት" ይላቸዋል። [ዘፍ.32፥5 ግዕዙን ንባብ ተመልከት]
♦ ዓመት የሚለው ደግሞ በብዙ ቁጥር "ዓመታት" ሲባል ዘመን፥ ዘመናት፥ ብዙ ቀን፥ የዕለታት ድምር ማለት ነው። "በባቢሎን ንጉሥ በብልጣሶር በመጀመሪያው ዓመት" ዳን.7፥1 የሚለውን ግዕዙ "በቀዳሚ ዓመተ መንግሥቱ።" ይለዋል። "የዕድሜህም ቁጥር ብዙ ነውና፥" ኢዮ.38፥21 የሚለውን ግዕዙ "ኊልቆ ዓመታቲከ፥" ይለዋል።
✍ ስለሆነም አንድ ሰው 'እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰን' ሲል 'እንኳን ለአዲሷ ገረድ አደረሰን' አለ ማለት ነው። ይኼ ደሞ ጸያፍ ነው።
♦ "እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን" ሲል "እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሰን ማለቱ ነው። ይኸውም የተገባ ነው።
✔ መልካም ምኞታችሁን የገለጻችሁ መስሏችሁ 'መልካም አዲስ አመት' አትበሉን!!!!!
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ