፩ ሃይማኖት
8.99K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
💢💢💢💢ይነበብ💢💢 💢💢

አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆዩልንን እምነት እኛም ደምና አጥንታችንን እኛነታችንን ገብረን እናስቀጥላለን። እኛ ብናልፍም ተዋህዶ ግን ለዘልአለም አለሞች ትቀጥላለች። ስጋዊ የሆነ ሁሉም ነገር ይቀራል እንጂ በአንዲት እምነት በተዋህዶ ምንም ድርድር የለም። ያገሬ ሰው ባንዲት እምነቱ ባንዲት ርስቱ ባንዲት እናቱ ድርድር አያውቅም። ማህተብ በአንገትታችን ያደረግንበት ሚስጥር አንገታችንን ለሃይማኖታችን እንሰጣለን ስንል ነው። "#የምሞትለት_ሃይማኖት_እንጂ_የምሞትለት_ብሔር_የለኝም!"

#ይህ_የኦርቶዶክሳውያን_ጉዳይ_ብቻ_አይደለም_የሁላችንም_ነው። እኔ ክርስቲያን ብሆንም መስኪድ ሲቃጠል እያየው ዝም የሚል ህሊና የለኝም ቸርች ሲፈርስ ፓስተር ሲታረድ እያየው ምን አገባኝ የሚል እሳቤ የለኝም ይህ የሰብአዊነት ጉዳይ ነው ሁላችንንም ይመለከተናል አንዳችን ስለሌላችን ያገባናል እኔ በወገኔ ላይ በሃይማኖቴ ላይ ለሚፈፀም በደል ዝም አልልም ያገባኛል። የወዳጄ ቤት ሲቃጠል እያየው ዝም ብል ትንሽ ቆይቶ ወደኔ ቤት እንደሚመጣ አላውቅም ማለት ነው። ይህንን መልእክት ሃይማኖት ሳትለዩ ለሁሉም ታካፍሉ ዘንድ አሳስባለው ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ሃገራዊ ግዴታችን ነው!። 04-01-2012 መስቀል አደባባይ
#ሁላችንም እንገናኝ! #Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot