፩ ሃይማኖት
8.97K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
እግዚአብሔር ሲቀጣ ሰው እንደሚቀጣ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ቅጣት የፍቅር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቁንጥጫ
የአባትነት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ተግሳጽ አሮጌይቱን ኢየሩሳሌም ከማንነታችን ነቅሎ አዲሲቱን ኢየሩሳሌም ለመገንባት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ተግሳጽ አንካሳው ልባችንን ለማቅናት ነው፤ ጠላትን ለመጣል ነው፤ ክፉውን እንዳናይ ነው፤ ስድብን ለማራቅ ነው፤ ከምርኮ ለመመለስ ነው፤ ለከበረ
ስምና ለምስጋና ነው፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የድንግል ማርያም ልጅ የአለም ሁሉ ቤዛ
🔷 🔷 🔷 🔷
🙏 መድኃኔዓለም - የገዢዎች ሁሉ ገዢ
🙏 መድኃኔዓለም - የነገስታት ሁሉ ንጉስ
🙏 መድኃኔዓለም - የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
🙏 መድኃኔዓለም ከአለም በፊት የነበር
🙏 መድኃኔዓለም - አለምን አሳልፎ የሚኖር
🙏 መድኃኔዓለም - አልፋና_ኦሜጋ ዘላለም የሚኖር
🔴 የአባቶቻችን አምላክ ለኛም አምላክ ቸሩ መድኃኔዓለም ምህረቱን ያብዛልን ~አሜንንን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
"አብያተ ክርስቲያናትን፣ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስን የሚያፈርስ ወይም የሚያቃጥል ሰው፥ እርሱ የእግዚአብሔር
ጠላት፣ ጣዖት አምላኪ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ማደሪያ የኾነ
ሰውነቱን፣ ቤተ መቅደስ ሰውነቱን በዘረኝነት እሳት የሚያቃጥል
ሰውም፥ እርሱ የእግዚአብሔር ጠላት፣ ጣዖት አምላኪ ነው፡፡"
መጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
"ነገርህ የተወደደ የዕውቀት መገኛ ጳውሎስ ሆይ እንድታማልደን እንለምንሃለን የትምህርትህን ፍለጋ እንከተል ዘንድ በርስትህ በመንግሥተ ሰማያት ዕድል ፈንታ እናገኝ ዘንድ።

የምዕመናን አለቃ ሹመትህ ከሐዋርያት በላይ የሚሆን ክቡር ጴጥሮስ ሆይ እኛን ወገኖችህን እጅህን ጭነህ ባርከን አክብረን ካንተ ጋር ባንድነት እንቆም ዘንድ።"

#መጽሐፈ_ሰዓታት

@And_Haymanot
@And_Haymanot
እኔስ እዘምራለሁ

እኔስ እዘምራለሁ ለሥላሴ /2/ 
ፈጥሮኛለና እና በሥጋ በነፍሴ 

እኔስ እዘምራለሁ ለሥላሴ 
ሥሉስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገን 
ሰውን ከመከራ ከሞት የምታድን 
ነፍሴ ትገዛልህ ትንበርከክልህ 
ቅዱስ ፈጣሪዬን አንተን ታምልክህ 

በመሐሪነትህ ጠብቀህ ያኖርከኝ 
በማዳን ችሎታህ ለዚህ ያደረስከኝ 
ለአንተ ለአምላኬ ምስጋና አቀርባለሁ 
ስምህን ለዘለዓለም ሁሌም እጠራለሁ 

አብርሃም ለአምላኩ በቀና ቢታዘዝ 
ሥላሴ ገቡና ቤቱን ባረኩለት 
ሣራንም ጎበኛት በእርጅናዋ ጊዜ 
ይስሐቅን ሰጧት ዘለዓለም ሥላሴ 
@And_Haymanot  
@And_Haymanot_bot
ካለ መኖር ወደ መኖር መምጣታችን የእግዚአብሔር የመጀመሪያው ስጦታ ነው

ይህን የምናውቀው በቅዳሴ ጎርጎርዮስ ውስጥ " እኔ ሳልኖር አንተ አበጀህኝ! " ተብሎ የተጠቀሰውን ቃል ስናስታውስ ነው። እግዚአብሔር ይህን የሕልውና ስጦታ ባይሰጠን ኖሮ ምንም አልነበርንም። ይህ በመሆኑም እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠን የመጀመሪያ ስጦታ እኛን መፍጠሩ ነው ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ! !

@And_Haymanot
@And_Haymanot
የ"ቶ" መስቀል

@And_Haymanot

1.ሰባተኛ ሳብዕ ፊደል ናት።ፍጹምነትን ታመላክታለች።
2.ክርስቶስ በቀራኒዮ በመስቀል ላይ መሰቀሉን የምታመለክት ናት።ክርስቶስ ሲሰቀል ፀሐይና ከዋክብት የ"ቶ" ቅርፅ ሰርተው በኢየሩሳሌም አናት ላይ ታይተዋል።

3.ቅዱስ ሚካኤል እና ቅዱስ ገብርኤል በሳጥናኤል ሁለት ጊዜ ከተሸነፉ በኋላ በሶስተኛው የ'ቶ" ቅርፅ በክንፋቸው ተቀርጾላቸው አሸንፈውት ወደ በርባኖስ ወርውረውታል።
4.'ቶ'ን ኢትዮጵያዊያን የህይወት ምልክት አድርገው ይወስዷታል።በአማራ ሕዝብ በተለይም ሴቶች ግምባራቸው ላይ
'ቶ' ፊደል መነቀስ ጥንታዊ ታሪክና ምስጢር አለው።
5.የሰው ልጅ የተፈጠረው በ"ቶ" ቀመር ነው።'ቶ' የሰው ቅርጽ ከላይ ያለውን ክብ ጭንቅላት፣አግድሙ መስመር
እጅን ትወክላለች።የተሰቀለ ሰውንም ትመስላለች።

*"ቶ" በግብፅ የዋሻ ስዕሎች፣በሳባውያን የዋሻ ላይ ስዕሎችና ማህተሞች ላይ ተገኝቷል።'ቶ"በጥንታዊ ግብጽ ሄሮግላፊክ ጽሑፎች ላይ የተለመደ ነው።
*በታሪክ "ቶ" ከክርስቶስ ልደት በፊት ግብጻውያን የአምላክ ምድር የሚሏት ቶርኔተር ወይንም ፑንት ናት።ፑንት
ምድር"ሕብስቲ፥ኽብሲ"የተባሉ በኋላም የሐበሻዎች ምድር ስትሇን የዛሬው ሶማሌላንድ መሆኗ ተረጋግጧል። ሕብስቲ፥ኽብሲ በኋላም ሐበሻዎች ንጉሥ ኤዛና በአስቀረጸው የድንጋይ ላይ ጽሁፍ ስማቸው ይገኛል።

*ፑንት በዕጣን እና በወርቅ ምርቷ ትታወቃለች። ከ2ሺህ ዓመት ቅ.ል.ክ.በቴባድ ከተማ የተሰበሰበ ግብረ ኃይል እና በቴብስ ቤተ መቅደስ ውስጥ በውብ ሁኔታ የተሳለ ስዕል በ1600 ዓመት ቅ.ል.ክ.ከፑንት ዕጣን ለማምጣት ወደ ፑንት ስለአደረጉት ጉዞ በሐማት ሸለቆ ካሉ ፍርስራሾችና አለቶች ላይ
ተቀርጾ ተገኝቷል።የግብፅ ንግሥት ሃትሼፕሰት በቀይ ባሕር በኩል የላከቻቸው መርከቦች በቤተ መቅደሷ ግድግዳ ተስሎ ይታያል።

*በግብፅ 18 ኢትዮጵያዊያን እንደነገሱ ይታወቃል።የኢትዮ-ግብፅ ንጉሥ ታዋቂው ሜምኖን በአቆመው ሐውልት ላይ ጧት ጧት ላይ ፀሐይ ሳይርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበረ ሄሮዶቶስ
መዝግቦታል።ክራር ደግሞ የኛ ሀብት ነው።
*ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ቲርሐቅ ኢየሩሳሌም በአሶር ንጉሥ ሰናክሬም ስትወረር ከወታደሮቹ ጋሻ ላይ "ቶ" መስቀል እንዳስቀረጸና ራሱም በ'ቶ' የተሰራ መስቀል ማሰሩን በድንጋይ
ላይ ጽሁፍ ተረጋግጧል።
*በኢየሩሳሌም በደተረገ የአርኪኦሎጂ ቁፋሮ የአካዝ ልጅ ንጉሥ ሕዝቅያስን መንግሥት ምስል ያየዘ ሸክላ የተገኘ ሲሆን በላዩ ላይም የ'ቶ' ፊደል ተቀርጾበት ተገኝቷል።
*በጥቅሉ 'ቶ' ሰው የተፈጠረባት ቀመር፣ፍጹም፣የስቅለት
ተምሳሌት፣ህይወት፣ድል አድራጊነት ምልክት ናት።
በዲ/ን ቤርዚል
@And_Haymanot @And_Haymanot_bot
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ

@And_Haymanot

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን 
ተጽናናሁኝ እረሳሁ ሀዘኔን 
የአምላክ እናት እመቤታችን 
ሞገስ ሆኝኝ ቀሪው ዘመኔን 



የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ 
አንቺን ተጠግቼ የዓለምዋን ቤዛ 
የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት 
ባርያሽን ሰውረኝ ከአስጨናቂ ሞት 
እናቴ ስምሽን ስጠራ 
አለፈ ያሁሉ መከራ 
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ 
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ 
ሰላም ለኪ 

ልቤ በአንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ 
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ 
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል 
የኃያላንን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል 
እናቴ ስምሽን ስጠራ 
አለፈ ያሁሉ መከራ 
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ 
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ 
ሰላም ለኪ 

ደጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ 
በመርገም ምክአቸው ሊለያዩኝ ሲሹ 
እሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው 
እመቤቴ አለችኝ ብላ አሳፈርኳቸው 
እናቴ ስምሽን ስጠራ 
አለፈ ያሁሉ መከራ 
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ 
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ 
ሰላም ለኪ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ጥያቄ ነው።
*★★*
★ ጦማሩ የተጻፈው ለኦርቶዶክሳውያን
የተዋሕዶ ልጆች ስለሆነጉዳዩ የማይመለከታችሁ የገዳዩ ወሃቢያ
እስላምና የገዳዩ የኤጄቶ ጴንጤ ቡድን አስተያየት ባትሰጡ ይመከራል። ተናግሬያለሁ።
#ETHIOPIA | ~ [ ስለዚህ ጉዳይ መጀመሪያ እስቲ በየቤታችሁ ምከሩበት።]
•••
ኑሮ ተመችቷቸው የሞቀ እንቅልፍ በመተኛት የእርጅና ዘመናቸውን በሙዳየ ምጽዋት በሚገኝ ገንዘብ ፈታ ብለው
የሚኖሩትን አረጋውያኑን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪዎችን ለጊዜው በሞቀ ፍራሻቸው ላይ እንደተኙ ትቶ በየጊዜው በማንም ወጠጤ እሳት የሚለኮስባትን
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከአክራሪው የጃዋር መሃመድ የወሃቢያ አክራሪ እስላምና ቡድንና ከአዲሱ አክራሪ የጴንጤ ቡድን የሚከላከላት፣ የሚጠብቃት “ በአግባቡ የሰለጠነ የተዋሕዶ ወታደር“ ወደ ማደራጀቱ ብንሄድ ምን ይመስላችኋል?
•••
መንግሥቱም በውስጡ የጴንጤና የእስላሞች ስብስብ ነው። በዓመት ውስጥ ከ30 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ሲነዱ መከላከያው ዳር ቆሞ እንዲያይ ነው የተደረገው። ምክንያቱም
የመከላከያው ሚንስትር ለማ መገርሳ ጴንጤ ነው። ጠቅላዩ ዐቢይ አህመድ ላዩ ጴንጤ ውስጡ አክራሪ እስላም ነው።
ኤታማዦር ሹሙ ድብን ያለ አክራሪ እስላም ነው። እናም መሽኮርመሙን ትተን በጊዜ ለመፍትሄው መዘጋጀት አለብን።
•••
ያለበለዚያ አይናችን እያየ ግሸን ደብረ ከርቤ፣ ቅዱስ ላሊበላ፣ቁልቢ ገብርኤል፣ ሃዋሳ ገብርኤል። ዝቋላና ምድረከብድ አሰቦት ሥላሴም ታሪክ ይሆናሉ። ተናግሬያለሁ አስቡበት። ቅርሶችም
በጊዜ በጠንካራ ምሽጎች ውስጥ ይቀመጡ። ዘመኑ ዳግማዊ
ግራኝ አህመድ ከአክራሪ ጴንጤ ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ የፈጸሙበት ወቅት ነው። እናም እናስብበት።
•••
ቲሸርት የለበሱ ዐማሮች የሚታሰሩበት። ሜንጫ ይዘው የሚፎክሩ የፖሊስ ጥበቃ የሚደረግለት ለምን ይመስልሃል።
ወዳጄ ሃይማኖት ነው። አሳሪዎቹን በደንብ ተመልከታቸው። ሌላ ምንም አይነት ስምም አትስጣቸው። ሃይማኖት ነው።
•••
እነሱ ቤተ ክርስቲያን ያቃጥላሉ። እኛ ከሥር ከሥር እየተከተልን እንገነባለን። እነሱ በኢኮኖሚ ይመነደጋሉ። ባንክ እየዘረፉ ጭምር ይበለፅጋሉ። እናም መንግሥቱ ፀረ ኦርቶዶክስ ነው።
አውሬ ነው። የ666 መልእክተኛ ዘንዶ ነው። ብታምኑም ባታምኑም ወደፊት ኦሮሞው ኦርቶዶክስ፣ ደቡቡ ኦርቶዶክሳዊ፣ጉራጌ ትግሬው፣ ወላይታ ከምባታ፣ ዶርዜው ወዘተ ታራጅ ነው።
ምን አልባት ትግሬ አሁን ስላልተነካ ደስስ ብሎት ተረጋግቶ ተቀምጦ ሊሆን ይችላል። ነገ ግን አክሱም ድረስ ገብተው ሲለጠልጡት ያኔ ነገርየው ይገባዋል።
•••
እስላማዊ ባንክ፣ እስላማዊ ወታደር ሕጋዊ በሆነበት ሃገር የወደፊት ዕጣ ፈንታህን ከአሁኑ ወስን። የሰላሌ ሸዋ ኦሮሞን ቤተ ክርስቲያኑን ኦሮሞ ነህ ብለው ከማቃጠል አልተመለሱለትም።
እናም ወገኔ አስቡበት። በሕጋዊ መንገድ አስቡበት። ይሄ ምክሬ
ነው።
•••
ወዳጄ በብሄራዊ ቲአትር ስታንዳፕ ኮሜዲ የሚሠሩትን የኔታ
እሸቱ አለማየሁንና ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ከጴንጤዎቹ ከለማ መገርሳና ከዐቢይ አህመድ ጋር ሲያወደለድሉ እያየህ ኦርቶዶክስ ውክልና ያላት መሶልህ አትጃጃል። እነሱ
የራሳቸው ቢዝነስ ላይ ናቸው። እነሱን እያየህ አትጃጃል። ሲቆይ እንደ ማስቲካ እንደሸንኮራም ተመጥጠው አገልግሎታቸውን ሲጨርሱ የሚጣሉ ናቸው። እናም ዳኒንና የኔታን እያየን
አንጃጃል።
••• ★ “ስለዚህ፦ አንተ የምትተኛ ንቃ ።” ኤፌ 5፥14
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ሐምሌ 17/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሐምሌ 19 ዕለት


@Meserete_Yared_Asasa

❖የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።

❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡

❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡

❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡

❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡

❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡

❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል።

✞ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት፣ በረከትና ምልጃ አይለየን✞✞✞ አሜን✞

@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa

👉 የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ከ አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት የ Facebook ገጽ የተወሰደ
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ምንፍቅና በቅዱስ ቃሉ ሲፋቅ!
#ስግደት_ለመላእክት
👉ኢያሱ ለመልአኩ ሰገደ
👉ዮሀንስ ስለምን አትስገድልኝ ተባለ?

@And_Haymanot

መናፍቃን የሚያነሱትን ጥያቄ ቀለል ባለ
መንገድ ስንመልስ!!
👉1. የእስራኤል መስፍን የሆነው ኢያሱ “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን” ብሎ
እንዳላለ !!መጽ.ኢያሱ 5ቁ13“……እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኘ አሁን መጥቻለሁ አለ. ኢያሱም ‘ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና’ ጌታየ ለባሪያው
የሚነግረው ምንድር ነው አለው. የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን አውልቅ አለው” የምታመልኩትን ምረጡ ያለው ኢያሱ ለመልአኩ በስህተት ሰገደ ብለን አናምንም!!!ለመልአኩ በግንባሩ መደፋቱም መልአኩን ለማክበር እንጅ ለማምለክ እንዳልሆነ እናውቃለን!!!ዛሬም ኢያሱን ተከትለን እንዲሁ ስናደርግ አምላክን ከመልአክ ለይተን ነው!!!የአንዱን ላንዱ ሳንሰጥ፣ሳንቀላቅል!!

👉2. ወንጌላዊው ዮሐንስ፡በራእይ 19ቁ10 እና 22ቁ8 ….በመልአኩ እግር ፊት ሰገድኩለት እሱ ግን አትስገድልኝ፣ ሁለታችንም የእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን አለኝ….የሚለውን ጥሬ ንባብ ለመላእክት ስግደት እንደማይገባ ለማሳየት መናፍቃን ያቀርባሉ!!!ተሳስተዋል!!
✔️(ሀ)ወንጌሉን፣መልእክታቱን፣ራእዩን የጻፈው ዮሐንስ ለመልአኩ የሰገደው ባለማወቅ ነው ማለት ይሄን ሁሉ የጻፈውን ዮሐንስ ለማን መስገድ እንዳለበት እንኩዋ የማያውቅ አዲስ ምእመን ማስመሰል ነው!!!ዮሐንስ የሰገደው መስገድ ስለሚገባው ነው!!!
✔️(ለ)መልአኩ አትስገድልኝ ያለው ስግደት የበላይና የበታች መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ዮሐንስ በክብር እደተስተካከለው አውቆ ነው!!!ለትህትና!!!
✔️(ሐ)መልአኩ በምእራፍ 19 ቁ 10 እንደተገለጸው ዮሐንስን አትስገድልኝ ቢለውም ዮሐንስ ግን በምእራፍ 22 ቁ 8’ም ዳግመኛ ለመልአኩ ሲሰግድ እናገኘዋለን!!ዮሐንስን ያህል የጌታ
ወዳጅ(ፍቁረ-እግዚእ) ተብሎ የተነገረለትና በጰራቅሊጦስ
መንፈስቅዱስ የወረደበት አባት ለመልአክ መስገድ ስህተት
መሆኑ ጠፍቶ፣ እየተነገረው ጭምር ከአንዴም ሁለቴ ሰገደ ማለት ቅድስናውን መጠራጠር ይሆናል!!!ስለሆነም መልአኩ
አትስገድልኝ ያለው ለትህትና ነው ስንል እናምናለን!!!

👉3. የሞቱ ቅዱሳን ከእኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም የምትሉ ሰዎች አላችሁ!!!እሺ ቅዱሳኑስ ይሁኑ ታዲያ መላእክት እኮ አይሞቱም!!!ስለታናናሾች የአብን ፊት ያያሉ እንጅ-በማቴ 18ቁ 10 እንደተጻፈው!በዘካርያስ 1 ቁ 13 የመልአኩ ምልጃ እንዲህ
ተጽፉዋል “አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ እነዚህ 70 አመት የተቆጣሀቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተማዎች የማትምራቸው እስከመቼ ነው አለው እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው” ታዲያ ሳንለምነው እንዲህ የሚማልድልን መልአክ ብንለምነውማ ምን ያህል ይማልድልን?ሰአሉ ለነ ሚካኤል ወገብርኤል እንበላቸውማ!!!

👉4.የሞቱ ቅዱሳን በክርስቶስ ህያው ስለሆኑ ከእኛ ጋር በመንፈስ
እንደሚገናኙ ደግሞ ይሄው!!!የሞቱ ቅዱሳን “እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነሱ እንደማያፍር” በዕብ 11 ቁ 16 ተጽፉዋል!!!የሞቱ ቅዱሳን አላዋቂዎች ሳይሆኑ ወደፍጹምነት የተሸጋገሩ ‘ፍጹማን’ መሆናቸው በዕብ 12 ቁ 22 ሰፍሮልናል!!! ጌታም ከአመታት በፊት በሞት የተለዩትን አብርሃምን፣ይስሀቅንና
ያዕቆብን ጠቅሶ “የህያዋን አምላክ ነኝ” ሲል በማቴ 22 ቁ 32 ገልጹዋል!!!ጌታችን በስጋ ስለሞተው አብርሃም በዮሀንስ 8 ቁ56 ሲናገር፡ “አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴትን አደረገ፤አየም ደስ አለው” ይላል!!!በአጸደ ነፍስ ያለው አብርሃም የጌታን ቀን አይቶ የተደሰተው በሰማይ ያሉ ቅዱሳን በምድር ካለነው ጋር ህብረት ስላላቸው ነው!! ዮሐንስ በራዕዩ ምዕራፍ 8 ቁ 3 “የዕጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚብሔር ፊት ወጣ” ይለናል!!መላእክት ጸሎታችንን ያሳርጋሉ!!!አእርጉ ጸሎተነ የምንላቸውም ለዚሁ ነው-እንደ ቅ/ያሬድ-እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ!!ሙሴስ በዘጸአት 32 ቁ 13 “በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ይስሀቅንና እስራኤልን አስብ” ብሎ በአጸደነፍስ ነፍስ ባሉ ቅዱሳን ስም ጌታውን ሲማጸን ከሞቱ ቅዱሳን ህብረት ስላለን አይደለምን?ነው እንጅ!!!

👉5. ይሄን ሁሉ ስንል ባለቤቱን ረስተን አይደለም!!!በቀጥታም እሱን ማረን እንለዋለን-እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በምህላ- መሀረነ አብ በማስታኮት!!!ስማን፣ተማለደን፣ታረቀን እንለዋለን!!! ግን እንደሌሎቹ አማልደን አንለውም!!!ሌሎቹ የሚያማልደን ጌታ ነው እያሉ ቤዛነቱን እንደአማላጅነት ስለሚወስዱት ነው እኛ ቅዱሳንን አማልዱን ስንል አምላክ ያደረግናቸው የሚመስላቸው!!! አምላካችን አንድ ነው!!!የሃይማኖታችን መሰረትም እሱ-ለዚህም ነው ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን ስንል የሃይማኖት ጸሎታችንን የምንጀምረው!!!
ይቆየን
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
ደብተራ

@And_Haymanot

፠፠፠የደብተራ ትርጓሜ በመዛግበተ ቃላት ወጥበባት፠፠፠
፠ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላቸው፡- ‹‹ደብተራ - ድንኳን፡፡ ደበተረ - ደብተር ዘረጋ፣ ጻፈ፣ ከተበ ፡፡ ተደበተረ - ተዘረጋ፡፡ ደብተራ - የድንኳን ስም፡፡ ደብተራ - ዜማ. ቅኔ፣ ሳታት (ሰዓታት)
የሚያውቅ፣ በደብተራ (በድንኳን) ውስጥ የሚመራ፣ የሚቀኝ፣ የሚዘምር፣ መንፈሳዊ አገልጋይ፣ ካህን፣ አወዳሽ ሳታት ቋሚ፡፡ ደብቴ - ከፊለ ስም ወይም ቁልምጫ፣ የደብተራ ወገን፣ የኔ
ደብተራ ማለት ነው፡፡›› ይሉናል፡፡
፠ግእዙም፡- ‹‹ደብተረ› ማለትን በአወራረዱ ሕግ በተንበለ ቤት
አስገብቶ ሲያበቃ ‹‹ተከለ›› ሲል ይተረጕምና ለድንኳን ይሰጠዋል፡፡ ግእዝ ድንኳን ለሚለው ቃል ከደብተራ በተጨማሪ ኀይመትና ደበና ማለትን ይጠቀማል፡፡ ደበና የንጉሥ ድንኳን
የሚጠራበት ስም ነው፡፡ ደበናንሳ (ባለእጅ) የሚለው ቃል ከዚህ
ስም ጋራ ስለመያያዝ አለመያያዙ አላውቅም!
፠የፕ/ር ሥርግው አማርኛ የቤ/ክ መዝገበ ቃላት፡- ‹‹ደብተራ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጕም ድንኳን ማለት ነው፡፡ ግን በቤተ
ክርስቲያን ውስጥ በቅኔ ማኅሌት የያሬድን ዜማ የሚዘምር፣ የሚመረግድ እንዲሁም ቅኔን የሚቀኝ ደብተራ ይባላል፡፡›› ብሎናል፡፡

፠በኢንሳይክሎፒዲያ ኢትዮፒካ፡- ደብተራ የሚለው ቃል እንደ ወረደ ከግሪክ የተቀዳ ሲሆን ትርጓሜውም እንደ ድንኳን የሚያገለግል ውጥር ቆዳ /ሌዘር/ ማለት እንደሆነ ተገልጧል፡፡
ደባትርን በቤ/ክ ካሉ ምሁራን ሁሉ ለይቼ the most educated clerics ያልኳቸው እኔ አይደለሁም፤ እንደነ ደንጎለጥ አንጠልጥሎ ሳይሆን አንጠርጥሮ የተረዳቸው ፈረንጅ ነው፡፡ በቤ/ክ የውስጥ አገልግሎት የቅዳሴና ውዳሴ ይባላል፡፡ የውዳሴው ድርሻ የደባትር ነው፡፡ የሚያወድሱት አምላካቸውን ነው፡፡ ውዳሴ የሃይማኖት አገልግሎት ስለሆነ በመደበኛ ፍ/ቤት
እንኳ አይዳኝም፤ በመንፈሳዊ ፍ/ቤት ብቻ ነው! እኒያ እግራቸው እስኪቀበተት ቆመው የሚያነጉ አገልጋይ ምሁራን ከውጪ በድውያን መጽልማነ ስም ስማቸው ተቀረደደ፤ በውስጥም ቤተ
ክርስቲያንን እየጋጡ በሰቡና በረቡ አምስት ከለባት ተዘነጠሉ እንጂ አገልግሎታቸውስ ‹‹ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሎ ዓለመ - ዓለምን የፈጠረ (እርሱ) ፈጽሞ የተመሰገነ ነው›› እያሉ ማወደስ ነበር፡፡ እነርሱ ቢጽፉ ጠንቋይ፣ ቢያሸበሽቡ ደናሽ፣ በፈሊጥ ቢናገሩ ቃላቸው ‹‹ቃለ ደብተራ››፣ ቢቀኙ ሰዓት ገዳይና ምዕመን አሰልቺ፣ ሕክምና ባልነበረበት ጊዜ ቁስል በቅጠል ቢያደርቁ ‹‹ሥር ማሽ ቅጠል በጣሽ›› ተባሉ እንጂ የሙሉ ሰዓት
አገልግሎታቸውስ ውዳሴ አምላክ ነበር፡፡ ሙያዎች ሁሉ በተከበሩበት፣ የሃይማኖት ነጻነት በታወጀበት፣ የቡድን መብቶች
ሁሉ ልዕልና አግኝተዋል በተባለበት ዘመን እነሆ ‹‹ደብተራ›› የወግ ማሳመሪያ ሆነ፡፡
፠ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ትርጕም፡- ደብተራ - ተማሪ፣ መምህር ያልሆነ አዲስ ምሩቅ፣ ቄስም መነኩሴም ወይም ዲያቆን ያልሆነ፣ ሥልጣነ ክህነት የሌለው፣ ያፈረሰ፣ የድብትርና መሬት የያዘ፣
ጸሀፊ፣ መድኃኒት ዐዋቂ፣ ጥፈት የሚጥፍ … ደግነቱ ሁሉም መማሩን አይክዱበትም፡፡ ‹‹ቃለ ደብተራ›› የተባለ እንደሁ የአሽሙርና የኵሸት ማበረታቻ (ወደ ተንኮል የሚገፋ) ንግግር ነው፡፡ ‹‹ዕፀ ደብተራ›› የምትባል የኵሸት ዕፅ አለች፤ ቀጠጥናም ትባላለች፡፡

፠መንፈሳዊ ተምሳሌት፡- እመቤታችን፣ መስቀል፣ የጌታ ሥጋ፣ ቤተ መቅደስ ሁሉም ደብተራ ይባላሉ፡፡ ቅጽል ከፊቱ እየገባና እየተዛረፈ ‹‹ደብተራ ብርሃን፣ ደብተራ ፍጽምት፣ …›› ይዜማል፤
ይመሰጠራል፡፡ ሐዋርያው በዕብራውያን 9 እና 10 ነገረ ድኅነትን ይተርክበታል፤ ሐዲስን ከብሉይ ያነጻጽርበታል ደብተራን፡፡

፠ትርጕሙ ሲጠቃለል፡- ደብተራ ማለት በመደበኛ ትርጓሜው ማኅሌታዊ ማለት ነው፡፡ መዓርጉ ‹‹ተማሪ›› የመባል ያህል
ይመስላል፤ ከማንም አይሰጥም፤ ግን ደግሞ ለማንም አይሰጥም፡፡ ዜማ፣ ቅኔና አቋቋም መሞካከርን ይጠይቃል፡፡
በመርህ ደረጃ መነኮሳት ደብተራ አይባሉም፡፡ ...ይቆየን
በአማን ነጸረ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አስታርቂኝ


አስታርቂኝ ድንግል ማርያም /2/ 
ከልጅሽ /3/ ከመድኃኔዓለም 

አስታርቂኝ ኃጢአትን ሰርቼ 
አስታርቂኝ ጫካ ውስጥ ቆሜአለው 
አስታርቂኝ ሥራዬ አሳፍሮኝ 
አስታርቂኝ ዘወትር አነባለው 
አስታርቂኝ ልጄ አዳም ብሎ 
አስታርቂኝ አምላኬ ሲጠራ 
አስታርቂኝ እነሆኝ ለማለት 
አስታርቂኝ አንደበቴ ፈራ 
አዝ ------------ 
አስታርቂኝ ሀብትን ተካፍዬ 
አስታርቂኝ ከገዛ አባቴ 
አስታርቂኝ ከቤቴ ኮበለልኩ 
አስታርቂኝ ይሻለኛል ብዬ 
አስታርቂኝ ገፍቼ ወጥቼ 
አስታርቂኝ የቤቴን ገበታ 
አስታርቂኝ ልበላ ተመኘሁ 
አስታርቂኝ የእንስሳት ገፈራ 
አዝ--------- 
አስታርቂኝ ወደ አባቴ ልሂድ 
አስታርቂኝ አሁን ተነሥቼ 
አስታርቂኝ ይቅርታ ልጠይቅ 
አስታርቂኝ እግሩ ስር ወድቄ 
አስታርቂኝ ልጅነቴ ቀርቶ 
አስታርቂኝ አድርገኝ ባርያህ 
አስታርቂኝ ከሞያተኞችህ 
አስታርቂኝ እንደ አንዱ ቆጥረህ 
አዝ ------ 
አስታርቂኝ ገና ሩቅ ሳለው 
አስታርቂኝ አባቴ አይቶኝ 
አስታርቂኝ ወደእኔ ሮጦ 
አስታርቂኝ አቅፎ ነው የሳመኝ 
አስታርቂኝ ጠፍቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ተገኘልኝ አለ 
አስታርቂኝ ሞቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ደግሞ ሕያው ሆነ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot