፩ ሃይማኖት
8.97K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
† በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል ላይ የሚነሱ
አንዳንድ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

-(ለፕሮቴስታንቶችና ተሐድሶዎች የቀረበ)
፩. አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድለ ተክለ ሃይማኖትላይ ‘ሰይጣንን አጠመቁት’ ይላል እያሉ የተሐድሶ መናፍቃን ይተቻሉ፡፡ እውን ግን ጻድቁ አባታችን
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በቁሙ ሰይጣንን
አጥምቀዋልን?

መልስ፡- በቀድሞ መጻሕፍት ሥጋ ለበስ የሆኑ አጋንንት ታሪክ የታወቀ ነው፡፡ እነዚህ ሥጋ ለበስ አጋንንት የአጋንንትን ሥራ የሚሠሩ ቢሆኑም
የሚዳሰስ ሥጋ ግን አላቸው፡፡ ለምሳሌ ድርሳነ ሚካኤል ዘጥር ላይ እንደ ተገለጠው እነዚህ በሽታዎችን ሁሉ የሚያመጡ ሥጋ ለበስ አጋንንት
እንደ ሰው ሁሉ ይታመማሉ፤ ይራባሉ፤ ይሞታሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ
በበረሐ ውስጥ አንዳንድ ጊዜም በውኃ ውስጥ ይኖራሉ፡፡

+ በገድለ ተክለ ሃይማኖትና በልደተ አበው ላይ እንዲህ ይላል “አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእነዚህ አውራጃዎች ሲመላለስ አንድ ቀን በውኃ ዳር ዐረፍ አለ፡፡ ጋኔንም ከውኃው ወጣና ደቀ መዛሙሩን ያዘው፡፡ አሳመመውም፡፡ እርሱም ጋኔን መሆኑን ዐወቀ፡፡ በረድኡ ላይም በመስቀል ምልክት አማተበበት፡፡ ጋኔኑም ፈጥኖ ወጣ ሸሸ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በእጁ ያዘው፡፡ ሥራዩንም አወጣበት፡፡ ያን ጊዜም ለሁሉ ታየ፡፡ እርሱም “ማነው ስምህ?” አለው፡፡ ጋኔኑም “ባሕር አልቀም” አለው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም “ከኔ ጋር ትኖራለህን?” አለው፡፡ እርሱም ገዘረውና ወደ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ጥምቀት አገባው፡፡ ስሙንም ክርስቶስ ኀረዮ(ክርስቶስ መረጠው ማለት ነው) አለው፡፡ ረድእም አደረገው፡፡ ወደ በኣቱም አስገባው፡፡ እርሷም አስቦ ናት፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚወድና ወንድሞቹንም ሁሉ የሚያስደስት ሆነ፡፡” (ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፩፤ ገጽ. 177-178፤ Getachew Haile, Geneaology, P.11&12)

+ በጥንታውያን ሰዎች ዘንድ በአጋንንት አሠራር ተጠምደው የሚኖሩ ጣዖት አምላኪ ሰዎችን ባደሩባቸው አጋንንት ስም መጥራት የተለመደ ነው፡፡ ሰው በውስጡ ባለው ነገር ይጠራልና፡፡ ልክ ጌታ ጴጥሮስን “አንተ ሰይጣን ከኋላየ ሒድ” (ማቴ.16፡23) እንዳለው ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ታሪኮች በብዙ ጥንታውያን መጻሕፍት አሉ፡፡ ሥጋ ለበስ አጋንንት የሚሏቸው እነርሱን ነው፡፡ የተለያዩ የምትሐት ነገሮችን ይሠራሉ፡፡ በባሕር ይኖራሉ፣ በእሳት ውስጥም ገብተው በደኅና ይወጣሉ፡፡ ዋሊስ ባጅ ባሰተመው የደብረ ሊባኖስ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ላይ ጸሐፊው ከሌሎቹ የአካባቢው ቅጅዎች ለየት ብሎ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያጠመቁት ክፉ መንፈስ
ያለበትን ሰው እንጂ መንፈስ የሆነውን ሰይጣን አለመሆኑን በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች ያብራራል፡፡ (E.A.W. Budge, The Life and Miracles of Takla Hay-manot, (London,1906), P. 80).

የተሐድሶ መናፍቃን ገድለ ተክለ ሃይማኖት‘የተክለ ሃይማኖት ተቅማጥ ከክርስቶስ ደም ጋር እኩል ነው’ ይላል ይላሉ፡፡ በውኑ ይላልን?

መልስ፡- ሙሉ ገጸ ንባቡ “ክቡር አባታችንም ጌታዬ ወደ ሰማዕትነት ዐደባባይ ሄጄ በስምህ እንድሞት እዘዘኝ አለው፤ ጌታም መጋደልስ ፈጸምክ ከሞት በቀር ምንም አልቀረህም፡፡” አለው ነው የሚለው፡፡ [ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፯፤ ገጽ. 195] ከዚህም በኋላ፡- “ወናሁ ትመውት በሕማመ ብድብድ በእኩይ ሞት ወእሬሲ ለከ ኪያሃ ከመ ስቅለትየ በከመ ደመ ሰማዕት እለ እምቅድሜከ አኮ ለባሕቲትከ አላ ደቂቅከኒ እለ ይመውቱ በሕማመ ብድብድ በውስተ ዛቲ ገዳም እኌልቆሙ ምስለ ሰማዕታት ወአወፍዮሙ ለከ በመንግሥተ ሰማያት፡፡”[ዝኒ ከማሁ] ነው ያለው፡፡ + የቃሉ የግእዝ ትርጒም ሕማመ ብድብድ ማለት ቸነፈር ማለት ነው፡፡ ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት የሞቱት በቸነፈር በሽታ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዕለተ ዐርብ እንደ ተቀበልኩት መከራ መስቀል አደርግልሃለሁ ያለው፤ ገድላቸውንና በደዌ የተቀበሉትን መከራ ነው፡፡
በመልክዐ ጊዮርጊስ ላይም እንዲህ የሚል አብነት ይገኛል፡፡ ሰላም ለሰኳንዊከ ምስለ ክልኤሆን መከየድ፡፡ ለአጻብዒከ ሰላም ወለአጽፋረ እግርከ አምሳለ መረግድ፡፡ ገባሬ መንክራት ጊዮርጊስ በአቊጽሎ ይቡስ ዐምድ፡፡ አድኅነኒ በጸሎትከ እምነ መከራ ክቡድ፡፡ እስመ እምኔሁ ይወጽእ ቀታሊ ብድብድ፡፡ (መልክዐ ጊዮርጊስ) ትርጓሜውም፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ በሁለቱ ተረከዞችህ ጋር ለጫሞችህ ሰላም እላለሁ፡፡ እንደ ከበረ ዕንቊ ለሚያበሩት ለእግር ጽፍሮችህና ጣቶችህም ሰላም እላለሁ፡፡ ተአምር አድራጊው ሰማዕት ሆይ! ደረቁን ምሰሶ ለምለም ተአምራትህን ገልጸሃልና፡፡ ከጽኑ መከራ በጸሎትህ አድነኝ፡፡ ሰውስ ለሥቃይ የሚዳርጉ ረኀብ ቸነፈር ከእሱ ይፈልቃሉና፡፡ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም "ብድብድ" የሚለው ረኀብ፤ ቸነፈር
ተብሎ ይተረጎማል፡፡

+ የተሐድሶ መናፍቃኑ እንደ ሚሉት ‘ተቅማጥህ እንደ ስቅላቴ ደም ነው’ የሚል ሐረግም ከገድሉ ላይ አይገኝም፡፡ “… እሷንም እንደ ስቅላቴና ካንተ በፊት እንደ ነበሩ ሰማዕታት ደም እቆጥርልሃለሁ፤” [ዝኒ ከማሁ(Ibid)] ነው ያለው፡፡ ይህም ማለት የተክለ ሃይማኖት ሕማም ከሰማዕታት ደም ጋር እኩል እንደሆነ እንጂ ከክርስቶስ ደም ጋር እኩል እንደሆነ አያስረዳም፡፡
ይህም የሆነበት ምክንያት ከገድሉ ላይ እንደምንረዳው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባ ተክለ ሃይማኖት ብዙ ተጋድለሃል ከእንግዲህ ይበቃሃል ነፍስህ ከመከራ ተለይታ ወደ እረፍት መሄጃህ ጊዜ ደርሷል ባላቸው ጊዜ አባ ተክለ
ሃይማኖት በሰማዕትነት እንድሞት አድርገኝ ብለው ስለለመኑት ነው፡፡ + በሚሞቱበት ጊዜ የሚደርስባቸውን
ሕማም እንደ ራሱ መከራና በጦር ተወግተው በስለት ተቆርጠው ደማቸው እንደ ፈሰሰው ሰማዕታት ደም ሲቆጠርላቸው ነው፡፡ ሰማዕታት ለክርስቶስ ሲሉ በጦር ተወግተው በስለት ተቆርጠው ደማቸው እንደሚፈስ አባ ተክለ ሃይማኖትም ለክርስቶስ ሲሉ
ሃገር ለሃገር ጫካ ለጫካ ሲንከራተቱ ሕማመ ብድብድን (ቸነፈርን) በጦር ተወግተው ደማቸው እንደፈሰሰው ሰማዕታት ቆጠረላቸው፡፡ ስለዚህ የአባ ተክለ ሃይማኖት ሕማመ ብድብድ (ቸነፈር) እንደ ሰማዕታት ደም
ሆኖ ቢቆጠር ሃይማኖት ላለውና ለሚያስተውል ሰው አያደንቅም፡፡

፫. “ከሩቅም ከቅርብም ቢመጣ ወደ መቃብርህ የሄደውን እኔ ወደ መቃብሬ ኢየሩሳሌም እንደ ሄደ አደርገዋለሁ፤ በመታሰቢያህ ቀን ሥጋውን ደሙን የተቀበለውንም ስማቸው ከተጠራው ገድላቸው ከተነገረው ልጆችህ ጋራ እኔ እቈጥረዋለሁ፡፡” [ገድለ ተክለ
ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፯፤ ገጽ. 193] ማለት ምን
ማለት ነው?

+ መልስ፡- ወደ መቃብርህ የመጣውን ወደ መቃብሬ እንደመጣ አደርገዋለሁ ማለት በአንተ አማላጅነት በእኔ በርነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ማለት
ነው፡፡ ይህም እናንተን የተቀበለ
እኔን ተቀበለ ያለው የወንጌል ቃል በተግባር ሲተረጎም ነው፡፡ + በተክለ ሃይማኖት በመቃብር ላይ በተክለ
ሃይማኖት ስም በተሠራው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደ ሚገኝበት በመምጣት በመጸለይ ወደ
መንግሥተ ሰማያት መግባት ነው፡፡ የእግዚአብሔር በረከት ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ ዋጋ እንደሚገኝም መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ 2ኛ.ነገ.5፡1፤
ዕብ. 11፡23፤ ሩት. 1፡16-18፡፡
+ “በመታሰቢያህ ቀን ሥጋውን ደሙን
የተቀበለውንም ስማቸው ከተጠራው ገድላቸው ከተጻፈው ልጆችህ ጋር እኔ አኖራቸዋለሁ፡፡” የሚለውም ቃል የኢየሱስ ክርስቶስን መግቢያ
በርነት የበለጠ ያስተምራል እንጂ
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አያስቀርም፡፡ በአንተ መታሰቢያ
ዕለት የእኔን ሥጋና ደም ተቀብሎ በአንተ አስተማሪነት በእኔ በርነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ማለት ነው፡፡

፬ የመናፍቃን ጥያቄ ከገድለ ተክለሐይማኖት ውስጥ: "እባብን የገደለ ይጽድቃል" ይላል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሁሉ እባብን እየፈለጉ ለመጽደቅ እባብን መግደል አለባቸው ወይ የሚል ነው። አይ ይህቺ የመናፍቃን ጭንቅላት ትንሽ ብትሰፋ! ወገኖቼ መጸሐፍ ቅዱስ እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል መግባት ነው ይላል:: አንዱ ብርሃን መሆን አለበት:: ዛሬ ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ታውረዋል፡፡ አባታችን ተክለ ሐይማኖት ይፈውሱዋቸው
አሜን :: ወገኖቼ እባብን የገደለ
ይጸድቃል ማለት እባብ የተባለ ዲያቢሎስ ነው:: ለምሳሌ ያህል በመዝሙር ምህራፍ 73 ቁጥር 14
እንዲህ ይላል “አንተም የዘንዶውን እራስ
ቀጠቀጥክ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው፤” ይላል :: ታዲያ አንተ የዘንዶውን እራስ ቀጠቀጥክ
ሲል ታዲያ እግዚአብሔር ዘንዶ
ያለበትን እየሔደ እራስ እራሱን ቀጠቀጠው ማለት ነውን? አይደለም :: ዘንዶ የተባለው ሰይጣን ነው:: ሰይጣንን ደግሞ እግዚአብሔር በመስቀሉ
ቀጥቅጦታል ::
እንዲሁም ገድለ ተክለ ሐይማኖት
ላይም እባብን የገደለ ይጽድቃል ሲል ሰይጣንን የገደለ ይጸድቃል
ማለቱ ነው :: ሰይጣንን የምንገለው ደግሞ በጾም በጸሎት እና በስግደት
ነው:: በነዚህ እባብ (ዲያቢሎስን ) መግደል እንችላለን:: በተጨማሪም ደግሞ ራእይ ዮሐንስ ምህራፍ 12 ቁጥር 7 እንዲህ ይላል፡- “በሰማይም
ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና ሰራዊቱ ዘንዶውን ተዋጉት :: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም::
ዓለሙን ሁሉ የሚያስት ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፡፡ ወደ ምድርም ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ፤” ይላል:: ታዲያ ሚካኤልና ቅዱሳን መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ ሲል ከእንስሳ ጋር ተዋጉ ማለት ነውን? አይደለም፡፡ ዘንዶ የተባለው የቀደመው ሰይጣን እርሱ ዲያቢሎስ ነው ይለናል:፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
† በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል ላይ የሚነሱ
አንዳንድ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
👆👆👆👆
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
[የሕሙማን እናት የተባለችው ሐምሌ 25 ያረፈችው በብዙ ሊቃውንት የተወደሰችው የቅድስት ቴክላ ድንቅ ታሪክ]

በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
@Meserete_Yared_Asasa

❖ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረችው ብዙዎች አበው በድርሳናቸው የመሰከሩላትን በድንግልናዋ ጸንታ የኖረችውን ቅድስት ቴክላ ናት፤ ይኽቺ ቅድስት ሴት፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ከተከተሉት ቅዱሳን ሴቶች አንዷ ስትኾን እጅግ ውብ፣ ሀብታምና የተማረች ነበረች ፤ በዚኽም ከልዑላኑ ታሚሪስ የሚባል ወጣት ሰው አጭቷት ነበር፤ ቅዱስ ጳውሎስ በ45 ዓ.ም. ከአንጾኪያ ከተማ ወደ ኒቆምድያ ከተማ ኼዶ ወንጌልን ሲሰብክ በተመስጦ ኾና ትምህርቱን ትከታተል እንደነበር ከሊቃውንት ቅዱስ አምብሮስና ቅዱስ አውግስጢኖስ ጽፈዋል።

❖ በሐዋርያውም ትምህርት ልቧ በመነካቱ የድንግልና ሕይወትን በመምረጥ ለእናቷ የታሚሪስ እጮኝነቷን ማፍረሷንና ክርስቲያን እንደምትኾን ነገረች፤ ወላጆቿ ግን ርሱን እንዳትሰማ ቢያግባቧትም ርሷ ግን እነርሱን አልሰማቻቸውም፤ በዚኽ ምክንያት አባቷ ዲማኖስና ርምጋኖስ ከሚባሉ ዳኞች ኺዶ ከሰሳት፤ እነርሱም ሊያስገድዷ ቢሞክሩም አልቻሉም፤ ከዚያም የቀደመ ልብሷንና ጌጦቿን ኹሉ ትታ ከቅዱስ ጳውሎስ ጉባኤ ተቀመጠች፡፡

❖ በዚኽ ተበሳጭተው በመኰንኑ ዘንድ እንደገና ከሰዋት፤ ርሱም ሌሎቹ ፈርተው ወደ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳይኼዱ በእሳት እንዲያቃጥሏት አዘዘ፤ ርሷ ግን በሚያቃጥሏት ጊዜ ልቧን አጽንታ ቅዱስ ጳውሎስን ተመለከተችው፤ ያን ጊዜ ሐዋርያው በመስቀል ምልክት ባማተበ ጊዜ ወደ እሳቱ ምድጃ ተወረወረች፡፡

❖ “ፈነወ እግዚአብሔር ዝናመ ብዙኀ ወበረደ ወመብረቀ ወኮነ ዕቶነ እሳት ከመ ጠል ቈሪር ወሮጸት ቴክላ ወበጽሐት ኀበ ቅዱስ ጳውሎስ ኀበ ኀሎ መካነ ኅቡአ” ይላል፤ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ብዙ ዝናብን፣ በረድን፣ መብረቅን ላከ፤ የእሳቱም ምድጃ እንደ ቀዝቃዛ ጠል ኾነ፤ ቴክላም ሩጣ ቅዱስ ጳውሎስ ተሰዉሮ ወደ አለበት ቦታ በመድረስ፤ ወንጌልን ለመማር በኼደበት ኹሉ ትከተለው ዘንድ ለመነችው፡፡

❖ ከዚያም ከርሱ ጋር አንጾኪያ ከተማ በመኼድ ለዐዲስ አማኞች የእግዚአብሔርን ቃል ትነግራቸው ነበር፤ ከመልኳ ውበትም የተነሣ ከመኳንንቶቹ አንዱ ሊአገባት ፈለገ፤ ርሷ ግን ዘለፈችው፤ ከዚያም ለአንበሶች እንድትጣል ቢደረግም ልክ እንደ ነቢዩ ዳንኤል አንበሶቹ ሳይነኳት በነርሱ መኻከል ኹለት ቀናት ቆየች፤ ከዚኽም በኋላ በኹለት በሬዎች መኻከል አስረው በከተማው ውስጥ አስጐተቷት፤ ነገር ግን ምንም ክፉ ነገር አልደረሰባትም፤ ከዚያም በኋላ ለቀቁዋት፡፡

❖ ርሷም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ኼደች ርሱም አጽንቶና አረጋግቶ የሰማችውን እንድትመሰክር አዘዛት፡፡ ርሷም ወደ ወላጆቿ ሀገር በመኼድ ስለ ክርስቶስ መሰከረች፤ አባትና እናቷም አምነው ክርስቲያን ኾኑ፤ ሀብተ ፈውስም ተሰጥቷት ብዙዎችን ትፈውሳቸው ነበር በዚኽም “የሕሙማን እናት” በመባል ትታወቃለች፤ በመጨረሻም ተጋድሎዋን ፈጽማ ሐምሌ ፳፭ ዐረፈች፤ መስከረም ፳፯ም ትታሰባለች፤ ሥጋዋም በግብጽ ደቡብ ሰንጋር በሚባል ቦታ ተቀመጠ፤ በዚያም ከሥጋዋ የተነሣ ብዙ ድንቅ ተአምር ተገልጧል፡፡

❖ በርካቶች ቅዱሳን አበው በየድርሳናቸው የቅድስት ቴክላን ቅድስናና ተጋድሎ ጽፈውላታል፤ በተለይ ቅዱስ ሜቶዲየስ ቅድስት ቴክላ ከቅዱስ ጳውሎስ በተማረችው ትምህርት ምን ያኽል ጠንካራ እንደነበረች፤ በጊዜው ከነበሩት የደናግል ኅብረት ከፍ ከፍ ያለች፤ ድንግልናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ በዝማሬም ትመራቸው እንደነበር ይገልጣል ፡፡

❖ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም ስለ ርሷ ክብር ሲጽፍላት፡- የተባረከች ድንግል ቴክላ ንጽሕናዋን ሰማዕትነቷን ለልዑል እግዚአብሔር በማቅረብ በአንድ እጇ በሥጋው በደማዊ ፈቃድ ላይ የድል ዘውድን ስትይዝ፤ በሌላኛው እጇ በአደገኛ ሥቃይና መከራ ላይ የክብር አክሊሏን እንደያዘች ዐውቃለኊ” ብሏል፡፡

❖ ቅዱስ ጀሮምም በደብዳቤው ላይ “የጌታ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም የደናግልን ማኅበር አስከትላ እናንተን ለመገናኘት የምትመጣባት የዚያቺ ቀን ክብር እንደምን ያለ ነው!... ያን ጊዜ ቴክላ እናንተን ለማቀፍ በደስታ ትበርራለች” ብሏል፡፡

❖ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያም የድንግልና ሕይወቷን አብነት እንዲያደርጉ ሲያስተምር “የንጽሕና አምሳል ከምትኾን ወደር ከሌላት ከአምላክ እናት በመቀጠል ከሴቶች አስቀድማ ሰማዕት የኾነች ቴክላን ምሳሌ አድርጌ አነሣለኊ፤ እናንተም የርሷን መንፈሳዊ ውበት ተላብሳችኊ ሰማያዊ ጸጋን ለማግኘት ነፍሳኹን በተለያዩ መንፈሳዊ መልካሞች ሥራዎች ታስጌጧት ዘንድ ይገባል” በማለት አስተምሯል፡፡

❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም ተጋድሎዋን በማዘከር፡-
“ሰላም እብል ለሐዋርያዊት ቴክላ
እግዚአብሔር ዘአኀየላ
ኢያቊስልዋ አናብስት ወእሳተ ዕቶን ኢያሕልላ
እስመ አምነት ትምህርተ ጽድቅ ከመ ጳውሎስ ይቤላ
እስከ ኀደገት አበዊሃ ወገደፈት ብዕላ”
(አንበሶች እንዳያቈስሏት የእሳት ምድጃም እንዳያቃጥላት እግዚአብሔር ያበረታት ሐዋርያዊት ለኾነች ለቴክላ ሰላምታ ይገባል፤ አባቶቿን እስክትተውና ሀብቷን እስክትጥል ድረስ ደርሳ ጳውሎስ እንዳላት የእውነት ትምህርትን አምናለችና) እያለ የተቀደሰ ሕይወቷን በአድናቆት ጽፎላታል፡፡

❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለጤቅላ (ቴክላ)
ዘሞአቶ ለተኲላ በገድል
ንጽሕት ድንግል”፡፡
(ንጽሕት ድንግል በገድል ተኲላውን ያሸነፈችው ለኾነች ለጤቅላ ሰላምታ ይገባል)እያለ ያወድሳታል።

የጽሑፉ ምንጭ [አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የጻፈው ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው፤ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የተተረጎመ]

[የቅድስት ቴክላ በረከት ይደርብን]
[ከቅድስት ቴክላ ሕይወት ምን ተማርን? በተለይ እኅቶች]

@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
#መልአካይ_ሰይጣን ~ ሰባሪ ዜና

@And_Haymanot

👉 "ኦርቶዶክስ" የሚለው ስም የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ነው!!!!!

√Share √Share √Share

«ውሉደ ብርሃን የክርስቶስ ቤ/ክ» ብሎ ራሱን ሲጠራ የነበረው የውጉዙ አሰግድ ሣህሉ (?) የተሐድሶ መናፍቃን ቡድን ያሰበውን ያህል በጎችን ከበረት ማውጣት ስላልቻለ ስሙን «ቃለ ዐዋዲ ዘኦርቶዶክስ የክርስቶስ ቤ/ክ» ብሎ ቀይሮ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ነኝ በማለት ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ይህ በእምነታችን ኃጢአት፣ በባህላችን ነውር፣ በሕጋችንም ወንጀል የሆነ ቅጥፈት ነው። መንግስትም የሌላን ቤተ እምነት ስም በመጠቀምህ ፍቃድ አልሰጥም ማለት እየቻለ "ተቃዋሚ ካለ ሰኞ ሐምሌ 29 3:00 ሰዓት በሰላም ምኒስቴር የሃይማኖት ድርጅቶችና ማሕበራት ምዝገባ ዳይሪክቶሬት ይቅረብ" ብሎ የማርያም መንገድ የሰጠ ይመስላል።
ሰይጣን ሰዎችን ሲያታልል መልአክን እንጂ ራሱን መስሎ አይደለም። የራሱን ኃይልና ብርታት በመግለጥ፣ ከመልአክነት ይልቅ ሰይጣናዊነት እንደሚልቅ በማስረጃ በማስረገጥ አይቀርብም። ስለ ራሱ የሚያቀርበው ነገር የሌለው ባዶ ነውና፣ ሌላን መምሰል እንጂ ራስን መሆን አይሆንለትምና መልአክ-መሳይ (መልአካይ) ሆኖ ይቅበዘበዛል። ተሐድሶዎችም እንዲሁ በመብከን ተሐድሶነታቸውን ሳይሆን ኦርቶዶክስ-መሳይነታቸውን ሊነግሩን ሽሩገድ ይላሉ። 2 ቀናት ብቻ ቀርተውናል! ይህ የብሔርህ አልያም የፖለቲካ ወሬ አይደለም፣ የእውነትም የእምነትም ጉዳይ ነው! ይህንን መልዕክት በውስጥ መስመር ለመምህራን፣ ለሕግ ባለሞያዎች፣ ለባለሥልጣናትና ለብጹዓን አባቶች በማካፈልና በመላክ በቤ/ክ ጉዳይ ለውጥ እንፍጠር! ዳይ ወደ ስራ [©Binyam ZeChristos ሐምለ 26 - 2011]

፪ኛ ቆሮ ፲፩

26 “ብዙ ጊዜ በመንገድ ኼድኹ፤ በወንዝ ፍርኃት፥ በወንበዴዎች ፍርኃት፥ በወገኔ በኩል ፍርኃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርኃት፥ በከተማ ፍርኃት፥ በምድረ በዳ ፍርኃት፥ በባሕር ፍርኃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርኃት ነበረብኝ፤
27 በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርኹ።
28 የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ኹሉ ዐሳብ ነው።”


@And_Haymanot
@And_Haymanot
“ግርግር ለሌባ ያመቻል” እንዲሉ አበው አሁንም መዘናጋታችንን እና በሌሎች ሥጋዊ ተግባራት መጠመዳችንን
ያዩ ተግባራቸውን አንድ እርምጃ ከፍ በማድረግ ከንዋያተ ቅድሳት ዘረፋ ወደ ስያሜ እና መጠርያ ዘረፋ ተሸጋግረዋል፡፡ እኛም ተኝተናል!
መናፍቃን ስማቸውን ከ"ውሉደ ብርሃን የክርስቶስ ቤተክርስትያን" ወደ "ቃለ ዘአዋዲ ዘ ኦርቶዶክስ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን" ሊያስለውጡ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል፡፡ እውነተኛ የኦርቶዶክስ ልጆች ከሆንን እና ስለቅድስት ቤተክርስቲያናችን የሚገድደን ከሆነ ይህንን መቃወም ግድ ይለናል! በቤተክርስቲያን ነዋያት
እና ስያሜ መጠቀም ይብቃ!

²⁶ “ብዙ ጊዜ በመንገድ ኼድኹ፤ በወንዝ ፍርኃት፥ በወንበዴዎች
ፍርኃት፥ በወገኔ በኩል ፍርኃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርኃት፥ በከተማ
ፍርኃት፥ በምድረ በዳ ፍርኃት፥ በባሕር ፍርኃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርኃት ነበረብኝ፤
²⁷ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና
በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርኹ።
28 የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ
የአብያተ ክርስቲያናት ኹሉ ዐሳብ ነው።” ፪ኛ ቆሮ ፲፩
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሰበር ዜና
እንኳን ደስ አላችሁ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስም "ውሉደ ብርሃን የክርስቶስ ቤተክርስቲያን" እያለ ራሱን የሚጠራው ጸረ ወንጌል ድርጅት ሕዝብን ለማወናበድ እንዲመችው በማቀድ የስም ለውጥ እንዲሰጠው ማለትም ቃለ አዋዲ ዘኦርቶዶክስ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተብሎ እንዲጠራ ለኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዴሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የሰላም ሚኒስተር ቢያመለክትም ተቃዋሚ ካለ እንዲቀርብ በሚንስትሩ ጽ/ቤት የሃይማኖት ድርጅቶችና ማህበራት ምዝገባ ዳሬክትሬት ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓም ከጠዋቱ 3:00 እንዲቀርብ ትእዛዝ መሥጠቱ በጋዜጦች እና በማህበራዊ ሚድያ ሰዘገብ ቆይቷል በዚህም ይህንን የተዋህዶ ልጆችን ድምፅ ችል ባለማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሕግ መምሪያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አባ ገብረ ስላሴ እና የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ መላአከ ሰላም ቀሲስ ሰሎሞን ቶልቻ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ሐምሌ 29 ቀን በቀጠሮው ሰአት ተቃውሞአቸውን ይዘው እንደሚቀርቡ ከታመኑ ምንጭ ታሰምቷል ድል በክርስቶስ ደም ለተዋጀች ለኦርቶዶክስዊት ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን በጸሎት አስቧቸው፡፡

መረጃው ከማህበራዊ ድህረ ገፅ ተገኘ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
​​ጾመ ፍልሰታ


ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገው ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት ኦርቶዶክሳዊያን የሚጾሙት ጾም ነው።

ፍልሰታ የግዕዝ ቃል ሆኖ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል።
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለሆነ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን 48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች።
ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት ወደ መኖሪያ ቤቷ (የዮሐንስ ቤት) መጥተው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች አስከሬኗን ገንዘውና ከፍነው ወስደው
ለመቅበር ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንም ማድረግ
የፈለጉት የሐዋርያት ትምህርት የጌታችን ከሞት መነሣትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ
እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። የፈሩት ይነግሣል የጠሉት ይወርሳል እንዲሉ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት
አይቀሬ ሆኗል።

አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፊኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ
ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነትና ክብር ለመመስከር በቅቷል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር ይቀመጥ እንጂ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር
ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ዮሐንስ ስለሥጋዋ ነግሯቸዋል።
ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ለስድስት ወራት ከአሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህ በኋላም ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው
ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን
አምጥቶ ስለሰጣቸው ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።

ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት
አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ ፪፥፲/።
እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ /ሕንድ/ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ
ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በስተቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት
እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን /የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።
ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ
ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት
አስረዱት። እርሱ ግን ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን
ለማሳመን መቃብሯን ለማሳየት ወሰዱት ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት
የነበረውን ጨርቅ/ የራሱን ድርሻ አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው ዛሬም ካህናቱ ከእጅ መስቀላቸው ጋር መሐረብ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ
ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት
በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለሁለተኛ ጊዜ ለሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ
ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

በአጠቃላይ የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ሐዋርያት ያገኙትን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በዶ/ር ሙሉጌታ ማርቆስ
@And\
Haymanot
@And_Haymanot_bot
​​ የያረድ ዉብ ዜማ

የያረድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታየ ነሺ / 2/ 
በምን አንደበቴ እንደምን ባለ ቃል ማርያም ልበልሺ/ 2 

ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ 
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ 
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሺ 
ድንግል ሆይ እናተ አምሳያም የለሺ 
ማርያም ድንግል እረዳተ 
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀተ 
ታምርሺን በአይነ አይቻለሁ 
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ 
አዝ - - - 
የእግዚአብሀር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ 
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ 
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሺ 
ነገን ባላውቅ እነም ቢያስፈራኚ 
አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም 
በፊትሺም እንድቆም ለምስጋና 
ማርያም ልበልሽ በትህትና 
አዝ - - - 
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም 
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም 
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር 
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሺን ይናገር 
ጨለማው ከፊተ ተገፈፈ 
ማርያም በምልጃሽ ልበ አረፈ 
ከጎነ ነይ ስልሺ እጽናናለሁ 
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት????
@And_Haymanot
አንድ እህታችን በውሥጥ የላከችልን መልዕክት ነው፡፡
ስለ እመቤታችን ሲነሳ አይናቸው ደም የሚለብሰው የተሃድሶ መናፍቃን ዛሬም ከእናታችን እቅፍ ሊለዩን ተነስተዋል ከጥፋት ትምህርታቸ አንዱ
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት። በዛ ዘመን ብንኖር ከእኛ መሃል ከአንዳችን ኢየሱስ ይወለድ ነበር ብለው ያስተምራሉ ያምናሉ።

-ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን ከመውለድዋ በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች ሴት ናት ።
እንኳን የአምላክ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለም ማንኛችንም እግዚአብሔር የፈጠረን ፍጡር ወደዚህ አለም ከመምጣታችን በፊት ለምን አላማ እንደምንወለድ
እንኳን ገና ሳንፈጠር እግዚአብሔር ያውቃል:: ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ኤርምያስ 1:5 እንዲህ ይላል ።
የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ
ለአህዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።

-ቅድስት ድንግል ማርያም ለአምላክ እናት እንድትሆን ገና ሳትፈጠር እግዚአብሔር የመረጣት ሴት ናት።
ከእሷም ባይሆን ከሌላ ይወለድ ነበር ለሚሉ የጥፋት ልጆች ከእግዚአብሔር አላማና ሃሳብ ጋር የተጣሉ የእግዚአብሔርን ሃሳብ በራሳቸው አመለካከት እና ሃሳብ ለመቀየር የሚያስቡ ደፋሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም
እንዲወለድ ነበር የእግዚአብሔር አላማ::
ከእሷ ባይሆን ለሚሉት የእግዚአብሔር ሀሳብ ሳይሆን የቀረበት ግዜ የለምና ከእሷ ውጭ ከማንም ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ሃሳብ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲወለድ እንጂ ሌሎች እንደሚፈላሰፉት ከአዳራሽ ጨፋሪዎቻቸው ሴቶች መሃከል ኢየሱስ ሊወለድ አይችልም::
ከፍጥረት ሁሉ ፣የአምላክ እናት እንድትሆን የተመረጠች ቅድስት ማርያም ብቻ ናት። ለመዳናችን ምክንያት ለሆነች ከሴቶች ሁሉ ለተለየች የአምላክ እናት ክብር ይገባታል ።

በተጨማሪም ሊታወቅ የሚገባው ማንኛውም ሠው በነብያትና በሐዋርያት መንገድ መጓዝ ከቻለ ሐዋርያት የደረሱበትን የክብር ደረጃ መድረስ ይችላል፡፡ ነገር ግን በክብር ላይ ክብር ብናገኝ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኝ ስራ ብንሠራ እንኳ ድንግል ማርያም የደረሰችበት የክብር ደረጃ ላይ መድረስ
የሚችል ሰው ማንም የለም፡፡ ወደፊትም እንደዚህ አይነት ክብር እና ጸጋ ለማንም አይሰጥም፡፡፡፡
.....ይቆየን ከሰሞኑ እመቤታችን አንዲት ድንግል እናት ሥለመሆኗ በሰፊው እንመለሳለን፡፡
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን
፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው
ለእኛም ግለጽልን።
አሜን አሜን አሜን!!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሐይማኖት አይወረስም?

@And_Haymanot

ተወዳጆች የተሃድሶ መናፍቃን ሃይማኖት አያስፈልግም፤አያድንም፤አይወረስም በማለት ብዙዎችን ለማደናገር ይሞክራሉ ከዚህ በፊት በስፋት የዳሰስነው ርዕሳችን ቢሆንም በውስጥ ለጠየቀን ወንድማችን እነሆ ብለናል

ሐይማኖት አይወረስም ላልከን እንዲህ የምናምነውንም እንመሠክራለን! > እንግዲያውስ ከኃይማኖት በላይ ሊያወርሱት እና ሊወርሱት የተገባ የከበረ ነገር በዚች አለም የለም። ሰው መልካም መልካሙን ነገር ለልጆቹ ያወርሳል ከመልካም ስጦታዎች ሁሉ የሚልቀውን የዘላለም ሕይወት የሚገኝበትን ሐይማኖት ከማውረስ የበለጠ ታላቅ ውርስ እንዳውም በጭራሽ አይገኝም።

ሰው በምድር ላይ ለልጆቹ የሚሆን ታላቅ መኖሪያ ቢያወርስ ነገር ግን የዘላለም ሕይወት የሚያገኙበትን ሐይማኖቱን ግን ባያወርስ ምን ይረባቸዋል! ??
ሁለት ነገርን አደፈረስክ! መጀመሪያ ሐይማኖት ሊወረስ የተፈቀደ መሆኑን ካድክ ሲቀጥል ደግሞ በገዛ ድምዳሜክ ገባህና ሐዋርያት ከሀድያን ናቸው አልክ! እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።
አስቀድመህ በራስህ አላዋቂነት የደመደምከው ድምዳሜ ላይ የተመረጡትን ሁሉ አጋጭተሀል።
በመሰረቱ ሀይማኖት ለሰው ልጆች የተሰጠችው ልንጠብቃት እና ለትውልድም ልናወርሳት ነው።
አብርሃም አባታችን ለአይሁድም ሆነ ለሀዲስ ኪዳን ህዝቦች አባት ነው። ከህግ ለሆኑት የመገረዝ አባት ነበረ። ከእምነት ለሆንነው ደግሞ የእምነት አባት ነው። የፃድቅ አብርሃም
ሕይወት ለእኛ ምሳሌ ነው። አብርሃም እግዚአብሔር ን አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት ነገር ግን ይህ ብቻ አልነበረም ጉዳዩ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም ትዛዝን ሲሰጠው ልጆችህ ቃል ኪዳኔን እንዲጠብቁ አድርግ በሚል ጠንካራ
ማሰሪያም ጭምር ነው። አብርሃምም በቤቱ ለተወለዱት ልጆች ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ገና በተወለዱ በ8 ቀናቸው ጀምሮ ይፈፅምላቸው ነበር። የእርሱን ሐይማኖት ለልጆቹ ገና በስምንት ቀን ጨቅላነታቸው እያሉ ጀምሮ እንዲቀበሉ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ ነው። ልጆችም በአባቶቻቸው
ሐይማኖት ተወስነው እንዲኖሩ ነው የጌታ ትእዛዝ። ስለዚህ ሐይማኖት ይወረሳል። ከሐይማኖት የበለጠ ለልጅ ሊያወርሱት የሚገባ መተኪያ የሌለው ውድ ነገርስ ከየት ይገኛል???
ዘፍጥረት 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥
#ለአንተና_ከአንተ_በኋላ_ለዘርህ_አምላክ_እሆን_ዘንድ
⁸ በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ለዘላለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ አምላክም እሆናቸዋለሁ።
⁹ እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፥ አንተ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው።
¹⁰ በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
¹¹ የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ
መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
¹² #የስምንት_ቀን_ልጅ_ይገረዝ ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።
¹³ በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
¹⁴ የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ፥ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።//

ሮሜ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ
አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው።
¹³ የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው
የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም።
¹⁴ ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል
የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤
¹⁵ ሕጉ መቅሠፍትን ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።
¹⁶-¹⁷ ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ
ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት #የሁላችን #አባት #ነው
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
እኔስ እዘምራለሁ


እኔስ እዘምራለሁ ለሥላሴ /2/ 
ፈጥሮኛለና እና በሥጋ በነፍሴ 
እኔስ እዘምራለሁ ለሥላሴ 

ሥሉስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገን 
ሰውን ከመከራ ከሞት የምታድን 
ነፍሴ ትገዛልህ ትንበርከክልህ 
ቅዱስ ፈጣሪዬን አንተን ታምልክህ 
አዝ...
በመሐሪነትህ ጠብቀህ ያኖርከኝ 
በማዳን ችሎታህ ለዚህ ያደረስከኝ 
ለአንተ ለአምላኬ ምስጋና አቀርባለሁ 
ስምህን ለዘለዓለም ሁሌም እጠራለሁ 
አዝ...
አብርሃም ለአምላኩ በቀና ቢታዘዝ 
ሥላሴ ገቡና ቤቱን ባረኩለት 
ሣራንም ጎበኛት በእርጅናዋ ጊዜ 
ይስሐቅን ሰጧት ዘለዓለም ሥላሴ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
አዎ መልስ አለን!

ተወዳጆች የተሃድሶ መናፍቃን በፍልሰታ ፆም ዙርያ ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን ይዘንላችሁ ቀርበናል የምትፈልጉትን ርዕስ 👉 Read more በማለት ማንበብ ትችላላችሁ።
ምላሽ የሚፈልጉ የተዋህዶ ልጆች በርካቶች ናቸውና ለሌሎች ሼር ማድረግ አንዘንጋ።

ኦርቶዶክስ መልስ አላት።
@And_Haymanot

በእንተ ቅድስት ድንግል ማርያም
👉 ስለ ቅድስናዋ - የቅዱስ አምላክ እናት በመሆኗ
👉 ስለ ድንግልናዋ
👉 ምስጋና እንደሚገባት
👉 ክብር እንደሚገባት 👉 Read more

👉 የተሐድሶ መናፍቃን የፍልሰታ ጾምን በእጅጉ ይተቹታል:: ሐዋርያዊ ውርርስ የሌለው እንግዳ ትምህርት እንደሆነም ይናገራሉ:: ሲያልፍም እመቤታችን አርጋለች ማለት ስሕተትም ነው ይሉናል፤ ይህንንም ያስተማረው በ 16ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ነው ይላሉ::
👉 ለመሆኑ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት (Assumption of Mary) ትምህርት በኢትዮጵያ ሊቃውንት ብቻ የታወቀ ነው?
👉 ትዛታው ሳሙኤልን ዕርገተ ማርያምን ሲነቅፍ የተሰጠ ምላሽ 👉 Read more

ስለ እመቤታችን ዕርገት የሚያትት በPdf የተዘጋጀ 👉 Read more

የተሃድሶ ሲናፍቃን ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት በዛ ዘመን ብንኖር ከእኛ መሃል ከአንዳችን ኢየሱስ ይወለድ ነበር ብለው ያስተምራሉ ያምናሉ። 👉 Read more

ተአምሯን የሰማ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል 👉 Read more

       የድንግልን ትንሣኤ በኩረ ፕሮቴስታንት የኾነው ማርቲን ሉተር እንኳን በአንክሮ ያምናል ታድያ የዛሬዎቹ ስለምን ካዱ???? 👉 Read more

ድንግል ማርያምን ጨካኝ ለማድረግ የሚባዛው መልዕክት 👉 Read more

💗 "ቅድስት ድንግል ማርያምን መውደድ ከሚገባኝ መጠን በላይ አልፌ ወድጄያት ይሆን? ብለህ ሥጋት አይግባህ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከወደዳት በላይ ልትወዳት አትችልምና" 💗
ቅዱስ ማክሲሚሊያን ኮልብ
@And_Haymanot
💗 "ለሚያምን(ለማመን) ይኼ የሚጸን(የሚከብድ) ነገር አይደለም/ To believe this is no doubtful matter/." ዕርገተ ማርያም(Assumption of Mary)💗
መልካም ፆም
፩ ሃይማኖት የቴሌግራም ቻናል
Share Share Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
​​አንተም አንቺም እኔም
ያገባናል!!!

ቤተ ክርስቲያን ዋስትናዋ ይጠበቅ
ቤተ ክርስቲያን ለጠፉ ንብረቶች ካሳ ይከፈላት
በቤተ ክርስቲያን ውድመት ያደረሱ በህግ ይጠየቁ
የቤተ ክርስቲያን አባቶች መውገር ይቁም
የቤተ ክርስቲያን ልጆች ምእመናን ማሳደድ ይቁም
በተደጋጋሚ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ላለው ውድመት
ከንፈር ከመምጠት የዘለለ ነገር ተደርጎ አያውቅም እናት
ስትበደል እናት ስትከፋ እናት ስትቃጠል ዳር ሆኖ ማየት
የሚያስችል አንጀት እንዴት ሊኖረን ቻለ?? ከላይ እስከታች
በኃይለኛ እንቅልፍ ተወስደን ስንት ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ?
ስንት መንጋ ተሰደደ? ስንት ካህናት ተገደሉ? ስንት ምዕመናን
ታረዱ? ሚልዮኖች ሳይፈልጉ ወደ ሌላ በረት ገቡ?
የኢትዮጵያ መሰረት ኢትዮጵያን በዓለም ከፍ ያደረገች ቤተ ክርስቲያን ስደተኛ ትሁን?? አገልጋዮች ምእመናን በስጋት
የሚኖሩ እንዲሁኑ ለምን ተፈረደባቸው??
ህዝብን አንድ አድርጋ የኖረች ትውልዱ በዘር ሳይከፋፈል በኢትዮጵያዊነቱ እንዲኮራና እንዲተዛዘን አድርጋ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራ ፊደል ቀርጻ ብራና ድጣ ቀለም በጥብጣ
መሀይምነትን አጥፍታ ዓለም የሚኮራበትን ቅርስ አክሱም
ላሊበላ ፋሲል የመሳሰሉትን ድንቅ ቅርሶች አበርክታ ዳር ድንበሩን አስጠብቃ በኖረች ለምን ይሄ ሁሉ ውድመት ሲደርስ ተመልካች ለምን ጠፋ??
መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ዝም አንልም!!
እኛ የድርሻችንን ከተወጣን ስራውን የሚሰራው ፈጣሪ ነው የኛን ድርሻ ግን እኛ እንወጣ ዳር እንቁም በጸሎትም
በእውቀትም በምንችለው ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንቁም ለኛ ቤት ሌላ የሚቆረቆር የለምና በጋራ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን እንጠይቅ የጠብታ ውሃ ድንጋይ ትሰብራለችና እንተባበር !!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ይድረስ ለዘረኞች

🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏
ቤተ ክርስቲያን ኦሮሞ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን አማራ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ትግራይ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ጉምዝ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን አፋር አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ሱማሌ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ሲዳማ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ጉራጌ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ስልጤ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ወላይታ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ጋንቤላ አይለችም
ቤተ ክርስቲያን ሀድያ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ኮንሶ አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ሀመር አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ምድራዊት አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊት ናት
ቤተክርስቲያን ክርስቶሳዊት ናት
ቤተ ክርስቲያን አምላካዊት ናት
ቤተ ክርስቲያን ህያዊት ናት
ቤተ ክርስቲያን በዘር የተመሰረተች አይደለችም
ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ናት እንጅ ስለዚህ
ቤተ ክርስቲያን የብሔር አይደለችም የእግዚአብሔር ቤት እንጂ
🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏
አምኖ ለመጣው ሁሉ ኦሮሞ አማራ ደቡብ ትግሬ ሳትል ለሁሉ እኩል ታስተምራለች እኩል ሲሞት ትፈታለች እንግዲህ ሰው በዘር ሲተራመስ ቤተ ክርስቲያንን ኢላማ ማድረግ ተገቢ
አይደለም ቤተ ክርስቲያን መንግስተ እግዚአብሔር መንግሥተ ሰማያትን እንጅ መንግስተ ምድርን ዘርን አሰብክም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ዓይን ብሌናችን እንጠብቃት መንግሥተ
ሰማያትን የምናይባት ናትና።
@And_Haymanot
በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤
ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።
አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና። ገላትያ 3:26-28
(መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ)
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ጎንደር

ቤተ ክርስቲያን አምኖ ለመጣው ሁሉ ኦሮሞ አማራ ደቡብ ትግሬ ሳትል ለሁሉ እኩል ታስተምራለች እኩል ሲሞት ትፈታለች እንግዲህ ሰው በዘር ሲተራመስ ቤተ ክርስቲያንን ኢላማ ማድረግ ተገቢ
አይደለም ቤተ ክርስቲያን መንግስተ እግዚአብሔር መንግሥተ ሰማያትን እንጅ መንግስተ ምድርን ዘርን አሰብክም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን እየደረሰባት ካለው ፈተናና ወደፌት ከሚደርስባት ፈተና እንደ ዓይን ብሌናችን እንዴት እንደምንጠብቃት ለመወያየት
በዕለተ ሰንበት በ19/12/2011
ከቀኑ 4:00 ጀምሮ ልዩ ጉባኤ ተዘጋጅቷል ስለሆነም እርስዎና ሌሎች ጓደኞችዎን በመጋበዝ በሰ/ት/ቤታችን አዳራሽ እንገናኝ
የደ/ስ/ ቀኃ ኢየሱስ ሰ/ት/ቤት ጎንደር
ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
​​በየገዳማቱ
ዘማሪ ይልማ

በየገዳማቱ በየበረሃው ውስጥ
ስለተሰደዱት ፍቅርህን በመምረጥ
የዓለም ውደቂ ምናምንቴ ሆነው
ስለ ፍቅርህ ሲሉ ክብራቸውን ትተው
እግዚአብሔር ሆይ ማረን /2/
አዝ---------------//
የዓለም ውዳቂ ጉድፍ በተባሉት
በምድር እየኖሩ በጽድቅ ህይወት ባሉት
ዓለም አና አምሮቷን ትተው በመነኑት
ኢየሱስ ሆይ ማረን እግዚአብሔር ሆይ ማረን /2/
አዝ---------------//
ህያዋን በሆኑት እስከ ዘለዓለም
ከኢየሱስ ጋራ ሞተው በመስቀል ዓለም
ዓለም የናቃቸው እነርሱም የናቁት
አምላክ እራራልን አትጨክን በእውነት /2/
ዝማሬያችንን ይቀበልልን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ደብረ ታቦር

የደብረ ታቦር በዓል በደብረ ታቦር ከተማ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot