Yismake Worku
20.6K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
"...ዝቅ ዝቅ ያለው፣
ከፍ ከፍ ይላል፣
እንደ ባንዲራው፡፡"
ደረጄ ኃይሌ (ምርጡ ኮሜዲያን)፣ መሳይ ወንድሜነህ (ምርጡ ጋዜጠኛ)፣ ሜላት ኃይለ ማርያም (ምርጧ የጎልድ ጂ ሰው)፣ የእኔ ፎቶ እንኳን አይታየኝም፡፡ በሰዎቼ ተሸፍኜአለሁ፡፡ @yismakeworku
መጽሀፉን ጃፋር መፅሀፍት መደብር ማግኘት ትችላላችሁ።

አድራሻ :- ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያው አጠገብ ተወልደ ሕንጻ ስር ::
@yismakeworku
🔥1
ይህን የማያውቁ፣ጥቂቶች አሉና፣ ቢያልመዘምዟቸው
እንዲመረመሩ፣ የፈጣሪ መስኮት፣ይከፈትላቸው

...
ዘላለም ምህረቱ እንደፃፈው
#ከመቃብር_ቆፋሪዎች_ማዶ
(ከቅንነት የመነጨ ፈገግታ )
ብዙ ሰው ብዙ ነገር አለው። በተፈጥሮ ወይም በጥረት። ያላቸውን በቅንነት እንበለ-ግብዝነት የሚሰጡ ትቂቶች ናቸው። ሀብታሙ በመስገብገብ፥ምሁሩ በመታበይ፥ባለስልጣኑ በመሰይጠን፤ ድርጊታችን ሁሉ ለታይታ ወይም "በግብር ይውጣ" እንጂ የቅንነት ፀዳል ያረፈበት አይደለም። ሁሉም ነገር የፍቅር፥የታጋሽነት እና የቅንነት ፀዳል ካልለበሰ ለተቀባዩ ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ እርካታ አይኖረውም። ለዚህም ነው የሀገሬው ሰው "ከፍትፍቱ ፊቱ" የሚለው።
ዶ/ር ተሻገር ለእኔ እውቀት ብቻ ሳይሆን ቅንነት ከጎበኛቸው ሰዎች አንዱ ናቸው። ሰው በሰው ጉዳይ እንደዚህ ሲብሰለሰል፥ በታጋሽነትና በቅንነት ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ሲያደርግ ያየሁ እሳቸውን ነው። መሠል ነገሮች ለእኔ ተፈጥሮና ሰብዕና አዲስ ባይሆኑም፤በዘመነ "እኔነት" ከግብዝነት ነፃ የሆነ ቅንነት የተላበሱ ሰዎችን ማግኘት በርባኖስ ነው። የብዙ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ጥረት፣ የዶ/ር ተሻገር ቅንነት፣ የሾን ሜዲካል ሴንተር እና የሌሎች ተቋማት ባለሙያዎች ጥረት ይስማዕከን ዳግም ወደ ደራሲነቱ እንዲመለስ ከፈጣሪ በታች ውለታ ውለውለታል።
"ያልተሳለ የለም፥ ያልተወረወረ
ስጋዬ እንጂ ቅሉ፥ መንፈሴ አልደደረ" በሚል የትካዜ ጉዞ ይመስላል ደራሲው፤ ከባህር ማዶ መልስ ወደ ትናንት ለመመለስ እራሱን መፅሐፍ ውስጥ ቀብሮ ማደር ጀመረ። መድኃኒቱን በኮረጆ አንጠልጥሎ ተራራና ጋራውን፥ ሜዳና ሸንተረሩን መውጣትና መውረድ ጀመረ። በብዙ የደህንነት ስጋት ውስጥ " #ደህንነቱ "ን ወለደ። ደህንነቱ ዳግም በአካለ ሰብዕ ሳይሆን በአካለ መንፈስ እንዲቆም ጠጠረ ለደገፉ ሰዎች ሁሉ በስጦታ የተበረከተ የዘመናችን "ኢትዮጵያ" ስንክሳር ነው። ፅድቃችንንና መርገማችንን መሳ ለመሳ የሚተርክ ስንክሳር።
ይህ ስጦታ ከሚበረከትላቸው ሰዎች ቀዳሚው ሰው ደግሞ ቅኑ ዶ/ር ተሻገር ናቸው። የፈጣሪ ነገር ሁለት ነገሮችን ግጥምጥም አደረጋቸው። "ደህንነቱ"የተሰኘው መፅሐፍ ታትሞ ወደ ገባያ ሲወጣ እኒህ ቅን ሰው ቤተሰብ ጥየቃ አዲስ አበባ መጡ። ደራሲ ይስማዕከም አፍታውን በክብር አበረከተላቸው። እኛም "ያለቀሱ ሁሉ ይስቃሉ አንድ ቀን" ብለን በፈገግታ አጀብን። እኔም በቅንነት ለቅኑ ሰው ዝቅ ብዬ አመሰገንሁ። ለወትሮው የተደበቀ ፊቴን ከቅኑ ሰው ጋር ፊት ለፊት አሰጣሁት። በአካል ስላገኘሁዎት ደስ ብሎኛል። ስላሳለፍናት አጭር ጣፋጭ ጊዜም እንዲሁ! የቅንነትዎን ዋጋ ፈጣሪ በቤተሰብዎ ይከፈልዎ!
የእኔም ትንሽ ጠጠር መደገፍ መሠል ሀሳቦችን ዳግም እንዲያበረክት ከመመኘት እንጂ ፎቶ አብሮ ለመነሳት የመጎምጀት አልነበረም። ወይም እንደ ዘመኑ ሰዎች አልነበረም። እሱም ከፈጣሪ ጋር ተሳክቶልኛል። ከዚህ ባለፈ "ዛፍ አድርቅ" የሆንን ማህበረሰቦች ነንና ስላለፈውና ስለሆነው ነገር ሁሉ ቅር አይለኝም። "ሲኖሩ ከሳሽ፥ሲሞቱ አልቃሽ" የሆነው ማህበረሰባዊ የስነ-ልቦና ስሪታችን ከ"መቃብር ቆፋሪነት" ወደ "ሰው ሰሪነት" እንዲመለስ ፅኑ ምኞቴ ነው።
መልካም ንባብ!
ሻሎም!
ከአንድ ዓመት በፊት ስለ ዶ/ሩና ስለ እኔ ተምኔት እንዲህ ብዬ ነበር፤
¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢
ከጀርመኑ ሆስፒታል ጋር የተደረገው የህክምና ሂደት እንዲሳካ ትልቅ እገዛ ያደረገው እዛው ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩት ቅን ኢትዮጵያዊ ዶ/ር ተሻገር (ኒሮሎጅስት፣ ሳይካትሪስት) ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ከእንደዚህ አይነት ቅን ሰዎች ልብ ውስጥ ብቻ ያለች ይመስለኛል፡፡ እኒህ ሀኪም ሆስፒታሉ የህክምና ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ለአስታማሚ የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ፣ እራሳቸው እንደ ቤተሰብ አስታማሚ በመሆን ትልቅ እገዛ አድርገውለታል፡፡ ለ10 ሳምንታት የታቀደውን ህክምና አሁንም በገንዘብ እጥረት ምክንያት በ4 ሳምንት እንዲደረግ እገዛ ያደረጉት እኒህ ሰው ናቸው፡፡ ዋጋቸውን እሱ ይክፈላቸው!
የህክምናው ውጤት፡
ሆስፒታል በገባበት እለት ጀምሮ በተለያዩ መሳሪያዎች ሙሉ የጤና ምርመራ ተደርጎለታል፡፡ በየዘርፉ የተመደቡት 10 ስፔሻሊስት ሐኪሞች (በውሉ በተስማማንበት መሰረት) እና ነርሶች ከፍተኛ የሆነ ህክምና እገዛ አድርገውለታል፡፡
ይስማዕከ በድርሰቱ ባለው የምናብ ጥልቀት እና የፈጠራ ትርክት በአዳዲስ ስራዎችና አስተሳሰቦች ከተፍ ብሎ ከጎኑ የነበሩ አድናቂዎቹንና መላ ወገኖቹን እንደሚያስደስት ሙሉ ተስፋ አለኝ፡፡
መልካም ጤና!
¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢¢





!
@yismakeworku
👍3
<<...በአንድ ወቅት የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት የነበሩት
አሊ ሶሊህ ደሴት በሚያክለው የቤተ መንግስት አልጋቸው ላይ ተኝተዋል። መጥፎ ህልም እንደ ሱፐር ማን ከፍቅ ፎቅ ከጉድማ ጉድባ ያዘልላቸዋል። ሰፊው አልጋ ጠቧቸዋል ህልሙ በድንቃድንቅ ድርጊት የታጀበ ትንፋሽን የሚያቋርጥ ነበር። አንድ ድንክ አንበሳ በሚመስል ውሻው የታጀበ ሰውዬ ፕሬዝዳንት አሊን ያሳድዳቸዋል። የውሻው የሾሉ ክራንቻዎች የሶሊህን ጅማቶች ሊበጥሱ ከባታቸው ሲሰነቀሩ ፕሬዝዳንቱ ከእንቅልፋቸው ይባንናሉ። ፕሬዝዳንቱ ይህ ግብግብ ህልም መሆኑን ያወቁት በላባቸው እየዋኙ ከነቁ በኋላ ነበር።

ህልሙን ለማባረር ብራንዲያቸውን ቀድተው ከጨለጡ በኋላ አንድ አዋጅ ያወጣሉ። የፕሬዝዳንቱ አዋጅ በመላ ኮሞሮስ የሚገኙ ውሾች እንዲረሸኑ ጥብቅ ትዕዛዝ የሚሰጥ ነበር። በነጋታው የወጣቶች ውሻ ገዳይ ብርጌድ ተቋቁሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ውሾት አለቁ። አገዳደሉ ልክ ናዚዎች በእስራኤሎች ላይ እንደፈጸሙት ግድያ 'ማገዶ ቆጣቢ' እንዲሆን ተደርጎ በጥቂት ማገዶ ብዙ ውሻ እንዲሞት ተደረገ(አይ አፍሪካ ስንት ጅሎች እስከመቼ ያጃጅሉሽ ይሆን)። ጅሎቱ በሱፍ ደንቅረው በፕሮቶኮል ተጠብቀው ሲታዩ ልዕለ ሰብ(Superhuman) ይመስላሉ። እነሱ ያለነሱ አዋቂ ያለ አይመስላቸውም እኛም ያወቁልን ይመስለናል። በውስጣቸው ግን ባዶ የባዶ ባዶ መሆናቸውን የኮሞሮስ ውሾች ተገንዝበዋል። በህልም ባዩት አንድ ተናካሽ ውሻ ምክንያት አዋጅ አውጥተው የመላ ሀገሪቱን ውሾች ፕሬዝዳንት ሶሊህ ጨርሰዋል። ይህ ድርጊት፣ የሌሎችም ጓዶቻቸው መገለጫ ነው።

ለጥቂት ደቂቃዎች ጸለይኩ። የውሻ ጸሎት። የእኛውንም ሰውዬ በሕልማቸው ውሻ እንዳያባርራቸው ጸለይኩላቸው ። ካባረራቸው እኛ ውሾች አለቀልን በቃ ። የኛውም ሰውዬ አንድ ሰው ለማሰር አዋጅ እንደሚያረቁ፣ ህጋዊ ለማስመሰልም በፓርላማ እንደሚያጸድቁ በትግል ጓደኞቻቸው ሳይቀር ይታማሉ።....>>

ከክቡር ድንጋይ መጽሀፌ የተወሰደ..
ከገጽ 49-50
@yismakeworku
ብቸኝነት ሲሰማህ ማሰብ ከቻልክ የአሳብህ ጓደኛ ነህ። ማሰብ ካልቻልክ ብቻህን ነህ። መነጠል የስጋ ሳይሆን የአሳብ ስሜት ነው። ብቸኝነትህን አሳብህ ሲጋራ የአሳብ ጓደኛ አለህ። ብቸኝነትም ጓደኝነትም ስጋ አይደለም። የአብሮነትና የመነጠል ስሜት ነው።
ከሰው ጋር ስትሆን ለብቻህ እንደሆንክ ከተሰማህ በግርግር መሀል ብቸኛ ነህ። በስጋህ ብቻህን ሆነህ ከአሳብህ ጋር አብረህ ከሆንክ አንተማ ጓደኛ አለህ። ከቻልክ የወዳጅ አስፈላጊነትን ቀንስ። ሰው ብታጣም ያጣኸው ስጋ ነው። አብሮህ የሆነ አላቂ ነው። ዛሬ የሚቀርብህ ነገ የሚርቅ ነው። ወሳኙ ጉዳይ ህሊናህን አለማጣትህ ነው። የሌላ ስጋ ሲለይ አሳብህ ካንተ ጋር ነው።

መለየት የስጋ ነው። ብቻህን እንዳልሆንክ ከተሰማህ የአንተ ጓደኛ ስሜትህ ነው።
@yismakeworku
ገጽ 30 ክቡር ድንጋይ ላይ... @yismakeworku
በዚህ የጭንቅ እና የሀዘን ጊዜ ሰዎችን በመርዳት እና በማገዝ ነፍሳችንን ማከም አለብን። መቼ እንደምንሞት አናውቅምና ደግ በመሆን ፈጣሪያችንን እናስደስት።
#ሼር በማድረግ ብቻ ምናልባት ለሚረዷት ግለሰብ ልናሳውቅ እንችላለን እና እንተጋገዝ። #ሼር @yismakeworku
👍2
ሁለት መልእክቶች አሉኝ፡፡
1ኛ፦ የኮሮና ቫይረስን መድሃኒት አግኝቻለሁ፡፡ እርሱም ቤትን ሸግጦ (ዘግቶ) መዋል ነው፡፡
ቤት ስትውሉ ግን፣ ማንበብ አለባችሁ፡፡ ይህ የእኔን መጽሐፍ ለማሸጥ ብዬ አይደለም፡፡ የእኔ መጽሐፍ ከሰአት ወጥቶ ከሰአት ያለቀ መጽሐፍ ነው፡፡ በአንድ ቀን ወጥቶ በአንድ ቀን ያለቀ መጽሐፍ፡፡ በቀጣዩ ቀን ደግሞ አሳታሚው እኔን ቀጣዩን መጽሐፍ ለማሳተም እንዲችል ሊያስፈረመኝ የመጣ ነው፡፡ የእኔን ብቻ ሳይሆን፣ የሌሎቹንም አንብቡ፡፡ ለህጻናት የህጻናት መጽሐፍ ገዝታችሁ እንዲያነቡ ስጡአቸው፡፡ ለአዋቂዎች ደግሞ የአዋቂ መጽሐፍ ገዝታችሁ አንብቡ፡፡ ከዚሁ ጋርም የተያያዘ እኛ የምንታማበትን በሽታችን እንድናጠፋው፡፡ አለማንበብ ነው ትልቁ በሽታችን፡፡ ተረት ተተርቶብናል፡፡ ከመቶ ሚሊዮን በልጠናል በቁጥር፡፡ አምስት ሺህ መጽሐፍ ታትሞ ለአመታት ሳይሸጥ ይቆያል፡፡ ስለማናነብ፡፡ ሊቁም ደቂቁም አናነብም፡፡ ዝም ብለን ስድብ ብቻ፡፡ ያውም አንብበን አይደለም፡፡ ሳናነብ ስድብ ብቻ፡፡ የሚያነብ ሰው አይሳደብም፡፡ ለደውዬው መድኃኒት ከሚያነበው ይቀምማል እንጂ፡፡ አዋቂ ሰው ስድብ አይቀምም፡፡ ለበሽታው ካነበበው ውስጥ ቅመም ይፈልጋል እንጂ፡፡

2ኛ፦ እኔ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ያገኘሁት የጤና ባለሙያ ሆኜ ነው፡፡ ማስተርሴን ያገኘሁት በሌላ ሞያ ነው፡፡ ፒ . ኤች ዲዬን ደግሞ በሌላ ሞያ፡፡
የጤና ባለሙያ የጎደለባችሁ ሆስፒታሎች ጥሩኝ፡፡ ከነጋወኔ ወዲያውኑ እመጣለሁ፡፡ ደመወዝ አልጠይቅም፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ @yismakeworku
👍5
ወደ ወዳጄ ስልክ በጠዋቱ ደወልኩ። ወዲያው አነሳው። "በዚህ ብዙ ሰው ቤት በሆነበት ሰዓት ለምን መልካም ነገር አናደርግም?" አልኩት። "ምን?" አለኝ። "የአቋረጥከውን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ለምን አትጀምርም?" ተስማማን።

እና ወዳጆች እናንተም በዚህ ጊዜ ቤታችሁ ቁጭ ብላችሁ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት በቴሌግራም ብቻ መማር ከፈለጋችሁ ይሄንን ገፅ ተቀላቀሉ https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEdFR8GOZaON_GweXQ

ይሄንን ጊዜ እየተማማርን እናሳልፈው።
ገፀ ምድሪ ግራካሕሱ
@yismakeworku
ከዚህ በፊትም እኔ አሳውቂያችሁ፤ ተወዳድራችሁ 4 ሰዎች እንደተሸለማችሁ ተነግሮኝ ተደስቻለሁ። አሁንም ሌላ ዜና አምጥተዋል። ወዳጄ አልተቻለም።

እያስተማረ የሚሸልምውን የወዳጇን የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል አንድን የእንግሊዘኛ እውቀትዎን ያዳብሩ ሌላም ይሸለሙ።

የቻናሉ አድራሻ https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEdFR8GOZaON_GweXQ
ወደ እኔ ማንኛውንም አስተያየት፣ ጥቆማ፣ ሀሳብ፣ እምነት፣ መልዕክት እንዲሁም ሌላም ሌላም ነገሮች ለመወርወር ይሄንን አድራሻ ተጠቀሙ።
@YismakeworkuBot ላይ በመግባት ያሻዎትን ነገር ያስቀምጡልኝ። ይደርሰኛል።

ይህን ያዘጋጀልኝን ወዳጄ አመሰግናለሁ።
ይሄንንም በመሳቅ እናልፈዋለን @yismakeworkuBot
"ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ"
ማን ነው ብሎ ያለ
ታዲያ አሁን ታዲያ ፣ ምን ነክቶት ዝም አለ
ምንቸቶችም ጠፍተው፣ ገሎች ቀርተው ሳለ።

ይስማዕከ ወርቁ! @yismakeworku
👍3
በዚህ ጊዜ ቤታችሁ ቁጭ ብላችሁ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት በቴሌግራም ብቻ በመማር ክህሎቱን ማሳደግ ከፈለጋችሁ እንዲሁም ስለተማሩ ብቻ ሽልማት የሚሸልማችሁን የወዳጄን የቴሌግራም ገፅ መቀላቀል ከፈለጋችሁ አድራሻው ይሄ ነው። https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEdFR8GOZaON_GweXQ