Yismake Worku
20.6K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
ከአጥቂ ጋር አታጥቃ
የጨለመ ቢመስል፣ ፀሐዩ ባይወጣ፣ ሌሊቱን ብታየው፣
አይነጋም አትበል፣ ለፅልመያኮሱ ነውና ሚታየው፡፡
ጉረኛ ለጊዜው፣ ለጊዜው ቢጥርም፣
ከአጥቂ ጋር አታጥቃ፣ እንደመሸ አይቀርም፡፡
@yismakeworku
መልካም የደመራ በዓል!
@yismakeworku
ዴርቶጋዳ
እንዲህ ታዝቢያለሁ....
ይስማዕከ ወርቁ።
እንዲህም ብያለሁ....
ይስማዕከ ወርቁ።
በቀስተ ደመና የታጀበው የጎንደር የምህላ ፀሎት 28ኛ ቀን
በቅርቡ አዲስ መፅሀፍ ይዤ እመጣለሁ። ይጠብቁኝ።
ሁልጊዜም ለእኛ ለተራማጆች ቀኑ ልደታችን ቢሆንም ህዳር 7 ግን የልጄ የልደት ቀኑ ነው። የሰባትን ምስጢር በልጄ ውስጥ ፈለግኩት። እርሱም የበደሉህን ሁሉ ይቅር በል ይላል።
@yismakeworku
@yismakeworku
ትዝበቴ ይህ ነው።
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
@yismakeworku
ለማጋራት ያክል...
እንኳን ለድንግል ማርያም አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ።
#አክሱም_ፅዮን_ለማርያም!
@yismakeworku
👍2
ያሳመረኝ ቀለሜ ነው።
💚💛
ከስድስት አመታት በፊት፣ ብዙ ክስትቶች እኔ ጋር ከመፈጠራቸው አስቀድሞ።

የንግስተ ሣባ ቤተ መንግሥት ላይ ፣ አክሱም።
@yismakeworku
ይህች ተራራ አድዋ አካባቢ የምትገኝ ተራራ ናት። ድሮ መንጥረን ጣልያንን እንዳላባረርነው። አሁን ልጇን አዝላ እርቃን የቆመች ተራራ ቀረችን። እንደ ኢትዮጵያ፤ ልጇን አዝላ የምትሰደድ ተራራ።
@yismakeworku
👍1
እየተጎነጨን😁
ጠላቴ ይቅርታ
ጠላቴ ሆይ በርታ፣
ተበራታ በርታ፡፡
ፊቴም እንዲወዛ፣
እግሬ እንዲወረዛ፡፡
ጠላቴ ሲበዛ፣
ጦሬም እንዲበዛ፡፡
"ሰው አለሁ እንዲለኝ"
በርታና በድለኝ፡፡
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ እግር የሚወለድፍ፣
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ የሚያስቀድመውን መድፍ፣
ህልሜን ልይዘው ስል፣ እጄን የሚመታ፡፡
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ እግሬን የሚመታ፡፡
ጠላት የሌለው ሰው፣ ቢወጣ ቢወርድም፣
ወይ ህልም አላለመም፣ ወደ ህልሙ አይሄድም፡፡
ውሎዬ እንዲሰምር፣ ቀኔን የሚመቀኝ፣
አዳሬ እንዲሰምር፣ ሌሊት የሚመቀኝ፣
ጠላቴን አትንሳኝ፣
ጠላት አታሳጣኝ፡፡
ተባለ ምኑን ሰው ፣
ጠላት የሌለው ሰው!
እባክህ ፈጣሪ፣ ጥሩ ጠላት ፍጠር፣
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ የሚያስቀድም ጠጠር፡፡
(ይስማዕከ ወርቁ)
"ደህንነቱ" በሚል ስያሜ ለሚወጣው አዲሱ መጽሀፌ ዝግጁ ናችሁ?
@yismakeworku
(አይስበርህ ሀዘን፣
አይዝራህ ሰቀቀን፤
ከመጠበቅ ማዶ፣
ይመጣል ያንተ ቀን፡፡)
ደህንነቱ የሚለው መጽሐፌ ደርሷል፡፡ ጭንቅላቴ ከውጭ ተተርትሮ፣ ከውስጥም እኔ እያማጥኩበት ምጤን እነሆ፡፡ ለማንኛውም የሁላችንም ፈጣሪ ይመስገን ብያለሁ፡፡ በወዳጆቼ ፀሎት እንጂ በእኔ ሥራ አይመስለኝም፡፡ ሁሉን ነገር ፈልፍያለሁ፡፡ የተቻለኝን እነሆ፡፡
@yismakeworku
👍3