Yismake Worku
20.5K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
ሕክምናዬ በፎቶ ሲገለፅ. . .
( @yismakeworku )
👍2
በግማሹ ቁስሌን አስታገሳችሁት...ጠፈፍ ብሏል። እወዳችኋለሁ... ለእናታችን የጠየቋችሁን ነገር በአጭር ጊዜ አሳክታችሁልኛል።
ጓደኛዬ በውቄ ከምወዳት ግጥሙ ሁለት ስንኞችልምዘዝ
"...ባዶ ድስቴን ልጣድ ባዶ ለማገንፈል
ከንፈገት ይሻላል እጦትን ማካፈል!"

እንደዚህ አይነት ደግ ተግባራት ማለትም መድረስ ለሚገባን ሰው መድረስ አለብን የምትሉና ይሄንንም ነገር እንዳሳውቃችሁ የምትፈልጉ ሰዎች ይሄን 🔵በመንካት አሳውቁኝ
አይ ይቅር የምትሉ ደሞ🔴 በዚህ መልሳችሁን አሳዩኝ።

ስለኔ ደህንነት የጠየቃችሁኝ ደሞ በሰፊው በቅርቡ እነግራችኋለሁ።
"ህልሜን አላቀልጥም"
(ይስማዕከ ወርቁ፡ ከጀርመን-13ኛ ቀን)
;
ወታደርም ቢባል
ያው በቀቀናም ነው፣
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
አሸናፊም ብትል
ይፈራል ነገውን
ፍርሃት አለው ነውጡ፣
ንጉሠ ነገሥትም
ፍርሃት አለ ቆጡ፣
አንበሳ ደቦሉም
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
ማንኛውም ብትል
ጠልፎ የሚጥል ሰው
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
"ብተወውስ" ብሎ
ይፈራል ታንቲራ፤
እኔ ግን የምልህ
ህልምህን አትፍራ፣
ድፈረው፣ ድፈረው
ወንጀለኛ አይልህም ፍርድ ቤቱ ደፍሮ
አቃቤ ህግ አይከስ፣
እንዲያውም ይፈራል-ይፈራል ወጥሮ
ህልምህን የምተው...
ወመኔ 'ሚዘራው
ገንዘብ ስላጣህ ነው?
ተስፋ ስላጣህ ነው?
ያዘው ግፋ ብሎ
ተስፋን የሚመግብ
ቤተሰብ ነው ያጣህ?
ወይስ ነው ከጀርባህ
ኦና ሆኖ ታየህ?
እኔ ግን የምልህ
እኔ የምመክርህ፣
እንዳትመለስ ነው
ከተስፋ ከእድልህ
እኔ የሚታየኝ
እኔ እንደሚሰማኝ፣
ችግርም ብትፈጥር
በራስህ ላይ ወጥር
ለውጥ አምጣ
ለውጥ አምጣ
ቀን አውጣ
ቀን አውጣ
ችግርና ፍዳህ የመኖርህ ትርጉም
ላብ ነህ ለዚህ ምድር
ወዝ ነህ ለዚህ ዓለም፡፡
ወዝና ጊዜየን በቁሜ ብቀማም
እንደ አሸን ተራግፈው
ጓደኞቼን ባጣም
ወደሁዋላ ስዞር
አንድም ሰው ባይመጣም
ተስፋዬን አልሸጥም
ህልሜን አላቀልጥም፡፡
-----------------------
(ፀሐፊ-ይስማዕከ; ህዳር 14፣ 2011 ዓ.ም)
👍3
ከላይ ካሰፈርኩት ግጥም ጋር ይሄ ፎቶ ይያያዝ!
@yismakeworku
👍1
የልጄ ናፍቆት ከህመሜ በላይ ውስጤን ሰርስሮት ገብቷል።
ሀኪሞች ይሄንንስ እንዴት ልትፈውሱልኝ ትሞክሩ ይሆን?
@yismakeworku
አሁን ያለሁበት ሁኔታ... @yismakeworku
የኔ ደስታ ለሚያስደስታችሁ በሙሉ. . . በጣም ደስ
ብሎኛል።
በከፊል ማውራት ጀመርኩ!
.
(ሼር በማድረግ ለተጨነቁልኝ ይሄን ዜና አብስሩልኝ)
ይሄን በመንካት ❤️ የተደሰታችሁልኝ ወገኖች ብዛት ልየው
4👍2
ማውራት ከጀመርኩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃለ ምልልስ ያደረግኩት ከኮሜዲያን ደረጀ ሀይሌ ጥበብ በፋና ጋር ነው። እንዴት ተመለከታችሁት ዝግጅቱን?

አሁንማ ፈጣሪ ይመስገን ጤንነቴ ከሞላ ጎደል ተመልሷል። ማውራት ጀምሪያለሁ። ወደ እናንተ ደጋግ ሰዎች የበለጠ ለመቅረብም የዩቱብ አካውንት ለመክፈት አስቢያለሁ።
በድረገፁ ውሥጥ
ስለኔ ወቅታዊ መረጃ
ትረከቶች
እና መሰሎች መቅረባቸው እሙን ነው።
እናንተስ ምን አሰባችሁ?
🅰 ሀሳብህን ደግፌዋለሁ
🅱 ሀሳብህን አልደገፍኩትም

ፈጣሪ ስለሁሉም ነገር ይመስገን - እናንተን ስለሠጠኝም ጭምር።
Audio
ለመጀመሪያ ጊዜ መናገር ከቻልኩ በኋላ ከኮሜዲያን ደረጀ ሃይሌ ጥበብ በፋና ጋር የነበረኝ ቃለመጠይቅ...
#ክፍል_አንድ
@yismakeworku
@yismakeworku
ይስማዕከ ወርቁ ከጥበብ በፋና ጋር ያደረገው ቆይታ ክፍል 2
<unknown>
#ክፍል_ሁለት
ከኮሜዲያን ደረጀ ሃይሌ ጥበብ በፋና ጋር የነበረኝ ቃለመጠይቅ!
@yismakeworku
@yismakeworku
👍1
"በኡባልም ወንዝ መካከል። ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ
ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ
ሰማሁ።"
(ትንቢተ ዳንኤል- 8:16)
👍1
አምሮብኝ ይሆን!? @yismakeworku
👍3
👍1
#ቁራኛዬ ⬆️
እንቢ ለማለት የማልደፍረው ወዳጄ ስለጋበዘኝ ብቻ እሺ ብዬ ያየሁት የአማርኛ ድንቅ ፊልም ነው። ፊልሙ ከዚህ ዘመን
አውጥቶ የዛሬ መቶ ዓመት በ1911 ዓ/ም ንግሥት ዘውዲቱ
ዘመነ መንግሥት ላይ ወስዶ፤ እጀ ጠባብ አስታጥቆ ሸማ
አልብሶ፤ የሚገርም ታሪክን በሳቅ አሹሮ ያስኮመኩመናልና ታዩት እና
ትገረሙበት ዘንድ ጋበዝኳቹ፡፡
ግን የድሮ ዘመንን በዘንድሮ መነፅር ማየት የሚሻ የለምና እምብዛም ተመልካች አላየሁበትም።
እጅግ በጣም ውብ ፊልም ነውና ያላያችሁ እዩልኝ፣ ተጋበዙልኝ። የተመለከታችሁት ደሞ እንዴት እንደነበር አሳውቁኝ
"እንኳን ለጌቶች ጌታ፣ ለንጉሦች ንጉሥ ለሆነው
ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም
አደረሳችሁ፡፡"
...ዮሐንስ መልሶ። እኔስ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን
የጫማውን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ
ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡
መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥
ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ
እሳት ያቃጥለዋል አላቸው።
ስለዚህ ሕዝቡን በብዙ ሌላ ምክር እየመከራቸው ወንጌልን
ይሰብክላቸው ነበር፡፡
የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ ግን፥ ስለ ሄሮድያዳ ስለ
ወንድሙ ስለ ፊልጶስ ሚስትና ሄሮድስ ስላደረገው ሌላ
ክፋት ሁሉ ዮሐንስ ስለ ገሠጸው፥ ይህን ደግሞ ከሁሉ
በላይ ጨምሮ ዮሐንስን በወኅኒ አገባው።
ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ።
ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፣
መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ
ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል
የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።
(የሉቃስ ወንጌል 3)
በሰላም ነው የጠፋሁት!
ለተጨነቃችሁልኝ በሙሉ አመስግኛለሁ።
@yismakeworku
አርቲፊሻል ፀጉሬና ጓደኞቼ 😁
ለትውሥታ
ወዳጆቼ ግራ ተጋባሁኝ!
በዚህ መድረክ በይበልጥ ምን እንድታገኙ ትሻላችሁ?
🅰ጽሁፍና ግጥሞቼን
🅱ስለኔ ወቅታዊ መረጃዎች