#ቁራኛዬ ⬆️
እንቢ ለማለት የማልደፍረው ወዳጄ ስለጋበዘኝ ብቻ እሺ ብዬ ያየሁት የአማርኛ ድንቅ ፊልም ነው። ፊልሙ ከዚህ ዘመን
አውጥቶ የዛሬ መቶ ዓመት በ1911 ዓ/ም ንግሥት ዘውዲቱ
ዘመነ መንግሥት ላይ ወስዶ፤ እጀ ጠባብ አስታጥቆ ሸማ
አልብሶ፤ የሚገርም ታሪክን በሳቅ አሹሮ ያስኮመኩመናልና ታዩት እና
ትገረሙበት ዘንድ ጋበዝኳቹ፡፡
ግን የድሮ ዘመንን በዘንድሮ መነፅር ማየት የሚሻ የለምና እምብዛም ተመልካች አላየሁበትም።
እጅግ በጣም ውብ ፊልም ነውና ያላያችሁ እዩልኝ፣ ተጋበዙልኝ። የተመለከታችሁት ደሞ እንዴት እንደነበር አሳውቁኝ