YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ጠ/ሚ ዶ/ር አበይ #ከምሁራን ጋር በነበራቸው #ውይይት ያነሷቸው ዋና ዋና አሳቦች
====================
1.ኢህአዴግ በቅርቡ ፍልስፍናውን እና ምልክቱን ይቀይራል ፡፡ አብዛኛዎቹ የክልል መስተዳደሮችም ይቀየራሉ
2. ብዙ ወንጀል ሠርተው ትግራይ ውስጥየተደበቁ ሠዎች አሉ፡፡ እነሡ ናቸው ያልሆነ መረጃ የሚለቁት
3. በስልጣን እስከቆው ድረስ የትግራይን ህዝብ ጠቅሜ ነው የምወርደዉ ፡፡ ከጥቅምቹ አንዱ የኤርትራን ጉዳይ መጨረስ ነው
4. ኢሳያስን መቀሌ ይዤው ብሄድ ደስ ባለኝ ግን እንደለመዱት የሆነ ነገር አድርገው ሁለቱን ህዝቦች ያልሆነ ነገር ውስጥ የከቱናል ብዬ ነው
5. የኔ ዋና ግብ በሚቀጥለው ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ ነው
6. የህዳሴው ግድብ በሚቀጥሉት 10 አመታት ላይጠናቀቅ ይችላል ፡፡ ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ በቻ ነበር
7.ችግሮች እንዲፈቱ ስለፈለኩኝ የጉራጌ ብሔረሠብን በባለፈው የወልቂጤ ውይይት ተጨኜዋለው፡፡ የጉራጌ ዘርማ ታሪክ ሠርቷል ፡፡ ጉራጌ አሁንም ያለ ቀቤና አያምርበትም፡፡
8. የባንድራው ጉዳይ ልክ እንደ ሀገ መንግስቱ የማይሻሻልበት ምክንያት የለም፡፡
9. አብዛኛዎቹ ሚዲያዎች የሆነ ቡድን አሳብ ማስፈፀሚያ ናቸው፡፡ የENN ቴሌቪዝን ስለ በደሌ ያቀረበው የተሳሳተ መረጃ የተፃፈውና የተዘጋጀው መንግሰት ቢሮ በባለ ስልጣን ነው፡፡
10. የት/ት ጥራትን በተመለከተ በሠፊው እየሠራን ነው
11. የመምህራን ደሞዝና ጥቅም በተመለከተ ዝቅተኛ መሆኑን እናውቃለን ስለ እሱም እንወያያለን
#ጠ/ሚ_ዶክተር_አብይ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የዚህን ዓመት የመከላከያ እዝ ኮሌጅ ተመራቂዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡

©የጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ
#ጠ/ሚ_ዶ/ር_አብይ⬇️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለው የመንጋ_ፍትህ እና አላስፈላጊ ሁከት ተቀባይነት የሌለው እና የህግ የበላይነትን አደጋ ውስጥ የሚጥል መሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ11ኛው እነ 12ኛው ዙር የሰለጠኑ የመከላከያ መኮንኖችን ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው።

በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ድርጊቱ የህግ የበላይነትን የሚነድ በመሆኑ በአስቸካይ ሊቆም እንደሚገባው ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ የተሳሳተ መረጃን መሰረት በማድረግ ለህግ ቅድሚያ ሳይሰጥ የሚፈጽማቸው ድርጊቶች እየተገነባች ያለችን ሃገር ከማፍረስ ውጭ ዋጋ እንደሌለውም ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የህግ የበላይነት ለአንድ ሀገር ማህበረሰብ መጠበቅ መሠረት መሆኑንም በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻርም መንግስት አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለውን ከህግ በላይ የመሆን ዝንባሌ እንደማይታገስም አንስተዋል።

“እንደመር ስንል ባለፍንበት መንገድ ያጣነውን ለመመለስ እንጅ ሃገሪቱን ውጤት ለከፋ_ቀውስ ለመዳረግ አይደለምም” ብለዋል በንግግራቸው።

መንግስትም እነዚህን ክስተቶች ለመቆጣጠር የመከላከል እና ህግ የማስከበር ስራዎችን ይሰራልም ነው ያሉት።

©FBC
@YeneTube @Fikerassefa
#ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆች ለሆኑ 200 ተማሪዎች ዛሬ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ለግሰዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ድህነትን እና በሽታን የመዋጋቱን ጥረት ሁላችንም ተቀላቅለናል የሚል መልዕክትንም አስተላልፈዋል።

©Fbc
@fikerassefa @Yenetube
#ጠ/ሚ_ዶ/ር_ዐብይ⬆️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹኩሪ ጋር ውይይት አድርገዋል።

©አቶ ፍፁም አረጋ ቲዊተር
@YeneTube @Fikerassefa
#ለ27 ዓመታት በጣሊያን ኤምባሲ በጥገኝነት የቆዩት የቀድሞ #ባለሥልጣናት ምሕረት እንዲደረግላቸው መጠየቁን ዶቸቬሌ ዘግቧል፡፡

#በወታደራዊው መንግስት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት #ብርሀኑ ባየህ እና ኤታማዦር ሹም ሆነው ለአጭር ጊዜ የሰሩት #ሀዲስ ተድላ (ሌ/ጄኔራል) በሌሉበት ክስ ተመስርቶባቸው የሞት፣ በኋላም ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡

የባለሥልጣናቱ የቅርብ ተጠሪ የምሕረት ጥያቄውን ያቀረቡት የሰዎቹን ዕድሜና ጤና እንዲሁም ላለፋት ዓመታት የቆዩበትን አስቸጋሪ ሁናቴ ከግምት በማስገባት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ በቅርቡ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ #በቀይ ሽብር ለተከሰሱ ሰዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግስት ምሕረት እንደሚከለክል ተናግረዋል፡፡
© wazema
@YeneTube @mycase27
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ፡፡

#ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ዛሬ ማለዳ ላይ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለ2 ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኤርትራ ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂን አቀባበል
አድርገውላቸዋል።
ምንጭ ፦ ሸገር 102.1
@yenetube @mycase27
#ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ_አህመድ_ያስተላለፉት መልክት

በአገራችን በዛሬው እለት አንድ ኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው የተገኘ በመሆኑም ህብረተሰቡ እነዚህን ምክሮች በመከተል እራሱን እና ቤተሰቦቹን ከበሽታው እንዲከላከል አሳስባለሁ።

* እጃችንን በውሃ እና በሳሙና አዘውትሮ መታጠብ

* የጉንፋን ምልክት ከታየብን ከቤት አለመውጣት፣ ሰው የሚበዛብት ቦታ አለመሄድ

* ንክኪ የሚያስፈልጋቸው የሰላምታ መንገዶችን መተው

* ሰው በብዛት የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ

* ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በንቃት የራሱን እና የቤተሰቡን ጤና መጠበቅ

Via:- አብይ አህመድ
@Yenetube @FikerAssefa
#ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ_አህመድ_ያስተላለፉት መልክት

ህብረተሰቡ እነዚህን ምክሮች በመከተል እራሱን እና ቤተሰቦቹን ከበሽታው እንዲከላከል አሳስባለሁ።

* እጃችንን በውሃ እና በሳሙና አዘውትሮ መታጠብ

* የጉንፋን ምልክት ከታየብን ከቤት አለመውጣት፣ ሰው የሚበዛብት ቦታ አለመሄድ

* ንክኪ የሚያስፈልጋቸው የሰላምታ መንገዶችን መተው

* ሰው በብዛት የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ

* ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በንቃት የራሱን እና የቤተሰቡን ጤና መጠበቅ

Via:- አብይ አህመድ
@Yenetube @FikerAssefa