YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ለ27 ዓመታት በጣሊያን ኤምባሲ በጥገኝነት የቆዩት የቀድሞ #ባለሥልጣናት ምሕረት እንዲደረግላቸው መጠየቁን ዶቸቬሌ ዘግቧል፡፡

#በወታደራዊው መንግስት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት #ብርሀኑ ባየህ እና ኤታማዦር ሹም ሆነው ለአጭር ጊዜ የሰሩት #ሀዲስ ተድላ (ሌ/ጄኔራል) በሌሉበት ክስ ተመስርቶባቸው የሞት፣ በኋላም ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡

የባለሥልጣናቱ የቅርብ ተጠሪ የምሕረት ጥያቄውን ያቀረቡት የሰዎቹን ዕድሜና ጤና እንዲሁም ላለፋት ዓመታት የቆዩበትን አስቸጋሪ ሁናቴ ከግምት በማስገባት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ በቅርቡ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ #በቀይ ሽብር ለተከሰሱ ሰዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግስት ምሕረት እንደሚከለክል ተናግረዋል፡፡
© wazema
@YeneTube @mycase27