YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ሜቴክ

#የዓለም ገነት ቆርቆሮ ፋብሪካ እና በግንባታ ላይ ያለው ፎር ፖይንት #ሸራተን ሆቴል ባለቤት አቶ #ዓለም ፍፁም ገብረስላሴ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ግለሰቡ ራቤራ የተባለን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኝ ሆቴልን #እጅግ በተጋነነ ዋጋ 128 ሚሊየን ብር #ከሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ጋር የነበራቸውን ጥሩ ግንኙነት በመጠቀም በመሸጥ ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በተጨማሪም ሆቴሉ #በባንክ ተይዞና እዳ እያለበት የባንክ እዳውን ገዢው ሜቴክ እንዲሸፍን ተደርጎ እንደተሸጠም ነው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለፀው።

የግለሰቡ የሀብት ምንጭ ህብረተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ #መቆየቱ አይዘነጋም።

ሰሞኑን መንግስት በተለይም በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ውስጥ ከተፈፀመ የሙስና #ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወቃል።

እነዚህም ተጠርጣሪዎች እስከ ትናንት ድረስ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው መታየት ጀምሯል።
ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27