YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ወልዲያ ከተማ ላይ የሰላማዊ ሰልፉ ገጽታ እና መልዕክቶች

📌የራያ እና የወልቃይት የማንነት ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል፤
📌ራያ ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይማሩ፤
📌በራያ እና በወልቃይት እየተፈጸመ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ይቁም፤
📌ላልይበላ በኛ ጊዜ አይፈርስም፤ ጣና በኛ ጊዜ አይደርቅም፤
📌የፌዴራል መንግስቱ ለጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጥ ይገባል፤የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
ፎቶ ፦ AMMA
@yenetube @mycase27
#ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አለመረጋጋት ዛሬም መቀስቀሱን ሰምተናል ተማሪዎች እንደገና ፍርኃት ውስጥ ገብተዋል።

#jimma university

ጅማ ዩንቨርስቲው ላይ ምንም አይነት ችግር ባይኖርም ተማሪዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ለየኔቴዩብ ተናግረዋል። በቤተክርስቲያን ውስጥም የተጠለሉ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።

#Hawassa

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ በወልድያ ዩንቨርስቲ በተከሰተው የተማሪዎች ሞትን ለማውገዝ ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቢሞክሩም እርስ በእስር ባለመግባታ መጠነኛ ግርግር መነሳቱን ስምተናል። እንዲሁም አሁን ላይ ዩንቨርስቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደቀጠለ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

#Adama

አዳማ ዩንቨርስቲ ያለፉትን ሶስት ቀናት ተማሪዎች ትምህርት ገበታቸው ላይ አልተገኙም፣ ነገር ግን ዩንቨርስቲው ከነገ ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ አሳስቧል። ያናገርናቸው ተማሪዎች ለህይወታችን እንሰጋል ሀላፊነት የሚወስድ አካል በሌለበት ወደ ትምህርት ገበታችን ላይ ለመመለስ ይከብደናል ብለውናል።
እንዲሁም የማስተርስ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በትክክል እየተከታተሉ መሆኑን አሳውቀውናል።


#bulehora_university

ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ትላንትና ዕለት ዋዜማ ሚዲያ 10 ተማሪዎች መቁሰላቸውን የዘገበ ቢሆንም ባደረግነው የማጣራት ስራ ምንም አይነት ችግር አለመኖሩን ለማወቅ ችለናል።

@Yenetube @Fikerassefa
ዩንቨርስቲዎቻችን እንዴት ሰነበቱ ??

#ሀዋሳ_ዩንቨርስቲ

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዘንድ በማን እንደተሰራጨ ለጊዜው ባልታወቀ አካል ተማሪዎች የሚያሸብር ፁሁፍ በብሄር ተከፍሎ ለሁለት ወገን ብቻ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል።

ይህ መረጃ ከተሰራጨበት ሰዐት አንስቶ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ተማሪዎች ለየኔቲዩብ ተናግረዋል።

#ድሬደዋ_ዩንቨርስቲ

የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ተማሪ ከፎቅ ወድቆ ሞተ የሚል ዜና ዩንቨርስቲው በፌስቡክ ገጹ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ተማሪዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ነግረውናል።

ከዚው ጋር በተያያዘ የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ከግቢው ለቀን እንወጣለን ቢሉም ዩንቨርስቲው መከልከሉን ተከትሎ ተማሪዎች በአጥር ዘለው መውጣታቸውን ሰምተናል።

#ወልዲያ_ዩንቨርስቲ

ተማሪዎች ዛሬ ወደ ቤታችን መልሱን እያሉ ይገኛሉ ግቢው በመከላከያ እየተጠበቀ ይገኛል። የፊታችን ሰኞ ትምህርት እንደሚጀመር ዩንቨርስቲው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ገልፅዋል።

#አዳማ_ሳይንስ_እና_ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ

አዳማ ዩንቨርስቲ የፊታችን ሰኞ Mid Exam ይጀምራል ብሏል ነገር ተማሪዎች ትምህርት ካቆሙ አንድ ሳምንት አልፏቸዋል፤ ተማሪዎቹ ግን ስጋት ውስጥ ሆነን ስለ ትምህርታችን እናስብ ወይስ ስለ ህይወታችን በማለት ዩንቨርስቲ ያወጣውን የፈተና ፕሮግራም ኮንነዋል።

#ደብረብርሀን

እንደሚታወቀው ደብረብረሀን ዩንቨርስቲ ዛሬ የአንድ ተማሪ ህይወት አልፏል። ከዚህ ክስተት በኋላ ግን ዩንቨርስቲው ሰላም መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።ነገር ግን ተማሪዎች እንደነገሩን ከሆነ ነገ ምንም እንደሚከሰት መገመት አንችልም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነን ብለውናል።
_______________________________
በዚህ መሰረት ችግር የሚታይባቸው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ዩንቨርስቲዎች መሆናቸው ለማወቅ ችለናል ነገር ግን ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ችግር ባይኖርም የተበተነው መረጃ ተማሪዎች ላይ ስጋት ጥሏል።

@Yenetube @Fikerassefa