YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሀዋሳ‼️

የሲዳማ ዞን የክልል ጥያቄን አስመልክቶ ዛሬ ጨምሮ ለ3 ቀን የሚቆይ የስራ አድማ ምክንያት የተለያዩ ተቋማት የሀዋሳ ከተማ የንግድ ተቋማት እና የመንግስት ቢሮዎች ተዘግተው እንዳሉ የኔቲዩብ ቤተሰቦች ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ #ሀዋሳ_ዩንቨርስቲ በአድማው ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደት መቋረጡን ተማሪዎች ገልፀዋል።

ያናገርኳቸው አድማውን ያስተባበሩ አካላት #የከተማው ነዋሪ ምንም አይነት #ድንጋጤ ውስጥ እንዳይገብ እና እኛ በሰላማዊ መንገድ ጥያቆዎቻችንን እየጠየቁ መሆኑ አክለሁ ገልፀውልኛል።
@YeneTube @FikerAssefa
ዩንቨርስቲዎቻችን እንዴት ሰነበቱ ??

#ሀዋሳ_ዩንቨርስቲ

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዘንድ በማን እንደተሰራጨ ለጊዜው ባልታወቀ አካል ተማሪዎች የሚያሸብር ፁሁፍ በብሄር ተከፍሎ ለሁለት ወገን ብቻ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል።

ይህ መረጃ ከተሰራጨበት ሰዐት አንስቶ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ተማሪዎች ለየኔቲዩብ ተናግረዋል።

#ድሬደዋ_ዩንቨርስቲ

የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ተማሪ ከፎቅ ወድቆ ሞተ የሚል ዜና ዩንቨርስቲው በፌስቡክ ገጹ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ተማሪዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ነግረውናል።

ከዚው ጋር በተያያዘ የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ከግቢው ለቀን እንወጣለን ቢሉም ዩንቨርስቲው መከልከሉን ተከትሎ ተማሪዎች በአጥር ዘለው መውጣታቸውን ሰምተናል።

#ወልዲያ_ዩንቨርስቲ

ተማሪዎች ዛሬ ወደ ቤታችን መልሱን እያሉ ይገኛሉ ግቢው በመከላከያ እየተጠበቀ ይገኛል። የፊታችን ሰኞ ትምህርት እንደሚጀመር ዩንቨርስቲው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ገልፅዋል።

#አዳማ_ሳይንስ_እና_ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ

አዳማ ዩንቨርስቲ የፊታችን ሰኞ Mid Exam ይጀምራል ብሏል ነገር ተማሪዎች ትምህርት ካቆሙ አንድ ሳምንት አልፏቸዋል፤ ተማሪዎቹ ግን ስጋት ውስጥ ሆነን ስለ ትምህርታችን እናስብ ወይስ ስለ ህይወታችን በማለት ዩንቨርስቲ ያወጣውን የፈተና ፕሮግራም ኮንነዋል።

#ደብረብርሀን

እንደሚታወቀው ደብረብረሀን ዩንቨርስቲ ዛሬ የአንድ ተማሪ ህይወት አልፏል። ከዚህ ክስተት በኋላ ግን ዩንቨርስቲው ሰላም መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።ነገር ግን ተማሪዎች እንደነገሩን ከሆነ ነገ ምንም እንደሚከሰት መገመት አንችልም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነን ብለውናል።
_______________________________
በዚህ መሰረት ችግር የሚታይባቸው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ዩንቨርስቲዎች መሆናቸው ለማወቅ ችለናል ነገር ግን ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ችግር ባይኖርም የተበተነው መረጃ ተማሪዎች ላይ ስጋት ጥሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ጥብቅ ማሳሰቢያ ❗️

ለሀዋሳ ዩንቨርስቲ መምህራንና ተማሪዎች በሙሉ

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ከቀን 08/03/12 ጀምሮ ትምህርት እንደሌለ ምንጩ #ያልተረጋገጠ መልዕክት በመተላለፉ ምክንያት እንዳንድ ተማሪዎች #ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

ነገር ግን ከዩንቨርቲው ዕውቅና ውጪ ስለሆነ ሰላማዊ መማር ማስተማር ላይ የተፈጠረ ምንም ዓይነት ችግር ባለመኖሩ የተለመደወ መማር ማስተር ሂደት የሚቀጥል መሆኑን እየገለጵን። የፊታችን ረቡዕ እለት ብቻ ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በተላለፈው መልክት መሰረት ትምህርት የማይኖር መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

#ሀዋሳ ዩንቨርስቲ

@Yenetube @Fikerassefa