YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አለመረጋጋት ዛሬም መቀስቀሱን ሰምተናል ተማሪዎች እንደገና ፍርኃት ውስጥ ገብተዋል።

#jimma university

ጅማ ዩንቨርስቲው ላይ ምንም አይነት ችግር ባይኖርም ተማሪዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ለየኔቴዩብ ተናግረዋል። በቤተክርስቲያን ውስጥም የተጠለሉ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።

#Hawassa

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ በወልድያ ዩንቨርስቲ በተከሰተው የተማሪዎች ሞትን ለማውገዝ ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቢሞክሩም እርስ በእስር ባለመግባታ መጠነኛ ግርግር መነሳቱን ስምተናል። እንዲሁም አሁን ላይ ዩንቨርስቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደቀጠለ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

#Adama

አዳማ ዩንቨርስቲ ያለፉትን ሶስት ቀናት ተማሪዎች ትምህርት ገበታቸው ላይ አልተገኙም፣ ነገር ግን ዩንቨርስቲው ከነገ ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ አሳስቧል። ያናገርናቸው ተማሪዎች ለህይወታችን እንሰጋል ሀላፊነት የሚወስድ አካል በሌለበት ወደ ትምህርት ገበታችን ላይ ለመመለስ ይከብደናል ብለውናል።
እንዲሁም የማስተርስ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በትክክል እየተከታተሉ መሆኑን አሳውቀውናል።


#bulehora_university

ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ትላንትና ዕለት ዋዜማ ሚዲያ 10 ተማሪዎች መቁሰላቸውን የዘገበ ቢሆንም ባደረግነው የማጣራት ስራ ምንም አይነት ችግር አለመኖሩን ለማወቅ ችለናል።

@Yenetube @Fikerassefa