YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ህወሓት 44ኛ ምስረተ በዓል ‼️

የህወሓት 44ኛ የምስረታ በዓል የትግልና ድል ጉዞ የምንዘክርበት ብቻ ሳይሆን ለነገ #ትምህርት #የምንወስድበትም ነው- የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ

የህወሓትን 44ኛ የምስረታ በዓል የካቲት 11 ምክንያት በማድረግ የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ፥ በዓሉ የትግልና ድል ጉዞ #የምንዘክርበት ብቻ ሳይሆን ለነገ ትምህርት የምንወስድበት ቀን ነው ብሏል።

ህወሓት ከ44 ዓመት በፊት ትግል ሲጀምር በሀገሪቱ የነበረው ፍፁም ፀረ #ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በመገርሰስ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በእኩልነት የሚኖርባት ዴሞክራሲያዊት #ኢትዮጵያን ለመፍጠር አላማ ያነገበ እንደነበርም መግለጫው አስታውቋል።

በ17 #የትጥቅ ትግል አመታት ለመገመት የሚያስቸግር የህይወት፣ አካልና ንብረት መስዋእት መከፈሉን ያስታወሰው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ፥ በዚህም ኢትዮጵያን ከመበታተን በማዳን ባለፉት 27 ዓመታት ወደ አዲስ የልማትና #የዴሞክራሲ ምዕራፍ መሸጋገር መቻሉን ገልጿል።

ከብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ በመሆን በተደረገው ትግል የኢትዮጵያ ህዝቦች በሀገራዊ ጉዳዮች በእኩልነት የሚወስኑበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ መፈጠሩም አንስቷል።

በዚህም መሰረት “የህወሓት 44ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ስናከብር ባለፉት አመታት የተመዘገቡትን ድሎች በመያዝ ሀገራችን ባለፉት 27 አመታት የጀመረችው የለውጥ፣ ሰላምና ብልፅግና ጉዞ ወደኋላ እንዳይመለስ አጠናክረን ለመስራት ቃል በመግባት ነው” ብሏል።

የትናንት ወጣቶች ለህዝቦች ነጻነት፣ ሰላም መረጋገጥና እኩልነት ሲሉ ለፈጸሙት ጀግንነትና ለከፈሉት መስዋእትነት ዘላአለማዊ ክብር ይገባቸዋል ያለው ኮሚቴው፥ ለህዝቦች ነጻነት፣ እኩልነትና ሰላም መረጋገጥ ሲሉ በጀግንነት ያለፉት ታጋዮችን ከድህነት የማውጣት አላማን ከግብ ለማድረስ ዛሬም እንደ ትናንቱ በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የሰላም እጦቶችን በመቅረፍ፥ የህዝብ በተለይም የወጣቱን መሰረታዊ የልማትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በመመለስ የተጀመረውን የተሃድሶ ጉዞ ማሰቀጠል እንደሚገባም ገልጿል።

የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዋስትና የሆነው የኢፌዴሪ ህገ መንግስትና ፌዴራላዊ ስርዓት በመጠበቅ የህግ የበላይነት እንዲከበር ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግም መግለጫው አሳስቧል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ለወንድም ኤርትራ ህዝብ ባስተላለፈው መልእክት፥ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰስ በትጥቅ ትግሉ ሁለቱም ህዝቦች አብረው መታገላቸውና መስዋእት መክፈላቸውን አንስቷል።

የደርግ ስርአት ከወደቀ በኋላም ህወሓት የኤርትራን ህዝብ ውሳኔን በመደገፍ ከህዝቡ ጎን መሰለፉን በመግለፅ፥ በአሁኑ ወቅት ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ትግልም ከኤርትራ ህዝብ ጎን እንደሚሰለፍ አረጋግጧል።

ባለፉት 20 አመታት በማያስፈልግ ጦርነት ቆይተናል ያለው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ፥ የነበረው ሁኔታም በሁለቱም ወንድም ህዝቦች ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ማለፉን ገልጿል።

ይሁን እንጂ አሁን በተከፈተው አዲስ የሰላምና የወንድማማችነት ምዕራፍ በመጠቀም ተደጋግፈን ወደ ብልፅግና ልንጓዝ ይገባል ብሏል።

በዚህ ጉዞ ሁለቱም ህዝቦች ተጠቃሚ ማድረግ ስለሚቻል፥ ይህን እውን ለማድረግም የትግራይ ህዝብና መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ በማለትም አረጋግጧል።

የህወሓት 44ኛ የምስረታ በዓል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት በተለያዩ ሁነቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
⬇️ኮሜንት መስጠት ከፈለጉ ⬇️
የአውሮፓ ህብረት #ኢትዮጵያን_ጨምሮ_ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ድርቅ ተጎጅዎች የ50 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ይፋ አደረገ፡፡

ድጋፉ በቀጠናው የድርቅ ተጎጂዎች ለሆኑ እንሰሳት አርቢዎች፣ ዘላኖች እና ምርታቸው ከእጅ ወደ አፍ ለሆነ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ድጋፍ እንደሚውል ተነግሯል፡፡
@Yenetube @FikerAssefa
#update

#ኢትዮጵያን_ከኤርትራ የሚያገናኘው የየብስ መንገድ በአዲስ ዓመት ይመረቃል።

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በየብስ የሚያገናኛትን ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አጠናቃ፣ በመጪው መስከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም እንደምታስመርቅ ተገለጸ፡፡ ባለፈው አመት ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ የተጀመረው የ90 ኪ.ሜትር የመንገድ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ መጠናቀቁን የዘገበው ኤርትሪያን ፕሬስ፤ ቀሪው 10 በመቶ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል ብሏል፡፡ ኤርትራን ከኢትዮጵያ በየብስ እንደሚያገናኝ የተነገረለት ይኼው መንገድ፤ ቀደም ሲል በ6 ሜትር ስፋት የተሰራ ሲሆን አሁን በተደረገው ማሻሻያና ተጨማሪ ግንባታ፣ በእጥፍ ጨምሮ፣ ከ12 እስከ 20 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጓል፤ 25 አዳዲስ ድልድዮችም ተገንብተዋል ተብሏል፡፡

በሁለቱ አገራት ግንኙነት ላይ ወሳኝ ሚና እንዳለው በሚነገርለት በዚህ የመንገድ ግንባታ ላይ በርብርብ የተሳተፉት 5 የኤርትራ የመንገድ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን ጨምሮ የአገሪቱ መከላከያ ሀይል መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡የመንገዱ እድሳትና ግንባታ አንድ አመት የፈጀ ሲሆን ሙሉ ወጭው በኤርትራ መንግስት መሸፈኑ ታውቋል፡፡ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የመንገድ ግንባታው በአዲሱ ዓመት መስከረም 1 እንደሚመረቅና አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡

Via አዲስ አድማስ
@YeneTube @FikerAssefa
ለማስታወስ ያክል

የካቲት 14/2012 ከቀኑ 10 ሰዐት ጀምሮ #ኢትዮጵያን_ወደ_ፍቅር የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ነገ ይካሄዳል።
@YeneTube @Fikerassefa
#ቱርክ ሶተኛው ዙር ንግግር ከመደረጉ በፊት #ኢትዮጵያን እና #ሶማሊያን በተናጠል ልታነጋግር መሆኑን ገልጸች

ቱርክ በ #ኢትዮጵያ እና #ሶማሊያ መካከል ሶተኛው ዙር ንግግር ከመደረጉ በፊት ሁለቱም አገራት ጋር በተናጠል ልታነጋግር ማቀዷን የቱርክየ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊዳን ሃካን ተለጹ።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባር በር ስምምነት መፈጸሟን ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት በቱርክ አመቻችነት ሁለት ዙር ንግግር ተደርጓል።

ማክሰኞ ዕለት በአክራ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ሶስተኛው ዙር ንግግር ቀኑ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጋር በመገጣጠሙ መራዘሙ ይታወቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፊዳን፤ ቱርክየ የሁለቱን አገራት ሚንስትሮችን እና መሪዎች ለማነጋገር እየጣረች መሆኑን ለአናዶሉ ገልጸዋል። በአንካራው ንግግር ወቅት ሁለቱ አገራት “በተወሰኑ ነጥቦች መቀራረብ” በመቻላቸው ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ ሊገኝ እንደሚችል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቱርክ ካለፉት ሁለት ዙር ንግግሮች ልምዶች በመነሳት ሁለቱን አካላት በአንድ ላይ ከማነጋገር ይልቅ ብቻ ለብቻ በማነጋገር የጋራ አስማሚ ነጥብ ላይ ሲደርሱ ለማገናኘት ማቀዷን ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍82