YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ትናንት ምሽት ከ#አዳማ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የስደተኞች ሰፈራ ጣቢያ በደረሰው ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል ወደ ሀያ የሚሆኑ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
#አዳማ

በአዳማ  ተፈናቃዮች በሰፈሩበት አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ ዘጠኝ ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ከተያዙት ግለሰቦች መካከል  አራቱ ከተፈናቃዮቹ ሲሆኑ አምስቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው።

የግጭቱ መንስኤ ተፈናቃዮች በአካባቢው የግንባታ ድንጋይ ለማውጣት ከተሰማሩ ግለሰቦች ጋር ከስራው ጋር በተያያዘ ባለመግባባት በተነሳ ፀብ እንደሆነ የከተማው አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነተ  ባለሙያ ሳጅን ወርቅነሽ ጋልሜቻ ገልጸዋል።

በወቅቱ በተፈጠረው ችግር የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ጠቁመው 18 ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውሰዋል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
በ#ቄሮ ስም ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉት ግለሰቦች ተይዘዋል

በአሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በቄሮ ስም ወንጀል ፈፅመዋል በተባሉ ከ170 በላይ በሚሆኑ ግለሰቦች ላይ የክልሉ መንግስት ርምጃ መዉሰዱ ተገለፀ። ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የክልሉ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

የፌስቡክ ዘገባው ነሃሴ 6 ቀን 2010 ዓ/ም በሻሻማኔ ከተማ አቶ ጃዋር መሐመድን ለመቀበል በተሰናዳ መርኃ-ግብር ላይ በአንድ ወጣት ላይ በተፈፀመው ግድያ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተካሄደባቸዉ እንደሆነም ገልጿል።

ሰሞኑን በ#አዳማ ከተማ የተፈጠረዉ ግጭት የብሔር መልክ እንድይዝ ሰዎችን ሲያነሰሱ ነበር የተባሉ ስምንት ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ፅህፈት ቤቱ አስታዉቋል።

በ#ሱሉልታ በ#ቄሮ ስም የግለሰብ ቤት የጣሪያ ቆርቆሮ ሲነቅሉ የተያዙና በቡራዩ እንዲሁም በለጋ-ጣፎ ለጋ-ዳዲ ከተሞች የ#ቄሮ መሪ ነኝ በማለት የዉሸት መታወቂያና ሌሎች ሰነዶች ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብም በቁጥጥር ስር መዋላቸዉም ተዘግቧል።

በተመሳሳይም በጅማና በሰበታ ከተማ በሕገ-ወጥ ስራና ግንባታ ላይ የተሰማሩ 56 ሰዎች በቁጥጥር ስረ መዋላቸዉን የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ገልፀዋል።
©DW
@Yenetube @Fikerassefa
⬆️⬆️የሰብአዊ መብት ተሟጋች #አክቲቪስት አርቲስት ታማኝ በየነ ዛሬ በአዳማ ከተማ #አዳማ ስታድየም አቀባበል #እየተደረገለት ነው፡፡

የአደማ ከተማ ነዋሪዎች አርቲስት ታማኝ በየነን አቀባበል እያደረጉለት ነው፡፡
©AmmA
@yenetube @mycase27
ዩንቨርስቲዎቻችን እንዴት ሰነበቱ ??

#ሀዋሳ_ዩንቨርስቲ

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዘንድ በማን እንደተሰራጨ ለጊዜው ባልታወቀ አካል ተማሪዎች የሚያሸብር ፁሁፍ በብሄር ተከፍሎ ለሁለት ወገን ብቻ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል።

ይህ መረጃ ከተሰራጨበት ሰዐት አንስቶ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ተማሪዎች ለየኔቲዩብ ተናግረዋል።

#ድሬደዋ_ዩንቨርስቲ

የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ተማሪ ከፎቅ ወድቆ ሞተ የሚል ዜና ዩንቨርስቲው በፌስቡክ ገጹ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ተማሪዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ነግረውናል።

ከዚው ጋር በተያያዘ የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ከግቢው ለቀን እንወጣለን ቢሉም ዩንቨርስቲው መከልከሉን ተከትሎ ተማሪዎች በአጥር ዘለው መውጣታቸውን ሰምተናል።

#ወልዲያ_ዩንቨርስቲ

ተማሪዎች ዛሬ ወደ ቤታችን መልሱን እያሉ ይገኛሉ ግቢው በመከላከያ እየተጠበቀ ይገኛል። የፊታችን ሰኞ ትምህርት እንደሚጀመር ዩንቨርስቲው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ገልፅዋል።

#አዳማ_ሳይንስ_እና_ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ

አዳማ ዩንቨርስቲ የፊታችን ሰኞ Mid Exam ይጀምራል ብሏል ነገር ተማሪዎች ትምህርት ካቆሙ አንድ ሳምንት አልፏቸዋል፤ ተማሪዎቹ ግን ስጋት ውስጥ ሆነን ስለ ትምህርታችን እናስብ ወይስ ስለ ህይወታችን በማለት ዩንቨርስቲ ያወጣውን የፈተና ፕሮግራም ኮንነዋል።

#ደብረብርሀን

እንደሚታወቀው ደብረብረሀን ዩንቨርስቲ ዛሬ የአንድ ተማሪ ህይወት አልፏል። ከዚህ ክስተት በኋላ ግን ዩንቨርስቲው ሰላም መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።ነገር ግን ተማሪዎች እንደነገሩን ከሆነ ነገ ምንም እንደሚከሰት መገመት አንችልም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነን ብለውናል።
_______________________________
በዚህ መሰረት ችግር የሚታይባቸው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ዩንቨርስቲዎች መሆናቸው ለማወቅ ችለናል ነገር ግን ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ችግር ባይኖርም የተበተነው መረጃ ተማሪዎች ላይ ስጋት ጥሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
በአማራ ክልል በ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በተፈጸመ ጥቃት 27 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን #ጂሌ_ጥሙጋ ወረዳ፤ ከየካቲት 30፣ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጸመ “የተቀናጀ ጥቃት” 27 ነዋሪዎች መገደላቸውን እና ከ40 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።
ጥቃቱ በጂሌ ጥሙጋ ወረዳ በሚገኙ ከ20 በላይ ቀበሌዎች እንደተፈፀመ ተገልጿል።

“በጥቃቱ ህጻናት፣ እረጋውያን እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። በተጨማሪም መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ንብረቶች ወድመዋል” ሲል ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

እስከ ዛሬ ቀጥሏል በተባለው ግጭት ጉዳት ከደረሰባቸው 40 ሰዎች ውስጥ 20 የሚሆኑት ወደ አዲስ አበባ መንገድ ዝግ በመሆኑ በ #አፋር ክልል አቋርጠው በ #አዳማ ከተማ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ የለን፣ዋጮ፣ነገሶ እና ሞላሌ በሚባሉ ቀበሌዎች ከብሄረሰብ ዞኑ የመጡ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል።

ስምንት ሰዎች ሞተዋል፣ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል። ከ300 በላይ ከብቶች ወደ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞኑ ተወስደዋል ሲሉ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አጣዬ ዙሪም ዛሬ ተመሳሳይ ግጭት አለ ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭19👍176👏4😁1
#ከአዲስ አበባ ወደ #አዳማ ማንኛውም መልዕክት ይላኩ ይቀበሉ

22 ጎላጎል አከባቢ ኳሊቲ ህንፃ

ስልክ :- 0980526262

@addisexpressdelivery
👍131