ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የኢትዮጵያ መንግስት በሶማሌ ክልል ለዓመታት ሲፈጸሙ በቆዩ የመብት ጥሰቶች እና ህገወጥነቶች ላይ ምርመራ ለማካሄድ ቁርጠኛ መሆን አለበት" ሲል አሳሰበ።
የምርመራ ሂደቱ የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት #አብዲ መሀመድ ዑመር እና አሁንም የክልሉ ልዩ ፖሊስ ኃላፊ የሆነውን #አብዱራህማን አብዱላሂ ቡረሌን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ሚና በጥልቀት የሚመረምር መሆን እንዳለበትም ጠቁሟል።
ተቋሙ በመግለጫው "የኢትዮጵያ መንግስት፣ በዓለምአቀፉ ህግ መሰረት የጦር ወንጀል የፈጸሙ የመከላከያ አባላትን እና ግለሰቦችን መርምሮ ለህግ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
የሰብአዊ ወንጀል እና ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ግለሰቦች በይቅርታ ሊታለፉ አይገባም" ብሏል።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27

በሽሽት ላይ የነበሩ የሶማሌ ክልል ሁለት ባለስልጣናት ሶማሊላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የሶማሊላንድ ፖሊስ እንዳስታወቀው የኢትዮ ሶማሊ ክልል የፍትህ ቢሮ ሀላፊ #አብዲ ጃማ እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ #ኢብራሒም አደን መሀድ ሀርጌሳ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ እጅ ይገኛሉ።
ሁለቱ ሀላፊዎች የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በፌደራል መንግስት ሀይሎች መያዛቸውን ተከትሎ ከጅጅጋ ወደ ጎረቤት ሶማሊላንድ እንደሸሹ ጋሮዌ የተባለው የሶማሊላንድ ጋዜጣ ዘግቧል።
*በሌላ በኩል ለዓመታት በስደት የቆዩት የሶማሌ ክልል የመብት ተሟጋቾች የቀድሞ የፓርላማ አባል መሀመድ ድርዬ እና የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌ አማካሪ አብዱላሂ ሁሴን ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። በሶማሌና ኦሮሞ ማህበረሰብ መካከል የነበረውን ግጭት ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል። ለውጡን ለመደገፍም መዘጋጀታቸውን ነግረውናል።

Update #አብዲ ኢሌ⬇
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው እለት ባካሄደው አስቸኳይ የአቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወሳል።
መነሳቱንም ተከትሎ ዛሬ አዲስ አበባ አትላስ ከሚገኘው ቤቱ መያዙ ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa

#update አቶ አብዲ መሐመድ
የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ከእስር ቤት መስኮት ሰብረው #ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ፖሊስ ገለጸ።
አቶ አብዲ መሐመድ ከሐምሌ 26 ቀን እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ፥ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሳቢያ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
አቶ አብዲ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀጠሮ ችሎት በቀረቡበት ወቅት፥ ለደህንነታቸውና ለጤናቸው ሲባል የፖሊስ ቢሮ ውስጥ ታስረው መቆየታቸውን ፖሊስ ገልጿል።
ይሁንና አቶ #አብዲ የታሰሩበትን ቢሮ መስታወት በመስበርና አንድ የጥበቃ አባልን ጉሮሮ በማነቅ ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ብሏል ፖሊስ #በማብራሪያው።
አቶ አብዲ መሐመድ በበኩላቸው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን በመጥቀስ፥ ሆን ተብሎ ስሜን ለማጥፋትና እኔን ለመምታት የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል።
ድርጊቱን ፈጽመዋል መባሉ ውሸት መሆኑንና በእርሳቸው ላይም ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው እንደሆነም ተናግረዋል።
ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታሳሪ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነታቸው ላይ ስጋት እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል።
በአንድ አጋጣሚም አንድ እስረኛ የሽንት ቤት በር ገንጥሎ እሳቸው ላይ በመጣል ጉዳት ሊያደርስ መሞከሩንም ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።
የታሰሩበት እስር ቤትም የማይመችና በጤናቸው ላይ እክል እንደፈጠረባቸውም ነው አቶ አብዲ የተናገሩት።
መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ አቶ አብዲ መሐመድ ማንኛውም እስረኛ በሚቆይበት እስር ቤት እንደታሰሩ ጠቅሶ፥ በእርሳቸው ላይ ምንም አይነት ጫና አለመደረጉን ገልጿል።
በተጨማሪም ፖሊስ ከእርሳቸው ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ለግጭቱ መቀስቀስ ተጠያቂ መሆናቸውንና በዚህም ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸውንም አስረድቷል።
ፖሊስ በአብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው #ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም ምርመራውን እያካሄደ ያለው ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ይዞ እንዲቀርብ በማሳሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#update አብዲ መሐመድ
ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ #አብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ #ፈቀደ።
በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሃመድ ዑመር ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የፈቀደው።
ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ መሐመድ ላይ የ10 ቀን ምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ይታወሳል ።
በዚህም መሰረት መርማሪ ፖሊስ ከሃምሌ 26 ቀን እስከ 30 /2010 ዓ/ም በሱማሌ ክልልና በአካባቢው #በተፈጸመው ወንጀል ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን ምስክሮች ቃል መቀበሉን፣30 ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና ማስረጃ ማሰባሰቡን፣የ62 ሰዎች የጉዳት መጠንን ማስረጃ #በአማረኛ ማስተርጎሙን ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል።
በተጨማሪም #ለኤጎ ቡድን ለወንጀሉ መፈጸሚያ የዋለውን ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣ የገንዘብ መጠን እና የገንዘቡ 16 ገጽ የኦዲት ማስረጃ ማምጣቱን እና በንግድ ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚገልጽ 35 ገጽ ማስረጃ ማቅረቡን ለችሎቱ #አስረድቷል።
በሌላ በኩል ፖሊስ #በኦሮሚያና ሱማሌ ክልል ጠረፍ አካባቢ 200 ግለሰቦች መገደላቸውን ፥በቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #አብዲ መሃመድን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ላይ በሚደረግ ምርመራ #ማግኘቱን ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል።
በመቀጠልም ፖሊስ ቀረኝ ያለውን በጅምላ የተቀበሩ 200 በላይ ግለሰቦች አስከሬን መለየትና የዚህን ድርጊት መፈጸም የሚያረጋገጡ #ምስክሮች ቃል ለመቀበል፥እንዲሁም በተለያዩ ዞኖች ጉዳት የደረሰባቸው 37 ግለሰቦች ማስረጃ ተርጉሞ ለማምጣት እና ለወንጀሉ ተግባረ የዋለ ገንዘብና መሳሪያን ለመያዝና ሌሎች ስራዎችን ለማከናወን 14 ቀን ጊዜ ይፈቀድልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን #ጠይቋል።
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ያቀረበው የምርመራ ስራ ተመሳሳይ በመሆኑና፥የሚያቀርበው ምክንያትንም አግባበነት የሌለውና የተጠርጣሪዎችን አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብትን የሚጎዳ ነው #ብለዋል ።
ሰለሆነም ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው አደረሱት የተባለው ጉዳት መጠን በተናጠልና #በዝርዝር ሊቀርብ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በተጨማሪም #በኦሮሚያና ሱማሌ ጠረፍ 200 ሰው ተገደለ የተባለው አዲስ ምርመራ በመሆኑ ፥ለብቻው ተነጥሎ ሊታይ ይገባል ሲሉ የፖሊስን ምርመራ በምክንያት #ተቃውመዋል።
ፖሊስ በበኩሉ 200 አዲስ ሰዎች ተገደሉ የተባለው በዚሁ ምርመራ ሲከናወን የተገኘ በመሆኑ አንድ ላይ ሊካተት ይገባል ሲል ፍርድ ቤቱን #ጠይቋል።
ሰለሆነም ከወንጀሉ ከባደና ውስብስበነት አንጻር ተጨማሪ 14 ቀን መጠየቄ አግባበ ነው ሲል ምላሽ #ሰጥቷል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ምርመራው #በአጭር ጊዜ ሊከናወን የማይችል በመሆኑ እና ከወንጀሉ ከባድና ውስብስብነት አንጻር ፖሊስ የ 14 ቀን ጊዜ መጠየቁ ትክክል ነው ብሏል።
በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የምርመራ ስራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለህዳር 13 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ #ሰጥቷል።
ምንጭ ፦ኤፍ.ቢ.ሲ

#በነብስና_ንብረት_ማስጠፋት ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሠ መስተዳድር #አብዲ_መሐመድ_ዑመርና ሌሎች ባለስልጣናት ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት #ዉድቅ አደረገዉ።ይሁንና ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት በአንደኛ ተከሳሽ አብዲ መሐመድ እና በ43ኛ ተከሳሽ ሐኒ መሐመድ የተመሠረተዉ ክስ እንዲሻሻል በይኗል።
ችሎቱ እንደወትሮዉ ለጋዜጠኞች ክፍት ቢሆንም ጋዜጠኞች ሒደቱን ሳያዘቡ እንዲዘግቡ የመሐል ዳኛዉ ያልተለመደ ማስጠንቀቂያ ብጤ ሰጥተዋል።
@YeneTube @FikeAssefa