YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#እስካሁን 930 ሺህ 150 የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቄያቸው ተመልስዋል፦ኮሚሽኑ

በሀገሪቱ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 930 ሺህ 150 ገደማ ሰዎች ወደ ቄያቸው መመለስ መቻሉን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር #ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በተለያዮ ጊዜያት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት አያሌ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለው ለእንግልት #መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡

ግጭቶቹም በዋናነት #በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል፣ በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ፣ :በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ባሉ አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም በሶማሊያ ክልልና በቡራዮ ከተማ #የተከሰቱ ናቸው፡፡

በእነዚህም ግጭቶች ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 930 ሺህ 150 ገደማ ሰዎች ወደ ነበሩበት አካባቢ መመለስ መቻሉን በብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ #ደበበ ዘውዴ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃዮቹንም ለመደገፍ መንግስት አስቸኳይ እርዳታ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ለተፈናቃይ ዜጎች የሚደረገው የድጋፍ ጥረት የተለያዮ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙም ችግሮቹን ለመፍታት #ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ዳይሬክተሩ፡፡

መንግስት ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ተፈናቃይ ዜጎችን የማቋቋም ስራ እየሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

ይህም ስራ የሚሰራው ተፈናቃዮቹ ካጋጠማቸው አደጋ የሚያገግሙበት ድጋፍ በመስጠትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በመፍጠር መሆኑን አቶ #ደበበ ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃይ ዜጎች ወደ ነበሩበት አካባቢ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የሚያነሱትን የፀጥታ ስጋት ለማስወገድ የፀጥታ አካላትንና ባህላዊ የሰላም ማስፈኛ መንገዶችን በመጠቀም እየተሰራ ነው #ብለዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት በሀገሪቱ በተከሰተ ግጭት በደረሰ መፈናቀልና በድርቅ 8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸውን ከብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ ፦ኢቢሲ
@YeneTube @Mycase27
#update አብዲ መሐመድ

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ #አብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የ14 ቀን  ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ #ፈቀደ

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሃመድ ዑመር ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የፈቀደው።

ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ መሐመድ ላይ የ10 ቀን ምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ይታወሳል ።

በዚህም መሰረት መርማሪ ፖሊስ ከሃምሌ 26 ቀን እስከ 30 /2010 ዓ/ም በሱማሌ ክልልና በአካባቢው #በተፈጸመው ወንጀል ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን ምስክሮች ቃል መቀበሉን፣30 ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና ማስረጃ ማሰባሰቡን፣የ62 ሰዎች የጉዳት መጠንን ማስረጃ #በአማረኛ ማስተርጎሙን  ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል።

በተጨማሪም #ለኤጎ ቡድን ለወንጀሉ መፈጸሚያ የዋለውን ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የወጣ የገንዘብ መጠን እና የገንዘቡ 16 ገጽ የኦዲት ማስረጃ ማምጣቱን እና በንግድ ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚገልጽ 35 ገጽ ማስረጃ  ማቅረቡን ለችሎቱ #አስረድቷል

በሌላ በኩል ፖሊስ #በኦሮሚያና ሱማሌ ክልል ጠረፍ አካባቢ 200 ግለሰቦች መገደላቸውን ፥በቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #አብዲ መሃመድን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ላይ በሚደረግ ምርመራ #ማግኘቱን ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል።

በመቀጠልም ፖሊስ ቀረኝ ያለውን በጅምላ የተቀበሩ 200 በላይ ግለሰቦች አስከሬን መለየትና የዚህን ድርጊት መፈጸም የሚያረጋገጡ #ምስክሮች ቃል ለመቀበል፥እንዲሁም በተለያዩ ዞኖች ጉዳት የደረሰባቸው 37 ግለሰቦች ማስረጃ ተርጉሞ ለማምጣት እና ለወንጀሉ ተግባረ የዋለ ገንዘብና መሳሪያን ለመያዝና ሌሎች ስራዎችን ለማከናወን 14 ቀን ጊዜ  ይፈቀድልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን #ጠይቋል

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ያቀረበው የምርመራ ስራ ተመሳሳይ በመሆኑና፥የሚያቀርበው ምክንያትንም አግባበነት የሌለውና የተጠርጣሪዎችን አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብትን የሚጎዳ ነው #ብለዋል

ሰለሆነም ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው አደረሱት የተባለው ጉዳት መጠን በተናጠልና #በዝርዝር ሊቀርብ  ይገባል በማለት ተከራክረዋል።

በተጨማሪም #በኦሮሚያና ሱማሌ ጠረፍ 200 ሰው ተገደለ የተባለው አዲስ ምርመራ በመሆኑ ፥ለብቻው ተነጥሎ ሊታይ ይገባል ሲሉ የፖሊስን ምርመራ በምክንያት #ተቃውመዋል

ፖሊስ በበኩሉ 200 አዲስ ሰዎች ተገደሉ የተባለው በዚሁ ምርመራ ሲከናወን የተገኘ በመሆኑ አንድ ላይ ሊካተት ይገባል ሲል ፍርድ ቤቱን #ጠይቋል

ሰለሆነም ከወንጀሉ ከባደና ውስብስበነት አንጻር ተጨማሪ 14 ቀን መጠየቄ አግባበ ነው ሲል ምላሽ #ሰጥቷል

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ምርመራው #በአጭር ጊዜ ሊከናወን የማይችል በመሆኑ እና ከወንጀሉ ከባድና ውስብስብነት አንጻር ፖሊስ የ 14 ቀን ጊዜ መጠየቁ ትክክል ነው ብሏል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የምርመራ ስራውን  አጠናቆ እንዲቀርብ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለህዳር 13 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ #ሰጥቷል
ምንጭ ፦ኤፍ.ቢ.ሲ
@yenetube @mycase27