YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሽሽት ላይ የነበሩ የሶማሌ ክልል ሁለት ባለስልጣናት ሶማሊላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሶማሊላንድ ፖሊስ እንዳስታወቀው የኢትዮ ሶማሊ ክልል የፍትህ ቢሮ ሀላፊ #አብዲ ጃማ እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ #ኢብራሒም አደን መሀድ ሀርጌሳ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ እጅ ይገኛሉ።

ሁለቱ ሀላፊዎች የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በፌደራል መንግስት ሀይሎች መያዛቸውን ተከትሎ ከጅጅጋ ወደ ጎረቤት ሶማሊላንድ እንደሸሹ ጋሮዌ የተባለው የሶማሊላንድ ጋዜጣ ዘግቧል።

*በሌላ በኩል ለዓመታት በስደት የቆዩት የሶማሌ ክልል የመብት ተሟጋቾች የቀድሞ የፓርላማ አባል መሀመድ ድርዬ እና የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌ አማካሪ አብዱላሂ ሁሴን ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። በሶማሌና ኦሮሞ ማህበረሰብ መካከል የነበረውን ግጭት ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል። ለውጡን ለመደገፍም መዘጋጀታቸውን ነግረውናል።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27