YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ከዘጠኝ ሀገራት የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመጎብኘት ላይ #ይገኛሉ

የኢንዱስትሪ ፓርኩን ከዘጠኙ የውጭ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተውጣጡ 32 ተወካዮች ናቸው እየጎበኙ የሚገኙት።

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ፥ ለጎብኚዎቹ ስለ አጠቃላይ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ማብራሪያ #ሰጥተዋል

በማብራሪያቸውም የኢንዱስትሪ ፓርኩ ስለ ፈጠረው የስራ እድል፣ የወጪ ንግድ መር ስለመሆኑ እንዲሁም የኢትዮጵያን ወደ ኢንዱስትሩ ሽግግር ያረጋግጣል ተብው ከሚጠበቁ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከማብራሪያው በመቀጠልም ፓርኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች፤ በተለየም የውሃ ማከሚያ ተቋሙ እና አንድ የተመረጠ ፋብሪካን ይጎበኛሉ።

የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ በትናንትናው እለት በተጀመረው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በግንግድነት ተጋብዘው የመጡ ናቸው

የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ የጅብቲው ገዥ ፓርቲ አር ፒፒ፣ የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ ሲፒሲ፣ የኬንያው ገዥው ፓርቲ ጁብሊ፣ ሩዋንዳው ገዥ ፓርቲ አርፒኤፍ፣ የጀርመን የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ፣ የሱዳን፣ ታንዛኒያ የደቡብ አፍሪካ እና የታንዛኒያ ፖለቲካ ፓርቲ #ናቸው
©fbc
@yenetube @mycase27
#update ቤኒሻንጉል ክልል ⤵️⤵️

#ከቤኒሻንጉል ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል እርዳታ የጫኑ 9 መኪኖች በጸጥታ ችግር #ምክንያት ወደ ካማሺ ዞን መንቀሳቅስ አልቻሉም ተባለ።

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአሶሳ ከተማ ቆመው የሚገኙት እኒህ መኪኖች 2, 358 ኩንታል ስንዴ፣ በቆሎና የተለያዩ አልሚ ምግቦችን የጫኑ #ናቸው

የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከቤኒሻንጉል የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮና ከመከላከያ ጋር በመተባበር መኪኖቹን ወደ ቦታው ለማንቀሳቀስና ወደ ተፈናቃዮቹ ለማድረስ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።

በተያያዝ ዜናም የቤኒሻንጉሉን ግጭት የሚያጣራው ኮሚሽንም በመንገድ መዘጋት ምክንያት ስራ አለመጀመሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን #አስታውቋል

የደረሰውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማጣራት የተቋቋምው ኮሚቴ ወደ ቦታው ለመደረስ አለመቻሉን የኮሚሽኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ሃላፊ ኮሚሽነር ዶክተር #አታክልቲ ገብረህይወት አስታውቀዋል።

ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ምርመራውን #እንደሚጀምርም ጨምረው ተናግረዋል።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27
#update
አቶ #እንደሻው ጣሰው የቀድሞው ኮሚሽነር አቶ #ዘይኑ ጀማል የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ፥ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አቶ እንደሻው ከ1983 እስከ 1992 ዓ.ም ድረስ #በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከመምህርነት እስከ ክፍለ ጦር አመራርነት በትምህርቱ ዘርፍ አገልግለዋል።

ከዚያም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች በትጋት የህዝብንና የመንግስትን ሃላፊነት ሲወጡ የቆዩ #ናቸው

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ #በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባው #የህዝብ ግንኙነት አማካሪ እና የአዲስ አበባ ከተማ #ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነውም አገልግለዋል።

በትምህርታቸውም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን #በጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በውጭ ሃገር ተከታትለው #በከፍተኛ ውጤት አጠናቀዋል።
ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27
#በሰሜን ሸዋ ዞን የሸኖ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ #ተሾመ ሙሉጌታን ጨምሮ 26 ተከሳሾች እስከ 8 ዓመት የሚደርስ እስራትና በገንዘብ #ተቀጡ

ተከሳሾቹ ያለአግባብ 60 ሺህ 556 ካሬ ሜትር መሬት በመሸንሸን ከ12 በላይ ለሚሆኑ ባለሀብቶች በመስጠት እና በመቀበል ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም በሙስና ወንጀል ነው የተከሰሱት።

የቅጣት ውሳኔውን #የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው የበየነው።

አንደኛ ተከሳሽ የሸኖ ከተማዋ ከንቲባ የነበሩት #ተሾመ ሙሉጌታን ሲሆኑ ከአንደኛ እስከ 11 ያሉት ተከሳሾች ደግሞ በከተማው መሬት አስተዳደር ውስጥ በተለያዩ ሙያ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ ናቻ፡፡

ከ11ኛ እስከ 26 ያሉ ተከሳሾች በኢንቨስትመንት መሬት የወሰዱ ተከሳሾች #ናቸው
ምንጭ ፦ OBN
@yenetube @mycase27