YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update
አቶ #እንደሻው ጣሰው የቀድሞው ኮሚሽነር አቶ #ዘይኑ ጀማል የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ፥ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አቶ እንደሻው ከ1983 እስከ 1992 ዓ.ም ድረስ #በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከመምህርነት እስከ ክፍለ ጦር አመራርነት በትምህርቱ ዘርፍ አገልግለዋል።

ከዚያም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች በትጋት የህዝብንና የመንግስትን ሃላፊነት ሲወጡ የቆዩ #ናቸው

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ #በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባው #የህዝብ ግንኙነት አማካሪ እና የአዲስ አበባ ከተማ #ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነውም አገልግለዋል።

በትምህርታቸውም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን #በጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በውጭ ሃገር ተከታትለው #በከፍተኛ ውጤት አጠናቀዋል።
ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27