YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በጅማ ከተማ ቂቤና ማርን ከበአድ ነገር ጋር በመቀላቀል ሲያዘጋጁ ነበር የተባሉ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀው፥ ግለሰቦቹ በጅማ ከተማ ስምንት ቤቶችን በመከራየት ለዓዲስ ዓመት ለሽያጭ የሚቀርቡ ቂቤና ማር ከበአድ ነገር ጋር በመቀላቀል ሲያዘጋጁ ነበር።
ከቂቤና እና ማሩን ከበአድ ከበአድ ነገሮች ጋር ለማዋሀድ ሲጠቀሙበት የነበረ አንድ ማሸንም በቁጥጥር ስር ውላል።

የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዢን ሃላፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አጉቾ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህብረተሱ በደረሰ ጥቆማ ነው።

ፖሊስም የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ በትናንትናው እለት ማካሄድ በጀመረው የዘመቻ ስራ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሰር መዋላቸወን ተናግረዋል።

በዚህ ዘመቻም በጅማ ከተማ ወረዳ ሁለት በቾ ቦሬ ቀበሌና አዌቱ መንደር አካባቢ በሚገኝ የውስጥ ለውስጥ መንደር ውስጥ በተከራዩበት ስምንት ቤት ውስጥ በርካታ የተለያ ኬሚካሎች መያዛቸውን ተናግረዋል።

እንደ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ተቀላቅሎባቸው የተገኙ ቅቤ እና ማሮች ለላብራቶሪ ምርመራ ይደረግበታል ብለዋል።

ህብረተሰቡም ለዓዲስ አመት የሚገዛቸውን ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ግብአት ላይ ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ ኢኒስፔክተር ገዛሀኝ አሳስበዋል።
©fbc
@YeneTube @Mycase27
#update
አቶ #እንደሻው ጣሰው የቀድሞው ኮሚሽነር አቶ #ዘይኑ ጀማል የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ፥ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አቶ እንደሻው ከ1983 እስከ 1992 ዓ.ም ድረስ #በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከመምህርነት እስከ ክፍለ ጦር አመራርነት በትምህርቱ ዘርፍ አገልግለዋል።

ከዚያም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች በትጋት የህዝብንና የመንግስትን ሃላፊነት ሲወጡ የቆዩ #ናቸው

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ #በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባው #የህዝብ ግንኙነት አማካሪ እና የአዲስ አበባ ከተማ #ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነውም አገልግለዋል።

በትምህርታቸውም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን #በጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በውጭ ሃገር ተከታትለው #በከፍተኛ ውጤት አጠናቀዋል።
ምንጭ ፦ FBC
@yenetube @mycase27