YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሀረር ከተማ የአለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል መሆኗ ተገለጸ

#ሆንግ_ኮንግ በተካሄደው የአለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን ጉባኤ ሀረር ከተማ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን የሀረሪ ክልል ርዐሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

አቶ ኦርዲን በድሪ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ሀረር ከተማ “የፌደሬሽኑ አባል መሆኗ” ሀረርን ከሌሎች ከተሞች ጋር ለማስተሳሰር እና አብሮ ለመስራት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023 ሀረር ከተማ ከሰሃራ በታች ካሉ ከተሞች የመጀመሪያዋ የዓለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት አባል ከተማ ሆና መመዝገቧ ይታወሳል፡፡

እንዲሁም ከተማዋ የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስን ጨምሮ በተባበሩት መንግስት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የተመዘገቡ ዓለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ ከተማ መሆኗ ይታወቃል፡፡

በተጨማሪም ከተማዋ ዜጎች በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የሚኖሩባት ከተማ በሚል ዩኔስኮ እውቅና ተሰጥቷቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍24😁96🔥1
የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌 
#ምርቶቻችንን ከ :-
🥣 ሸዋ ሾፒንግ 
🥣 በሽ ገበያ
🥣 ባምቢስ(ልዊስ)
🥣 ሎሚያድ
🥣 ጋራ ማርት
🥣 ዴይሊ ሚኒማርት
🥣 ጋራድ ሱፐርማርኬት
እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል። 

🥣 መልካም በዓል   / 2017 ዓ.ም 🥣
#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
📲 0911 664775 / 0911 872827
👍81
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በ #ሩዋንዳ እያደረጉ ነው

#ኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ ከሚያዚያ 5 ቀን ጀምሮ የአራት ቀን የስራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ ተዘገበ።

ጉብኝቱ ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር እያደረጉ ያሉትን ጥረት ተከትሎ የተካሄደ ነው።  የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ መበጋቢት ወር  በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተፈራርመዋል።

እንደ ዘኒው ታይምስ ዘገባ፤ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ሰኞ ዕለት፤ ኪሚሁሩራ በሚገኘው የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት  ዋና መስሪያ ቤት ከጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ይህንንም ተከትሎ የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት በሰጠው መግለጫ፣ ጉብኝቱ "የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብርን” ለማስፋት "ቁልፍ ዕድል" መሆኑን በመግለጽ ውይይቶቹ "በመከላከያና በሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች  አዲስ የትብብር መስኮች" ላይ ያተኮሩ ናቸው ብሏል።

ፌልድ ማርሻል ብርሃኑ  የኪጋሊ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሙዚየምን እንደሚጎበኙ ዘኒው ታይምስ ዘግቧል። የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ በመጋቢት ወር ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት ልዑካቸው በ #ቢሾፍቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም በወቅቱም ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በወታደራዊ አቅም ግንባታ ስልጠና፣ በተሞክሮ ልውውጥ፣ ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና በሌሎችም ተያያዥነት ባላቸው ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁40👍196👎2🔥2
ለ150 ሺህ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በበየነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል

ለ150ሺህ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ፈተናን በበየነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።

በዘንድሮው ዓመት 150ሺህ ተማሪዎች በበየነ መረብ ለመፈተን ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ 3 ሺህ 222 ትምህርት ቤቶች የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጡ ሲሆን ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 936 ሺህ 624 ተማሪዎች መካከል 416 ሺህ 284 ተማሪዎች በ48 ሺህ 242 መምህራን ማጠናከሪያ ትምህርት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በ2016 ዓ.ም ምንም ተማሪ ከለሰለፉ ትምህርት ቤቶች መካከል 700 ትምህርት ቤቶች ተለይተው የአንድ ዓመት ሙሉ ድጋፍ በተለያዩ ዘርፎች እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።

ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ 294 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 783 ርዕሰ መምህራን፣ 19ሺህ 566 መምህራንና 3ሺህ 628 የአስተዳደር ሰራተኞች በአጠቃላይ 23ሺህ 977 የትምህርት ማህበረሰብ በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል።

በ2016 ዓም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገውንና ውጤት የተገኘበትን የማጠናከሪያ ትምህርት በስፋት ለመስጠት የንቅናቄ ሰነድ በማዘጋጀት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

በ2016 ዓም 674 ሺህ 814 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲው መግቢያ ፈተና ወስደዋል። ከዚህ 29ሺህ 727 ተፈታኞች በተመረጡ ቦታዎች በበየነ መረብ መፈተናቸው ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍24👎6😁21🔥1
የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአስተማሪዎች የ17 ወራት ውዝፍ ደምወዝ እንዲከፈል ወሰነ

የትግራይ ክልል አስተማሪዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያልተከፈላቸው ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ለማድረግ ጉዳያቸውን ፍርድ ቤት ወስደው እንደነበር ይታወሳል። ከክልሉ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ጉዳዩን ተከሳሾቹ የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ የፋይናንስ ቢሮና ጊዝያዊ አስተዳደሩ በሌሉበት ሲከታተል የቆየው የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሚያዝያ ሰባት ቀን ውሳኔ መስጠቱን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ በውሳኔውም ተከሳሾች የአስተማሪዎችን ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፍሉ በመወሰን የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ ወስኗል። የፍርድ ሂደቱ 1ኛ ተከሳሽ የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ 2ኛ ተከሳሽ የትግራይ ፋይናንስ ቢሮ፣ 3ኛ ተከሳሽ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደርና 4ኛ ተከሳሽ የገንዘብ ሚኒስቴር ባልተገኙበት የተደረገ ነዉ።

@Yenetube @Fikerassefa
👍46👀3
በእስር ላይ የሚገኙት ቲክቶከር ጆን ዳንኤል እና ናዮ( ዪዲዲያ) ዛሬ ሚያዝያ 7 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበራቸው የናዮ የመውለጃ ጊዜዋ መድረሱን ተከትሎ ልጄን ለመውለድ ጋንዲ ሆስፒታል ይፈቀድልኝ ብላ መጠየቃን የተሰማ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ባለችበት እስር ቤት (ቃሊት እስርቤት) እንድትወልድ ፍርድ ቤት ወስኗል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭132👍49😁204👎2
🔥 በTelegram ላይ የተረጋገጠ ምልክት (Verified Checkmark) ለማግኘት የእርስዎን አካውንት አሁን Premium ያድርጉት

Telegram Premium በመግዛት የተረጋገጠ ምልክት ያግኙ!

አስደናቂ ፊቸሮችን ያግኙ!
- 4GB እስከሆኑ ፋይሎችን ይጫኑ
- በፍጥነት ያውርዱ
- የእርስዎን online status ከሌሎች ይደብቁ
- እስከ 4 accounts ድረስ ይጠቀሙ
- ልዩ ስቲከሮች እና ኢሞጂዎች 🎭
- የድምፅ መልእክቶችን ጽሁፍ ያድርጉ
- ልዩ badges ያግኙ
- ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ
አሁኑኑ ይቀላቀሉ እና የእርስዎን Telegram ተሞክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩ! 🚀

📲 ሁሉፔይን ለመጠቀም ሁሉፔይ ሚኒ አፕን
https://tttttt.me/HuluPayOfficialBot/start?startapp እዚህ ሊንክ ጋር ያገኛሉ 🔗

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍113
Forwarded from YeneTube
🌿🌿እንኳን አደረሳችሁ 🌿🌿

በአልን ምክንያት በማድረግ እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ!!!

በ 900,000 ብር ምን ያደርጋሉ❗️

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

እንዲሁም የመኖሪያ አፓርትመንቶችን

📍 ሊሴ ገብረማርያም  ት/ቤት ጀርባ
ሙሉ ለሙሉ ለመኖሪያ ብቻ

ባለ 1 መኝታ
ባለ 2 መኝታ
ባለ 3 መኝታ

ከ66ካሬ - 142ካሬ ለመኖር  ለኢንቨስትመንት ምቹ

⚠️ቅድመ ክፍያ ከ693ሺ ብር ጀምሮ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ እስከ 25% የሚደርስ ቅናሽ

ቴምር ሪልስቴት

ለበለጠ መረጃ 

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍7
Forwarded from YeneTube
ዛራ ሽቶዎች
በተለያዩ ፍሌቨሮች
Red Zara temptation ,Zara golden decade and Zara hypnotic vanilla
Europe standard
Size: 80ml
በብዛት ወይም በችርቻሮ መረከብ ሚፈልግ እናስረክባለን

ዋጋ በችርቻሮ:7000br
በብዛት:6000br

ስልክ: +251919492435 & +251934003462

ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል 👇
https://tttttt.me/+zRyCg_U0QGZmMzY0

ቲክቶክ አካዉንት 👇
www.tiktok.com/@bt_onlineshopping
👍1
Forwarded from YeneTube
የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌 
#ምርቶቻችንን ከ :-
🥣 ሸዋ ሾፒንግ 
🥣 በሽ ገበያ
🥣 ባምቢስ(ልዊስ)
🥣 ሎሚያድ
🥣 ጋራ ማርት
🥣 ዴይሊ ሚኒማርት
🥣 ጋራድ ሱፐርማርኬት
እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል። 

🥣 መልካም በዓል   / 2017 ዓ.ም 🥣
#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
📲 0911 664775 / 0911 872827
👍53
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኤርትራ የሚገኘውን ጨምሮ አስር ኤምባሲዎችን ለመዝጋት ማቀዱ ተገለጸ

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር #በኤርትራ እና ደቡብ #ሱዳን የሚገኙትን ጨምሮ 10 የአሜሪካ ኤምባሲዎችን ለመዝጋት ማቀዱ ተገለጸ።

ከኤምባሲዎቹ በተጨማሪ 17 ቆንስላዎቹንም ለመዝጋት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ማቀዱን ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ተመለከትኩት ያለው ያስተዳደሩን ማስታወሻ ዋቢ በማድረግ ባቀረበው ዘገባው ጠቁሟል።

የትራንፕ አስተዳደር እንዲዘጉ በሚል በእቅድ በያዛቸው ሀገራት ውስጥ በሚገኙ ኤምባሲዎች ይከናወኑ የነበሩ ስራዎች በአጎራባች ሀገራት ባሉ ኤምባሲዎች ለማከናወን ማቀዱንም ዘገባው አስታውቋል።

የኤምባሲዎቹ እና ቆንስላዎቹ መዘጋት የትራንፕ አስተዳደር የፌደራል መንግስትን ባጀት ለመቀነስ እየወሰደ ያለው እርምጃ አካል ነው ተብሏል።

የትራንፕ አስተዳደር ከሚዘጋቸው አስር ኤምባሲዎች መካከል ስድስቱ በአፍሪካ የሚገኙ መሆናቸውን ዘገባው አስታውቋል።

የአስተዳደሩ እቅድ ዩናይትድ ስቴትስ የነበራት የዲፕሎማሲ የበላይነት ያሳጣታል፣ ለቻይና አዲስ እድል ይፈጥርላታል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ እንደሚገኙም ዘገባው አመላክቷል።

እቅዱ ተግባራዊ ከሆነ ቻይና በአፍሪካ ያላትን የዲፕሎማሲ የበላይነት ይበልጥ ያጠናክርላታል መባሉን ዘገባው አካቷል።

ጋዜጣው በተጨማሪም በሶማሊያ ሞቃዲሾ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ካልሆነ ደግሞ በከፍተኛ ቁጥር ሰራተኞቹ እንዲቀነሱ ሃሳብ መቅረቡን አመላክቷል።


@Yenetube @Fikerassefa
👍141🔥1
ኢትዮጵያ የብሪክስ ልማት ባንክ አባልነት በቅርቡ እንደምታጠናቅቅ ገለጸች

ኢትዮጵያ ለአዲሱ የልማት ባንክ ( በቀድሞው ስሙ የብሪክስ ልማት ባንክ) በይፋ አባልነት ለመቀላቀል ማመልከቻ ማስገባቷንና የዚህ ሂደት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ አስታውቃለች። ይህ የአገሪቱ የዘንድሮ ዓመት ዋነኛ ትኩረት እንደሆነም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር የሆኑት አቶ ልዑልሰገድ ታደሰ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ለአባልነት ጥያቄዋ ከሁሉም የ ብሪክስ አባል ሀገራት የፖለቲካ ድጋፍ አግኝታለች። የአባልነት ሂደቱም በተጠናከረ ሁኔታ እየተከናወነ በመሆኑ በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

አቶ ልዑልሰገድ አክለውም ኢትዮጵያ የአዲሱ የልማት ባንክ አባል ከሆነች በኋላ ባንኩ ትኩረት በሚሰጣቸው እንደ ግብርና፣ ኢነርጂ እና ማኑፋክቸሪንግ ባሉ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥታ ለመስራት እቅድ አላት ብለዋል።

የቀድሞ ስሙ የብሪክስ ልማት ባንክ የነበረው አዲሱ የልማት ባንክ በብሪክስ አባል ሀገራት የተቋቋመ ሁለገብ የልማት ባንክ ነው።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ባንኩ  በብድር፣ በዋስትና፣ በፍትሃዊ ተሳትፎ እና በሌሎች የፋይናንስ መሳሪያዎች የህዝብ ወይም የግል ፕሮጀክቶችን ይደግፋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍334👀2🔥1😁1
ነገ  ብሔራዊ ባንክ የ70 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚካሄድ ገለፀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀጣዩን በየሁለት ሳምንቱ የሚካሄደውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ነገ ሐሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም.  እንደሚካሄድ ዛሬ አስታውቋል።

በዚህ ጨረታ የሚቀርበው ጠቅላላ የውጭ ምንዛሬ መጠን 70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሆኑን ባንኩ አሳውቋል። ፍላጎት ያላቸው ባንኮች በተሰጠው መመሪያ መሰረት በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍13😭41
"የኬንያ ዜጎች እንኳን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጭምር ተጓጉዘው ሀገራቸው ገብተዋል"- በሚያንማር የሚገኙ ዜጎች በስልክ ከነገሩኝ

በሚያንማር የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ አሳሳቢም፣ አስገራሚም እየሆነ ነው። ከ740 በላይ ዜጎቻችን ተይዘውበት ከነበረው አደገኛ ካምፕ በአንድ ታጣቂ ቡድን ነፃ ሆነው አሁን ላይ በግዜያዊ መጠለያ ውስጥ ቢገኙም ተረክቧቸው ወደ ሀገራቸው የሚመልሳቸው አካል አጥተው እንዳሉ በርካቶች በአጭር ፅሁፍ መልዕክት እና በስልክ ነግረውኛል።

አንዳንዶቹ በተስፋ መቁረጥ ራስን የማጥፋት ሙከራ አርገዋል፣ ኮማ ውስጥ ያሉ አሉ፣ የአካል ጉዳትም የደረሰባቸው አሉ። ውጭ ጉዳይ አንድ ሰሞን ጉዳዩን ይዞት እንደነበር ሰምተን ነበር፣ አሁን ላይ ምንም ነገር የለም፣ ሲጠየቁ "ፕሮሰስ ላይ ነው" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ።

ዜጎቻችንን ከካምፑ ነፃ ያወጡት ታጣቂዎች እንኳን "መንግስታችሁ በፍጥነት ካልወሰዳችሁ ወደነበራችሁበት ካምፕ ከመመለስ ውጭ ምርጫ የለንም" እያሏቸው ነው።

ኬንያን ጨምሮ ሌሎች 25 ሀገራት ዜጎቻቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በመጠቀም አጓገዘው አውጥተዋል። ጉዳዩን በቶክዮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይዞት ነበር ተብሎ ነበር፣ አሁን ደህሞ ህንድ ያለው ኤምባሲ እየተከታተለው ነው ከሚል ውጭ ምላሽ የለም።

የሚገርመው 400 የሚሆኑት የመመለሻ ትኬት አላቸው፣ ሊረዷቸው የሚችሉ NGO ድርጅቶችም አሉ፣ ነገር ግን መንግስት የመመለስ (repatriation) ሂደቱን ካልጀመረ ምንም ማድረግ አይቻልም።

ልጆቹ አንዴ ተታለው ተወስደዋል፣ መንግስት ግን ሊደርስላቸው አይገባም? ሀገር ማለት ህዝብ ማለት አልነበር?

በአፋጣኝ ትኩረት ካልተሰጠው አሳዛኝ ውጤት ይታየኛል።

መረጃው የኤልያስ መሰረት ነው።
👍183🔥1😭1
ፓኬጅ

Gift For Her
         Gift sets
- የእጅ ሰዓት Brand Watch
- ፅጌረዳ አበባ Roses bouquet 💐
- ሕማማት መፅሀፍ Book spiritual


FREE DELIVERY
ይደውሉ

Inbox for Order @Fikerassefa
👍12👎4
በምስራቅ ወለጋ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል በመንግስት የጸጥታ ሀይል መገደሉን ተከትሎ ታጣቂዎቹ በወሰዱት የበቀል ጥቃት 29 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሐሮ ሊሙ ወረዳ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል እና የቡድኑ መሪ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) "የቅርብ ሰው" የነበሩት ሾዴ በመንግስት የጸጥታ አካላት መገደላቸውን ተከትሎ በተፈጸመ የበቀል ጥቃት 29 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የሟች ቤተሰቦች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

እንደ ነዋሪዎች እና የሟች ቤተሰቦች ገለጻ፣ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሐሮ ሊሙ ወረዳ ጎርባ ጉዲና እና ሱጌ ቀበሌዎች የተፈጸሙት ጥቃቶች "የሾዴን ሞት ለመበቀል በኦነሠ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል" ብለዋል።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ እና በጋብቻ ከሟች ቤተሰቦች ጋር ዝምድና እንዳላቸው የገለጹልን በጎርባ ጉዲና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት፣ ከመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2017  ዓ.ም በተፈጸሙ ተከታታይ ጥቃቶች ቢያንስ የአሥር ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስረድተዋል።

የአካባቢው ነዋሪ አክለውም በ"ኦነሰ ታጣቂዎች" የሚፈጸሙ ጥቃቶች በአካባቢው እንደቀጠሉና በዚህም ምክንያት የአቶ ፋይሳ ተጨማሪ ሰባት ዘመዶች መገደላቸውን ገልጸዋል፤ "እነዚህ ሰዎች ሾዴን ለመያዝ የጸጥታ ኃይሎችን ረድተዋል ተብለው ስለተጠረጠሩ ነው ኢላማ የተደረጉት" ሲሉም አክለዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7615
👍15😭2
ትራምፕ በቻይና ላይ የጀመሩትን ታሪፍ 245 ከመቶ አደረሱ

አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችዉን ቀረጥ ወደ 245 በመቶ አሳድጋለች።

አሜሪካ በቻይና ላይ እየጣለች ያለችዉን ቀረጥ ወደ 245 በመቶ ከፍ ማድረጓን የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማሳወቃቸዉን ኢንዲያ ደይሊ ዘግቧል።

ዛሬ በነጩ ቤተ መንግስት ፕሬዚዳንት ትራምፕ እንደገለፁት፤ ቻይና ከሰሞኑ ወደ አገሯ የሚገቡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ ያሳየችዉን አፀፋዊ ምላሽ ለመቀልበስ ጭማሪውን ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ትራምፕ፣ ይህ ርምጃ አሜሪካን በኃያልነቷ ለማስቀጠል ከተያዘዉ መርህ አንዱ ነዉ ብለዋል።

75 የሚሆኑ አገራት በቀረጥ ዙሪያ ንግግር ማድረግ እንደሚችሉ ጠቅሰዉ፤ ቻይና ግን ቀረጥ በመጨመር ምላሽ ስለሰጠች ጭማሪዉ ተደርጎባታል ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍18👀5😁3
ክልሉ ለ1 ሺህ 216 ታራሚዎች ምህረት አደረገ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ለ1 ሺህ 216 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ ፡፡


ቢሮው እንዳስታወቀው ታራሚዎቹ ምህረቱን ያገኙት መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ነው ፡፡

ታራሚዎቹ ይቅርታው ሊደረግላቸው የቻለው በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት ያቀረቡትን የይቅርታ ማመልከቻ በመመርመር  መሆኑን የጠቀሰው ቢሮው “ በተለይም በማረሚያ ተቋማቱ በነበራቸዉ ቆይታ ስለመታረማቸዉ፣ ስለመታነጻቸዉና ስለመልካም ጠባያቸዉ በየደረጃዉ ከሚገኙ የፀጥታ ተቋማት ማረጋገጫ አግኝተዋል ነው የተባለው፡፡

በቀጣይ ለህብረተሰቡ የወንጀል ስጋት ሳይሆኑ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጋ ሆነው በሰላም መኖር እንዳለባቸው ገለጻ ተደርጎላቸዋል  መባሉን ከDW ተመልክተናል።
👍201