YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
👆👆

በአማራ ክልል የዞኖች፣ የብሔረሰብ አስተዳደሮች እና የከተሞች የፖሊስ እና የመብራት ኃይል ስልክ ቁጥሮች ለመረጃና ለጥቆማ

@YeneTube @FikerAssefa
በድብቅ ሲጓጓዝ የነበረ አምስት የብሬል መትረየስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዋና ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ውብነህ አስናቀው ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ መሳሪያዎቹ የተያዙት ትናንት ማምሻውን በዞኑ አለፋ ወረዳ ፍንጅት በተባለው የጥበቃ ኬላ ፈታሾች ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ነው ተብሏል።የጦር መሳሪያዎቹ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-55523 አዲስ አበባ በሆነ ቶዮታ ፒካፕ መኪና በድብቅ ተጭኖ ወደ ባሕርዳር ሊገባ የነበረ መሆኑ ተገልጿል።የጦር መሳሪያዎቹን በድብቅ ጭኖ ሲያጓጉዝ ነበር የተባለ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን ኮማንደሩ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ለተሰናባች የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥሪ አቀረበ!

የአማራ ክልል መንግስት ከመከላከያ ሰራዊት በተለያየ ምክንያት የተሰናበቱ አባላት፤ የክልሉን የጸጥታ ኃይል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀረበ። ክልሉ ለሰራዊቱ አባላት ጥሪ ያቀረበው የሕወሓት ኃይልን “ስርዓት ለማስያዝ እና ህግ ለማስከበር” እወስደዋለሁ ባለው “ጥቃት” ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ነው።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ ጠዋት በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት የሕወሓትን ኃይል “ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ” ከፌደራል መንግስት ጋር ተባብሮ የሚሰራ ይሆናል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግም ከክልሉ አጠቃላይ የጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ ተመላሽ የሰራዊት አባላትም የዘመቻው አካል እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

“ከሰራዊት በተለያየ ምክንያት ተገፍተው በነበረው ስርዓት የተመለሱ ምልስ የሰራዊት አባላትም በዚህ አጋጣሚ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል። [አባላቱ] ወደ ሰራዊት ተቀላቅለው፤ እስካሁን ሲያሸብር እና ሲያስቸግር የነበረን ኃይል ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ስርዓት ማስያዝ እንዳለብን በዚህ አጋጣሚ ጥሪ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ” ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ በክልላቸው ቴሌቪዥን ጣቢያ በተላለፈ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

[AMMA/Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ለ2012 ዓም ተመራቂ ተማሪዎች አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት 27 እና 28 ምዝገባ ለማድረግ ያደረገውን ጥሪ ወደፊት እስኪገለፅ ድረስ ማራዘሙን አስታውቋል፣ ተማሪዎች ባሉበት ሆነው እንዲጠብቁም ጥሪ አስተላልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላትና አዛዦች ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን ለመሰለፍ መወሰናቸውን አሳውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ክልሉን በሚያስተዳድረው ሕወሃት ላይ ጦርነት መከፈቱን ማስታወቃቸውን ተከትሎ ክልሉ ባወጣው መግለጫ

የፌደራል መንግሥትን በሕገወጥ መንገድ የተቆጣጠረው አሃዳዊና ግላዊ መንግሥት የትግራይን ክል ሕዝብ ለማንበርከክ ከውጪ ኃይሎች ጋር በመሻረክ የአገርን ሉዓላዊነት አሳልፎ በመስጠት ክህደትና በደል እየፈፀመ ነው ሲል በመግለጫው ላይ አትቷል።

የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገመንግሥቱን አክብሮ ምርጫ በማካሄዱ ተከታታይ "በደሎች" እየደረሱበት መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በመላው አገሪቱ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለመውረር በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን መታዘዙን መግለጫው አክሎ ገልጿል።

የትግራይ ክልል መንግሥት የተፈጠሩት የፖለቲካ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም የተሰጠው "እንደ ሕዝብ ቅጣት ነው" በማለትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሰራዊትና አባላት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን በመቆም አብረው መታገል መጀመራቸውን ገልጿል።

መግለጫው ከዛሬዋ እለት ጀምሮ ጥቅትም 25/ 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ውስጥና ድንበር አካባቢ ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ የተከለከለ እንደሆነ ያትታል።

በተጨማሪም ወደ ትግራይ ክልል የሚደረግ ማንኛውም በረራ እንዳማይኖር የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል።

ይህንን ውሳኔ በመጣስ በሕዝብ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚወሰድ እርምጃ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።።

ለሌሎች የሰራዊት አባላት እና አዛዦችም ከሰሜን እዝ ሰራዊትና አዛዦች ጎን በመቆም ታሪካዊ ኃላፊነታቸውነ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የትራንስፖርት አገልግሎትም እንደማይኖር በተጨማሪ ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው የመከላከያ ሠራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ "ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል" በማለት ገልፀዋል።

ክራይስስ ግሩፕ፤ የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ እየተፈጠረ ያለው የፖለቲካ ችግር በሃገራዊ ውይይት እንዲፈታ መጠየቃቸው ይታወሳል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikeassefa
በጅማ ዞን ትናንት ማታ በተደረገ ኦፐሬሽን በርከት ያሉ የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎችን ከተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከደቂቃዎች በኋላ የጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ በኢትዮጵያ የሮይተርስ ዘጋቢ(Correspondent) ጂውሊያ ፓራቪቺኒ ዘግባለች።

@YeneTube @FikerAssefa
የዜጎችን ደህንነትና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለማሳካት በግንባር ቀደምትነት እንሰለፋለን" - የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

- ከሀረሪ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ

መከላከያ ሠራዊታችን የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ሉዓላዊነት ለማስከበር፣ ሰላምና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የገነቡት ጠንካራ፣ ብሔራዊና ሀገራዊ ተቋም ለመሆኑ በተግባሩ ደጋግሞ አረጋግጧል።

ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን መሠረት አድርጎ የተሰጠውን ተልዕኮ በላቀ ወታደራዊ ዲስፕሊንና ብቃት በመወጣት ከራሱ አገርና ህዝብ አልፎ በአህጉራዊና አለም አቀፋዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ታላቅ ከበሬታ፣ አመኔታና ይሁንታ ያተረፈ ተቋምና ሰራዊት እንደሆነም ይታወቃል።

https://telegra.ph/Harara-11-04
በአማራ ክልል ለቤተ እምነቶች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ

በአማራ ክልል ለቤተ እምነቶች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጸጥታ አካላት ባገኘው መረጃ መሰረት፣ የኦርቶዶክስ አልባሳት ለብሶ መስጅድ፣ እንዲሁም የሙስሊም አልባሳት ለብሶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ የያዙ አካላት ወደ ክልሉ ገብተዋል።

በመሆኑም በክልሉ ያሉ ሁሉም አማኞች ቤተ እምነታቸውን በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኛ የሆነው በቃሉ አላምረው ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት አካባቢ በሶስት ፖሊሶችና አንድ የፀጥታ ባለሙያ ተወስዶ እንደታሰረ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦንግ ሸኔን የጦር መሳሪያ ስታመላልስ የነበረች ላንድ ክሮዘር መኪና መያዙን በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የጓንጓ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የኦንግ ሸኔን ቁሳቁስ ስታመላልስ የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥሯ 30534 የሆነች ላንድ ክሮዘር መኪና መያዙን በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የጓንጓ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል፡፡የጓንጓ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ደመላሽ ብርሃኑ ለአብመድ በስልክ እንደተናገሩት ለኦነግ ሸኔ የተለያዩ ቁሳቁሶችን የምታመላልስ የሰሌዳ ቁጥሯ 3054 ደቡብ በሚል የሀሰት ታርጋ የተለጠፈላት ላንድክሮዘር መኪና በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ጥቅምት 19 እና ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም የጓንጓ ወረዳ ፖሊስ ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን በተለያዩ ቦታዎች ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 240 የክላሽ ጥይት እና ከ400 በላይ ስለታማ የጦር መሳሪያዎችን ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ የጦር መሳሪያው ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሊገባ የነበረ እና በንፁሃን ላይ ጉዳት ለማድረስ ታቅዶ እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የኢፌዴሪ መከላለከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን ጥቃት በፅኑ አወግዛሁ ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት:

በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረዉን ትምህርት ለማስቀጠል ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ ተማሪዎቻቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ ማስታወቂያ ማውጣታቸዉ ይታወቃል፡፡ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ ለጊዜዉ መግታት አስፈልጓል፡፡ በዚሁ መሰረት:-

1. እስካሁን ዩኒቨርሲቲወቻችሁ ላይ የደረሳችሁ ተማሪወች በግቢያችሁ እንድትቆዩና በየግቢያችሁ የሚሰጣችሁን ማሳሰቢያ እየተከታተላችሁ እንድትንቀሳቀሱ፤ አካባቢያችሁ ያለ የትኛውም የተለየ ጉዳይ ለተቋሞቻችሁ ሃላፊዎች እንድታሳውቁ

2. እስካሁን ከወላጆቻችሁ አካባቢ ያልተነሳችሁ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ከወላጆቻችሁ ጋር እንድትቆዩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

[ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር]
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ውጥረት እንዲረግብ አሳሰበች። ሀገሪቱ በአዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ በኩል ከደቂቃዎች በፊት ባወጣችው አጭር መግለጫ፤ ሁለቱም ወገኖች “የተመጠኑ እርምጃዎች” እንዲወስዱ ጠይቃለች። የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬ መግለጫው “ሁሉም ወገኖች የሰላማዊ ህዝብን ደህንነት እና ጸጥታ ቅድሚያ እንዲሰጡ አበክረናል እናበረታታለን” ብሏል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
ህዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም አካባቢውን፣ ሰላሙን፣ ደህንነቱን እና ሃብት ንብረቱን እንዲጠብቅ የሲዳማ ክልል ጥሪ አቀረበ

ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም አካባቢውን፣ ሰላሙን፣ ደህንነቱን፣ እና ሃብት ንብረቱን እንዲጠብቅ የሲዳማ ብራዊ ክልላዊ መንገስት ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከየትኛውም አጥፊ አካል ሀገርን ለማዳን በሚደረግ ጥረት ጎን ለጎን የህዝቡ ሰላምና ደህንነት በሚገባ እንዲጠብቅም ነው ክልሉ ያሳሰበው፡፡

በሀገረቱ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ አልቀበልም በማለት አፈንግጦ የወጣው ህወሃት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል ብሏል ክልሉ በመግለጫው።
የፌዴራል መንግስት በተደጋጋሚ የሚደርሰውን ሀገር አፍራሽ ተግባር በመመከት እስከዛሬ የቆየ ቢሆንም ህወሃት በትናንትናው እለት በሰሜን ዕዝ ካምፕ ላይ እና በአማራ ክልል ጥቃት በማድረስ ጦርነት ማስጀመሩን አውስቷል፡፡

የሀገር መከላከያ ሰራዊትም የሀገር ልዑላዊነትን የመጠበቅና የማስጠበቅ ሃላፍነቱ ለመወጣት ጥቃት የተፈጸመባቸው አከባቢዎችን በመቆጣጠር ጽንፈኛውን ቡድን የመደምሰስ ስራ እየሰራ እንደሚገኘ ጠቁሟል፡፡

“በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ ሃይሎች በሲሳማ ክልል ስፍራ እንዳይኖራቸውና ምንም አይነት ኮሽታ እንዳይሰማ በንቃት እየተከታተልን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም የሰፈነበት፣ የዜጎች መብት የተከበረበት ምቹ ክልል ለማድረግ እና በሀገሪቱ የተጋረጠብንን አስቸጋሪውን ፈተና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን የምንሻገር መሆኑን እየገለጽን የተከበረው የክልላችን ህዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም አካባቢውን፣ ሰላሙን፣ ደህንነቱን፣ እና ሃብት ንብረቱን እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለል” ብሏል ሲል #የደቡብ_ሬዲዮና_ቴልቪዥን ዘግቧል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
በሰሜን ዕዝ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ደርሶበት የነበረውን ጥቃት በማካካስ አሁን ላይ የህግ የበላይነትን የማስከበር ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን አዲስ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አስታውቋል፡፡

በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ በትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ደርሶበት የነበረው ጥቃትን ተከትሎ ሠራዊቱ ህግ ወደ ማስከበር ስራ መግባቱን ሴክሬታሪያቱ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳሉት የትግራይ ልዩ ኃይል ከአማራ ክልል ጋር ግጭት እንዲፈጥር የሚታዩ ትንኮሳዎች እየታዩ ነው፡፡

ሠራዊቱ አሁንም ቢሆን የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየሰራ መሆኑን የገለፁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የትግራይ የመከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ህዝብ ጋር ዋጋ በከፈለ የጥቃት ዒላማ መሆኑ የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልልም ሆነ ኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ተገንዝቦ ከሠራዊቱ ጎን እንዲሰለፍ አሳስበዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት ኃላፊ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው የተፈጠረው ግጭት በአጠቃላይ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል ሳይሆን ከተወሰኑ ጥቅመኛ ስብስቦች ጋር የተፈጠረ ግጭት መሆኑን የክልሉ ህዝብ ሊረዳ ይግባል ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊቱ ደርሶበት የነበረውን ጥቃት በማካካስ አሁን ላይ የህግ የበላይነትን የማስከበር ተግባር እና ቦታዎችን የመቆጣጠር ሥራዎችን በመሥራት ላይ መሆኑንም አምባሳደር ሬድዋን ገልፀዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያቱም ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ ለህዝቡ እንደሚያደርስ አስታውቋል፡፡

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ከዚህ በፊት ከመከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መኮንኖች ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል:-

1. ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ
2. ሌ/ጄኔራል ዬሐንስ ገ/መስቀል
3. ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ዙሪያ የተጠናከረ የጋራ የጸጥታ ጥበቃ እንደምታከናውን አስታውቃለች ተብሏል!

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ኃላፊ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ዙሪያ የተጠናከረ የጋራ የጸጥታ ጥበቃን ለማከናወን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መስማማታቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ኃላፊ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን የሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወቃል።

ጉብኝቱን እና የተደረጉ ውይይትችን በማስመልከት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦሜር ጋማር ኤልዲን እንደተናገሩት፤ ሁለቱ አገራት በተለይም በድንበርና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።ሁለቱ ወገኖች “በድንበር፣ በልማትና በቀጠናዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የአል-ቡርሀን ጉብኝት የተካሄደው የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ከትግራይ ክልል ጋር ችግር ውስጥ ባለበት ወቅት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሱዳን የድንበር አካባቢዎችን ለመቆጣጠር እና በግዛቷ በኩል የአማፅያን ጥቃቶችን በመከላከል ለኢትዮጵያ ስታደርግ የቆየችውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በማጠናከር የሁለቱን ህዝቦች ፍላጎት መሰረት በማድረግ መስራት እንደሚያሰፈልግም መሪዎቹ ተስማምተዋል ብለዋል፡፡የድንበር ጥቃቶችን ለመከላከልና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመዋጋት ሁለቱ አገራት መስማማታቸውንም ሚኒስትሩ መግለፃቸውን ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa