ህዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም አካባቢውን፣ ሰላሙን፣ ደህንነቱን እና ሃብት ንብረቱን እንዲጠብቅ የሲዳማ ክልል ጥሪ አቀረበ
ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም አካባቢውን፣ ሰላሙን፣ ደህንነቱን፣ እና ሃብት ንብረቱን እንዲጠብቅ የሲዳማ ብራዊ ክልላዊ መንገስት ጥሪ አቅርቧል፡፡
ከየትኛውም አጥፊ አካል ሀገርን ለማዳን በሚደረግ ጥረት ጎን ለጎን የህዝቡ ሰላምና ደህንነት በሚገባ እንዲጠብቅም ነው ክልሉ ያሳሰበው፡፡
በሀገረቱ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ አልቀበልም በማለት አፈንግጦ የወጣው ህወሃት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል ብሏል ክልሉ በመግለጫው።
የፌዴራል መንግስት በተደጋጋሚ የሚደርሰውን ሀገር አፍራሽ ተግባር በመመከት እስከዛሬ የቆየ ቢሆንም ህወሃት በትናንትናው እለት በሰሜን ዕዝ ካምፕ ላይ እና በአማራ ክልል ጥቃት በማድረስ ጦርነት ማስጀመሩን አውስቷል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊትም የሀገር ልዑላዊነትን የመጠበቅና የማስጠበቅ ሃላፍነቱ ለመወጣት ጥቃት የተፈጸመባቸው አከባቢዎችን በመቆጣጠር ጽንፈኛውን ቡድን የመደምሰስ ስራ እየሰራ እንደሚገኘ ጠቁሟል፡፡
“በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ ሃይሎች በሲሳማ ክልል ስፍራ እንዳይኖራቸውና ምንም አይነት ኮሽታ እንዳይሰማ በንቃት እየተከታተልን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም የሰፈነበት፣ የዜጎች መብት የተከበረበት ምቹ ክልል ለማድረግ እና በሀገሪቱ የተጋረጠብንን አስቸጋሪውን ፈተና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን የምንሻገር መሆኑን እየገለጽን የተከበረው የክልላችን ህዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም አካባቢውን፣ ሰላሙን፣ ደህንነቱን፣ እና ሃብት ንብረቱን እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለል” ብሏል ሲል #የደቡብ_ሬዲዮና_ቴልቪዥን ዘግቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa