ውዝግብ የበዛበት የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ
አሸናፊው ባለየበት የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ የዴሞክራቶች ዕጩ የሆኑት ጆ ባይደን የማሸነፍ ከፍተኛ ግምት ቢሰጣቸውም አወዛጋቢው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን አሸንፊያለሁ ብለዋል፡፡240 ሚሊዮን አሜሪካዊያን ድምፅ እንደሚሰጡበት በተጠበቀው የ2020ው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል፡፡ባገኟቸው ተቀራራቢ የምርጫ ወረዳ ድምጾች አንገት ላንገት የተያያዙት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ጆ ባይደን እንደ አፍሪካ ሀገራት ሁላ ‹‹ምርጫውን እኔ ነኝ ያሸነፍኩት›› ትርክት ውስጥ ገብተዋል፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ድምፆች ውጤት ባልተገለጸበት ሁኔታ የ2020 የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫን ማሸነፋቸውን የተናገሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ‹‹ምርጫውን ባሸንፍም ማጭበርበር እየተፈጸመ ነው›› በማለት ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት አስታውቀዋል፡፡ የሪፐብሊካኖች አብላጫ ያለው ፍርድ ቤቱ፤ በፖስታ የተሰጡ ድምፆች ቆጠራን እንዲያስቆምላቸው እንደሚፈልጉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡በዘንድሮው ምርጫ 102 ሚሊዮን ዜጎች ቀድመው ድምፅ የሰጡ ሲሆን ይህም በአገሪቱ የምርጫ ታሪክ ከፍተኛ ያደርገዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከመጀመሪያውም በፖስታ በሚሰጥ ድምጽ ላይ ጥርጣሪያቸውን ሲያነሱ የነበሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ‹‹ከምርጫ መጭበርበር ጋር እየሆነ ያለው ዩናይትድ ስቴትስን የሚያዋርድ ነው›› ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በድምሩ 85 የምርጫ ወረዳ ድምፅ ባላቸው ሶስት ግዛቶች ማለትም ቴክሳስ ፣ ፍሎሪዳ እና ኦሃዮ ማሸነፋቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
በ2016ቱ ምርጫ ትራምፕ አሸንፈውት የነበረውን የአሪዞና ግዛትን ድምፅ ማግኘት የቻሉት ጆ ባይደን፤ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኦሬጎን፣ ኒው ዮርክ፣ ኮሎራዶና ቨርጂኒያ በመሳሰሉት ግዛቶች በማሸነፍ፤ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት 238 የምርጫ ወረዳ ድምፅ ማግኘት ችለዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው 213 የምርጫ ወረዳ ድምፅ አጊኝተዋል፡፡
በተወሰኑ ግዛቶች የድምፅ ቆጠራ ተከናውኖ ውጤቱ ይፋ ያልተደረገ ሲሆን፤ ጆ ባይደን በዊስከንሰን፣ ሚቺጋን እና ኔቫዳ እየመሩ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ ይህም ምርጫውን ለማሸነፍ የሚያስፈልጋቸውን 270 ድምጽ ያስገኝላቸዋል፡፡ውጤቱ ባልተገጸባቸው ሌሎች ግዛቶች ማለትም ፔንሲልቫኒያ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ጂኦርጂያ እና አላስካ ግዛቶች፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እየመሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ከእነዚህ ግዛቶች ትራምፕ ሊያገኙ የሚችሏቸው ድምጾች በድምሩ 54 ሲሆኑ ይህም ጠቅላላ የሚያገኙትን ድምጽ 267 ያደርሰዋል፡፡
ምንጭ:- አሐዱ ቴሌቪዥን
@Yenetube @Fikerassefa

በአሶሳ ከተማ በድብቅ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 20 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፡፡
ከህወሃት ጋር ድብቅ ግንኙነት በመፍጠር በአሶሳ ከተማ ጥፋት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ የተጠረጠሩ 20 ግለሰቦች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱላዚዝ መሐመድ ተናገሩ።ኮሚሽነሩ ለኢዜአ እንዳሉት፤ግለሰቦቹ በአሶሳ ከተማ ኢንቨስትመንትን ሽፋን በማድረግ ጥፋት ለመፈጸም ከህወሃት ድብቅ ትልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው።ከዚህ ቀደም በክልሉ መተከል ዞን የተፈጸመውን ጥቃት ያስታወሱት ኮሚሽነሩ፤ ግለሰቦቹ ይህንን ጥፋት ዳግም ማስቀጠል ዋነኛ ግባቸው እንደነበር አስረድተዋል፡፡ግለሰቦቹ "ከመስከረም 30፣2013 ዓ.ም. በኋላ መንግስት የለም" በሚል ከሃገር ውስጥ እና ከውጪ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ከሚሠራው የጥፋት ሃይል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የፖሊስ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

የዕለት ጉርስ እየደረሰላቸው አለመሆኑን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጥቃት የደረሰባቸው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
-የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በበኩሉ የዕለት ጉርስ የሚሆን ወደአካባቢው ልኬያለሁ መንገድ ላይ ነው ብሏል፡፡
ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በኦነግ ሸኔ በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ንፁኃን አማራዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ንብረት ወድሟል፣ ከቀያቸውም ተፈናቅለዋል፡፡ አሁንም በርካቶች በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ነው የሚገኙት፡፡ ከስፍራው ለአብመድ ስላለው ሁኔታ ሃሳባቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ‹‹የዕለት ጉርስ የሚሆን ነገር የለም፤ ህፃናት እየተራቡ ነው፤ የጠፉት ሰዎችም እስካሁን አልተገኙም›› ነው ያሉት፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ ከሆነ የወረዳው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የትም አትሄዱም ወደቀያችሁ ትመለሳላችሁ እያሉን ነው ነገር ግን ለሕይወታቸው እንደሚሰጉ ነው የተናገሩት።
የክልሉ ልዩ ኃይል ወደሥፍራው ገብቷል፤ ከእነርሱ መካከል ነው እየኖርን ያለነው ነገር ግን በየቦታው ትንኮሳ እየበዛ ነው፤ አስተማማኝ አይደለም ነው ያሉት፡፡ የክልሉ ልዩ ኃይል አይኑን ቢያነሳ አንድ ሰው ስለማይተርፍ ስጋት ላይ ነንም ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በመጠለያ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የዕለት ጉርስ እየደረሰ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ጥቃቱ የደረሰው በድንገት ስለሆነ ማህበረሰቡ ለችግር እየተጋለጠ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ለጊዜያዊ ማረፊያ የሚሆን ሸራ እንደሌለም ነው የጠቀሱት፡፡የክልሉ ልዩ ኃይል በቀበሌዎቹ ካምፕ ሰርተን ከእናንተ ጋር እንሆናለን ወደቀያችሁ ተመልሳችሁ አዝመራችሁን ትሰበስባላችሁ እያለን ነው፤ ነገር ግን የደረሰው ጥቃት ክፉኛ ጉዳት ስላደረሰ አምኖ ለመቀጥ እንደሚቸገሩም ተናግረዋል፡፡ወደስፍራው በሄሊኩፍተር ምግብ ይደርስላችኋል ተብለን ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እንዳልደረሰላቸው ነው የተናገሩት፡፡
የኦሮሚያ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስተና ኮሚሽን ኮሚሽነር አባደር አብዳ ለነዋሪዎቹ የዕለት ጉርስ የሚሆን ምግብ በሶስት መኪና ተጭኖ ወደሥፍራው እየሄደ ነው ብለዋል፡፡ ሌላ ተጨማሪ አንድ መኪና አልባሳትና ፍራሽ ይዞ እንዲከተል እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በሄሊኩፍተር ለመላክ አልተቻለም ነው ያሉት፡፡ በዞኑና በወረዳ የሚገኜው የህብረተሰብ ክፍልም ለተጎጂዎቹ በሚችለው ሁሉ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
[አብመድ]

ተመድ በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ ማንነት ተኮር ጥቃቶች እንዳሳሰበው ገለፀ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በኢትዮጵያ ስለሚፈጸሙ ማህበረሰብ ተኮር ሁከቶችና በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በቅርብ ቀናት እየወጡ ያሉት ሪፖርቶች በጥልቅ እንዳሳሰቧቸው አስታወቁ።
በጥቃቶቹ ብዛት ያላቸው ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ዋና ፀሃፊው ትናንት ባወጡት መግለጫ ጠቅሰው ለተገደሉት ሰዎች ቤተሰቦች ጥልቅ ሃዘኔን እገልጻለሁ ብለዋል። የጥቃቱ አድራሾች ለፍርድ እንዲቀርቡም ዋና ፀሃፊው ጨምረው አሳስበዋል።
አስከትለውም ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች በአስቸኳይ ውጥረቱን የሚያረግቡ ርምጃዎች እንዲወስዱ እና ያሉ ተግዳሮቶች አሳታፊ እና ሰላማዊ በሆነ ንግግር መፍትሄ እንዲፈለግላቸው የተመዱ ዋና ፀሃፊ ተማጽነዋል።
(VOA)

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 379 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,945 የላብራቶሪ ምርመራ 379 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ9 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,503 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 902 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 56,156 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 97,881 ደርሷል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች በትግራይ ክልል የተቋረጠው የቴሌኮምንኬሽን ግንኙነት ወደ መደበኛ አገልግሎት እንዲመለስ ጠየቀ!
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች፤ የኢትዮጵያ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናት ጸጥታን በተመለከተ የሚወስዷቸው እርምጃዎች፤ የዜጎቻቸውን “መብት በሚጠብቅ መልክ ሊሆኑ እንደሚገባ” አሳሰበ። የሀገሪቱ ባለስልጣናት በትግራይ የተቋረጠውን የቴሌኮምንኬሽን ግንኙነቶች ወደ መደበኛ አገልግሎት እንዲመልሱም ጠይቋል።
ተቋሙ ይህን ያስታወቀው በትግራይ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ከሰዎች መብቶች ጋር በተያያዘ ያሉ አሳሳቢ ጉዳዩችን በተመለከተ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ ነው። “ኢትዮጵያውያን ባለፈው ዓመት በየዕለቱ ብጥብጥ እና ስቃይ ሲጋፈጡ ቆይተዋል” ሲሉ በመግለጫቸው ያመለከቱት የሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ዳይሬክተር ማውሲ ሴጉን፤ “በኢትዮጵያ የቀጠለውን ቀውስ ለመፍታት ቀላል መፍትሄ የለም” ሲሉ ችግሩ ጥልቅ መሆኑን አመልክተዋል።
[Ethiopia Insider]

"ዛሬ በነበረው ኦፐሬሽን በሁሉም ግንባር የጠላትን ፍላጎት ያኮላሸ ስራ ተሰርቷል"-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ምሽት ለኢቲቪ በሰጡት መግለጫ "በዛሬው ዕለት በነበረው ኦፐሬሽን በሁሉም ግንባር የጠላትን ፍላጎት ያኮላሸ ስራ ተሰርቷል" ብለዋል።መንግሥት ተገዶ ወደጦርነት ገብቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የሕወሓት ትንኮሳ ሁሉ ከሽፏል ሲሉ ተናግረዋል።መከላከያ ሰራዊት ትንኮሳውን እስከመጨረሻው እንዲያከሽፍ ጥሪ ያቀረቡም ሲሆን በቀጣይ ቀናት ስለሚኖሩ ኦፐሬሽኖች እንደአስፈላጊነቱ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ የጸጥታ ሃይል በዛሬዉ እለት ከሰዓት በኋላ በወሰደዉ ቅንጅታዊ የማጥቃት እርምጃ ከቅርቃር በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘዉ ከፍተኛ ቦታ ላይ የነበረዉን 'አጥፊ ቡድን' ሃይል በከፍተኛ ሁኔታ በማጥቃት ቦታዉን በሰራዊታችን ቁጥጥር ሥር አዉሎታል ብሏል፡፡
Via ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
Via ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ያለው ውጥረት እንዲረግብ አሳሰቡ!
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ) በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በሚገኙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ካምፖች ላይ ጥቃቶችን ማድረሱን የተመለከቱ ዘገባዎች በጥልቀት አሳስበውናል” ብለዋል። ሰላምን ለማስመለስ እና ውጥረቶችን ለማርገብ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድም ፖምፒዮ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አሳስበዋል፡፡

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነው ዛሬ የሚያካሂደው፡፡ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሂዳል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ከፀጥታ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ ማንኛውንም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥመው ከዚህ በታች በተገለጹት ስልክ ቁጥሮች አማካይነት መረጃ እንዲያደርስ አሳውቋል።
ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን 0462212870/
0462202069
ደ/ኦሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0467750521
ጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0468810025
ጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0467771367
ጌዲኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0463312687
ወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0461803821
ከምባታ ጠምባሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0465540644
ጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0113300323
ስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0467710022
ሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0475560530
ቤን/ሸኮ ፖሊስ መምሪያ 0478359130
ካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0473310568
ዳውሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0473450431
ሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0465550330
ሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0465560032
ኮንሶ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0941460363
ምዕራብ ኦሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0474524527
አማሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0902951364
ባስኬቶልዩወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0462400125
ኮንታልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0472270011
የም ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0474519051
ቡርጅ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0916424032
ደራሽ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0467740019
አሌ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0916708156
[ደቡብ ፓሊስ]
@YeneTube @FikerAssefa
ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን 0462212870/
0462202069
ደ/ኦሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0467750521
ጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0468810025
ጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0467771367
ጌዲኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0463312687
ወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0461803821
ከምባታ ጠምባሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0465540644
ጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0113300323
ስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0467710022
ሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0475560530
ቤን/ሸኮ ፖሊስ መምሪያ 0478359130
ካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0473310568
ዳውሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0473450431
ሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0465550330
ሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0465560032
ኮንሶ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0941460363
ምዕራብ ኦሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ 0474524527
አማሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0902951364
ባስኬቶልዩወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0462400125
ኮንታልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0472270011
የም ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0474519051
ቡርጅ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0916424032
ደራሽ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0467740019
አሌ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት 0916708156
[ደቡብ ፓሊስ]
@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ስኬታማ ድል ማስመዝገባቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በይፋዊ ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
እጅግ ስኬታማ ውሎ ነበረን:: የክልላችን ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው ያሉ ዓመራሮች እና አባላት በተቀናጀ መልኩ ያደረጉት ተጋድሎ ስኬታማ ነበር:: በትናንትናው ዕለት በሶሮቃ እና ቅራቅር ከዕኩለ ሌሊት እስከ ረፋድ ተደጋጋሚ ማጥቃት ተሰንዝሮብን ነበር:: ከረፋድ በኋላ በሰነዘርነው ማጥቃት በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥረናል:: በተቆጣጠርናቸው ቦታዎች ያለው የህዝብ ድጋፍ ድንቅ ነበር:: በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን ሰጥቷል:: እዋጋለሁ ብሎ የመረጠም ፊቱን አዙሮ እኛን ሲያግዝ ውሏል:: ጦርነት አንፈልግም ስንል ጠላታችን ድህነት ነው ከሚል እንጅ ጦርነት ካለማወቅ አይደለም:: ዛሬም በሌላ ድል ታጅቦ ያልፋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፟ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እየተባባሰ የመጣው የትግራይ ክልል የፀጥታ ሁኔታ እንደሚያሳስበው እና ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው እንደሆነ ገልጿል፡፡
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የፌዴራል እና የትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይሎች የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት እና ሰብዓዊ መብቶች በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንዲጠብቁና እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም ምግብና መድኃኒት የመሳሰሉ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶችን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡የመገናኛና የትራንስፖርት አገልግሎቶችም ሙሉ በሙሉ እንዳይቋረጡ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።

YeneTube
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነው ዛሬ የሚያካሂደው፡፡ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመቀበልና ለማጽደቅ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ አዋጁን የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጣ 7 አባላት ያሉት ግብረኃይል ተቋቁሟል።ግብረኃይሉ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን ‘‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረኃይል’’ ተብሎ ይጠራል።
አዋጁ በመላው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ተፈፃሚ የሚደረግ ሲሆን፣ እንደየአስፈላጊነቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚ ወይም ቀሪ የሚሆንባቸው ተጨማሪ አካባቢዎች ግብረኃይሉ በሚያወጣው መመሪያ ይወስናሉ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ በየጊዜው ለህብረተሰቡ የሚሰጥ ይሆናል።
Via ETV

ፌዴሬሽን ምክርቤት ለቅዳሜ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ።
ምክር ቤቱ 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቿኳይ ስብሰባ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይካሄዳል ብሏል፡፡የፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት ጥቅምት 27 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
ምክር ቤቱ 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቿኳይ ስብሰባ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይካሄዳል ብሏል፡፡የፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት ጥቅምት 27 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመቀበልና ለማጽደቅ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ አዋጁን የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና…
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ላይ ተፈጻሚ የሚሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማፅደቅ ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን ሰይሟል።
በዚህም መሰረት፤
1. አቶ ለማ ተሰማ - ሰብሳቢ
2. ወ/ሮ ጀምበርነሽ ክንፈ
3. ወ/ሮ ሃዋ አሊ
4. አቶ አለባቸው ላቀው
5. አቶ ዘርይሁን ጴጥሮስ
6. ወ/ሮ አስካለ ጥላሁን
7. አቶ ወንድሙ ግዛው
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
በዚህም መሰረት፤
1. አቶ ለማ ተሰማ - ሰብሳቢ
2. ወ/ሮ ጀምበርነሽ ክንፈ
3. ወ/ሮ ሃዋ አሊ
4. አቶ አለባቸው ላቀው
5. አቶ ዘርይሁን ጴጥሮስ
6. ወ/ሮ አስካለ ጥላሁን
7. አቶ ወንድሙ ግዛው
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ማብራሪያ ሰጠ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርምሮ ማጽደቁን ተከትሎ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ህገ መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ምክንያት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስተባብረው ግብረ ሃይል የተቋቋመ ሲሆን ግብረ ሃይሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የሚኖረውን ስልጣንና ተግባር በዝርዝር ተቀምጧል፡፡
በዚህ መሰረት በመጀመሪያ በተቀመጠው በትግራይ ክልል ላይ ተፈጻሚ በሚሆነውና ለስድስት ወር በሚቆየው በዚህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ግብረ ሃይሉ በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ሰብሳቢነት የተቋቋመ ሲሆን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሆን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ተናግረዋል፡፡
ግብረ ሃይሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማስፋትም ሆነ የማጥበብ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን፥ ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል በማስተባበር በአንድ ዕዝ ስር እንዲመራ ማድረግ ይችላልም ነው የተባለው፡፡በትግበራው ወቅትም ተልዕኮውን ተፈጻሚ በሚያደርግበት ጊዜ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ድንጋጌዎች ማውጣትም ሆነ መተግበርም ይችላል ነው ያሉት፡፡
የመደበኛ የዜጎች መብት ሳይጣስ አዋጁ በተጣለባቸው አካባቢዎች ላይ ተልዕኮውን ማስፈጸም የሚያስችለውን እርምጃ መውሰድም ይችላል ነው የተባለው፡፡ከዚህ ባለፈም ፖሊስን ጨምሮ ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል ትጥቅ እንዲፈቱ ማድረግም እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡
የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብም መጣል፣ የሰአት እላፊ ገደብ የማውጣት፣ የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴዎችን የማስቆም፣ የመገናኛ ዘዴዎች እንዲቋረጡ የማድረግ፣ ለተልዕኮ እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸውን መግለጫዎች መከልከል፣ ህገ ወጥ በሆነ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች የመያዝና የማቆየት እንደሚችል በተግባር አፈጻጸጸሙ ላይ ተቀምጧልም ብለዋል፡፡
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተደነገገባቸው አካባቢዎች ላይ ለተልዕኮ ተፈጻሚነት ያግዙኛል ብሎ ሲያምን ሰዎችን በአንድ ቤት፣ ቦታ ወይም አካባቢ እንዲቆዩ የማድረግ ስልጣን እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡ቤትና አካባቢዎችን ጨምሮ መጓጓዣዎችንም በማንኛውም ጊዜ መበርበርና መፈተሽ እንዲሁም አገልግሎት ሰጭ ተቋማትና መሰረተ ልማቶችን ለተልዕኮ መሳካት ያስችሉኛል ካለ ማስቆም እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡ግብረ ሃይሉ ለተልዕኮ ተፈጻሚነት አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ማድረግ እንደሚችልም ስልጣን የተሰጠው ሲሆን በሂደቱ ተመጣጣኝ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
Via Fana

አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ።
የኦሮሚያ ከልል የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው ቀጠሮ የተሰማውን የዐቃቤ ህግ ምስክር ማስረጃን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ በያዘው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት ተሰይሟል፡፡በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ በተከሰሱበት ወንጀል ዐቃቤ ህግ ያሰማቸውን ምስክሮች መከላከል የሚያስችል የመከላከያ ማስረጃ ካላቸው እንዲያቀርቡ ለህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ለአቶ ልደቱ በዚህ ክስ የ100 ሺህ ብር ዋስትና መፍቀዱ የሚታወስ ነው።ህገ መንግስቱን በኃይል ለማፍረስ በማሰብ የሸግግር መንግስት ሰነድ ማዘጋጀት ወንጀል ክስ ላይም አቶ ልደቱ አያሌው የጤና ሁኔታቸው አስጊ ደረጃ ላይ መሆናቸውን ገልጸው የሃኪም ማስረጃ በማቅረብ የጠየቁት የዋስትና ጥያቄን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።