በአሰገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የ25 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት፡፡
ተከሳሽ ደስታ ገበየሁ የተባለ ግለሰብ ቀኑ ነሀሴ ወር 2011 ዓ.ም ዕድሜቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆነ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ውስጥ በሚገኝው ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመባቸው በመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዐቃቂ ቃሊቲ ምድብ ፅ/ቤት የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን መስርቶበታል፡፡ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ ማስረጃ አቅርቦ በማሰማቱ እንዲሁም ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ በማለት ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ60 አመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሴቶችና ህፃናት ወንጀል ጋር ተያይዞ ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ 19 የምርመራ መዝገቦች ቀርበው የተጣሩ ሲሆን በ8 መዝገቦች ላይ ክስ ተመስርቶ ለችሎት መቅረባቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ጽፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሲሳይ ጎኣ የገለጹ ሲሆን ቀሪዎቹ መዝገቦች በምርመራና በመወሰን ሂደት ላይ እንደሆኑ ምክትል ኃላፊ አብራርተዋል፡፡
በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲያገኝም በተቻለ ፍጥነት ለፓሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
Via FDRE Attorney General
@YeneTube @FikerAssefa

ባለፉት ሶስት ወራት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል!
ባለፉት ሶስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ከኅብረተሰብ ተሳትፎ መገኘቱን የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ።ገቢው የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ከተረጋገጠበት ካለፈው መጋቢት እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።
#Walta

በቦሌ ሚካኤል አየር አንባ ት/ቤት አካባቢ ዛሬ እኩለ ቀን ለደቂቃዎች የቆየ ተኩስ ልውውጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡
ከተኩስ ልውውጡ በኋላ ካፒታል ጋዜጣ በቦታው በመገኘት እንደታዘበችው በጥይት ተመቶት የወደቀ ሆኖም በሸራ የተሸፈነ ሰው መኖሩን አረጋግጧል፡፡ እንዲሁም አንድ ግለሰብ መሬት ላይ ተኝቶ ማየት የተቻለ ሲሆን ግለሰቡ እንቅስቃሴ ያሳይ እንደነበር የካፒታል ዘጋቢ ከርቀት ለመታዘብ ችሏል፡፡ባካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ለካፒታል ጋዜጣ እንዳረጋገጡት የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከዝርፊያ ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ በዘራፊነት የተጠረጠሩት ግለሰቦችም የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ለወንጀል የተሰማሩ የነበሩ ሆኖም አባል ያልሆኑ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡የአይን እማኞች እንደገለፁት የተኩስ ልውውጡ ከሁለቱም ወገን ማለትም ከፀጥታ አካላት እንዲሁም ተጠርጥረው ከሚያመልጡት ወገን እንደነበር አስረድተዋል፡፡ተጠርጣሪዎቹ በመኪና ለማምለጥ ጥረት እያደረጉ እንደነበር የገለፁት የአይን እማኞች መኪናዋ በጥይት ተመትታ ትዛዝ ሆቴል የሚባል አካባቢ ቆማለች፡፡ባካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉዳዩ ገና በመጣራት ላይ ያለ ነው ሆኖም ከዝርፊያ ጋር የሚገናኝ ነው ብለዋል በቦታው ለነበረው የካፒታል ዘጋቢ፡፡
Via Capital

ገዥዉ ፓርቲ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ድርሻ ለመሸጥ እሄደበት ያለውን ጥድፊያ በአስቸኳይ እንዲያቆም ኢዜማ አሳሰበ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ገዥዉ ፓርቲ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ለመሸጥ እያደረገዉ ያለዉ ሂደት ግልጸኝነት የጎደለዉና ጥድፊያ የተሞላበት ነዉ ብሏል፡፡የኢኮኖሚ ዘርፎች ተወዳዳሪነት ዋነኛ ሞተር የሆነን የቴሌኮም ኢንደስትሪ እንደ ተራ መረጃ ማስተላለፍያ ብቻ በማየት ለውጪ ድረጅት ለመሸጥ የጀመረው መንገድ ፍፁም አደገኛ እና የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ሲል ጠይቋል፡፡

6 ዩኒቨርስቲዎች የጉና ተራራ አከባቢን ለማልማት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ዛሬ ደብረታቦር፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ እንጅባራ እና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲዎች "ጣናን ለመታደግ የጋራ፣ የትብብርና የፍቅር አረንጓዴ አሻራ - ዘመቻ ወደ ጉና" በሚል መሪ ቃል የጉና-ጣና ተፋሰስ ቦታዎች ላይ ችግኝ የተከሉ ሲሆን ከችግኝ ተከላው በኃላም የጉና ተራራ አከባቢን ለማልማት፣ በአካባቢ እንክብካቤና ሌሎች ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የጉና ተራራ የ41 ወንዞችና የ77 ምንጮች መገኛ ሲሆን የጣናና የአባይ ገባሮች በሙሉ የሚነሱበት እና የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ ተብሎ የሚጠቀስ ስፍራ ነው።የጉና ተራራን ማልማት ጣና ሃይቅን ከእንቦጭ ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑና ጣና ከደለል በሚጠበቅበት ጊዜ የእምቦጭ አደጋውን መከላከል እንደሚቻል እና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስተማማኝ የውሃ አቅርቦት ለማግኘት እንደሚረዳ ተገልጿል።
#MoSHE

በቦሌ ክፍለ ከተማ ከዘራፊዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ!
በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ የቻይናዊያን መኖሪያ ቤት ላይ የዘረፋ ወንጀል ፈጽመው ለማምለጥ የሞከሩ በቁጥር 8 ግለሰቦች ከፖሊስ ጋር በከፈቱት ተኩስ ሞትና ጉዳት መድረሱን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል። ተጠረጣሪዎቹ በፖሊስ ኢንተለጀንስ አባላት ክትትል እየተደረገባቸው ሳለ ወደ ቻይናውያኑ ቅጥር ጊቢ መግባታቸውን የጠቆመው መረጃው፥ ዘረፋውን ፈጽመው ሲወጡ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ብለው ተኩስ መክፈታቸው በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ሂደት ሊያመልጡ የሞከሩ ሁለት ግለሰቦች አንዱ ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው ቆሰሎ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ስድስቱ በቁጥጥር ሰር እንዲውሉ ተደርጓል።
ግለሰቦቹ ቀደም ሲልም የተለያዩ የጸጥታ አካላትን የደንብ ልብሶች በመልበስ እና የጦር መሳሪያ በመታጠቅ እንዲሁም የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም በተለያዩ ስፍራዎች የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን ሲፈጽሙ ለመቆየታቸው ከህብረተሰቡ በተለያዩ ጊዜ የደረሱ ጥቆማዎች የሚያመላክቱ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በተለመደው ሁኔታ የወንጀል ድርጊታቸውን ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።ህብረተሰቡ የጸጥታ ኃይሎችን የደንብ ልብስ በመልበስ፣ የጦር መሳሪያ በመታጠቅ እና ህግ አስከባሪ በመምሰል ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚመጡ ግለሰቦች ሁኔታ አጠራጣሪ ሆኖ ሲያገኝ ለአካባቢው ፖሊስ በመጠቆም ወይም በ987 ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም የወንጀል ድርጊቱ እንዲገታ ለፖሊስ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል።
#ETV

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 250 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5414 የላብራቶሪ ምርመራ 250 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5425 ደርሷል።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 32 (11 ከጤና ተቋም እና 21 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 6 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ከዚህ ባለፈ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 89 ደርሷል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 250 ሰዎች ሲሆኑ ከአስሩ በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(158) ሴት(92) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ3 ወር-90 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 144 ሰዎች (124 ከአዲስ አበባ፣ 7 ከትግራይ ክልል፣ 5 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከኦሮሚያ ክልል እና 7 ከአማራ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1688 ነው።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(177)፣ ከትግራይ ክልል(21)፣ ከኦሮሚያ ክልል(8)፣ከሶማሊ ክልል(4)፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል(1)፣ ከጋምቤላ ክልል(18)፣ ከአማራ ክልል(20) እና ከድሬዳዋ(1) በድምር 250 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5425 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 27 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 8 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 89 ነው።

12 ድርጅቶች በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት አሳዩ!
ባሳለፍነው ሰኞ እኩለ ቀን በተዘጋው የፍላጎት መጠይቅ 12 ድርጅቶች ፍላጎታቸውን መግለፃቸውን የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ለካፒታል ጋዜጣ በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡ከ12ቱ ድርጅቶች ዘጠኙ የቴሌኮም ድርጅቶች ሁለቱ በሌላ ዘርፍ ያሉ እና አንድ ድርጅት ያልተሟላ ሰነድ ያስገቡ እደሆኑ ታውቋል፡፡የቴሌኮም ድርጅቶቹ Vodafone, Vodacom, and Safaricom (በጋራ) Etisalat, Axian, MTN, Orange, Saudi Telecom Company, Telkom SA, Liquid Telecom እና Snail Mobile ሲሆኑ፡፡ ሁለቱ የቴሌኮም አንቀሳቃሽ ያልሆኑት ድርጅቶች ደግሞ Kandu Global Telecommunications እና Electromecha International Projects የተባሉ ናቸው፡፡ከሁለት አመት በፊት የቀድሞው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ የመንግስት ግዙፍ ድርጅቶችን በከፊል ወይም በሙሉ ለመሸጥ እንዲሁም በመንግስት ሙሉ ድርሻ ተይዘው የነበሩ ዘርፎችን ለተጨማሪ አንቀሳቃሾች በከፊል እንዲከፈቱ በወሰነው መሰረት የቴሌኮም ዘርፉ ቀዳሚ ሆኗል፡፡ለአንድ ወር የቆየው የፍላጎት መጠይቅ ሁለት ተጨማሪ የቴሌኮም አንቀሳቃሾችን በአገሪቱ ለማስገባት ያለመ ነው፡፡
#Capital

ለጤና ተቋማት የሕክምና ግብዓቶችና የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁስ ለሟሟላት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ገለጹ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ለጤና ተቋማቱ በግዥ አልያም በዕርዳታ የሚገኙ የሕክምና መሳሪያዎችና ግብዓቶችን የማሰባሰብ ሥራው ተጠናክሯል ብለዋል።በተለይም በጽኑ ሕሙማን ክትትል ለሚገኙ የኮቪድ-19 ታካሚዎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የሕክምና ግብዓቶችን ለማሟላት አጽንኦት መሰጠቱን ገልጸዋል።ያም ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የግብዓት እጥረትና አንዳንድ አምራች አገራት ምርታቸውን ወደ ሌሎች አገራት መላክ ማቆማቸው ጫና አሳድሯል ነው ያሉት።ይህን ክፍተት ለመሙላት በተለይም የአገር ውስጥ አምራች ኩባንያዎች በስፋት ወደ ምርት ሥራ እንዲገቡ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምንጭ: ኢዜአ

ከሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል አመራሮች እና የጸጥታ አካላት ግድያ ጋር ተጠርጥሮ በእስር የቆየው መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸሙ የሚያስረዳ የሰውም ሆነ የጽሁፍ ማስረጃ ባለማግኘቱ መዝገቡን መዝጋቱን የክልሉ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 177 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ በተደረጉ የላቦራቶሪ ምርመራዎች አድራሻቸው አዲስ አበባ የሆኑ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3545 ደርሷል፡፡ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በከተማዋ የ7 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 123 ሰዎች ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን የጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 24
👉ቦሌ 4
👉ጉለሌ 11
👉ልደታ 26
👉ኮልፌ ቀራንዮ 12
👉ቂርቆስ 6
👉አራዳ 9
👉የካ 4
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 4
👉አቃቂ ቃሊቲ 7
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 4
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 24
👉ቦሌ 4
👉ጉለሌ 11
👉ልደታ 26
👉ኮልፌ ቀራንዮ 12
👉ቂርቆስ 6
👉አራዳ 9
👉የካ 4
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 4
👉አቃቂ ቃሊቲ 7
👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 4
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ ለሕዝብ ውይይት እንደሚቀርብ የፕላንና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የመነሻ ሰነዱ ውይይት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለ11 ቀናት ይካሄዳል።የውይይቱ ዓላማ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በዕቅድ ዝግጅቱ እንዲሳተፉ ማስቻል፣ ከኅብረተሰቡ በሚገኝ ግብዓት ዕቅዱን ማዳበርና ግልጽ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠት መሆኑን ጠቁሟል።የተቋማት የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ በሃላፊዎቻቸው በተሰጣቸው የጊዜ ሰሌዳ ለውይይት እንደሚቀርብም ተገልጿል።ዝግጅቱ በተቋሙ የፌስ ቡክ ገጽ፣ በዩቲዩብ ቻናልና በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ ለሕዝብ ይቀርባል።
ምንጭ:ኢዜአ

የሲዳማ ክልል በጀት ለብቻ እንዲቀርብ ተወሰነ!
ዛሬ በገቢ፣ በጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ በተጠራው እና በ2013 ዓ/ም በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ በተደረገው ውይይት በቅርቡ በክልልነት ለተደራጀው የሲዳማ ክልል በጀት ለብቻ መቅረብ እንዳለበት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ለምለም ሃድጉ አሳሰቡ፡፡ክልሉ እንደ ክልል እንዲደራጅ መወሰኑን ያስታወሱት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የክልሉ በጀት ለብቻ የማይቀርብበት ምንም ምክንያት የለም በመሆኑም ከደቡብ ክልል ተነጥሎ ለብቻ ይቅረብ ብለዋል፡፡በሰኔ 4 የበጀት መግለጫቸው ወቅት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የሲዳማን በጀት ለምን ለብቻ አልቀረበበም ለሚል ተደጋጋሚ የፓርላማ አባላት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ የአዲሱን ክልል በጀት ለብቻ ማቅረብ በቀላሉ የመነጠል ስራ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ወ/ሮ ለምለምም ዛሬ በነበረው ከባለድርሻዎች እና ከህዝብ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በሚመክረው የረቂቅ በጀት መድረክ የክልሉ በጀት ለብቻ እንደሚቀርብ ገልፀዋል፡፡

በሐይማኖት በዳዳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ወጣት "ተገድጄ ነው ወንጀሉን የፈፅምኩት" ሲል ለፍርድ ቤት ዛሬ ቃሉን ሰጥቷል።
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ኮሌጅ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪ የነበረችው እና ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ/ም በኮሌጁ አስተዳደር ህንፃ ላይ በሚገኘው የላቦራቶሪ ቤተ ሙከራ ክፍል ለምርምር በገባችበት ሁኔታ ህይወቷ ያለፈው ሀይማኖት በዳዳ በመግደል የተጠረጠረው ደግነት ወርቁ የተባለው ወጣት ዛሬ ፒያሳ በሚገኘው አራዳ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ወንጀሉን የፈፀመው ተገዶ አንደሆነ ቢናገረም ማን እንዳስገደደው ግን አልተናገረም።ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ 14 ቀናትን የጠየቀ ሲሆን ቀጣዩም ችሎት ለሐምሌ 3/2012 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።
Via Fidelpost

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን "ታላቁ የኅዳሴ ግድብን በውኃ መሙላትን ጨምሮ አንዳች ስምምነት ሳይደረስ የተናጠል እርምጃ ላለመውሰድ መስማማታቸውን" የግብጽ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ባሳም ራዲ በጽሁፍ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።ባሳም እንዳሉት ሶስቱ አገሮች የግድቡን የውኃ አሞላል እና አስተዳደር የተመለከተ የመጨረሻ ስምምነት ለማዘጋጀት የቴክኒክና የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ እንዲዋቀር ተስማምተዋል።የደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የአሜሪካ እና የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጽህፈት ቤት ታዛቢዎች የኮሚቴው አባል ይሆናሉ።አገራቱ በግድቡ ድርድር ላይ በመጪው ሰኞ ሊመክር ለቀጠረው የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ስለ ጉዳዩ ደብዳቤ ይጽፋሉ።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን "ታላቁ የኅዳሴ ግድብን በውኃ መሙላትን ጨምሮ አንዳች ስምምነት ሳይደረስ የተናጠል እርምጃ ላለመውሰድ መስማማታቸውን" የግብጽ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ባሳም ራዲ በጽሁፍ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።ባሳም እንዳሉት ሶስቱ አገሮች የግድቡን የውኃ አሞላል እና አስተዳደር የተመለከተ የመጨረሻ ስምምነት ለማዘጋጀት የቴክኒክና የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ እንዲዋቀር ተስማምተዋል።የደቡብ…
የውሃ ኢነርጂና መስኖ ሚንስትር አቶ ስለሺ በቀለ በዚህ ዙሪያ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት በተመራው ስብሰባ የሶስቱ ሀገራት መሪዎች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከ2-3 ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተግባብተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት በበኩላቸው ሶስቱ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት እንዲያደራድራቸው መስማማታቸውን ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት በበኩላቸው ሶስቱ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት እንዲያደራድራቸው መስማማታቸውን ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ሊሰጥ የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ "በፕሮግራም መጣበብ" ምክንያት ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተገልጿል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የጠ/ሚር ጽ/ቤት አሁን ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ግድቡን በሚቀጥሉት 2 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለመሙላት ያቀደች ሲሆን በዚሁ ጊዜ ውስጥ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሶስትዮሽ ድርድሩን ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል፣ ውሃ ለመሙላት ያላለቁ የግንባታ ስራዎችም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ይከናወናሉ ተብሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa