YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ።የክልሉን መንግስት ለማደራጀት የሚያስችል የሴክሬቴሪያት ጽ/ቤት እንዲቋቋም እና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንዲከናወኑም ወስኗል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ግብጽ ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት የአረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች ነገ በሚያደርጉት የቪዲዮ ስብሰባ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ የገቡበት ውዝግብ ላይ እንደሚወያዩ AFP ዘግቧል። ሊጉ ለግብጽ ያደላል እየተባለ ይወቀሳል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠና ስምንት (98) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሶስት (3203) ደርሷል፡፡ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረጉ የአስከሬን ምርመራዎች አንድ (1) ሰው ቫየረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሰባ ዘጠኝ (79) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-

👉አዲስ ከተማ 22
👉ቦሌ 20
👉ጉለሌ 4
👉ልደታ 3
👉ኮልፌ ቀራንዮ 4
👉ቂርቆስ 9
👉አራዳ 0
👉የካ 14
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 21
👉አቃቂ ቃሊቲ 1

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ እንደሚደረግ ገለጹ!

አዲሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።አፈ ጉባዔው ከምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ከጽ/ቤት ሃላፊ እና ዳይሬክቶሬቶች ጋር አዲሱ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ በተገኙበት ትውውቅ እና በአሰራር ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በውይይቱ የጽ/ቤቱ የሶስቱ ዓላማ ፈጻሚዎች እና የሕዝብ ግንኘነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እስካሁን የተሰሩ ዋና ዋና የስራ አፈጻጸሞችን ላይ ውይይት ተካሂዷል።በተጨማሪም የ2012 በጀት ዓመት እቅድ እና አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ተገምግሟል።ከዚህ መነሻነት የምክር ቤቱ ሁለንተናዊ አሰራር እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጎበት አጠቃላይ የአሰራር ማሻሻያ እንደሚደረግበትም ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ 100 ቀናቶች
(መጋቢት 4 - ሰኔ 14)

@YeneTube @FikerAssefa
በፈረንሳይ ከወራት በኋላ ታዳጊዎች ትምህርት ጀመሩ!

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በፈረንሳይ ከሦስት ወራት በላይ ተዘግተው የቆዩ ትምህርት ቤቶች በመከፈታቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ።አገሪቱ ለወራት ጥላው የነበረውን ገደብ ቀስ በቀስ ለማንሳት በወሰነችው መሰረት እስከ 15 ዓመት የሚሆኑ ታዳጊዎች ወደ ትምህርት ቤቶቻቸው እየተመለሱ ነው።ኒስ በተባለችው የፈረንሳይ ከተማ ነዋሪ የሆነች እናት ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል እንደተናገረችው ሁለት ልጆቿ ሙሉ ለሙሉ ወደ ትምህርት ቤታቸው እንደሚመለሱ ስትነግራቸው “በደስታ እንባ እየተናነቀኝ ነበር” ብላለች።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የወላይታ ዞን ምክር ቤት "የደቡብ ክልል ፀጥታ መዋቅር በሚመሩ አካላት እምነት ስለሌለንና ገለልተኛ ባለመሆናቸው" የጸጥታ ጥበቃ በዞኑ መዋቅር እንዲከናወን መወሰኑን አስታውቋል። ወላይታ ድጋፍ ሲፈልግ ከፌድራል ፀጥታ መዋቅር መተባበርን መርጧል።የደቡብ ክልል የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች በዞኑ ይሁንታ ካላገኙ በቀር ተግባራዊ እንዳይሆኑ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ወስኗል። የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከደቡብ ምክር ቤት ራሳቸውን ያገለሉ የወላይታ ተወካዮችን ያነጋግር ብሏል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት መዘጋጀቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት መዘጋጀቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።ስፖርት አካዳሚው 300 ቀላል ምልክት የሚያሳዩና ምንም ምልክት የሌላቸው ነገር ግን በቤታቸው ለመቆየት አመቺ ሁኔታ የሌላቸውን ታካሚዎች ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡ይህንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሳካ ላደረጉት የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ቡድንም ዶክተር ሊያ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
የኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ለ1 አመት ከመንፈቅ ሲመሩ በነበሩት አበበ አበባየሁ ምትክ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ስራ አስፈጻሚዋ ሌሊሴ ኔሜ ተተኩ። ጠ/ሚ አብይ አህመድ ሹመቱ ከነገ ጀምሮ እንዲጸና ወስነዋል ተብሏል።አዲሷ ተሿሚ ሌሊሴ ከሚያዝያ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ሲሰሩ ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም ብሎ በኦሮሚያ ክልል የኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሰርተዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድህረ ገፅ ያንብቡ👇👇
ethiopiainsider.com/2020/1280/

@YeneTube @FikerAssefa
በሽፍትነት ተግባር ላይ ተሰማርተው ህዝብን ሲዘርፉ የነበሩ "ፀረ-ሰላም" ሃይሎች መመታታቸውን የጠገዴ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ በጠገዴ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች እየተዘዋወሩ በሽፍትነት ተግባር ተሰማርተው ሰዎችን በማገትና በመዝረፍ የአካባቢውን ህዝብ ሠላም አሳጥተው የነበሩ ዋሴ ፈለቀ እና አበረ ታፈረ የተባሉ "ፀረ-ሠላም ሃይሎች" በጠገዴ ወረዳ ሰጋሎ ቀበሌ ልዩ ስሙ አዲባራ ከተባለ ቦታ ሰኔ 13/2012 ዓ/ም ከቀኑ 11:00 አካባቢ የአማራ ልዩ-ሃይል ከቀበሌው ሚሊሻ ጋር በጋራ በመሆን ባደረገው ጥረት እንደተመቱ የጠገዴ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ታደለ ይስማው ተናግረዋል።ሃላፊው አያይዘው እንደገለፁት በወረዳው ያለውን የፀጥታ ችግር የበለጠ ለማስተካከል ሲባል የወረዳው የህብረተሰብ ክፍል በመሰል ተግባራት ላይ የተሰማሩ ፀረ-ሰላም ሃይሎችን በማጋለጥና በመከላከል ረገድ ከፀጥታ አካላት ጎን ሊሰለፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ: የጠገዴ ወረዳ ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ግብፅ ባለፈው ቅዳሜ ለሁለተኛ ግዜ ያስገባችውን አቤቱታ ተከትሎ በግድቡ ዙርያ አቋሟን የሚገልፅ ደብዳቤ አስገብታለች።ሙሉ ደብዳቤው ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሊደርሱ የነበሩ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፍ ተችሏል-- ኢመደኤ

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን የኢትዮጵያ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ሰኔ 10፣ 12 ፣ 13 እና 14/2012 ዓ.ም መቀመጫቸዉን ግብጽ ያደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታውቋል።የሳይበር ጥቃት ሙከራው የተቃጣው ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ (Cyber_Horus Group)፣ አኑቢስ ዶት ሃከር (AnuBis.Hacker) እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ (Security_By_Passed) በተባሉ የሳይበር አጥቂዎች አማካይነት መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

ምንጭ ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ከቦስተን የመጡ 38 የኦስጅን ኮምፕረሰሮችን ጨምሮ የተላኩልንን 61 ፓኬጅ የ8ኛ ዙር የህክምና መሳርያዎችናና ቁሳቁሶችን በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ልከናል:: ለወገን ደራሽ ወገን ነው:: የቻላችሁ ወደ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ኤምባሲያችን በሚከተለው አድራሻ ላኩልን:: ስለመልካም አሳቢነታችሁ እናመሰግናለን!

-Ambassador Fitsum Arega
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላቸውን አለመግባባት ለመፍታት ሰለማዊ በሆነ መንገድ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፋን ጃሪክ እንዳሉት ሀገራቱ በህዳሴ ግድቡ ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በልዩነቶቻቸው ላይ በጋራ መምከር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ቃል አቃባዩ ሀገራቱ እ.ኤ.አ. በ2015 በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነቶች ዓለም አቀፍ ህጎችን መሰረት በማድረግና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ ሁኔታ በትብብር መንፈስ ለመፍታት ያስቀመጡትን መርህ በመከተል ለችግሮቻቸው እልባት ማበጀት እንደሚገባቸውም ነው የገለፁት።

ምንጭ፦ ሲጂቲ ኤን/ETV
@YeneTube @FikerAssefa
‹‹የጊዮን ሆቴሉ ሳባ አዳራሽ በድንገት አልፈረሰም››
-አዲስ ማለዳ የሰኔ 13፣ 85ኛ እትም

በግዮን ሆቴል ስር ይገኝ የነበረው ሳባ አዳራሽ ህዳር 23/2012 በድንገት ፈርሷል መባሉ ሐሰት እንደሆነ ማንነታቸው እንዲጠቀስ የማይፈልጉ የሆቴሉ ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

ከ7 ወር በፊት በድንገት ፈርሷል ተብሎ በመገናኛ ብዙኋን የተዘገበው ሳባ አዳራሽ አፈራረስ ድንገተኛ እንዳልነበረ፣ ነገር ግን እንደዛ እንዲታወቅ እንደተፈለገ ሠራተኞቹ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።አሁን ድርጅቱን እያስተዳደሩ ካሉት ሰው በፊት የነበሩት ሥራ አስኪያጅ ሰፊ አዳራሽ እንዲፈጠር ሳባ አዳራሽን ከሌላ አዳራሽ ጋር ለመቀላቀል ሲያደርጉ በነበረው ጥረት ችግር ተፈጥሮ አዳራሹ መፍረሱን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ሠራተኞቹ ሳባ አዳራሽ 73 ዓመት የቆየ እና ከዚህ በኋላም ረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል ቅርስ ነበር፤ ነገር ግን እውቀትን መሰረት ያደረገ ሥራ ባለመሰራቱ የመደርመስ አደጋ ሊደርስበት ችሏል ሲሉ አስረድተዋል።

በጊዜውም ባለሙያ አይቶት የሳባ አዳራሽ ዋናው ምሰሶ ከተነካካ እንደሚፈርስ እና የቆመውም በእርሱ ድጋፍ እንደሆነ እንደተነገራቸው ሠራተኞቹ ያነሳሉ።ነገር ግን በጊዜው የነበሩት ሥራ አስኪያጅ የባለሙያውን ሀሳብ ወደ ጎን በመተው አንድ ላይ ለማድረግ ሲጥሩ እንደነበር እና በዚህ ሒደት ዋና ቋሚው (ምሰሶ) በመነካቱ ምክንያት አዳራሹ አቅም አጥቶ እንደተደረመሰ ምንጮቹ ተናግረዋል። ሠራተኞቹ ‹‹ይህ ህንጻ እንዴት ፈረሰ ተብላችሁ ብትጠየቁ፣ በእራሱ ሳይነካ በድንገት ተደረመሰ በማለት እንድትመልሱ›› ብለው የሆቴሉ አስተዳዳሪዎች እንዳስገደዷቸው ተናግረዋል።

በተጨማሪም ስለ አዳራሹ መፍረስ መንግሥት ምርመራ አላደረገም፣ ምንም ዓይነት የመቆርቆር ስሜትም አላሳየም ሲሉም ወቅሰዋል።በዚህም ምክንያት ይላሉ ሠራተኞቹ በመደርመስ አደጋ ሳባ አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ እንደወደመ ተደርጎ ህብረተሰቡ እንዲረዳ ተደርጓል። በተጨማሪ የሳባ አዳራሽ በተደረመሰ ጊዜ የጊዮን ሆቴል ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ገበረፃድቃን አባይ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ አዲስ ማለዳ በስልክ አግኝታቸው የነበረ ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ለተደረመሰው አዳራሽ የመድህን ክፍያ ሆቴሉ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት መደርመስ በስምምነቱ እንዳልተካተተ ጠቅሶ ውድቅ ማድረጉን አዲስ ማለዳ በ72ኛ እትሟ ጠቅሳ ነበር። ይህንን አስመልክቶ አዲስ ማለዳ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት መንግሥቱ መሃሩን ለውጥ እንዳለ አናግራ ተጨማሪ መረጃ በቅርቡ ከቅርንጫፍ እንዳልመጣ ምላሽ አግኝታለች።

ነገር ግን አዲስ ማለዳ በ72ተኛ እትሟ የመድህን ካሳ ሆቴሉ መከልከሉን አስመልክታ ባስነበበችው ዜና የመድን ድርጅቱ የጠቅላላ መድህን ጽ/ፈት ቤት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፍክሪ አብዱልመጅድ ሆቴሉ የረጅም ዘመን ደንበኛ በመሆኑ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የወደመውን ንብረት እያጠና መሆኑን ገልፀው ነበር። በዚህም መሠረት በጥናት የተገኘው 4.5 ሚሊዮን ብር ውድመት በእርዳታ መልክ ለሆቴሉ እንዲሰጥ በከፍተኛ አመራሮች መወሰኑን ገልፀው ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
ከአማራ ክልል ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል በተካለሉ አካባቢዎች ምርጫ እንዳይኬሄድ የእግድ ጥያቄ ሊያቀርብ መሆኑን አብን አስታወቀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫው የኮሮና ቫይረስ ስጋት መሆኑ ካቆመ ከዘጠኝ ወር በኋላ ይከናወናል ሲል ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚቀበለውና በህግ መንገድ እንደተካሄደ እንደሚያምን ገልጿል። የንቅናቄው ምክትል ሊቀ መንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት "የአማራ ህዝብ ግዛቶች በነበሩትና በትግራይ ክልል አስተዳደር በማን አለብኝነት ያለአገባብ በተወሰዱት አካባቢዎች ማለትም በወልቃይት፣ በሁመራ፣ በራያ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በመሳሰሉት አካባቢዎች ምርጫ እንደምንወዳደር በማኒፌስቷችን አስቀምጠናል" ብለዋል።ትግራይ ክልል ምርጫ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ተከትሎ በነዚህ ግዛቶች አሁን ሊደረግ የታቀደው ምርጫ እንዲታገድልን ለመጠየቅ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡

#Ethio_FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።

ማእከሉ መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን የካፌ አገልግሎትና ዋይፋይ የተዘጋጀለት ነው።በማእከሉ የትኛውም ዜጋ ስለከተማዋ እቅዶችና ፕሮጀክቶች መመልከትና የራሱን ሀሳብ በፅሁፍና በድምፅ መስጠት ይችላል።የተሰጡት አስተያየቶች በቦታው የሚገኙ ባለሙያዎች በማሰባሰብ ለከንቲባው በየጊዜው የሚያቀርቡ ይሆናል። የማእከሉ መቋቋም የከተማዋ ነዋሪ በከተማዋ ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲጨምርና ስለ ከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠርና ግልፅነት ለመፍጠር ያለመ ነው።

Via ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa