የአለም ጤና ድርጅት (WHO) ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከቀናት በፊት ሁለት ፈረንሳያዊያን ሳይንቲስቶች የኮቪድ-19 ሙከራ በአፍሪካ መደረግ አለበት ባሉት ዙሪያ ጋዜጠኞች ሲጠይቋቸው ሳይንቲስቶቹን "ዘረኛ" በማለት ኮንነዋል።
#AfricansAreNotLabRats
@YeneTube @FikerAssefa
#AfricansAreNotLabRats
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገረ ፈረንሳይ በ24 ሰዐት ሪፖርቷ 833 ሞት ሪፖርት ያደረገች ሲሆን ይህ ቁጥር ከዚህ በፊት በ(Nursing Home) ህይወታቸው አልፎ ያልተቆጠሩትን ይጨምራል። ይህንንም ተከትሎ እስካሁን የሞቱት ሰዎች ቁጥር 8911 መድረሱን የሀገሪቱን የጤና ሚኒስትር ጠቅሶ የዘገበው አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ ሰራተኞቼን እየቀነስኩ እንዳለው በየሚዲያው የሚወራው ሀሰት ነው ብሏል ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ። መግለጫው ግን በዋነኝነት ቅሬታውን ስላቀረቡት በኮንትራት ይሰሩ ስለነበሩ ሰራተኞች የሚለው ነገር የለም።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ቤኒን የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ማግኘቷን የሀገሪቱ የጤና ሚንስትር ይፋ አድርገዋል።
ተጠቂዋ የ43 አመት ሴት ስትሆን በስም ካተጠቀሰ ሀገር ትናንት የገባች መሆኗ ታውቋል፣ ይህም ቤኒንን በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ያለባት 52ኛ ሀገር ሆናለች።
ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
ተጠቂዋ የ43 አመት ሴት ስትሆን በስም ካተጠቀሰ ሀገር ትናንት የገባች መሆኗ ታውቋል፣ ይህም ቤኒንን በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ያለባት 52ኛ ሀገር ሆናለች።
ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
ጉራጌ ዞን - ማናቸውም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ተሽከርካሪዎች ከየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ወደ ጉራጌ ዞን እንዳይገቡ ተወሰነ።
በመንግስት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ገደብ መጣሉንም ተመልክቷል።
የዞኑ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ንዳ የቫይረሱ ስርጭት ለመከላከል የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ ዞኑ እንዳይገቡና መናኸሪያዎች አገልግሎት እናዳይሰጡ መደረጉን ተከትሎ በህገወጥ መንገድ ወደ ዞኑ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየተበራከተ ይገኛል።
የበሽታው አስከፊነት አሳሳቢ በመሆኑ ዞኑ ተጨማሪ እርምጃዎች እየወሰደ ሲሆን ከነገ 29/07/2012 ጀምሮ ትንንሽ የቤት መኪኖችና ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የግል ተሽከርካሪዎች ወደ ዞኑ እንዳይገቡ ተወስኗል ብለዋል።
ከዞኑ ወደ ወረዳዎች፣ ከወረዳዎች ወደ ዞን ማዕከል እንዲሁም ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ዞኑ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ገደብ መጣሉን አቶ ተሾመ ገልጸዋል ።
በዚሁ መሰረት፡-
1. ባለ ሁለት ገቢና (double cap ) ተሽከርካሪዎች ሁለት ሰዎችና ሹፌር
2. ሎንግ ቤዝና ሀርድቶፕ ተሽከርካሪዎች ሶስት ሰዎችና ሹፌሩ
3. ወደ ዞኑና ወረዳዎች የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ከቢሮአቸው የተፃፈ ደብዳቤ መያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን
4. ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ባህር ማዶንም ጨምሮ ወደ ዞኑ ሲመጡ ለ14 ቀናት በተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ስፍራዎች እንዲቆዩ ተወስኗል።
Via:- Gurage Zone Government Communication Affairs Department
@YeneTube @Fikerassefa

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ህመማቸው ስለጠናባቸው ወደ ጽኑ ህመምተኞች ክፍል መግባታቸው ተነግሯል ።
ምንጭ: ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 1,600 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል ::
የክልሉ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርና ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ በልዩ ሁኔታ 1,548 ወንድና 53 ሴት በድምሩ 1,601 ታራሚዎች እንዲፈቱ ወስኗል።
ምንጭ ~ #የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
@Yenetube @Fikerassef

#News_Alert
ጉራጌ ዞን የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ተከስቶ ወረርሽኙን ለመከላከል ግብረ ኃይል ተቋቅሞ እየተሰራ እንደሚገኝ ከጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።
ግብረ ሀይሉ ቤት ለቤት ክትባት በመስጠት ላይ ይገኛል እስካሁንም ከ21,829 ሰዎች በላይ ወረርሽኙኝ ለመከላከል ለጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ክትባት እንደተደረገላቸው ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ተመልክተናል።
የሚዲያ አካላት ህብረተሰብ እራሱን ከቢጫ ወባ እንዲሁም ከኮሮና ቫይረስ እንዲታደጉ የድርሻችሁን ተወጡ!!

YeneTube
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ ሰራተኞቼን እየቀነስኩ እንዳለው በየሚዲያው የሚወራው ሀሰት ነው ብሏል ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ። መግለጫው ግን በዋነኝነት ቅሬታውን ስላቀረቡት በኮንትራት ይሰሩ ስለነበሩ ሰራተኞች የሚለው ነገር የለም። @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየርመንገድ መሰረታዊ ሰራተኞች ማህበር ለአየር መንገድ ላወጣው የሰጠው ምላሽ ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰአታት በፊት ባወጣው መግለጫ መደበኛ ሰራተኞቹን እንደቀነሰ በየሚዲያው የሚወራው ሀሰት ነው ብሏል። መግለጫው ግን በዋነኝነት ቅሬታውን ስላቀረቡት በኮንትራት ስለሚሰሩ ሰራተኞች እና በህገወጥ መንገድ የስራ ውሉ ስለተቋረጠው ስለ ማህበራችን ሊቀመንበር ካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን የሚለው ነገር የለም።
ይሕ መግለጫ ፤ በተደጋጋሚ ማህበራችን እያሰማ ካለው የ ኮንትራት ሰራተኞች (የበረራ አስተናጋጆች፣ የትኬቲንግ ሰራተኞች፣ ቴክኒሽያኖች እንዲሁም ሌሎች) ያለ ደሞዝ እረፍት እንዲወጡ መደረግ ጉዳይ ጋር ግንኙነት የሌለው ፣ ቋሚ ሰራተኞችን ብቻ ማእከል ያደረገ ህዝብ እና መንግስት ላይ ብዥታ የሚፈጥር ሆኖ አግኝተነዋል!
ስለዚህ የማህበራችን አባላት ፣ ሰራተኞች፣ የኢትዮጲያ ሕዝብ እና መንግስት ማህበራችን በአሁኑ ወቅት በዋናነት እያነሳ ያለው ጉዳይ የኮንትራት ሰራተኞች ያለ ክፍያ እረፍት እንዲወጡ መደረጉ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ነገር አለመጠቀሱን ልብ እንድትሉልን እንወዳለን!
#ፍትህ_ለሰራተኞች!!
#ፍትህ_ለማህበራችን_ሊቀመንበር_ካፒቴን_የሺዋስ!
Via:- Tsefay Getent

በአፍሪካ አህጉር በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ መብለጡ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን 348 ሺህ መብለጡን የሚያሳየው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፤ ከእነዚህም ውስጥ 10 ሺህ 68ቱ በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ናቸው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ74 ሺህ ሲበልጥ፤ በአፍሪካም በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ480 ተሻግሯል።
በአፍርካ ከ990 በላይ ሰዎች ደግሞ ከወረርሽኙ ማገገማቸውንም ነው የዩኒቨርሲቲው መረጃ የሚያመላክት ሲሆን፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ284 ሒህ በላይ ሰዎች አገግመዋል።
Via:- FBC

ቻይና አዲስ ሞት እየተመዘገበ እንዳልሆነ አስታወቀች!
ቻይና ከትናንትናው እለት ጀምሮ በኮሮናቫይረስ የሞተባት ሰው እንደሌለ አስታወቀች።በባለፉት ቀናት ውስጥ የነበረው የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ የነበረ ሲሆን በትናንትናው እለትም አዲስ ሞት እንዳልነበር ተዘግቧል። ዘገባው አክሎም ከቻይና የሚመጣውን መረጃ ሙሉ በሙሉ ማመን ቢያዳግትም ሞት አለመከሰቱን ተስፋ ሰጭ ነው ብሎታል።የቫይረሱ መነሻ ናት የተባለችው ዉሃንም ወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ ተዛምቶ በነበረበት ወቅት ደንግጋቸው የነበሩ ህግጋትንም በማላላት ላይ ናት። ከወራትም በኋላ ሰዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡም ተፈቅዶላቸዋል።
Via BBC

ጠቅላይ ሚኒስትሯ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃባት እንግሊዝ #ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ማዘጋጀቷን አስታወቀች።
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪሰ ጆንሰን በኮቪድ 19 መያዛቸዉን ተከትሎ ሕመማቸው በመባባሱ ትናንት ምሽት ወደ ጽኑ ሕክምና ክትትል መግባታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመማቸው ቢጸና ወይም ሌላ የከፋ ችግር ቢገጥማቸዉ በሚል ዶሚኒክ ራብ በተጠባባቂነት መመረጣቸዉ ታዉቋል፡፡
የአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ዶሚኒክ ራብ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን መምራት የማይችሉ ደረጃ ላይ ከደረሱ እንደሚተኳቸዉም ሮይተርስ አስነብቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በፅኑ ህሙማን ክፍል እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን እንግሊዝ ግን አሁንም ድረስ በእርሳቸዉ ነዉ የምትመራዉ፡፡
የ46 አመቱ ዶሚኒክ ራብ እንግሊዝ ከአዉሮፓ ህብረት መዉጣት የለብትም በሚል የቦሪስን ሃሳብ ሲቃወሙ እንደነበረም ተነግሯል፡፡
ራብ እ.ኤ .አ በ2010 ወደ ፓርላማ ከመገባታቸዉ በፊት በተለያዩ የድፕሎማሲ ስራዎች ላይ አገራቸዉን አገልግለዋል፡፡
Via:- Ethio FM

ቶዮታ በኢትዮጵያ የመለዋወጫ ፋብሪካ ሊገነባ ነው!
የጃፓኑ ግዙፍ የአውቶሞቲቭ ኩባንያ ቶዮታ በኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎች ዕቃ መለዋወጫ ማምረቻ ለመገንባት ጥናት ማጠናቀቁ ተገለፀ። የብረታ ብረት ኢንዱሰትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቀው፣ ቶዮታ ኩባንያ በኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎችን ዕቃ መለዋለጫ ለመገንባት ጥናቱን ያጠናቀቀ ሲሆን፣ በቀጣይ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ወደ ግንባታ እንደሚገባ ገልጿል።
Via Addis Maleda

ባሕር ዳር የፀረ ተዋሲያን ኬሚካል ርጭት እያካሄደች ነው።
ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የኮሮና ወረርሽኝን ስርጭትን ለመቀነስ ዛሬ በአውራ ጎዳናወቿ የፀረ ተህዋሲያን ኬሚካል ርጭት ማድረግ ጀምራለች። ከረፋዱ 3፡00 ገደማ ጀምሮ ከፓፒረስ ፊት ለፊት ከሚገኘው አደባባይ አንስቶ በጥበብ ሕንጻ እስከ ሃኒ ጋርደን አደባባይ ያለው የከተማዋ አውራ መንገድ በፀረ ተህዋሲያን ኬሚካል ተረጭቷል።ርጭቱ በሁሉም የከተማዋ ክፍል እንደሚካሄድ የከተማዋ ከንቲባ ተቀዳሚ ምክትል መሐሪ ታደሰ (ዶክተር) አስታውቀዋል። ከዋና ዋና መንገዶች በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥና ሰው በብዛት ያስተናግዱ የነበሩ የገበያ ቦታዎችም የኬሚካል ርጭት ሊካድባው ነው።
ምንጭ:አብመድ

በጋምቤላ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተላለፉ ውሳኔዎችን የጣሱ 150 ተሽከርካሪዎች ተያዙ!
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡቲያንግ ኡቻን ለኢዜአ እንደገለጹት 150 የሞተርና የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በቀጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት አሽከርሪዎቹ የክልሉ መንግስት ቫይረሱን ለመከላከል ለ14 ቀናት ያስተላፋቸውን ውሳኔዎች ተላልፈው በመገኘታቸው ነው።ቫይረሱን ለመከላከል የባጃጅ ትራንስፖርት ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም የሞተር ሳይክሎች ደግሞ ከአንድ በላይ እንዳይጭኑ መንግስት ውሳኔ ቢያሳልፍም አሽከርካሪዎች ውሳኔዎችን ተላልፈው በመገኘታቸው ተሽከርካሪዎቻቸው እንዲያዙ ተደርጓል። ባለፉት ሁለት ቀናት በኮሚሽኑ ክትትል በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተሽከርካሪዎች መካከል 137ቱ ሞተሮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ባጃጆች መሆናቸውን ገልጸዋል።
Via ENA