YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#News_Alert

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ተያዘ

በተሽከርካሪ እቃዎች ንግድ ላይ የተሰማራው ግለሰብ ብዛት ያላቸውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ የአፍና የአፍንጫ መሽፈኛ ማስክ በሁለት ተሽከርካሪዎች አስጭኖ የተያዘው ግለሰብ በተሽከርካሪ እቃ ንግድ ሰራ ላይ የተሰማራ መሆኑን መርማሪው አስረድተው ግለሰቡ እነዚህን ምርቶች የማከፋፈል ሆነ የመሸጥ ፍቃድ እንደሌለው በምርመራ መረጋገጡ ገልፀዋል፡፡

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
#News_Alert

ጉራጌ ዞን የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ተከስቶ ወረርሽኙን ለመከላከል ግብረ ኃይል ተቋቅሞ እየተሰራ እንደሚገኝ ከጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።

ግብረ ሀይሉ ቤት ለቤት ክትባት በመስጠት ላይ ይገኛል እስካሁንም ከ21,829 ሰዎች በላይ ወረርሽኙኝ ለመከላከል ለጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ክትባት እንደተደረገላቸው ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ተመልክተናል።

የሚዲያ አካላት ህብረተሰብ እራሱን ከቢጫ ወባ እንዲሁም ከኮሮና ቫይረስ እንዲታደጉ የድርሻችሁን ተወጡ!!

@Yenetube @Fikerassefa
#News_Alert ጎረቤት ሀገር ጅቡቲ በ24 ሰዐት ውስጥ 141 ኬዝ ሪፓርት ተደርጓል። እስከዛሬ 732 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን ተነግሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
#News_alert በጣልያን በ24 ሰዐት ውስጥ 3,493 አዲስ ኬዝ እና 575 ሞት ተመዝግቧል።

በጣልያን 172,434 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ሲኖሩ 22,745 ህይወታቸውን አተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa