YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የማላዊ ፕሬዝዳንት እና ካቢኔዎች የደሞዛቸውን 10% ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እንዲውል መወሰናቸውን የማላዊ ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሃአሪካ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ቀናት የሚደርገው የገበያ ግብይት አካላዊ እርቀትን በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ አለመሆኑን የገመገመው የኮቪድ መከላከል ግበረ-ኃይል፣ በሳምንት 1 ቀን ይሄውም ቅዳሜ ቀን ብቻ እንዲሆንና እጅግ በተራራቀ መንገድ ግብይቱ እንዲያከናውን ያሳሰበ ሲሆን፣ የጸጥታ አካላት ክትትል እንዲያደርጉም ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በክልሉ ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በተሻለ መንገድ ለማስቀጠል ሲባል፣ ከአሶሳ ግልገል በለስ ከተማ የሚደረገው የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ለቀጣዮቹ 2 ሳምንታት እንዲቋረጥ ግብረ-ኃይሉ ወስኗል፡፡በከልሉ የሚንቀሳቀሱት ባለ 3 እግር ተሸከርካሪዎች 1 ሰው ብቻ እንዲጭኑ የተወሰነውን ውሳኔ ለመከታተል ያመች ዘንድ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሠዓት ብቻ እንዲሠሩ ገደም አስቀምጧል፡፡

ህብረተሰቡ የሚያከናውናቸውን የሠርግ ክንዋኔዎች ለሚቀጥሉት 2 ሳምንታት እንዲገታ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን፣ ሀዘንን ጨምሮ የተለያዩ አስገዳጅ ማህበራዊ ክንዋኔዎችን እጅግ ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንዲያከናውንም አሳስቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና በምጣኔ ኃብቷ ላይ የሚያደረስውን አደጋ ለመቀነስ የአለም ባንክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ። የባንኩ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ተጠሪ ካሮሊን ተርከ እንደገለፁት ከሆነ ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የሕብረተሰብ ጤና አገልግሎትን በማሻሻል ረገድ ውጤታማ ስራ የሰራች ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የአገሪቱን የጤና ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚፈታተነው አስታውቀዋል።

via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
ፈረንሳይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከፍተኛ የተባለ የምጣኔ ሃብት ወድቀት እያጋጠማት እንደሆነ የፈረንሳይ የምጣኔ ሃብትና እና ገንዘብ ሚኒስትር ብሩኖ ል ማይሬ አሳሰቡ፡፡

ፈረንሳይ በአውሮፓዊያኑ 2009 የተከሰተውን ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ተከትሎ ምጣኔ ሃብቷ በ2.2 በመቶ አሽቆልቁሏል፡፡
ባለፈው ወር መንግሥት የአገሪቷ ምጣኔ ሃብት በ2020 አንድ በመቶ እንደሚቀንስ ግምቱን ቢያስቀምጥም፤ ሚኒስትር ሌ ማይሬ አሃዙ ከተገመተው ማለፉን ዛሬ ለሴኔቱ አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በ2009 ከነበረው 2.2 በመቶ የምጣኔ ሃብት ውድቀት ሊበልጥ እንደሚችል በመግለጽ፤ አገሪቷ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ቀውስ እያጋጠማት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

via:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
በጃንሜዳ የተዘጋጀው የአትክልት ግብይት ቦታ ከነገ ጀምሮ ሥራውን እንደሚጀምር ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር በተወሰነው መሰረት ጃንሜዳን የማዘጋጀት ስራ መጠናቁን ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
ሩዋንዳ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል 109.4 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.አም.ኤፍ) በማግኝት የመጀመሪያዋ የአፍሪካ አገር ሆናለች። ብድሩን በንግድ፣ በቱሪዝም እና በውጪ ምንዛሬ ክምችት በኩል ያሉባትን ችግሮች ለመቅረፍ የምትጠቀመው ሲሆን አብዛኛውን ብድር ግን ለጤናው ዘርፍ እንደምታውለው ዲደብሊው አፍሪካ (ዶቼቬለ) ዘግቧል።
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር የተፈራረሙት የ24 ሚሊዮን ፓውንድ የድጋፍ ስምምነት በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን እና ስደተኞች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አስታውቋል።

በዚህም ትምህርት፣ ጤና እና መጠለያን ጨምሮ የተለያዩ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገልጿል።

via:- EBC
@Yenetube @fikerassefa
ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ከሚደረግባቸው ሀገራት አንዷ ነች!

ኢትዮጵያ አሁን ባሳየችው የምርመራ አቅም ከ1 ሚልየን ሰዎች ዉስጥ 16 ሰዎችን ነው እየመረመረች ያለቸው፡፡

Via Asham TV
@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ ውስጥ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል ።

ዛሬ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንደገለጹት በ24 ሰዓት ውስጥ 16 አዲስ ተጠቂዎች የተገኙ ሲሆን አጠቃላይ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 158 ደርሷል።

ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
#እጆን_ይታጠቡ #እቤት_ይቀመጡ #የሚያስፈልጎትን_እናመጣለን!

ማህበራዊ ርቀትን ለመደገፍ ከቤት ለማይወጡ ወገኖቻችን በጥንቃቄ የታሸጉ ለዕለታዊ ፍጆታዎችን እቤትዎ ድረስ ለማድረስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

ለበለጠ መረጃ 6081 ይደውሉ!

PUT YOUR AD FOR FREE
YeneTube
ኬንያ ውስጥ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል ። ዛሬ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንደገለጹት በ24 ሰዓት ውስጥ 16 አዲስ ተጠቂዎች የተገኙ ሲሆን አጠቃላይ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 158 ደርሷል። ምንጭ:CGTN @YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ ከመዲናዋ ናይሮቢም ሆነ ወደ መዲናዋ የሚደረግ ጉዞ ከለከለች።

ኬንያ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ከመዲናዋም ሆነ ወደ መዲናዋ ናይሮቢ የጉዞ እገዳ መጣሉን ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ አስታወቁ። የጉዞ እገዳው ከዛሬ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት (April 6, 2020 7:00 PM) ጀምሮ ለመጭዎቹ 21ቀናት የሚዘልቅ ነው።ከናይሮቢ በተጨማሪም በሌሎች ሦስት የባህር ዳርቻ ከተሞች፤ ሞምባሳ፣ ክሊፍ እና ኪዋሌ እገዳው ተጥሏል።

ምንጭ: በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ጉረቤት ሀገር ጁቡቲ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 90 ደርሷል። እስካሁን የሞት አልተመዘገበም።

@YeneTube @Fikerassefa
እንግሊዝ ውስጥ የሟቾች ቁጥር ቀንሷል።

ባለፉት 24 ሰአት ውስጥ 403 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ይህም በቅዳሜው ሪፖርት ከተመዘገበው 637 በትናንትናው ደግሞ 555 አንፃር መሻሻል ማሳየቱ ተጠቁሟል። እንደብሪታንያ ሲታይ ደግሞ ዌልስ 27፣ ስኮትላንድ ደግሞ ሁለት ሞት ሲመዘገብባቸው ቁጥሩን ወደ 433 ከፍ ያደርገዋል።

ምንጭ:ሜትሮ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከህብረተሰቡ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ የተጀመረውን ኢትዮ ቴሌኮም በ444 አጭር ቁጥር ገቢ ማሰባሰብ ስራ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ።በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ የተጀመረውን የመከላከል ስራ ለመደገፍ በሚል ኢትዮ ቴሌኮም በ444 አጭር ቁጥር አገልግሎት ገቢ ለመሰብሰብ አሰራር ዘርግቶ ነበር።በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ስራም 311 ሺህ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ብር መሰብሰቡን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።ኢትዮ ቴሌኮም ህብረተሰቡ ላደረገው ጥረት ምስጋናውን አቅርቦ ድጋፉ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በ51 የአፍሪክ አገራት እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 414 ሞት ተመዝግቧል!

ቫይረሱ በ51 የአፍሪክ ህብረት አባል ሀገራት እስካሁን ድረስ 414 ሰዎችን ለሞት ሲያድርግ 9 ሺህ 198 የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ሌሎች 813 ደግሞ ከበሽታው ማገገማቸውን የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል።ቫይረሱ መካከለኛው አፍሪካን ጭምሮ በአራቱም ማዓዘናት የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ድረስ በመካከለኛው አፍሪካ የ33 ሰዎችን ህይዎት ሲቀጥፍ 917 ሰዎችን ደግሞ አጥቅቷል። 30ዎቹ ደግሞ በተደረገላቸው ክትትል ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ አገግመዋል።

በሌላ በኩል በምስራቅ አፍሪካ ደግሞ በ778 ሰዎች ላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 16 ሰዎችን ለሞት ሲዳርግ 28 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው መዳን ችለዋል። እንደ ህብረቱ መረጃ ከሆነ በሰሜን አፍሪካ ባሉ አገራት ደግሞ 298 ሞት ሲመዘገብ በ4ሽህ 43 ሰዎች ላይ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። 420 የሚሆኑት ደግሞ ከበሽታው ማገገማቸው ተገልጿል።

በደቡባዊ አፍሪካ 16 ሞት ሲመዘገብ በ1ሺህ 756 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ሲገኝባቸው ሌሎች 53 ህሙማን ደግሞ ማገገማቸውን የህብረቱ መረጃ ይጠቁማል።በምዕራብ አፍሪካ ደግሞ የ51 ሰዎች ህይዎት ሲያልፍ 1ሺህ 707 ሰዎች በበሸታው ተጠቅተዋል።282 የሚሆኑት ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ሲል ህብረቱ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ችግሩ ቢከሰት በሚወሰደው እርምጃ የቅድመ ዝግጅት ገለፃ ተሰጠ።

ገለፃው የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ጄኔራል ብርሃኑ ጁላና የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጎልፍ ክበብ ተካሂዷል።በዚህ ስነስርዓት ሰራዊቱ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያደርገው እንቅስቃሴና ለመከላከል ስራው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸውና በተቋሙ አባላት የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ቀርበዋል፡፡

Via የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት/Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በታክሲዎች የአገልግሎት መስጫ ሰዓት ላይ ማሻሻያ ተደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በታክሲዎች የአገልግሎት መስጫ ሰዓት ላይ ማሻሻያ መደረጉን አስታወቀ።በመሆኑም ከነገ ጀምሮ በቀጣይ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ ታክሲም ሆነ ሃይገር አውቶቡስ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት በፊት እና ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደርጓል።በአንጻሩ አንበሳ እና ሸገር አውቶቡሶች በተለመደው የአገልግሎት መስጫ ሰዓታቸው አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን፥ ታክሲዎችና ሃይገር አውቶቡሶች የመጫን አቅማቸው ወደ መደበኛው እስከሚመለስ ቀደም ሲል የነበረው ታሪፍ በእጥፍ አድጎ ተሳፋሪዎች እንዲከፍሉ ይደረጋል ነው የተባለው።

የአንበሳ እና የሸገር አውቶቡሶች ታሪፍ በነበረበት የሚቀጥል ሆኖ መንግስት በሚያደርገው ድጎማ እንዲሸፈን ይደረጋልም ተብሏል።ማንኛውም ከተፈቀደው ሰው በላይ ጭኖና ከተፈቀደው ሰዓት ውጭ ሲሰራ የተገኘ ታክሲም ሆነ የሃይገር አውቶቡስ 5 ሺህ ብር የሚቀጣ ሲሆን፥ በተጨማሪም የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ እስከመጨረሻው እንዲታገድ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ተጠያቂ የሚደረጉም ይሆናል።

በሃይገር ባስ የተሳፋሪ ቁጥር በወንበር ልኩ በግማሽ ብቻ እንዲጭኑ የተደረገ ሲሆን፥ 14 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ውሳኔ መተላለፉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡሶች 40 ሰው ይጭን የነበረው መደበኛ አውቶቡስ 30 ሰው ብቻ የሚጭን ይሆናል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ም/ኮማንደር መንገሻ አውራሪስ የአማራ ክልል የሰላምና ህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የተሰጠ መግለጫ

"የዱከም ነዋሪ የሆኑት የ65 ዓመት ሴት በሌላ ተጓዳኝ ሕመም ምክንያት በሆስፒታላችን ለአንድ ቀን ቆይተው ነበር፡፡ይሁን እንጂ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት በማሳየታቸው የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ አንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡ ታማሚዋ በአሁኑ ሰዓት በኮተቤ ኤካ ሆሰፒታል ቀጣይ ሕክምናቸውን አንዲከታተሉ ተልከዋል፡፡
ለታማሚዋ የሕክምና አገልግሎትን ሲሰጡ ከነበሩ በርካታ የጤና ባለሙያዎች መካከል ፡ በወቅቱ አስፈለጊውን አልባሳት (PPE) አልተጠቀምንም ወይም አጠቃቀማችን በቂ አይደለም ያሉ ሰባት ባለሙያዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ባለሙያዎች መካከል ሁለቱ ታማሚዋን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው፡፡
እኝሁ ሴት በ ዛሬው የጤና ጥበቃ ሚኒስትርዋ ዶ/ር ሊያ ታደሰ መግለጫ የተገለጹት 44ኛዋ ታማሚ መሆናቸው ይታወቃል፡፡"

@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ አፍሪካ አቅማቸው አነስተኛ ለሆኑ አርሶአደሮች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ምርት እንዳያቆሙ የ1.2 ቢሊዮን ራንድ ድጎማ አደርጋለው ብላለች።

ጋና ደግሞ ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች ከደሞዛቸው የሚከፍሉት የስራ ግብር እንዲቀር ወስናለች።

ምንጭ: CGTN
@YeneTube @FikerAssefa