YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 ወቅታዊ

- በአሁን ሰዐት ማቆያ ያሉ ታማሚዎች :- 24

-ፅኑ ህሙማን : - 1

- ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ :- 3

-የተያዙ ሰዎች ድምር :- 29

- በበሽታው ተይዞ የሞተ :- 0

@Yenetube @Fikerassefa
የፊሊፒንሱ ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ሀገሪቱ የጣለችውን የእንቅስቃሴ ገደብ በሚተላለፉ ሰዎች ላይ የጸጥታ አካላት እንዲተኩሱባቸው ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። በጤና ባለሙያዎች ላይ ጥቃቶች እየደረሱ እንዳሉ መገንዘባቸውን ጠቅሰው ይህንን በሚያደርጉት ላይ ከበድ ያለ እርምጃ እንደሚወስዱ ማስጠንቀቃቸውን የሀገሪቱን ማዕከላዊ ቴሌቪዥን ጠቅሶ የዘገበው ፍራንስ 24 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
#News_Alert

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ተያዘ

በተሽከርካሪ እቃዎች ንግድ ላይ የተሰማራው ግለሰብ ብዛት ያላቸውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ የአፍና የአፍንጫ መሽፈኛ ማስክ በሁለት ተሽከርካሪዎች አስጭኖ የተያዘው ግለሰብ በተሽከርካሪ እቃ ንግድ ሰራ ላይ የተሰማራ መሆኑን መርማሪው አስረድተው ግለሰቡ እነዚህን ምርቶች የማከፋፈል ሆነ የመሸጥ ፍቃድ እንደሌለው በምርመራ መረጋገጡ ገልፀዋል፡፡

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስራ አላቆምም ብሏል!!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን እንደማያቋርጥ አስታወቀ፡፡ ምናልባት ሁኔታዎች ተባብሰው የመንግስት ተቋማት እስከ መዘጋት ቢደርሱ እንኳን ባንኩ አገልግሎት መስጠቱን እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

Via:- Ethiopian Press Agency
@Yenetube @Fikerassefa
በጣልያን ሚላን ከተማ ያለ 150 አረጋዊያን የተጠለሉበት ተቋም 63ቱ በአንድ ቀን በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ተገለጸ።

በጣሊያን ሚላን ከተማ በአረጋዊያን መንከባከቢያ ቤት ውስጥ ካሉ አረጋዊያን መካከል 63ቱ በኮሮና ቫይረስ ሂወታቸው ማለፉን CNN ዘግቧል፡፡

63ቱም አረጋዊያን ሂወታቸው ያለፈው በአንድ ቀን እንደሆነ ነው የሚላን ከተማ ከንቲባ ሳራ አራንጎ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባው አክለው እንደተናገሩትም በህይወት ያሉት አረጋዊያን በቫይረሱ እንዳይሞቱ ልዩ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

የአረጋዊያን መንከባከብያ ማእከሉ የሚገኝው ወረርሽኙ በብዛት ከተቀሰቀሰበት ከሎምባርዲ ግዛት በተወሰኑ ርቀቶች ላይ የሚገኝ ቦታ በመሆኑ ተጨማሪ ተጠቂዎች ሊኖሩ አንደሚችሉም ከንቲባው አስታውቀዋል።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @FikerAssefa
#Covid19 ምርመራ በአማራ ክልል በሶስት ከተሞች ደሴ : ባህርዳርና ጎንደር ላይ እንደሚጀምር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል ።

@Yenetube @FikerAssefa
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ክልል ለሚደረገው የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ የ200ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ።

@Yenetube @Fikerassefa
#ሰበር_ዜና : -

የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ መፈንቅለህ ርዕሰ መስተዳደር ተሞከረባቸው ስለ ተባለው ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው።

Via:- ሸምሱ ቢረዳ
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካ የተያዘው ሳምንት ሳያልቅ የንፅሕና መጠበቂያ አልኮል እና ሳኒታይዘር ማምረት እጀምራለሁ አለ፡፡

ፋብሪካው የዓለም የጤና ድርጅት WHO ያስቀመጠውን መስፈርት ተከትሎ በቀን 5 ሺ ሊትር ሳኒታይዘር ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን ለሸገር ነግሯል፡፡የብሔራዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካ በየዕለቱ ከሚያመርተው አልኮል በተጨማሪ በቀን ሩብ ሊትር መጠን ያለው 24 ሺ የፕላስቲክ ጠርሙስ ሳኒታይዘር በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ አምርቶ ለገበያ እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡በ3 ቀን ውስጥም ያመረትኩትን የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በገበያው ታገኙታላችሁ ያሉን የብሔራዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን አባተ ናቸው፡፡

ይኸው የሚመረተው ሳኒታይዘርም ከንፁህ አልኮል እንደሚዘጋጅ ሀላፊው ነግረውናል፡፡የአልኮል ፋብሪካው፣ አቅም በፈቀደ መጠን ዕለት ተዕለት ከምናመርተው አልኮል 3 እጥፍ፣ በየቀኑ 5 ሺ ሊትርም እያቀረብን ነው ብሏል፡፡ይህም ምርት በ3 እጥፍ ቢጨምርም በቂ እንዳልሆነ አቶ መስፍን ለሸገር ነግረዋል፡፡የፋብሪካው ስራ አስፈፃሚ ንጹህ አልኮልንም ለፅዳት አገልግሎት መሸጥ ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የዛሬ ዘጠኝ ኣመት ነበር በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜና መሪነት የህዳሴው ግድብ የተጀመረው።

ከዘጠኝ አመት ብኃላ 72.4 % መድረሱ ትላንት የውሃ እና መስኖ ሚንስቴር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ ሲሳይ መናገራቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከመባሉ በፊት "Project X" ይባል እንደ ነበር መረጃዎች ይጦቁማሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ!

➡️49 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።

➡️6,470 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

➡️241 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

➡️504 ሰዎች አገግመዋል።

ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
መስቀል አደባባይን በዘመናዊ መልኩ መልሶ ለማልማት ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። ቦታው ላይ ከመሬት በታች እስከ 1400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ ይገነባል ተብሏል።

ፋውንቴንና የተለያዩ መዝናኛዎችን ባካተተ መልኩ የሚገነባው መስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታው በለገሀር ቸርችል አደባባይ እስከ ፒያሳ ድረስ በሚሰራው አረንጓዴ ስፍራ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል።

Via:- Addis Ababa City PS
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በቻይና መንግስት በእርዳታ የተሰጠውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የሙቀት መጠን መለኪያ (ኢንፍራሬድን) ጨምሮ ሌሎች የህክምና ግብዓቶችን ማሰራጨት ጀመረ፡፡

ከ መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ከቻይና መንግስት በእርዳታ የተሰጠውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የህክምና ግብዓቶች ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች ያሰራጫል፡፡ የህክምና ግብዓቶቹ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዱ የሙቀት መጠን መለኪያ Infrared thermometer)፣ የፊት መሸፈኛ ጭምብል (protective face mask for medical use)፣ የፊት መሸፈኛ ፕላስቲክ (Medical Protective Goggles)፣ የህክምና ባለሙያዎች የሚለብሷቸው መከላከያ ልብሶች (Disposable Protective Clothing) ናቸው፡፡እነዚህ ለኮቪድ - 19 ኮሮና ቫይረስ ለመለየትና ለመከላከል የሚውሉ የህክምና ግብዓቶችን ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ላቋቋሟቸው የህክምና ለይቶ ማቆያ ተቋማት የሚሰራጩ ሲሆን በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሰጠው የስርጭት ክፍፍል መሰረት ይሰራጫል፡፡

Via MoHE
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ የአለም የኦቲዝም ቀን ነው!!

እንደ አለም ጤና ድርጅት ገለፃ በአለም ላይ ከሚወለዱ 160 ልጆች 1 ልጅ በኦቲዝም ይጠቃል::

ኦቲዝም ከልጅነት ጀምሮ ወደ ጉርምስና ድረስ የመቆየት አዝማሚያ አለው::

በብዛት ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ ይስተዋላል::

ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች የሚያሳዩቸው ባህርያት:-

1. በእድሜያቸው የሚጠብቅባችውን ቋንቋ አለምጠቀም ፣ ምንም ቋንቋ አለመጠቀም፣ አንዳንድ ድምጾቸን መጠቀም ፣ ትንሽ ቃላቶች መጠቀም።

2 .ከሰዎች ጋር የአይን ትይዩ ወይም ምልክታ አለመኖር እና በዙሪያቸው የሚደረጉ ነገሮች ብዙም ትርጉም አለመስጠት

3. የጋራ እይታቸው የተገደበ መሆን

4. ስማቸው ሲጠራ መልስ አለመስጠት

5. ያልተለመዱ ባህርያት ማሳየት

6. ያልተለመዱ የጣት እንቅስቃሴ ማሳየት

7. ብቻን መጫወት መምርጥ

8 .ከሰዎች የሚሰሙትን ቃላቶችን መድገም

9 .ድግግሞሽ ያለው እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም አንድ ጨዋታ መፈለግ

10. ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር ጓደኝነት መመስረት አለመቻል ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ልጆች የሚሰጡ ህክምናዎች መካከል የስፒች እና ላንጉጅ ቴራፒ እና የባህርይ ቴራፒ ዋነኞቹ ናቸው።

Via :- @speechtherapyethiopia

@Yenetube @FikerAssefa
ጣሊያን በ24 ሰዓት ሪፖርቷ 4,668 አዲስ ተጠቂዎችና 760 ሞት እንደተመዘገበባት አሳውቃለች። በእስካሁኑ ደግሞ 115,242 ሰዎች የተጠቁባት ሲሆን 13,915 ሰዎች ደግሞ ሞተውባታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ወይም በባለሥልጣናት መካከል ግጭት መኖሩን ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተለያዩ ምንጮች አስታውቀዋል።አንዳንዶቹ ምንጮች በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ ከሽፏል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ዑመርና በቀድሞ የክልሉ የፀጥታ ሃላፊ አብዱልሃዲል ሀሰን መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ወደ ውጥረት መሸጋገሩን ይገልጻሉ።ከክልሉ መንግሥት እና ከባለሥልጣናቱ ሁነኛ መረጃ ለማግኘት የድሬዳዋው ወኪላችን መሳይ ተክሉ ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ200,000 የበለጠ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 50,000ን ተሻግሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ ክልሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቋቋመው ክልላዊ ግብረሃይል የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ስምሪት ዕገዳ የተጣለበት ቢሆንም የቤት፣ የጭነት እና ለመንግስት ስራ አገልግሎት የሚሰጡ መኪናዎች ባልተገባ ሁኔታ ሰው በመጫን የሚያመላልሱ ሲሆን ይህም ህብረተሰቡን ለቫይረሱ የሚያጋልጥ በመሆኑ ተገቢ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ግብረሃይሉ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የመንግስት ሰራተኞች በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የተደረገ ቢሆንም የቫይረሱ ስርጭት እየሰፋ ስለሄደ አሁንም ሰራተኞች እንደየተቋሙ የስራ አስፈላጊነት ቁጥራቸው መቀነስ እንዳለበት አመላክቷል፡፡

ግብረሃይሉ ለክልሉ የጤና ባለሙያዎች ጥሪ አቅርቧል፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ህብረተሰቡ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲሁም በገበያ፣ በኃይማኖት ቦታዎችና በሌሎችም አካባቢዎች ከቫይረሱ ስርጭት እንዲጠነቀቅም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

Via:- SRTV
@Yenetube @Fikerassefa
በኤርትራ ዛሬ (መጋቢት 24) በተካሄደ ምርመራ አራት ሰዎች በCOVID19 ቫይረስ የተያዙ መሆናቸው መረጋገጡን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ተናገረ።

ከሕሙማኑ ሦስቱ ሴቶች ናቸው። ሁሉም ሀገሪቱ በመንገደኛ በረራዎች ላይ እግድ ከመጣሏ በፊት ከባህር ማዶ ወደ ኤርትራ የገቡ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።ይህም በኤርትራ እስከዛሬዋ ዕለት በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡትን ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር 22 አድርሶታል።ሁሉም ሕሙማን አስፈላጊ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የጤና ሚኒስቴሩ መግለጫ ጠቁሟል።

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa