YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#JustIn

በአለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚልዮን(1,000,000) አልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ ቴሌቪዥንና ኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ከነገ መጋቢት 25/2012 ዓ.ም ጀምሮ የጁመኣ ሐይማኖታዊ መልዕክትና ምክሮችን በየሳምንቱ አርብ ከ5:00 ጀምሮ በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ ገልጿል።

-አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
@YeneTube @FikerAssefa
የአለም ባንክ ሀገራት ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያደርጉትን ዝግጅት ለማገዝ ከያዘው 14 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 82 ሚልዮን ዶላሩን ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጉን የጠቅላይ ሚንስትሩ የፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአዳማ ከተማ በታገደዉ የህዝብ እንቅስቃሴ ምክንያት ቤት ለቀሩ እና ስራቸዉ በቫይረሱ ምክንያት ለተስተጓጎለ ለፍተዉ አዳሪዎች፣ አካል ጉዳተኞችና ጎዳና ተዳዳሪዎች ከነገ ጀምሮ በቀን 10,000 ዳቦ አቀርባለው ብሏል።

-ዩንቨርስቲው
@YeneTube @FikerAssefa
በደብረማርቆስ ከተማ 39 ሽጉጦችና በርካታ ጥይቶች በመኖሪያ ቤቱ ደብቆ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማዋ ፖሊስ ገለፀ።

Via:- ElU
@YeneTube @fikerassefa
Forwarded from YeneTube
All your favorite is here!
🇪🇹ሁሌ አዲስ MARKET ETHIOPIA
Have brought you multiple choices of items to choose from ! You can also order items from amazon.co.uk , ebay or alibaba.com!
🔶 Our pricing policy is enabling customers get items with better price!
🔶 ማንኛውንም ለ እርስዎ እና ለ ስራዎ አስፈላጊ የሆኑ እቃ እና የ እቃ መለዋወጫወችን በ ትዛዞ መሠረት እናመጣለን!

Join now👉https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEsVtSMmzvtMCoThQw

contact : 0929134433 /@Nty123
Forwarded from HEY Online Market
SAMSUNG:UHD Curved TV(2019)
55 Inches CURVED Screen TV
7 SERIES | RU7300
Price: 38,000

LG : UHD Flat TV (2019 )
55 Inches Flat Screen TV
With its own Decoder
Price: 59,000 birr

Contact US
0953964175
0925927457 @eBRO_4
0910695100
@HEYOnlinemarket
Forwarded from YeneTube
(ሺባ) በ 0941158969 ይደውሉልን
የተለያዩ ብራንድ ስአቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከኩባንያችን (ሺባ) ይግዙ ወደሚፈልጉት ቦታ እናመጣለን
Emporio Armani 1690
Tissot 1725
Montblanc 1600
Boss 1725
Seiko 1375
Rado 1425
ቻናላችንን በመቀላቀል የተለያዩ ምርጫዎችን አይተው ይግዙ https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFfS1CHMcuedhCLPBQ
በ0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ እናደርሳለን
አሜሪካ በኮሮናቫይረስ የሚሞቱት ዜጎቿ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል።

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እንደሚያመለክትው በትናንትናው ዕለት በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 1 ሺህ 169 አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ ሞተዋል። ይህም ወረርሽኙ በቻይና ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በአገር ደረጃ በአንድ ቀን ብቻ የተመዘገበ ከፍተኛው የሞት ቁጥር ሆኗል።

Via :- BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሸበሌ ባንክ

ሸበሌ ባንክ በመመስረት ላይ ያለ ባንክ ሲሆን 270 ሚሊዮን ብር አክሲዮን እንደተሸጠ ሰምተናል እንዲሁም 120 ሚሊዮን ብር እንደተከፈለ ለማወቅ ችለናል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፕሬዝዳንት ፓል ካጋሜ ጋር ተወያዩ።

ከወንድሜ ከፖል ካጋሜ ጋር፣ የኮቪድ19 ሥርጭት ለሚያስከትላቸው ፈታኝ ሁኔታዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል የጋራ አመራር ላይ የስልክ ውይይት አካሂደናል።

አፍሪካ ከቀውሱ በኋላ ሊያጋጥማት የሚችለውን የኢኮኖሚ መሰናክል ለመቋቋም፣ የጋራ ጥረት እጅግ ያስፈልጋል።

Via:- PM Abiy Ahemed Ali
@Yenetube @Fikerassefa
በጉራጌ ዞን የCOVID -19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አካል የሆነውን የትራንስፖርት አገልግሎት ከባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል ከአሽከርካሪው በቀር ከመጋቢት 25/ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም በዞኑ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና የቢጫ ወባና ወባ መከላከል ግብረ-ሀይል የወሰነውን ውሳኔ በዞኑ ህብረተሰብ ፣ በአሽከርካሪዎች ፣ በትራፊክ ደንብ አስከባሪዎችና በጸጥታ አካላት ከፍተኛ ተሣትፎ ተፈፃሚ መሆን ጀምሯል።

ምንጭ:-Gurage Zone Government Communication Affairs
@Yenetube @Fikerassefa
ማላዊ የኮቪድ-19 ተጠቂ ሪፖርት ያደረገች 50ኛዋ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገር ሆናለች።

አፍሪካ ውስጥ እስካሁን 7,028 ኬዝና 284 ሞት የተመዘገበ ሲሆን 561 ሰዎች አገግመዋል።

ምንጭ::CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
ዘመን ባንክ ለአበባ ላኪዎች የብድር ወለድ ምጣኔ ስረዛ ማድረጉን ይፋ አደረገ። የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ ደረጀ ዘበነ እንዳስታወቁት የወለድ ምጣኔ ስረዛው ከ መጋቢት 24 እስከ እስከ ሰኔ 23 የሚቆይ ነው።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ዜና እረፍት በአሜሪካን ሀገር አትላንታ ከተማ የሚሰራጨው የአድማስ ራዲዮ እንዲሁም ድንቅ መጽሄት አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ዳኜ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም በኤምሪ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በአፕሪል 1 ቀን ህይወቱ አልፏል።

@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በወንበር ልክ ብቻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

ከባቡሩ ጎን ለጎን የጎልዴን ባስ ትራንስፖርት ተመሳሳይ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑም ታውቋል።የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ከዛሬ ጀምሮ ተሳፋሪዎችን በወንበር ልክ ብቻ በመጫን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ባቡሩ በቀን በአማካይ 110 ሺህ ሰዎችን ያስተናግድ ነበር።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮናቫይረስ የተያዙ ስድስት ተጨማሪ ሰዎች ተገኙ!

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 35 እንዳደረሰው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት፤ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ውስጥ አምስቱ ከአዲስ አበባ ሲሆን አንድ ከድሬዳዋ ነው።

➡️በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን የመጀመሪያው የ35 ዓመት ወንድ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጣ፣ ሁለተኛው የ30 ዓመት ወንድ በተመሳሳይ ከዱባይ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም የመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለቱም አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የገቡ ናቸው።

➡️
ሶስተኛው የ28 ዓመት ወንድ፤ አራተኛውም የ56 ዓመት ወንድ፣ አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

እነዚህ ሰዎች ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

➡️
ስድስተኛዋ ሰው የ33 ዓመት ሴት ስትሆን በድሬዳዋ ከዚህ በፊት በኮሮናቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት የነበራት መሆኑ ታውቋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኤሌክትሪክ ፍጆታችሁ በኤሌክትሮኒክ ካርድ የምትጠቀሙ ደንበኞቼ በማንኛውም ጊዜ የካርድ አቅርቦቴን ስለማላቋርጥ አቅርቦት ይቋረጣል በሚል ስጋት አላስፈላጊ ጭንቀት ውስጥ አትግቡ ብሏችኋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በኮረና ቫይረስ ምክንያት የተጣለዉን የትራንስፖርት እገዳ በተላለፈዉ አሽከርካሪ ሳቢያ ሞት አደጋን ደረሰ ፡፡

ዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት ረፋድ ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ሀርላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በአስተዳደሩ የተላለፈውን የህዝብ ትራንስፖርት እገዳ በመተላለፍ ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ የነበረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦሮ 52818 ሚንባስ ተሸከርካሪ ከሀረር ወደ ድሬዳዋ አቅጣጫ ይጓዝ ከነበረ FCR አይሱዙ ጋር በመጋጨቱ በሚኒባስ ዉስጥ ተሳፍሮ የነበረ አንድ ታዳጊ ወጣት ህይወት ወዲያውኑ አልፏል፡፡

እገዳውን ተላልፎ ሲያሽከረክር የነበረው አሽከርካሪ የአካል ጉዳት ደርሶበት የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል:: አሽከርካሪው ከአደጋው ቀደም ብሎ በፖሊስ አባላት ማሽከርከርከሩን እንዲያቆምና የጫናቸውን ተሳፋሪዎች እንዲያወርድ ሲጠየቅ ጥሶ የሄደ ሲሆን ከዉስን ጉዙ በሀላ በድጋሚ ሌሎች የፖሊስ አባላትን ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር ነዉ አደጋዉ ሊደርስ የቻለዉ፡፡

Via Dire Police
@YeneTube @FikerAssefa