YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ተረጋገጠ

ኢትዮጵያዊያኑ እዚያው ጣሊያን ውስጥ በበሽታው ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ያናገራቸው የውጪ ጉዳይ ምንጮች አረጋግጠዋል።

በወርርሽኙ የሞቱት ሁለቱም ሰዎች ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የነበረ ወንድና ሴት ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ የታወቀ ሲሆን አንደኛው ለረጅም ዓመታት ጣሊያን ውስጥ የኖሩ መሆናቸውም ቢቢሲ ለመረዳት ችሏል።

ሁለተኛዋ ሟች መቼ ወደ ጣሊያን እንደሄዱ በትክክል ባይገለጽም ቤተሰብ ለመጎብኘት ወደ ጣሊያን በመሄድ እዚያው የቆዩ እናት እንደሆኑ ታውቋል። ሁለቱም ሟቾች ህመሙ ከታየባቸው በኋላ አስፈላጊውን የህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደቆዩና በመጨረሻም ለህልፈት መብቃታቸው ተገልጿል።

ባለሙያዎች እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ በሽታ በእድሜ በገፉና ሌሎች የቆዩ የጤና ችግሮች ባሉባቸው ሰዎች ላይ እስከ ሞት የሚያደርስ ከባድ ጉዳትን ያስከትላል።

ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው እንዳለፈ የተነገረው ሁለቱ የኢትዮጵያዊያንም ሞት የተፋጠነው ቀደም ባለ የጤና ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሎ ተጠርጥሯል።

Via:- ቢቢሲ አማርኛ
@Yenetube @Fikerassefa
WHO COVID19 ብሎ የሰየመውን አዲሱን አለምን እያመሰ ያለው ቫይረስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይና ቫይረስ በማለት በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
-70 የተማሪ ባሶች ተጨምረዋል

በመዲናዋ የትራስፖርት እጥረት እንዳይፈጠር በሚል 70 ሸገር የተማሪዎች ሰርቪስ ወደ ትራስፖርት ዘርፉ እንዲቀላቀል መደረጉን ቢሮው ለኢትይ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#ኬንያ_ለግብፅ_ደገፈች የሚለው ዜና ውሸት ነው

አምባሳደር መለስ ዓለም የአል-አህራም “ዘገባ ፍፁም ውሸት ነው” በማለት ለአሻም ቲቪ ተናገሩ

አል-አህራም፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ፤ ኬንያ የግብፅን “መልካም” አቋም ትደግፋለች ሲሉ በስልክ ለአብድል ፋታህ አል-ሲሲ ተናግረዋል በማለት የዘገበውን፣ በኬንያ የኢፌዲሪ አምባሳደር መለስ ዓለም ዘገባው ‹ፍፁም ውሸት እና የግብፅ ማደናገሪያ ፕሮፖጋንዳ ነው› ሲሉ ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓም ለአሻም ቲቪ ገልፀዋል፡፡

አል-አህራም ትናነት እንዳወጣው ዘገባ፤ ግብፅ በመግለጫዋ ኬንያታ “የግብፅ አቋም ‹ከቅን ፍላጎት› የመነጨ ነው” ሲሉ ተናግረዋል በማለት ገልጾ ነበር፡፡

አምባሳደር መለስ በተጨማሪም፣ የግብፅ ሚዲያዎች ከቀናት በፊት ጥቂት ግብፃውያን የተሰበሰቡበት ፎቶ በመለጠፍ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግብፅን ደገፉ በሚል የሀሰት ዜና ማሰራጨታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ወደ ኬንያ አቅንተው ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካውያን አለመግባባቶች በአፍሪካውያን መፈታት እንዳለባቸው የሚያምኑበት መሆኑን ያረጋገጡላቸው ሲሆን ይኸውም በፕሬዝዳንቱ የፌስቡክ ገፅ ላይ እንደሚገኝ አምባሳደር መለስ አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ያላትን አቋም ለማስረዳት ወደ ተለያዩ ሀገራት የልዑካን ቡድኖችን ልካለች፡፡ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴም ወደ ኬንያ አቅንተው ነበር፡፡ በንግግራቸው ላይም የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ የአባይን ወንዝ በተመለከተ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ ክፍፍል መኖር አለበት ሲሉ ተናግረው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ከኬንያ በተጨማሪም ወደ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ በመጓዝ ከሀገራቱ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተገናኝተው ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ያላትን አቋም ማስረዳታቸውና ፕሬዝዳንቶቹም ለኢትዮጵያ ያላችውን ድጋፍ መግለጻቸው ይታወቃል።

Via:- Spokeman office
@Yenetube @Fikerassefa
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ቡርኪነፋሶ ላይ ዛሬ የመጀመሪያ ሞተ ተመዝግቧል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሰብ ሰሀራን ላይ ሰው ሲሞት የመጀመሪያ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን የሚከታተል ግብረ ሃይል ተቋቋመ።

@Yenetube @Fikerassefa
#የኮሮና ማከሚያ መድሀኒት

በጃፓን የተመረተው መድሀኒት ለኮሮና ቫይረስ ውጤታማ መድሀኒት ሆኖ አግኝቼዋለሁ ስትል ቻይና ገለጸች፡፡

ዘጋርዲያን በዘገባው እንዳመለከተው አዲስ የጉንፋን ዝርያ ያለውን በሽታ ለማከም ጃፓን የምትጠቀመው መድሀኒት የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለማከም ውጤታማ መሆኑን የቻይና ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ በጃፓን ፋጂ ፊልም የተመረተው “ፋቪፒራቪር” የተሰኘው መድሀኒት በሁዋንና ሼንዜን ከተሞች በ340 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ላይ ተሞክሮ ጥሩ ውጤት መታየቱ ተገልጿል፡፡

የጃፓን ብሄራዊ ቴሌቪዥን NHK የሚኒስትሩን መረጃ ጠቅሶ እንደዘገበው የኮሮና ቫይረስ የነበረባቸው ሰዎች መድሀኒቱ ከተሰጣቸው ከቀናት በኋላ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ታውቋል፡፡

Via:- EBS
@Yenetube @Fikerassefa
የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለሚቀጥሉት 2 ሳምንታት "የዕሁድ አምልኮ ባይኖር" ስትል አሳሰበች።
@Yenetube @Fikerassefa
70 አዳዲስ የአንበሳ አውቶብሶች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።

እነዚህ አዳዲስ አውቶብሶች መጨናነቅን በመቀነስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን ለመከላከል ያግዛል ተብሏል።

ከገቡት ውስጥ 70 አውቶብሶች ዛሬ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በቀጣይ ቀናት ወደ ስራ እንደሚገቡ ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ላይ ጥቃት እየተሰነዘረ መሆኑን አስታወቀ።

ኢምባሲው በድረገጹ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ የውጭ አገራት ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ኮሮና አመጣችሁብን፣በእናንተ ምክንያት ነው በቫይረሱ የተጠቃነው በሚል ነዋሪዎች ጥቃት እያደረሱ ነው ብሏል።

ጥቃቱ በድንጋይ ከመምታት ጀምሮ፣ወደ ታክሲ እንዳይገቡ መከልከል፣ መስደብ እና ሌሎች ድርጊቶች በነጮች ላይ እየተፈጸመ በመሆኑ አሜሪካዊያንን ጨምሮ ሁሉም ነጭ ዜጋ በቤታቸው እንዲቆየ መክሯል።

Via:- American Embassy - Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በሃዋሳ ከተማ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ እና ባዕድ ነገር ቀላቅለው ለገበያ ባቀረቡ አካላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

በሃዋሳ ከተማ የኮሮና ቫይረስን መከሰት ምክንያት በማድረግ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ እና ባዕድ ነገር በመቀላቀል ለገበያ ሲያቀርቡ በነበሩ አካላት ላይ እርምጃ ተወሰደ። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ደቡብ ቅርንጫፍ፣ የደቡብ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪና የሀዋሳ ከተማ ንግድ መምሪያ ባደረጉት ድንገተኛ አሰሳ ነው እርምጃ ሊወሰድባቸው የቻለው።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል #150_ሚሊዮን ብር እንዲመደብ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ከተለያዩ አካላት በዓይነትና በገንዘብ ሀብት የሚያሰባስብ ኮሚቴ እንዲሁም ውሳኔ የሚያስተላልፍ ኮማንድ ፖስት አዋቅሯል፡፡

በተያያዘ መረጃ ከኮረና ተህዋሲ ጋር በተገናኘ በክልሉ በሚገኙ 82 ሆስፒታሎች የመለያ ቦታ መዘጋጀቱን የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ ገልጸዋል። 132 የጤና ሙያተኞችም ተዘጋጅተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮናን ተህዋሲ ለመከላከል የክልሉ ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10-24/2012 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
#ህንድ

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በህንድ ሀገር የሚገኙ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች የትኛውም የስልክ ጥሪ ከመጀመሩ በፊት ለ 30 ሴኮንድ ስለ ኮሮና ቫይረስ ትምህርት መስጠት ጀምረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ሲታዩ የሚደረጉ ነገሮች እና ቫይረሱን ለመከላከል ስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች በማወቅና በመተግበር ጤናዎን ይጠብቁ!

#የጤና_ሚንስትር
@Yenetube @Fikerassefa
ከ3 ሚሊየን ሊትር ቴክኒካል አልኮል መኖሩን አስታወቀ።

የስኳር ኮርፖሬሽን ለንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ማዘጋጃ የሚያገለግል ከ3 ሚሊየን ሊትር ቴክኒካል አልኮል መኖሩን አስታወቀ።

ኮርፖሬሽኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አልኮሉ በፊንጫ እና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች እንደሚገኝ አስታውቋል።

አሁን ላይም ፋብሪካዎቹ በቀን 100 ሺህ ሊትር ቴክኒካል አልኮል በማምረት ላይ መሆናቸውን ጠቅሶ፥ አልኮሉ የዓለም ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ የንጽህና መጠበቂያዎችን ለማምረት እንደሚውል ገልጿል።

በቂ የቴክኒካል አልኮል ክምችት መኖሩን የጠቀሰው ኮርፖሬሽኑ ከጤና እና ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር ከዚህ ቀደም ይወስዱ ከነበሩ ድርጅቶች በተጨማሪ ሰባት ድርጅቶች አልኮል እንዲወስዱ ተፈቅዷልም ነው ያለው።

ቴክኒካል አልኮል ለሳኒታይዘር፣ ለደረቅና ፈሳሽ ሳሙና እንዲሁም ለመጸዳጃ ቤት ማጽጃ መስሪያ በግብዓትነት ያገለግላል።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
በተፈጥሯዊ መንገድ በሽታ የመከላከል አቅምን እንዴት ማሳደግ ይቻላል?

1.ጭንቀትን መቀነስ

2. በቀን ቢያንስ 2 ሊትር ውሃ መጠጣት

3. የአልኮል መጠንን እጅጉን መቀነስ

4. ምግባችን ውስጥ አትክልት እና ፍራፍሬ ማዘውተር

5. ሰፕሊመንቶች መውሰድ

6. በቂ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ

7. በቂ እንቅልፍ ማግኘት

8. ሲጋራ ማጨስን ማቆም

10. የፀሐይ ብርሀን ማግኘት

11. እጅን በሳሙና መታጠብ

ጤናችንን መጠበቅ ላይ ማተኮር መሠረታዊ ነው፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት ማቆማቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት ማቆማቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

-በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ 6 ታካሚዎች ናቸው።

-ከእነዚህም አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት ያቆሙና በደህና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

- ሁለቱ ታካሚዎች በማገገም ላይ በመሆናቸው የቅርብ ህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
#ኮሮና ህፃናትን ያጠ ቃል?

የኮሮና ቫይረሱ ህጻናትን አያጠቃም በሚል እየተነገረ ያለው የተሳሳተ መረጃ ነው፡፡

ይህ ህጻናትን አያጠቃም የሚለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑና ቫይረሱ በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ ያለን ሰው እንደሚያጠቃ ባለሙያዎች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

ለአብነትም በቻይና ከ2 ሺህ በላይ ልጆች እንደተጠቁና አንድ የ14 አመት ልጅም ህይወቱ እንዳለፈ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በደቡብ አፍሪካም እንዲሁ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ 4 ህጻናት በቫይረሱ እንደተጠቁ ታውቋል ።

ምንም እንኳን ቫይረሱ በዕድሜ የገፉ ሰዎችን በከፍተኛ ደረጃ እያጠቃ ነው ይባል እንጂ ህፃናትም በቫይረሱ በመያዝና ከሞት መትረፍ አለመቻላቸው ከተላያዩ የዜና ምጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ጠቁመዋል።

ምንጭ:- ኢቢኤስ አዲስ ነገር
@Yenetube @Fikerassefa